TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ዘሓለፉ #ላለፉት #Kandarbaniif

በ2012 ዓ/ም በተለያዩ ምክንያቶች ከጎናችን ያጣናቸውና እና ያለፉ ዜጎቻችንን ዛሬ ጳጉሜ 4 እናስባቸዋለን።

- በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸው ያለፈ
- በ2012 ዓ/ም በነበሩ አለመረጋጋቶች የተገደሉ
- በተለያዩ ህመሞች ታመው ህይወታቸው ያለፈ
- በግድያ ህይወቱ ያለፈ (አርቲስት ሀጫሉን ሁንዴሳ ቦንሳ)
- በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ
- በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ
- በመሬት ናዳ ህይወታቸው ያለፈ
- በበቤሩት አደጋ ህይወታቸው ያለፈ በሌሎችም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ያጣናቸውን ወገኖቻችን 'ነፍስ ይማር' እያልን ዛሬ ጳጉሜ 4 በቲክቫህ ኢትዮጵያ እናስባቸዋለን።

#ዘሓለፉ #ላለፉት #Kandarbaniif

አዲሱ ዓመት ክፉ የማንሰማበት ፣ የሰላም ዓመት ያድርግልን!
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 230 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 408 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የለም።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 451 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 43 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,951 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 131 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 55 ከሰ/ወሎ ዞን
- 37 ከደ/ወሎ ዞን
- 19 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን
- 8 ከዋግ ኽምራ ብ/ሰብ ዞን ይገኙበታል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,211 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 208 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 89 ከምዕራብ ወለጋ
- 19 ከምስራቅ ሸዋ
- 11 ከቄለም ወለጋ
- 10 ከሆለታ ከተማ ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦ #Somali በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 230 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል። #BenishangulGumuz በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 408 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የለም። #Tigray በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 451 የላብራቶሪ…
ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 922 የላብራቶሪ ምርመራ 52 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ቫይረሱ የተያዙት፦
- ከካፋ ዞን 21 (19 ከቦንጋ ከተማ እና 2 ከጨና) ፣
- ከጌዴኦ ዞን 8 (4 ከረጲ፣ 2 ከይ/ጨፌ፣ 1 ከዲላ እና 1 ከቡሌ)፣
- ከቤንች ሸኮ ዞን 7 (5 ከደቡብ ቤንች እና 2 ከሚዛን ከተማ )፣
- ከጋሞ ዞን 6 (5 ከጋርዳ ማርታ እና 1 ከምዕራብ አባያ)፣
- ከሃዲያ ዞን 3 (2 ከአኔሌሞ እና 1 ከዱና)፣
- ከአሌ ልዩ ወረዳ 2፣
- ከሃላባ ዞን 2 (2ቱም ከዌራ)፣
- ከዳውሮ ዞን 1 (ከማሪ ማንሳ)፣
- ከጎፋ ዞን 1 (ከሳውላ ከተማ)፣ እንዲሁም 1 ከኦሮሚያ ክልል(ከሻሸመኔ ዙረያ የተላከ ናሙና)

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 188 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,185 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 676 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 41 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 35 ከሀዋሳ ከተማ
- 6 ከሸበዲኖ

@tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 15,561 የላብራቶሪ ምርመራ 916 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 377 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 61,700 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 966 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 23,054 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የተካሄደው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ ተጠናቋል። የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለምርጫ ከተመዘገበው መራጭ 97 በመቶ ያህሉ መርጧል ሲሉ ለBBC ተናግረዋል።

ለምርጫ የተመዘገቡ ነዋሪዎች ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምረው በመውጣት መምረጣቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ ከእኩለ ቀን በኋላ አብዛኛው የመራጭ ጣብያዎች ባዶ እንደነበሩ ገልፀዋል።

በምርጫው ወቅት ይህ ነው የሚባል ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን የገለፁት ኮሚሽነሩ ሙሉ ቀን ፣ ከተቃዋሚም ፓርቲዎችም ቢሆን የደረሳቸው ቅሬታ አለመኖሩን ገልፀዋል።

በአንዳንድ የምርጫ ጣብያዎች ለምርጫ የተመዘገበ ነዋሪ ሙሉ በሙሉ መምረጡን አንስተዋል።

የድምጽ ቆጠራው በጣብያ ደረጃ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ያልቃል ያሉት ኮሚሽነሩ የምርጫው ውጤት መስከረም 2 ይገለፃሉ ተብሎ መታቀዱን ለBBC ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሸገር ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው!

የሸገር ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት እየተካሄደ ነው።

በፓርኩ ምረቃ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የሸገር ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ለፓርኩ መገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተለይም ለቻይና መንግስት እና ለሌሎች አካላት እውቅና ተሰጥቷል።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በስራ ሂደቱ ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስጋና ስጦታ ማበርከታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

PHOTO : Reporter /FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ ይወጣል!

በ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር ፣ በ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር ፣ በ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን እንዲሁም ሌሎች በርካታ ዕጣዎችን የሚያሸልመው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ ጳጉሜ 05/2012 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በአስተዳደሩ የእጣ ማውጫ አዳራሽ (ዕድል አዳራሽ) በቀጥታ ስርጭት በኢትቪ 1 (etv) ይተላለፋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በአስሩ ክፍለ ከተማ በጥናት በተደረገ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኤፍ ቢ ሲ አስታውቋል።

በተደረገው ፍተሻ አንድ (1) ቦምብ እና አራት (4) ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ 180 ግለሰቦች ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህብረተሰቡ የራሱን ሰላም በመጠበቅ ፣ ሰላምን ሊያውኩ የሚችሉ ወንጀለኞችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለፀጥታ ሲባል ማንኛውም ግለሰብ ርችት መተኮስ እንደማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ርችት መተኮስን ምክንያት በማድረግ 'የሽብር ጥቃት' ለማድረስ እየተዘጋጁ ያሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ፖሊስ በጥናት ስለደረሰበት እንደሆነ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለኤፍ ቢ ሲ ገልጸዋል።

ስለሆነም ወንጀልን ለመከላከል ሲባል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማንኛውም ግለሰብ ሪችት መተኮስ አይችልም ብለዋል።

ይህንን ተላልፎ ሪችት የሚተኩስ ማንኛውም ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውል ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia