ከተማ አስተዳደሩ 7 ሚሊዮን ደብተር ሰብስቧል!
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በተያዘው ክረምት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚውል ደብተር ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶችና ግለሰቦች ያሰባሰበው 7 ሚሊዮን መድረሱን አስታወቀ። በመጪው ጳጉሜ ለ600 ሽሕ ተማሪዎች እንደሚከፋፈልም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የመቐለው ስብሰባ ተጠናቋል!
በህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት ዙሪያ በመቀሌ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ መድረክ የአቋም መግለጫ በማውጣት ማምሻውን ተጠናቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓት ዙሪያ በመቀሌ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ መድረክ የአቋም መግለጫ በማውጣት ማምሻውን ተጠናቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ የሚገኘዉ “ደብሊዉ ኤ” የዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ ግንባታው በ2006 ዓ.ም የተጀመረው የምግብ ዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ 85 በመቶ እንደደረሰ ታውቋል፡፡ ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በቀን ከ130 እስከ 150 ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ነው የተገለጸው፡፡ የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንግዳወርቅ መኮንን #ለአብመድ እንደገለፁት ፋብሪካው ሥራ ሲጀምርም አራት ዓይነት የምግብ ዘይት ለማምረት ነው የታቀደው፡፡
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_የፌስቡክ_ገፅ!
ከላይ የምትመለከቱት በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ስም የተከፈተው ገፅ ሀሰተኛ ነው። የገፁ ተከታይ ብዛት 20,000 ሲሆን ትክክለኛው የOBN የፌስቡክ ገፅ ያለው የLike ብዛት 111 ሺህ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ከዚህ ሀሰተኛ ገፅ ተጠንቀቁ!
#share #ሼር

ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ!
የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅበላ ጳጉሜ አምስት ድረስ ብቻ የሚከናወን ስለሆነ በሀዋሳ ከተማ የምትገኙና ልጆቻችሁን ትምህርት ቤት ያላስመዘገባችሁ አስመዝግቡ። በሁሉም የመንግስት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ምንም ዓይነት #ክፍያ አይጠየቅም።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

መልካም ተግባር!
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ #መምህራን በበጎ ፈቃድ ተነሳስተው የአንድ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥገናና እድሳት አከናወኑ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የምህንድስና ዲፓርትመንት መምህራን የከተማው ወጣቶችን በማሳተፍ ባደረጉት ጥረት ለሠላም በር መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ቀለም ቅብና እድሳት አድርገዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው በጎ አድራጎት ሥራው አስተባባሪ መምህር ዮሐንስ ፈይሳ እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የተከናወነው ሥራ 80 ሺህ ብር ይገመታል፡፡
Via ኢዜአ

TIKVAH-ETHIOPIA
የቴፒ ነገር... TIKVAH-ETHIOPIA ከቴፒ ከተማ ነዋሪ ቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እያስተናገደ ነው። ከተማይቱ አይሁንም ቢሆን አስተማማኝ ደህንነት የላትም፤ መንግስት ኃይሉን አጠናክሮ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል። በተለይም የከተማው መግቢያና መውጫዎች ላይ ከፍተኛ ወንጀሎች እንድሚፈፁ ገልፀዋል። "ከቴፒ ነው የምጽፍላቹ! N ነኝ ቴፒ ነዋሪ ነኚ ቴፒ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር አለ።…
#ቴፒ
"ከቴፒ የጻፍኩላቹ የናንተው ቤተሠብ ነኝ። ለ8 ቀን ተዘግቶ የነበረው የቴፓ መናህሪያ በመከላከያዎች ጥረትና አወያይነት ዛሬ ለመንገደኞች ክፍት ሁኖ እኛም መከላከያ ጫካውን አጅቦን ሸኚቶን ከቴፒ #ሚዛን ገብተናል መንገደኞችም ዛሬ ማንም ሣይዘረፍ ወደሚዛን ገብተናል! እድሜ ለፌደራልና ለመከላከያዋቹ ሁሉንም አመሥግኑልን የናንተው ቤተሠብ ከሚዛን ቴፒ!"
እኛ ደግሞ ይህን እንላለን...
የኢትዮጵያ መንግስት ለአካባቢው #ልዩ_ትኩረት ሰጥቶ ችግሮች በዘላቂነት የሚፈቱበትን መንገድ መፈለግ አለበት፤ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ላይ #ደህንነታቸው ተጠብቆ እንደልባቸው ወጥተው የሚገቡበትና ስራቸውን ያለእክል የሚሰሩበትን ሁኔታ መፍጠር ትልቁ የመንግስት ስራ በመሆኑ በተቻለ አቅምና ፍጥነት ይህን ማድረግ ይኖርበታል።

እንኳን ደስ አለን!
🇪🇹ኢትዮጵያ ሌላ ወርቅ🇪🇹
በ10 ሺ ሜትር ወንዶች ብርሀኑ_ወንድሙ የወርቅ ሜዳልያ ጀማል ይመር ነሀስ አስገኝተዋል። የብር ሜዳልያውን ኤርትራ ወስዳለች። በዛሬው የመላ አፍሪካ ዉድድር ላይ አትሌቶቻችን ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አለን።
Via Mekonen Hailu
ስፖርት ወዳድ ቤተሰቦቻችን በማራኪ አቀራረብ ከቅዱስና ከጎቶም ጋር👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

ETDevs is a community on Telegram that tries to gather developers around ethiopia and help them to chat and discuss about things they love.
Join Us: https://yangx.top/etdevs
Join Us: https://yangx.top/etdevs
#update የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታወቀ። በደቡብ ኮሪያው እና በጃፓኑ የስራ ጉብኝት የተሳተፉት የሚኒስትሮች ልዑካን ከ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት መድረክ ጎን ለጎን የጎንዮሽ ከጃፖኑ ማሪቦኒ ድርጅት ጋር የቢዝነስ ውይይቶችን አካሂደዋል።
በውይይቱ የማሪቦኒ ድርጅት በኢትዮጵያ መሰማራት በሚፈልግባቸው ዘርፎች ዙሪያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን፤ በአገሪቱ በኢነርጂ፣ በማዕድንና በቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመር ላይ ፍላጎት እንዳለው የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ማሳሜ ካሱካኪ አስረድተዋል።
ከኢትዮያ በኩል በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የሚያስችሉ የማሻሻያ እና የአሰራር ማስተካከያ መደረጉ ተመልክቷል። ባለሀብቶች በማዕድን፣ በኢነርጂ፣ በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ እንዲሁም፤ በቡና ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በማስረዳት በአገበኢትዮፕያ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል። መንግስት ለባለሀብቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ማበረታቻ እንደሚሰጥም ልኡካኑ ለባለሃብቶቹ ገልጸውላቸዋል።
Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvagethiopia

#update ጳጉሜ 2 የሠላም ቀን ምክንያት በማድረግ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። ጰጉሜን 2 በአገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው የሠላም ቀን ‘ሠላምን እንትከል’ በሚል መሪ ኃሳብ በሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስተባባሪነት ይካሄዳል። ይህንንም ተከትሎ ዛሬ የሠላም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሯ ወይዘሪት ሄርሜላ ሠለሞን በሰጡት መግለጫ ቀኑን በማስመልከት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ይካሄዳል ብለዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዋሽ - ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ግንባታ ቢጠናቀቅም የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳልቀረበለት ተገለፀ!
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ - ኮምቦልቻ የባቡርመስመር ግንባታን ማጠናቀቁን፤ ኤሌክትሪክ ከቀረበለትም ሥራ ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበኩሉ፤ ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ክፍያ እንዳልተፈፀመለት፤ አገልግሎቱን ለማቅረብም 18 ወራት እንደሚፈጅበት ገልጿል። በኮርፖሬሽኑ የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራገበያ የባቡር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም መሐመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የአዋሽ - ኮምቦልቻፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ከ99 በመቶ በላይ ተጠናቋል። በአሁኑ ወቅትም የኤሌክትሪክ አቅርቦት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለባቡር መስመሩ የሚያስፈልገውን የኤልክትሪክ ኃይል ካቀረበላቸው አገልግሎቱን ወዲያውኑ ማስጀመር የሚቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
Via #EPA

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እየተሳተፉ የሚገኝበት የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻው ላይ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ ጃፓን ለአፍሪካ በጤና እና በትምህርት መሰረት ልማት እያደረገች ያለውን #ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቲካድ አፍሪካ ከድህነትና ኃላቀርነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራር ለአፍሪካ ልማት የሚካሄድ ኮንፈረንስ ነው፡፡
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ቢሮ ስር የሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የዲጅታል ሊትሬሲ (መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትና ክህሎት) ስልጠና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሙያተኞች ለ4ኛ ዙር በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
Via Gondar University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Gondar University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሁሉም የደ/ጎን/አስ/ዞን/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ከዩኒቨርስቲው ለተወጣጡ 1500(አንድ ሺህ አምስት መቶ) ሠራተኞች ከነሐሴ 17/2011 ዓ/ም ጀምሮ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም (Digital Literacy) ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ሥልጠናው በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከ620 በላይ ሠልጣኞች ሥልጠናውን ለ15 ቀናት በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡
Via Debre Tabor University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Debre Tabor University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ2011
የአሸንዳ በዓል የፊታችን ነሃሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚሌኒየም አዳራሽ ይከበራል። ከሀገራችን በርካታ የባህል መገለጫ እሴቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የአሸንዳ በዓል በሁሉም ኢትዮጵያዊያን መዲና አዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶችና በድምቀትና ለማክበር የሚያስችል መርሃ-ግብር መውጣቱም የከተማ አስተዳድሩ ከንቲባ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ በበዓሉ ላይም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የከተማው መስተዳድር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#update በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ይግባኝ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዐቃቤ ህግ በአራት እና አምስት ጊዜ ቀጠሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ባለማቅረቡ ነው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግበኙ ውድቅ የተደረገው፡፡ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሀገራችን ለመስራት ምክንያት አንሻም!!
በደብረ ብርሀን ከተማ ቀበሌ 03 በተለምዶ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው የከተማው መንገድ ያጋጠመውን የመንገድ ብልሽት በማየት በከተማው የሚገኙ የቅን - ድል ኢትዮጲያ ቤተሰቦች እና ብሩሀን የወጣቶች በጎ ፍቃደኛ ማህበር አባላት ይህን ችግር ለመቅረፍ እና ተሽከርካሪዎች አደጋ እንዳያጋጥማቸው በመጠገን ላይ ይገኛሉ፡፡
በከተማው የምትገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ባለሀብቶች #የማቴሪያል ድጋፍ እንድታረጉላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር በ2 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሰርቶ አጠናቀቀ!
የአዋሽ ወይን አክሲዮን ማኅበር የምርት አቅሙን በሦስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለትን የማስፋፊያ ፕሮጀክት በ2 ሚሊዮን ዶላር ገንብቶ አጠናቀቀ። በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ በሚገኘው የመጥመቂያ ፋብሪካ የተገነባው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ፋብሪካው በአመት ሲመርተው የነበረውን የ6 ሚሊየን ሊትር ወደ 30 ሚሊዮን ሊትር የሚያሳድግ ሲሆን ከቻይና፤ ጀርመን እና ጣሊያን በተገኙ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ መሆኑ ተገጾል። በቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን ለመስራት 1 ሚሊየን ዶላር በጀት መያዙን በተጨማሪም ለማህበራዊ ስራዎች ከ 15 ሚሊየን ብር መመደቡን አሳዉቀዋል፡፡የአልኮል መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ዳንኪራ የተሰኘ አዲስ ምርት ለገበያ አቅርቧል፡፡