TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

#Emebet_Mekonen / #ሻደይ / #ሶለል #አሸንዳዬ - #ETHIOPIA #AMHARA

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው!! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን !

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጎባ ወረዳ የተሽከርካሪ አደጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ!

በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው ባደረሱት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቭዥን ባለሙያ ኮማንደር ናስር ኡመር እንዳሉት አደጋው የደረሰው የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 80852 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ተመሳሳይ ከሆነ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-84695 ኢት ተሽከርካሪ ጋር ትናንት ቀን 10 ሰዓት አካባቢ  በጎባ ወረዳ ሲንጃ የተባለ ስፍራ እርስ በርስ በመጋጨታቸው ነው። ተሽከርካሪዎቹ የተጋጩት ከጎባ ከተማ ወደ ሮቤ  አሸዋ ጭነው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነው።

በአደጋው ህይወቱ ካለፈው  ሌላ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። የሟቹ አስክሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ ተደርጓል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ያመለከቱት ኮማንደሩ ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እየጣለ ያለው ዝናብና ጉም ምክንያት እይታን እንደሚጋርድ በመገንዘብ  አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮሌራ በሽታ ተቀሰቀሰ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በምትገኘው የሻሸመኔ ወረዳ የኮሌራ በሽታ መቀስቀሱ ተሰማ። አንድ የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት የስራ ሃላፊ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ እንደገለፁት ወረርሽኙ ከባለፈው ስምንት መጀመሪያ አንስቶ የታየውና የተቀሰቀሰው በወረዳው ቶጋ፣ ቢሊቻ ፣ ጩሉሌ እና ቄሬሳ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው።

በአሁኑ ወቅት በበሽታው የተጠቁ ስድስት ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የወረዳው የጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ገመዴ ተናግረዋል።

አስከአሁን በወረርሽኙ ከተጠቁት ስድስት ሰዎች በስተቀር የሞት አደጋ #አለመድረሱን የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ገልጸዋል። ፅህፈት ቤቱ የበሽታው ስርጭት እንዳይስፋፋ ለማድረግ በአካባቢው በሚሰራጩ የራዲዮ ጣቢያዎች አማካኝነት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፈ ይገኛል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከአርቲስቶች ጋር ችግኝ ተከሉ!

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል፡፡

አርቲስቶቹ በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ተንቀሳቅሰው ህዝቡን በማነሳሳት ችግኝ ተከላው ከታቀደው በላይ እንዲከናወን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ፕሬዚዳንቷ አመስግነዋዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡ በስብሰባው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ብቻ ለልብ ቀዶ-ጥገና ሰባት ሺህ ህፃናት ተራ እየጠበቁ ነው ተባለ!

በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ለልብ ቀዶ-ጥገና ህክምና ሰባት ሺህ ህፃናት ተራ እየጠበቁ መሆኑን ማዕከሉ አስታወቀ፡፡ በተለያዩ ሆስፒታሎች እና በየክፍለ-ሀገራቱ ያሉት ደግሞ ከዚህ በላይ ይሆናሉም ተብሏል።

የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር እና የልብ ሕሙማን ሕፃናት ስፔሽያሊስት የሆኑት ዶ/ር ሔለን በፈቃዱ፣ የሠለጠኑ ባለሙያዎች እና ዋና ዋና መሣሪያዎችም ማዕከሉ ውስጥ እያሉ በገንዘብ እጥረት ምክንያት አስፈላጊ የሆኑ አላቂ መድኃኒቶችን ማሟላት አለመቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ መሥራት ከሚችለው የቀዶ-ህክምና ሥራ ከአንድ ሦስተኛው በታች ብቻ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን መሰል ቀዶ-ጥገና የሚሠራ ሌላ የግል ሆስፒታል ባለመኖሩም መክፈል የሚችሉት እንኳን ሕክምናውን ማግኘት አይችሉም፤ በተለይ ደግሞ መክፈል ለማይችሉ ብዙኃኑ ተስፋቸው በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ብቻ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-23-2
"አንድ ብር ለአንድ ልብ" 6710

እንደTIKVAH-ETH ቤተሰብ ድጋፋችን ተጠናክሮ ቀጥሏል!

የቤተሰባችን አባላት፦

•በሀገራቸው ስም
•በባለቤታቸው ስም
•በልጆቻቸው ስም
•በፍቅረኛቸው ስም
•በሚወዷቸው ታዋቂ ሰዎች ስም
•በአባባሎች ... 6710 ላይ እንደ ዜጋ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው። እርሶስ?

በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!

ወደዚህ ግሩብ ግቡና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ፤ ሀገር አለን የምንለው ለዚህ ነው። ሁሌም ለበጎ ስራ አብረን ስለቆምን!!

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://yangx.top/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ
#update ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ 4.23 ቢሊዮን ብር (120 ሚሊዮን ፓውንድ) እርዳታ መስጠቷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ምኒስትር ድኤታው አድማሱ ነበበና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ልማት ምኒስትር አሎክ ሻርማ ፈርመውታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የካሜሮን አምበሳደር ለነበሩትና በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት ለተለዩት #ጃክዬስ_አልፍሬድ ንዶምቤ ኤቦሌ በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ዛሬ ነሀሴ 17 ቀን 2011 ዓም ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ሚኒስተሯ በሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ባሰፈሩት መልዕክታቸው አምባሳደር ኤቦሌ ንቁ፣ ተግባቢና ከሌሎች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ስብዕናን የገነቡ ትልቅ ዲፕሎማት ነበሩ ብለዋል። አዲስ አበባ ከተመደቡበት ጊዜ አንስተው የኢትዮጵያና ካሜሮን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲጠናከር እንዲሁም በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመቀራረብ የአፍሪካን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ አስተዋጽዖ አድርገዋል ብለዋል።

ሚኒስትሯ በመጨረሻም ለአምባሳደሩ ቤተሶበች፣ ወዳጅ ዘመዶች አንዲሁም ለመላው የካሜሮን ህዝብ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ስም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ አምባሳደር ጃክዬስ አልፍሬድ ንዶምቤ ኤቦሌ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2008 ጀምሮ በኢትዮጵያ፣ በአፍረካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የካሜሮን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሃሰተኛ ወሬን ማስወገድ እና ተፈናቃዮችን ለመመለስ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ ይስራ" የመከተል ነዋሪዎች

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች የጋራ ኮማንድ ፖስት በአካባቢው ለወራት የዘለቀውን ግጭት በማስቆም ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡ አንዳንድ የመተከል ከተማ ነዋሪዎች ኮማንድ ፖስቱ ሃሰተኛ ወሬን ማስወገድ እና ተፈናቃዮችን ለመመለስ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የክልሎቹ የጋራ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ አቶ አበራ ባዬታ ለኢዜአ እንዳሉት ኮማንድ ፖስቱ በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች ባለፈው አንድ ወር ባከናወናቸው ሥራዎችን ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በእዚህም በአካባቢው ለወራት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም መቻሉን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-23-2
“ቤታችን እየነደደ ነው” ኢማኑኤል ማክሮን

ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን እና መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ላይ ለተነሳው ሰደድ እሳት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ገለጹ። መሪዎቹ በአማዞን ደን ለተነሳው እሳት አስቸኳይ መፍትሄ መስጠትና ጉዳዩ በቡድን ሰባት ሃገራት ስብስባ ላይ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። ማክሮን ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ በትዊተር ገጻቸው ላይ “ቤታችን እየነደደ” ነው ሲሉ አስፍረዋል። የአማዞን ህልውና የዓለማችን አንገብጋቢው ጉዳይ ነው ሲሉም የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸውታል።

ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ይሻል የሚሉት ማክሮን ሃገራቸው በምታስተናግደው የቡድን ሰባት አባል ሃገራት ስብሰባ ላይም አጀንዳ ሊሆን እና አስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባም ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብራዚል በተለይም በአማዞን ክልል የሚነሳው የእሳት አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በደኑ ከቀናት በፊት የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አድማሱን እያሰፋ ከፍ ያለ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪዎች ደግሞ ለተነሳው እሳት የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮን ይወቅሳሉ። ፕሬዚዳንቱ ገበሬዎችና ከደን ውጤቶች የጣውላ ምርት አምራቾች ደኑን እንዲጨፈጭፉ ፈቅደውላቸዋል በሚል ትችቱ በርትቶባቸዋል። እርሳቸው ግን ውንጀላውን ያስተባብላሉ፤ የማክሮንን አካሄድም “በብራዚል ጉዳይ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የታለመ” በሚል አጣጥለውታል።

Via #ቢቢሲ/#fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአማዞን ደን የተወሰኑ አካባቢዎች ዝናብ እየጣለ ይገኛል🌨

የምድራችን ሳንባ በመባል የሚታወቀውና የዓለማችን ትልቁ ደን አማዞን የአየር ንብረት ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል። ከዚህ ባለፈም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆነውን ኦክስጅን በብዛት አምቆም ይገኛል፤ የ3 ሚሊየን የዱር እንስሳት እና እፅዋት መገኛ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakePage በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ስም በርካታ ሀሰተኛ ገፆች አሉ። ትክክለኛውና የኤጀንሲው የፌስቡክ ገፅ የሆነው ከ114 ሺህ በላይ የላይክ ቁጥር ያለው ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ በEBS ስም የተከፈተና ከ46,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻናል የEBS ቴሌቪዥን #አይደለም

ከዚህ ቀደም "አዲስ ነገር" EBS በሚል በቴሌግራም ላይ የተከፈተ ገፅ ትክክለኛ እንዳልሆነ ከEBS ሰዎች የደረሰንን መልዕክት ማጋራታችን አይዘነጋም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ተቋቋመ። ምክር ቤቱ በክልሉ ፕሬዚዳንት የሚመራ ሲሆን ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ተወካዮች አባላት የሚሆኑበትና እስከ ቀበሌ ድረስ የተዋቀረ መሆኑ ተጠቁሟል። ምክር ቤቱ የክልሉ መንግስት፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የተለያዩ የህብረተሰሰብ ክፍሎችን ያካተተ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#roboticflyingbird በቻይና እየተካሄደ ባለው 5ኛው አመታዊ የዓለም ሮቦት ኮንፈረንስ ላይ ከታዩና የበርካቶችን ቀልብ ከሳቡት መካከል!!

ቪድዮ📹VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 1 ሚሊየን ደብተር ድጋፍ አድርጋለች፡፡ ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ነው፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ፓትሪያርኩ የከተማ አስተዳደሩ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት ቤተ ክርስቲያኗ እንደምታደንቅ እና በቀጣይነትም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረገችው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያለ ስራ #ደሞዝ እየወሰዱ ነውና፤ እኛ መንግስትም እንዲጠቀም ተገልጋዩ ህብረተሰብም ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ለቅሬታችን ሰሚ ጆሮ እንፈልጋለን" ቅሬታ አቅራቢዎች
.
.
ከሐምሌ 1 ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው አዲሱ የሰራተኞች ድልድል በጉለሌ ክፍለ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ቅሬታ አቅርበዋል ተብሏል፡፡ ሰራተኞቹ ድልድሉ ከመመሪያ ውጭ በትውውቅና በኔትወርክ ሆኗል ይላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም #አለቆቻችን የሚሰሩትን #አድሏዊ አሰራር ስንቃወም ስለነበር ከቦታው ገለል ለማድረግ ተጠቅመውበታል ይላሉ፡፡ ክፍለ ከተማው በበኩሉ በጥንቃቄ የከወንኩት ስራ ነው፣ ችግሮች ካሉም ለማስተካከል በሬ ክፍት ነው ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እንዴት በዚህ ዘመን አሁን #ኢትዮጵያ ውስጥ አደግን በምንልበት እንደዚህ አይነት ትምህርት ቤት..." ሻለቀ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia