#ባህርዳር
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በወረብ ቆላ ጽዮን አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላልቅሎ በጣለ ዝናብ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። ሐምሌ 18 ቀን 2011ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላለቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል። ሐምሌ 18/ 2011 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰው ውሽንፍር የቀላቀለ ዝናብ በርካታ ቤቶች የቆርቆሮ ክዳናቸውን አጥተዋል። ከቤቶቹ በተጨማሪ በጣለው በረዶ ሰብል ላይም ጉዳት ደርሷል። ነዋሪዎቹ የተነቀለው ቆርቆሮ ከአካባቢው እንደጠፋ እና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። የወረብ ቆላ ጽዮን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ጥጋቡ በለጠ እንደተናገሩት ከ300 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እገዛችንን ከፈለገ ከጎኑ እንቆማን አለ፡፡
.
“የደርግ ሰራዊት” የሚለው የበፊት መጠሪያው “የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት” በሚል ተቀይሮ ከመንግስት እውቅና እንደተሰጣቸውም የማህበሩ መሪዎች ተናግረዋል፡፡ “አሁንም የኢትዮጵያን #አንድነት ለማስጠበቅ ከቆመ መንግስት ጋር አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡
በመላው አገሪቱ 53 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ የማህበሩ ሀላፊዎች በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት ማለታቸውን ከጋዜጣዊ መግለጫው ሰምተናል፡፡ ማህበሩ ከቀድሞዎቹ ሚሊሺያዎች እስከ ከፍተኛ የጦር መኮንንነት የደረሱ አባላት እንዳሉት ተነግሯል፡፡
ምንጭ - ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሐምሌ 22 ቀን የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት👇
https://telegra.ph/PMO-07-26
#አረንጓዴአሻራ
#PMOEthiopia
https://telegra.ph/PMO-07-26
#አረንጓዴአሻራ
#PMOEthiopia
ኢራን የሚሳኤል ሙከራ አደረገች!
ኢራን የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ሙከራ #በመተኮስ፣ በፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ያለውን ውጥረት ማባባሷን፣ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለሥልጣን አስታወቁ። በስም እንዲጠቀሱ ያልፈለጉት እኝህ ወታደራዊ ባለሥልጣን ትናንት ሐሙስ እንደገለጹት፣ የዕሮብ ዕለታው የኢራን ሚሳይል ሙከራ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ወታደራዊ ጦር ሰፈር የሚያሰጋ አልነበረም።
ከደቡባዊ ኢራን ወደብ አካባቢ የተተኮሰው ሚሳይል፣ በ1,100 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ፣ በዋና ከተማዋ ምሥራቃዊ ቴህራን ላይ መውደቁም ተሰምቷል። ሚሳይሉ ከመተኮሶ አስቀድሞ ግን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የሚሳይል ሙከራ ጣቢያ ስትከተል እንደነበር እኝሁ በስም ያልተጠቀሱ ወታደራዊ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
Via #VOA

#ለጥያቄው_ምላሽ፦ TIKVAH-ETH የተመሰረተው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በሃምሌ 19/2009 ዓ/ም ነው። TIKVAH በተመሰረተበት ወቅት የቤተሰቡ አባላት 20 አይደርሱም ነበር። የነበሩትም #ንቁ ተሳታፊ አልነበሩም። ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኘው የቤተሰባችን አባል ከ320 ሺ በላይ ነው። በተመሰረተበት ወቅት ቀለል ያሉ የመዝናኛ ነክ ጉዳዮችንና ፎቶዎችን ያቀርብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ትውውቅ ከተደረገ በኃላ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ችግር ሳቢያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ድምፅ ሆኖ አገልግሏል።
TIKVAH ማለት #ተስፋ ማለት ነው!
√እኛ ማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት፤ ሰውነቱ ሲከበር ብሄሩ፣ ቋንቋው፣ ባህሉ፣ አመለካከቱ፣ እምነቱ የሚከበርበት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።
√እኛ አስተማማኝ ደህንንነት እና ሰላም ያለባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።
√እኛ ማንም ሰው በአመለካከቱ የማይገፋበት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን!
√እኛ አይደለም ለኢትዮጵያዊ በምድር ላይ ላለሰው ሁሉ የምትሆን ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።
√እኛ ዜጎቿ የማይበደሉባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።
#ተስፋችን_ደግሞ_በፍጡር_ሳይሆን_በፈጣሪ_ብቻ_ነው!
ይህ አቋማችን የዛሬ ሳይሆን የነበረ፤ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው!! #ETHIOPIA
🏷ይሄ ቤተሰብ "የኢትዮጵያ ተስፋ" ነው ብለን እናምናለን!! በመነጋገር የሚያምን ከጥላቻ የራቀ፤ ስድብ የሚፀየፍ አንድ ጠንካራ የሆነችን ሀገር ለመገንባት ዘውትር የሚተጋ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ስብስብ ነው።
ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን!

ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ።
ከተጠረጣሪዎች መካከል በነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 57 ጉዳያቸው ተጣርቶ ሐምሌ 19 ቀን 2011ዓ.ም ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/15-07-27

#update በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በመልካም አስተዳደር እና ሌሎች ጥያቄዎች ምክንያት በወረዳው በሚገኙ አንደንድ ቀበሌዎች ለ11 ወራት ተሷተጓጉሎ የነበረው መንግስታዊ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአበሽጌ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል። በወረዳው ዛሬ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮችን ያሳተፈ የእርቅ እና የሠላም ስነ-ሰረአት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላም ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ በራቸው ድረስ በመሄድ ለመሥራት ተዘጋጅተናል፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ
.
.
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአማራ ሕዝብ ክልል ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የአብመድን በጎበኙበት ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ ለመሥራት በራቸው ድረስ ለመሄድ ተዘጋጅተናል›› ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ በቅድሚያ የሚጠቅመው የክልሉን መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ‹‹የአማራ ክልል ሕዝብ ከክልሉም ውጭ ስለሚኖር የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታ የአማራ ክልልም ጉዳይ በመሆኑ ከክልሎች ጋር አብረን ለመሥራት ተዘጋጅተናል›› ነው ያሉት፡፡
‹‹ወደ ስልጣን የመጣሁበት ወቅት የክልሉ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው መልኩ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረበት ነው›› ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ክልሉን ከዚህ ቁዘማ ለማውጣትና የፀጥታ ስጋት የማይፈጠርበት እንዲሆን እየሠሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ማስጠበቅ የፀጥታ ኃይሉ ብቻ ኃላፊነት አለመሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ‹‹የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ብዙኃን መገናኛ ለክልሉ ሕዝብ ሠላም አበክረው ሊሠሩ ይገባል›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡
የሕዝቡን የሠላምና የፀጥታ ስጋቶች በመለዬት መሥራት የሚዲያው ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ እሴቶችን ሽፋን መስጠት ላይ ሚዲያዎች እንዲያተኩሩም ጠቁመዋል፡፡

#አምቦ
በአምቦ ከ5መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፖለቲካ ኃላፊም አባላትና፣ ደጋፊዎቼ እንዲሁም አመራሮቼ ታስረዋል ብሏል፡፡ የከተማው ፖሊስ መምሪያ የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል፡፡

‹‹ለክልሉ ሕዝብ ሠላም ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ በራቸው ድረስ በመሄድ ለመሥራት ተዘጋጅተናል›› - ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከተንከባከብነው የማይፀድቅ ችግኝ የለም። ካስተማርነው የማይለወጥ እና የማያድግ ወጣት የለም።" አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
.
.
"ከተንከባከብነው የማይፀድቅ ችግኝ የለም። ካስተማርነው የማይለወጥ እና የማያድግ ወጣት የለም" የሚሉ እና ሌሎች መርኾችን በመያዝ የአረንጓዴ ልማትን ለመደገፍ የመልካም ወጣት 2011 "መልካም ወጣት ለኢትዮጵያ አንድነት" የመጀመሪያው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ትላንት በሀዋሳ ታቦር ተራራ ተከናውኗል።
በዚህም የችግኝ ተካላ መርሀግብር አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ: የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና አባላት: የማርሲል ቴሌቪዥን ሰራተኞች እና ከ4000 የሚበልጡ የመልካም ወጣት የ2ኛው ዙር ሰልጣኞች ተሳትፈውበታል።
የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 22 በአረንጓዴ አሻራ ቀን በአንድ ጀንበር 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተያዘው ዕቅድ ለመሳተፍም ማር ሲል ቴሌቪዥን ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገልጿል።
Via #ማርሲል_ቲቪ

የእጅ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ...
በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በሕገ ወጥ መንገድ የተቀመጠ የእጅ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ባልደረባ ኮማንደር ናስር ኡመር ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት አደጋው በ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ላይ የደረሰው ትናንት ነበር።
አደጋው የደረሰው በከተማዋ ምዕራብ ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የተቀመጠ ቦምብ ወጣቷ ስትነካካት እጇ ላይ በመፈንዳቱ ነው ብለዋል፡፡
በአደጋው በቤት ውስጥ በነበረ ንብረት ላይም ጉዳት መድረሱንም ገልጸዋል።
ፖሊስ ቦምቡን አስመልክቶ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ኮማንደር ናስር አስረድተዋል። ኅብረተሰቡ ሕገወጥ መሳሪያዎችን በቤት ውስጥ ደብቆ ማስቀመጥ ወንጀል መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
Via #ENA

#update የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 72ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከስብሰባው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ
የጅማ ከተማ ምክር ቤት ከተማውን በአራት ክፍለ ከተሞች ለማዋቀር ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ጉባዔ አጠናቋል። በከተማው 17 የነበሩት ቀበሌዎች ወደ 23 እንዲያድጉም ውሳኔ ተላልፏል።

#ቢቂላ_አዋርድ
በካናዳ ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ትምህርት ክፍልን ለማጠናከር የአበበ ቢቂላ የባዶ እግር የሩጫ ውድድር (ቢቂላ አዋርድ) ሊካሄድ ነው። የባዶ እግር ሩጫው የተዘጋጀው በካናዳ ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ትምህርት ክፍልን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
የባዶ እግር የሩጫ ውድድሩ ዛሬ በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ታዋቂዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች በተገኙበት እንደሚከናወን ተገልጿል። የካናዳ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በካናዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት እና የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋሉ።
ምንጭ፡- ኢዜአ

#ደኢ01
ደኢሕዴን ለሰባት ወራት በልሒቃን ያሰራው የተባለ ጥናት የመጀመሪያ ክፍል በ-ዘፊንፊኔ ኢንተርሰፕት በኩል ይፋ ሆኗል። ይፋ የሆነው የሰነዱ ክፍል 59 ገፆች ያሉት ሲሆን የደቡብን ፖለቲካ ለሚከታተሉ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ጠቃሚ መረጃዎች ይገኙበታል። የደቡብ ክልል እና የዛሬው ደኢሕዴን እንዴት ተፈጠሩ የሚለው ታሪካዊ ዳራ በመግቢያው ላይ ይገኛል።
በመግቢያው የጥናቱ አከናዋኞች «የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለምን እንደተበራከቱ፤ ከዚህ በፊት በተሰጡ መልሶች የአደረጃጀት ጥያቄዎች መልስ ለምን ዘላቂ መሆን እንዳልቻለ፤ ከሀገራት ተሞክሮ አንጻር ዘላቂ የሆነ አደረጃጀት እንዴት እንደሚፈጠር፤ ከአደረጃጀት መስፋት ወይም መጥበብ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ፤ አደረጃጀት ኅብረ-ብሔራዊ ብዝኃነት ባላቸው ሀገሮች እንዴት እንደተተገበረ ወዘተ በማሰስ ለውሳኔ ሰጪው አካል ምክረ-ሀሳብ እናቀርባለን» ሲሉ ቃል ይገባሉ። ይሁንና በፌስቡክ በኩል በተሰራጨው ሰነድ ባለሙያዎቹ የደረሱበትን ድምዳሜ የያዘው ክፍል አይገኝም።
ባለሙያዎቹ የደቡብ አፍሪካን፣ የኬንያን፣ የናይጄሪያን እና ያደጉ አገራትን የፌድራላዊ መንግሥት አወቃቀር ለመፈተሽ መሞከራቸውን የሚያሳይ ክፍል አለው። በሰነዱ መሠረት በቃለ-መጠይቅ፤ በቡድን ውይይት እና ሰነዶችን በመፈተሽ ጥናቱ ተከናውኗል። ጥናቱ ከክልሉ 21 ሚሊዮን ነዋሪዎች በሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ያዳረሰ መሆኑን ቢጠቁምም ከጥቂት ቀናት በፊት ባለሙያዎቹ ካሉት ይጋጫል። ባለሙያዎቹ የሲዳማ ዞን እና የሐዋሳ ከተማ አለመካተታቸውን ገልጸው ነበር።
(PS፦የሰነዱ ትክክለኛነት አሊያም በጊዜ ሒደት የተቀየረ ነገር ይኑረው አይኑረው የተረጋገጠ አይደለም፤ በፌስቡክ በኩል ሲሰራጭ የክልሉ መንግሥት እና የደኢሕዴን ይሁንታን ስለማግኘቱም የታወቀ ነገር የለም)
Via #ESHET_BEKELE

#update ከማእድን ዘርፍ የሚገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ መምጣቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። የማእድን ዘርፍ በ2004 በጀት አመት 654 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት ከቡና ቀጠሎ በሁለተኛ ደረጃ የሃገሪቱ ከፍተኛ የውጥ ምንዛሪ ምንጭ ነበር። በ2002 እና በ2005 የበጀት አመታት ከአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ውስጥ የማእድን ዘርፉ በተለይም የወርቅ ማእድን የ19 በመቶ ድርሻ ነበረው። ይሁንና በ2010 በጀት አመት በ3•6 በመቶ ዝቅ ብሏል። በ2011 ም በ3•3በመቶ ዝቅ ብሎ 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገልጿል። የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፣የተለያዩ ፖሊሲዎችና የህግ ማዕቀፎች በተሟላ መልኩ አለመኖር፣ በቂ አቅም ያለው የሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ አለመኖር እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆን ለዘርፉ ውጤታማ አለመሆን ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA_2019
ታዋቂው ባለሃብት አቶ ድንቁ ደያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የOSA conference ላይ ተገኝተው ለታዋቂው ምሁር ዶ/ር #ገመቹ_መገርሳና ለባለቤታቸው ዶ/ር አኒሳ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክተዋል። በተጨማሪም ለታዋቂው ምሁርና የገዳ ተመራማሪ ፕሮፌሰር #አስመሮም_ለገሰ የ200,000 ብር ስጦታ አበርክተዋል።
Via THE FINFINNE INTERCEPT