TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ወደ ገደብ ወረዳ በመጓዝ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ #የጌዲዮ ማኅበረሰብ አባላትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎበኙ። ተፈናቃዮቹ #ቅሬታቸውን ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ አቅርበዋል። በአሁኑ ሰዓት ጠ/ሚሩ ከተፈናቃዮቹ ተወካዮች ጋር ረጅም #ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። ፌዴራል መንግሥት ከዞንና ክልል አስተዳደር ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በቀረበ ጥሪ መሠረት በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከመጋቢት 2 ቀን 2011 ጀምሮ አስቸኳይ የምግብና ሌሎችም አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለተረጂዎች በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ ዞን

ክቡር ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ እባኮት ወደጎዲቲ አምርተው ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ ቢጎበኙ መልካም ነው። እጅግ በጣም የተጎዱ ወገኖች በብዛት የሚገኙበት ቦታ እንደሆነ አካባቢው በተደጋጋሚ የጎበኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

በነገራችን ላይ ...

ክብርት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል የጌድኦ ተፈናቃዮችን በጎበኙበት ወቅት በርካቶች የተጎዱበትን ቦታ ሳይጎበኙ ነው የተመለሱት፤ ይህን ያጫወተኝ በጌዴኦ ተፈናቃዮች ዙሪያ የሚሰራ የህክምና ባለሞያ ነው።

የትኛው አካል ነው ይህ እያደረገ ያለው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የከተማዋን ነዋሪ በማስተባበር የቁሳቁስ እና ሌሎች ዕርዳታዎችን የሚያሰባስብ ኮሚቴ በከተማ አስተዳደሩ ተዋቅሯል፡፡

ይህም ኮሚቴ ከከተማዋ ነዋሪ የሚሰበስበውን ቁሳቁስ በመያዝ በዚህ ሳምንት በቦታው በመገኘት ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️

ለበርካታ አመታት በህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በሙያው ሀገሩን ሲያገለግል የኖረው በተለይም የጎንደርን ህዝብ የአይን ሀኪም senior ophthalmologist በአለም አቀፍ የአይን የጤና ማህበር የ 2015 ተሻላሚው ዶ/ር #ያሬድ_አሰፋ በድንገት አረፈ። ነብስ ይማር! ለወዳጅ ዘመዶች በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!

Via Endale Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ኬንያ በቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሲጓዙ ቢሾፍቱ አካባቢ #በመከስከሱ ሕይወታቸውን ያጡ ተጓዦችና የበረራ ሠራተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት #በቅድስት_ሥላሴ_ካቴድራል ተፈጽሟል።

ፎቶ፦ ዳንኤል ጌታቸው/ሪፖርተር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናይሮቢ🔝

ዛሬ በናይሮቢ መድኃኒያለም ቤተ ክርስትያን፤ ባለፈው ሳምንት መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ኢቲ 302፤ ሕይወታቸውን ላጡ 157 መንገደኞች የመታሰቢያ ፀሎት ተደርጓል።

በፀሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መለስ ዓለም፣ የፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን መልዕክት ያስተላለፉት አምባሳደር ማቻሪያ ካማዎ፣ በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር አቶ በየነ ርዕሶም እንዲሁም የኢትዮጵያውያንም የኬንያውያንም ሟች ቤተስቦችና ተወካዮቻቸው ተገኝተው ነበር። የሩስያና የታይላንድ የኤምባሲ ተወካዮችም እንዲሁም ሌሎች ዲፕሎማቶች በፀሎት ሥነ ሥርዓቱ ተገኝተዋል።

በፀሎት ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉትና የአውሮፕላኑ አደጋ በደረሰበት ዕለት ወደ ናይሮቢ የመጡት አቶ መለስ ዓለም በተከሰከሰው አውሮፕላን #ሊሳፈሩ እንደነበርም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ደብዳቤ ጻፈ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ #የሐሰት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃው “በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ የሐሰት መሆኑን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ እፈልጋለሁ” ብሏል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እንዲህ ያለ ደብዳቤ እንዳልጻፉ ማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በዚህ አጋጣሚ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲህ የመሰሉ የሐሰት ዜናዎችን እያጣሩና #በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia