TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
" መልሼ አጤነዋለሁ " - ሶማሊያ የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ " መልሶ ለማጤን " ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ " የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል " ሲሉ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ…
#Ethiopia #Somalia

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ።

በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ከኢፌዴሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንቱ የተላከ መልዕክትን አድርሰዋል።

" በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶማሊያ እና በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል " ያለው ሚኒስቴሩ " ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የAUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል " ሲል ገልጿል።

በቅርቡ የሶማሊያ ከፍተኛ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ ውይይት ለማካሄድ መስማማታቸውም ተመላክቷል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብድርቋድር ኑር ጃማ ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሶማሊያን ሰላም ለማረጋገጥ ለከፈለው መስዋትነት እና ላበረከተው አስተዋጽዖ ያላቸው አክብሮት እና ምስጋና ማቅረባቸው ተነግሯል።

#MinistryofForeignAffairsofEthiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት…
#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

በአሜሪካ ሀገር በደቡባዊ ካሊፎርኒያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

19 ሰዎችም ተጎድተዋል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ፉለርተን በተሰኘ ከተማ በአንድ የፈርኒቸር ውጤቶች ማምረቻ ህንጻ አናት ላይ ነው።

በህንጻው ውስጥ 200 የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ ላይ ነበሩም ተብሏል።

የሞቱት ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካካል እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በህንጻው ውስጥ ስራ ላይ የነበሩት ናቸው።

አውሮፕላኑ ፉለርተን ከተባለ ኤርፖርት በተነሳ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው በህንጻው አናት ላይ የተከሰከሰው።

መንስኤው እየተጣራ መሆኑን የኤፒ መረጃ ያሳያል።

ሰሞኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ አደጋዎች ተደጋግመው ተሰምተዋል።

በደቡብ ኮሪያ ሙዋን ሲያርፍ የነበረ አውሮፕላን ላይ አደጋ ደርሶ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 179 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

ሌላው ምንም እንኳን የተመዘገበ እጅግ የከፋ ጉዳት ባይኖርም በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ 71 መንገደኞችን የጫነ አውሮፕላን በእሳት መያያዙና በሚያስደነግጥ ሁኔታ መቆሙ ሰሞኑን ከተሰሙት ክስተቶች መካከል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum " በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ባልወጣበት ፤ የነበረውን የአለባበስ ስርዓት የሚቀይር አዲስ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። ቢሮ ለአክሱም የትምህርት ፅህፈት ቤት በፃፈው ደብዳቤ ፤ " ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ምን ዓይነት አለባበስ መከተል እንዳለባቸው የሚያዝ የቆየ መመሪያ…
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን "  - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚሁ መግለጫ " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ብሏል።

" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወስዳለን " ሲልም ገልጿል።

መግለጫውን የተከታተለው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጫው " ጠንከር ያለ ነበር " ብሏል።

ዝርዝሩ እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake  ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል። የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ። በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ።

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው " የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር " ብለዋል፡፡

መረጃው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (FMC) ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን "  - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ " የፌደራል…
#Update

" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃዎችን እንስወዳለን "   - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ 160 የያዝነው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ ጠቅሷል።

ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።

ምክር ቤት ባወጣው የ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ፦

1. የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው።

2. የትምህርት ቤቶች ህግ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች የሚፃረር መሆን የለበትም። በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ ተደንግጓል ስለሆነም ጥያቄያችን በዚሁ ደንብ በአስቸኳይ እንዲመለስ እንጠይቃለን።

3. ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን።

4. በጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን።

5. ጉዳዩ በማንኛውም መልኩ ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀምያ ማዋል ስለማይገባ ጉዳዩ እንዳይፈታ የሚያወሳስቡት ግለሰቦች ወይም አካላት መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ እናቀርባለን።

6. ኢ-ህገመንግስታዊ  ተግባሩን የሌሎች እምነት ተከታዮች እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች እንዲያወግዙት ጥሪ እናቀርባለን።

7. ከትምህርት ገበታ የተስተጓጎሉት ተማሪዎች የትምህርት ሚንስቴር ያወጣው ሁሉም ትምህርት ቤቶች መፈፀም የሚገባቸው የአለባበስ ሁኔታ የሚመለከት ህግና ደንብ ያልጣሱ ስለሆነ ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን።

8. ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ እየተደረገ ያለው ተግባር ሰብአዊ መብቶች ፣ ክልላዊ ፣ አገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ህጎች የሚፃረር በመሆኑ በጥብቅ እንኮንነዋለን።

9. ከትምህርት ሚንስቴር መመሪያ እና ደንብ ባፈነገጠ መልኩ በግል ፍላጎት ብቻ በመመራት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ህገ-ወጥ ተግባር የፈፀሙት ግለሰቦች እና አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጥሪ እናቀርባለን።

10. የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲወገዝ ድጋፍ የቸራችሁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ምክር ቤቱ ምስጋና ያቀርባል።

11. ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች ለህዝባችን እናሳውቃለን።

... ብሏል።

መረጃውን የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
🏑 የገና ስጦታ 100ሺህ ብር እና 50ሺህ ብርን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን ለዕድለኞች አበረከተ!!
አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ🎉🎉

ሽልማቱ ገና አልተነካም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ዕድልዎን ይሞክሩ፤ እስከ 100 ሺህ ብር ስጦታዎን ይውሰዱ!

🗓 እስከ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም ብቻ!

👉 ለተጨማሪ https://youtu.be/n39oHwYVXco ቤተሰብ ይሁኑ!


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ። ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ…
" እዛ አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል " -የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል።

ሁኔታውን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሊ ሷሊህ ፥ " ቅድሚያ ህይወት የማዳን ስራዎች እና ነዋሪዎችን አደጋው ከተፈጠረበት አካባቢ የማሸሽ ሥራ ከክልሉ መንግስት ጋር እየተሰራ ነው " ብለዋል።

" ማህበረሰቡ ደህንነቱ ወደ ተረጋገጠ አካባቢ ከመጣ በኋላ የችግሩን ስፋት እና መጠን የሚገመግም እና ምን ያህል ማህበረሰብ እርዳታ ይፈልጋል የሚለውን ለመለየት የሚያስችል ቡድን አዋቅረን ዛሬ ጠዋት ወደ አካባቢው ልከናል " ብለዋል።

" ጉዳዩ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል መጠለያ ጣቢያ ያስፈልጋል የሚለው በውል አልታወቀም "  ያሉት ሃላፊው " ዱለቻ አካባቢ ከሁለት ቀበሌዎች እንዲሁም አዋሽ ፈንታሌ ሳቡሬ አካባቢ በርካታ ሰዎች እየወጡ ነው ሦስት መጠለያ ጣቢያዎች ያስፈልጋሉ ብዬ አስባለሁ ትክክለኛ ቁጥሩን የምናውቀው የላክነው ቡድን መረጃውን ይዞ ሲመጣ ነው " ብለዋል።

አክለውም ፥ " ችግሩ ሊቀጥል እና ሊሰፋ ይችላል በሂደት ላይ ያለ ነገር ስለሆነ ተጨማሪ ቀበሌዎች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል እዛ አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል " ነው ያሉት።

አቶ አሊ ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድን መረጃዎችን ሰብስቦ ይመለሳል ያሉ ሲሆን ውጤቱ እንደቀረበ በ 72 ሰዓት ውስጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake  ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል። የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ። በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Earthquake

በዛሬ ሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

ትላንት ለሊት በሬክተር ስኬል 5.0 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ ዛሬ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

ከትላንት ለሊቱ በኃላ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.5
➡️ 4.7
➡️ 4.5
➡️ 4.5
➡️ 5.2 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እንደነበሩ የአሜሪካ ጆኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያሳያል።

በሬክተር ስኬል 5.2 በቅርብ ሰዓታት እና ባለፉት ቀናት ከተመዘገቡት ከፍተኛው ሆኗል።

ከመተሀራ 32 ኪሎ ሜትር ርቀር ላይ የተመዘገበው ይኸው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ተሰምቷል።

በሌለ በኩል ደግሞ ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀት በተደጋጋሚ እየተከሰተ በሚገኝባቸው የአፋር አካባቢዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እየተስተዋል ይገኛል ተብሏል።

ቪድዮ ፦ Enike

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake በዛሬ ሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ትላንት ለሊት በሬክተር ስኬል 5.0 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ ዛሬ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። ከትላንት ለሊቱ በኃላ በሬክተር ስኬል ፦ ➡️ 4.7 ➡️ 4.5 ➡️ 4.7 ➡️ 4.5 ➡️ 4.5 ➡️ 5.2 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እንደነበሩ…
#Earthquake

ዛሬ ምሽት 2:01 ላይ በሬክተር ስኬል 5.5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በዓለም ዙሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ  (USGS) አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 44 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከተሰቱ ተመላክቷል።

የዛሬ ምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ከእስካሁኖቹ ከፍ ያለ ነው።

ንዝረቱ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ። ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" አሁን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ማብቃቱ አይቀርም፤ ነገር ግን መች እንደሚያበቃ ማወቅ አይቻልም " - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

" ዛሬ በአፋር ክልል ፥ በዱለቻ ወረዳ በዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው ጭስ እና እንፋሎት የሚመስል ነገር እሳተ ገሞራ ሳይሆን በሙቀት አካባቢ ያለው የእንፋሎት ውኃ በኃይል እየተወረወረ በመውጣቱ የተፈጠረ ክስተት ነው።

በተፈጠረው ሁኔታ እሳት አይታይም ፤ ወደፊት አለት ሊረጭ እንደሚችል አመላካች ሊሆን ይችላል።

ከመስከረም ወር ጀምሮ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ንዝረቱ እየተሰማ ነው።

ከሰሞኑን በሬክተር ስኬል ከፍ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጦች በፈንታሌ እና ዶፈን አካባቢ ተከስተዋል።

የመሬት መንቀጠቀጡ በተደጋጋሚ መከሰቱ በአካባቢው እንዲሁም ንዝረቱ በሚሰማባቸው አካባቢዎች ጫና እየፈጠረ ነው።

በተለይም በአካባቢው በነበሩ በባህላዊ መንገድ የተሠሩ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

የዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተሰማ ነው። ለዚህም መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች አሉ። እነዚህም ፦

➡️ ቁምሳጥን ላይ የሚቀመጡ ውድ እና ተሰባሪ እንዲሁም ተቀጣጣይ የሆኑ ዕቃዎችን መሬት ላይ ማስቀመጥ፣

➡️ ቅጽበቱ እስኪያልፍ ማዕዘን አካባቢ መቆም፣

➡️ ጠረጴዛ ስር እና ጭንቅላትን መከላከል በሚያስችል ቦታ መከለል መደረግ ካለባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች መካከል ናቸው።

የመሬት መንቀጥቀጥን መተንበይ አይቻልም ያደጉ ሀገራት የጥፋት መጠኑን ሕዝባቸውን በማስተማር እንዲሁም በሕንፃ አሠራር ቴክኖሎጂ መቀነስ ችለዋል።

አሁን ላይ እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ማብቃቱ አይቀርም፤ ነገር ግን መች እንደሚያበቃ ማወቅ አይቻልም
"

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤኤምኤን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የዘር ፍሬ ልገሳ ማከናወንን የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ " ይሰኛል። አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ፦ - ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ - ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ - ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤ - ስለ…
#ኢትዮጵያ

ሰሞኑን በፓርላማ የፀደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?

➡️ የዘር ፍሬ በመለገስ ልጅ መውለድ እንዲቻል ለመፍቀድ ቀርቦ የነበረው የአዋጅ ድንጋጌ የለበትም።

➡️ በመሣሪያ ላይ የተመሠረተ አተነፋፈስ ማቋረጥ ተፈቅዷል።


" የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ " ለ3 ወር ያህል ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ከቀናት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ9 ድመጸ ተአቅቦ ፣ 1 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።

የዘር ፍሬን በመለገስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ልጅ መውለድ እንዲቻል እንዲፈቅድ በረቂቅ ሕጉ ተካቶ የነበረው አንቀጽ እንዲወጣ ተደርጓል።

ለጤና፣ ማኅበራዊና ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት ሲደረግበት በነበረው ረቂቅ አዋጅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት የሚፈቅደው ድንጋጌ እንዲወጣ ተጠይቆ ነበር።

ድንጋጌው እንዲወጣ ያደረገው " ልጅ እንዲኖረው የፈለገ ምን ይሁን ? " ለሚለው ጥያቄ፣ የጉዲፈቻ ልጅ በበቂ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተነጋግሮበት በመወሰኑ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ድንጋጌው ከረቂቁ እንዲወጣ የተደረገው ወላጆች ልጅ ለመውለድ ያላቸውን ፍላጎት ሳይሆን፣ ሕግ አውጪው የሚወለዱ ልጆች የማኅበረሰብ ቀውስ እዳያጋጥማቸው በማሰብ፣ ከእምነትና ከማኅበረሰብ መስተጋብር ጋር የተጣጣመ ሕግ መውጣት እንዳለበት ታስቦ ነው።

በተጨማሪም ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ ድንጋጌ ማውጣት ስለማይፈቀድ ነው።

ለተጋቢ ባለትዳሮች ፍላጎት ሲባል ይህ ሕግ ወጥቶ የሚወለደውን ሕፃን መብት መጋፋት አያስፈልግም።

ይሁን እንጂ የፀደቀው ሕግ በጋብቻ የተጣመሩ ባለትዳሮች ያለ ልገሳ የራሳቸውን የዘር ፍሬ ብቻ በመውሰድ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል " ብለዋል።

ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ሕግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ ወይም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይል ነበር፡፡

የምክር ቤት አባላት የዘር ፍሬን በሕጉ ከተፈቀደው ውጪ አሳልፎ የሰጠ አካል ከተገኘ በወንጀል ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዋጁ አንቀጽ 14 በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡

በዚህ ድንጋጌ በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓትን ማቋረጥ የሚቻለው፣ የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

አፈጻጸሙ አግባብነት ባላቸው ሶስት ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia