TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል። የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን 36 ኪ/ሜ በኩል ነው የተመዝገበው። የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ እና ቦታዎችም የተሰማ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ንዝረቱ በደንብ ይሰማ ነበር። አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ " የመሬት ንዝረት እየተሰማ ነው…
#Earthquake

ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል።

እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል።

ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው።

ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ነው።

ንዝረቱ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል። እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል። ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው። ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ…
#Earthquake 

ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል።

የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ።

በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም መንቀጥቀጡ ካየለበት ስፍራ ሸሽተው ለመውጣት ተገደዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተትና ተከትሎ የሚመጣው ንዝረት ድግግሞሹ የቀጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ " ምንም ነገር አይፈጠርም ፤ ለምደነዋል " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እንላለን።

አያድርገውና እጅግ የከፋ ነገር በሚመጣበት ጊዜ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዘውትር አስታውሱ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake  ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል። የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ። በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Earthquake

በዛሬ ሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

ትላንት ለሊት በሬክተር ስኬል 5.0 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ ዛሬ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

ከትላንት ለሊቱ በኃላ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.5
➡️ 4.7
➡️ 4.5
➡️ 4.5
➡️ 5.2 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እንደነበሩ የአሜሪካ ጆኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያሳያል።

በሬክተር ስኬል 5.2 በቅርብ ሰዓታት እና ባለፉት ቀናት ከተመዘገቡት ከፍተኛው ሆኗል።

ከመተሀራ 32 ኪሎ ሜትር ርቀር ላይ የተመዘገበው ይኸው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ተሰምቷል።

በሌለ በኩል ደግሞ ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀት በተደጋጋሚ እየተከሰተ በሚገኝባቸው የአፋር አካባቢዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እየተስተዋል ይገኛል ተብሏል።

ቪድዮ ፦ Enike

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake በዛሬ ሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ትላንት ለሊት በሬክተር ስኬል 5.0 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ ዛሬ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። ከትላንት ለሊቱ በኃላ በሬክተር ስኬል ፦ ➡️ 4.7 ➡️ 4.5 ➡️ 4.7 ➡️ 4.5 ➡️ 4.5 ➡️ 5.2 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እንደነበሩ…
#Earthquake

ዛሬ ምሽት 2:01 ላይ በሬክተር ስኬል 5.5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በዓለም ዙሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ  (USGS) አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 44 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከተሰቱ ተመላክቷል።

የዛሬ ምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ከእስካሁኖቹ ከፍ ያለ ነው።

ንዝረቱ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake

ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.6
➡️ በድጋሚ 4.7
➡️ በድጋሚ 4.6
➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

ሁሉም አዋሽ እና አካባቢው ናቸው።

ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል አፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።

በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

አሁን ላይ መሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ ሁኔታ በአከባቢው እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉ ተነግሯል።

ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በተያያዘ መረጃ ፥ መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ አካባቢዎች ነዋሪዎችን የማራቅ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።

በተለይም ደግሞ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማስፈር ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

#Ethiopia #Afar #Earthquake

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴና ወደ ላይ የመውጣት ግፊቱ እንደቀጠለ ነው።  ግን ቀዝቅዞ እዛው ሊቀር፣ ከመሬት በላይ ሊፈነዳ ይችላል ” - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በአዋሽ ፈንታሌና ዶፈን ቮልካኖዎች መካከል የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከርና ከፍ እያለ መምጣቱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰሞኑንም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ተስተውሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመሆኑ ምን መደረግ አለበት?…
#Earthquake

በአፋር ክልል አዋሽና አካባቢው እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።

ትላንት ቀን እንዲሁም ለሊቱን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በመዘገበው ብቻ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ 4.7 ፣ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ከሁሉም ከፍ ያለው ለሊት የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ አዋሽ እና አካባቢው በርካታ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅስቋል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው በነበረው ቃል ፤ ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል ሲሆን የሚታየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።

የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake በአፋር ክልል አዋሽና አካባቢው እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ትላንት ቀን እንዲሁም ለሊቱን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በመዘገበው ብቻ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ 4.7 ፣ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ከሁሉም ከፍ ያለው ለሊት የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ አዋሽ እና…
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር።

በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት  መንቀጥቀጡ እና ንዝረቱ ከእንቅልፋቸው እንደቀሰቀሳቸውና ጠንክሮ እንደተሰማቸው መልዕክት ልከዋል።

በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጠንከር ብሎ ንዝረቱ ተሰምቷል።

ከንዝረቱ ጋር በተያያዘ መልዕክት የላከ የቤተሰባችን አባል ፥ " 7:09 ለቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቶናል ከዚህ በፊት ተሰምቶን አያውቅም ፤ ኳስ እያየን ቆይተን በጥቂቱም ቢሆን ለ 5-10 ሰከንድ የቆየ ንዝረት ተሰምቶናል ፤ Odd የሆነ ስሜት አለው ግራ መጋባት ፈጥሮብን ነበር " ብሏል።

ውድ ቤተሰቦቻችን የጥንቃቄ እርምጃዎችን አንብቡ 
https://yangx.top/tikvahethiopia/93267?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🚨 #Alert ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 23 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.0 መመዝገቡን አሳውቋል። የአሜሪካ ጃኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 መለካቱን አመላክቷል። ንዝረቱ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች ተሰምቷል። @tikvahethiopia
#Earthquake

ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ አዋሽና አካባቢው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶቹ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረታቸው ተሰምቷል።

ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ፦
👉 4.6
👉 4.5
👉 5.2
👉 4.3
👉 5.2 የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

በተለይ 5.2 የተመዘገቡት ሁለቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገቡት ከፍተኛው ሲሆኑ በተለይ አንዱና ለሊት ላይ የተከሰተው ሰዎችን ከእንቅልፍ ያባነነ ጭምር ነበር።

አሁንም አዋሽ እና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ ተደጋግሞ እንደቀጠለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ አዋሽና አካባቢው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶቹ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረታቸው ተሰምቷል። ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ፦ 👉 4.6 👉 4.5 👉 5.2 👉 4.3 👉 5.2 የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።…
#Earthquake

" ቅልጥ አለቱ ባለፈው መስከረም ሲጀመር እስከ 10 ኪሎ ሜትር ነበር፤ በመሀል ቆም ብሎ ነበር፤ አሁን ግን እስከ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል " - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)

በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል መሬት ውስጥ ያለው ቅልጥ አለት ወደ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር ማዳረሱ ተነግሯል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

(ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሰጡት ቃል)

" በተራራዎቹ መካከል መሬት ውስጥ ያለው ቅልጥ አለት ወደ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል።

የርዕደ መሬቱ መነሻ በሁለቱ ተራራዎች መካከል ያለ ነው።

የንዝረቱ መጠን ቢለያየም አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ፣ መተሀራ እና ደብረ ብርሃን  ድረስ ተሰምቷል።

በአዋሻ አርባ፣ በሳቡሬ፣ በመተሀራ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው የንዝረት መጠኑ ከፍተኛ ነው።

ከፈንታሌ ወደ ዶፈን ባለው አቅጣጫ የውስጥ ለውስጥ ቅልጥ አለቱ ባለፈው መስከረም ሲጀመር እስከ 10 ኪሎ ሜትር ነበር፤ በመሀል ቆም ብሎ ነበር፤ አሁን ግን እስከ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል።

አዲስ አበባን ጨምሮ እየተከሰተ ያለው የንዝረት መጠን መነሻው በተራራዎቹ አካባቢ ነው በተለይም እዛው አካባቢ ቤቶችን እና ህንፃዎችን ሊያፈርስ ይችላል።

ቅልጥ አለቱ መሬት ውስጥ ሊቀር ይችላል በተቃራኒው ደግሞ እሳተ ገሞራ በማንኛውም ሰዓት ወደ ገፀ መሬት ሊወጣ የሚችልበት ዕድልም ስላለ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

በአካባቢው የፈላ ውሃ ፈንድቶ ፍል ውሃው ስብርባሪ ድንጋይ ይዞ ወደ ላይ እየወጣ ነው ወደ ላይ የሚፈነዳው ውሃ ከፍተኛ ሙቀት ያለው፣ ሰልፈር ዳይኦክሳይድና ሌሎች መርዛማ ጋዞችን የያዘ በመሆኑ ለሰው ልጆች ጤና አደገኛ ነው።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምድር ክፍል ቡድን ሰሞኑን እየወጣ ባለው ፍል ውሃ ባደረገው የናሙና ምርመራ፤ ውሃው ለእንስሳትም፣ ለሰው ልጅም አገልግሎት የማይሆን በመሆኑ ህብረተሰቡ ሊጠቀመው አይገባም።

የሰዎች ወደ ፍንዳታው ሥፍራ መጠጋት ችግር ሊያስከትል ስለሚችል ማህበረሰቡ በተቻለ መጠን ከአካባቢው ራቅ ማለት አለበት። "


ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ አዋሽና አካባቢው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶቹ አዲስ አበባ ድረስ ንዝረታቸው ተሰምቷል። ከትላንት ለሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ምሽት 12:20 ድረስ በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ፦ 👉 4.6 👉 4.5 👉 5.2 👉 4.3 👉 5.2 የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።…
#Earthquake : ዛሬ ሰኞ ምሽት 5:24 ሲል በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ተሰምቷል።

" አሁን ላይ ቀንሷል ቆሟል ፣ ከአሁን በኃላ ምንም ነገር አይፈጠርም " በሚል መዘናጋት ጥንቃቄ እና ትኩረት ማጣት እንዳይመጣ መጠንቀቅ ይገባል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ቅፅበታዊ  ፣  ተገማች ያልሆነና መተንበይ የማይቻል ነገር በመሆኑ ዘውትር ነቅቶ መጠበቁ የተሻለ ነው።

@tikvahethiopia
#Earthquake

ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በዓዲግራት ፣ በዓድዋ፣ ፣ ወቕሮ ፣ መቐለ ጨምሮ በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች ከቀኑ 5:30 ጀምሮ ለሰከንዶች የቆየ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘርት ተከሰተዋል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ከዓዲግራት 46 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንባር ላይ መከሰቱ ተነግሯል።

@tikvahethiopia