TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ ቀንድ 🇸🇴🇪🇹🇰🇪

እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ በአፍሪካ ቀንድ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች #በድርቅ#በግጭት እና #በምግብ_ውድነት ምክንያት አስከፊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ላሉ ቤተሰቦች እገዛ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

#ShareTheMeal (በUN | WFP ስር ያለ) በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ቤተሰቦች የድንገተኛ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ለዚሁ ስራ የሚውልን ገንዘብ ከለጋሾች በመተግበሪያው እንዲሁም በድረገፁ በኩል እያሰባሰበ ይገኛል። https://t.co/rjY1JlrJTl

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት #ነፃ እና #አስገዳጅ እንደሚሆን አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ይደረጋል " ብለዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን ገልፀው መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/MoE-08-16 (ኢቢሲ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲሱ ስርዓተ ትምህርት " የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ…
#HappeningNow #AddisAbaba

በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ በሚግባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዙሪያ ውይይት ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ስልጠና እና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባውን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ ከግል እና መንግስታዊ ካልሆኑ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ መካሄድ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደተገኘው መረጃ ፤ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የ2ኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

@tikvahethiopia
#Scotland

ስኮትላንድ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን የሚያስከብር ሕግን ማፅደቋን ቢቢሲ አስነብቧል።

ወዲያው ተግባራዊ እንዲሆን የተደረገው ሕግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን ለመጠበቅ አዲስ ሕግ ያወጣች የዓለማችን የመጀመሪያዋ አገር በመሆን እንድትመዘገብ አድርጓታል።

በዚህ ሕግም ሕዝብ የሚገለገልባቸው ህንጻዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ሌሎች ተቋማት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን #በነጻ_ለማቅረብ ይገደዳሉ።

የየአካባቢው ባለሥልጣናት ማንኛውም ምርቶችን የሚፈልግ ሰው በነጻ እንዲያገኝ የማመቻቸት ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#Amhara

አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም ፦

አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሲሾሙ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ም/ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኀላፊ አድርገው ሾመዋል።

በተጨማሪም ረ/ኮሚሽነር ሠይድ አህመድ ም/ኮሚሽነር እና የአስተዳደር ልማት ድጋፍ ዘርፍ ኀላፊ እንዲሁም ረ/ኮሚሽነር እንዬው ዘዉዴ ም/ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኀላፊ አድርገው ሾመዋቸዋል።

መረጃው ከአማራ ፖሊስ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ #YALI2023

የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎ ሺፕ ፕሮግራም የ2023 (Mandela Washington Fellowship) ማመልከቻ ዛሬ ክፍት ተደርጓል።

በአህጉሪቱ ያሉ ወጣቶች ተወዳድረው #በአሜሪካ ሀገር በሚደረግ ሥልጠና ላይ እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቶላቸዋል።

ከዚህ ቀደም በርካታ #ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እድሉን ተጠቅመው ይህንን ሥልጠና ወስደዋል።

በሥልጠናው ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶችን ለማየትና ለማመልከት ይህን ይጫኑ👇
https://www.mandelawashingtonfellowship.org/apply/

👉 Application Timeline :

• August 16, 2022 | Application opens

• September 13, 2022 | Application deadline

• November 2022 – January 2023 | Semi-finalists interviewed by local U.S. embassies and consulates

• March 2023 | Applicants are notified of their status

• May 2023 | Visa processing and Pre-Departure Orientations for Finalists

June 2023 | Fellowship begins in the United States

Via @tikvahethmagazine
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተነሳበት ተቃውሞ ምንድነው ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ስራ ሊጀምር በዝግጅት ላይ በሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።

የዘመቻው ምክንያት ቅጥር የሚፈፀመው እና ውክልና የሚሰጠው አግላይ በሆነ መንገድ ነው በሚል ነው።

#በተለይ ደግሞ በድርጅቱ የሰራተኞች አቀጣጠር እና ውክልና አሰጣጥ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተወላጆች ድርጅቱ ከአድሎ እንዲታቀብ ፣ ኢትዮጵያን እንዲመስል፣ ሁሉንም እንዲያቅፍ ካልሆነ በኦሮሚያ ክልል ያለው ህዝብ የድርጅቱ ደንበኛ እንዳይሆንና አገልግሎቱን እንዳይጠቀም ዘመቻ እንደሚያካሂዱ አስጠንቅቀዋል።

ከተነሱ ቅሬታዎችና ፍትሃዊ የሆነ አሰራር ተጓድሏል ከተባሉ ጉዳዮች መካከል የሲም ካርድና ሞባይል ካርድ አከፋፋዮች ላይ አድሎ አለ፣ የህትመት የማስታወቂያ የፕሮዳክሸን ስራዎች በአድሎ ተሰጥተዋል፤ እየተፈፀመ ያለው ቅጥር በቂ ልምድ ያላቸውን የኦሮሚያ ተወላጆችን ባገለለ መልኩ ነው፤ በድርጅቱ በየእርከኑ የተመደቡ ኃላፊዎች በአድሎ የተመደቡ ናቸው፤ ድርጅቱ ኦሮሚያ ክልል ላይ አፋን ኦሮሞ ላለመጠቀም ሲያንገራግር ነበር የሚሉ ናቸው።

ጉዳዩን በተመለከተ በቀጥታ ከድርጅቱ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ፤ ነገር ግን ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ ዘመቻውን እየመሩ ናቸው ካላቸው ተወካዮች ጋር መነጋገሩን አሳውቋል።

ሳፋሪኮም በውይይቱ የተወካዮቹን ስጋት በጥሞና ማዳመጡን ገልጿል። " ሁሉንም ኢትዮጵያ ሚወክል ድርጅት ያለአንዳች ወገንተኝነትና አድሎ እየገነባን እንደሆንን አረጋግጠንላቸዋል " ብሏል።

" በማንኛውም ጊዜ ለውይይት ዝግጁ ነን " ያለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፤ " ሁሉንም ቋንቋዎች እና ባህሎች ባከበረ መንገድ ሁሉንም ኢትዮጵያ ለማገልገል ቁርጠኞች ነን " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" 18 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባታል "

" ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል " በሚል ምክንያት የሶስት ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የገደለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ግለሰቧ ትዕግስት አዘዘው ትባላለች ፤ ወንጀሉን የፈፀመችው መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አንቆርጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሿ በዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የ3 ልጆቿ አባት የሆነው ባለቤቷን ሟች አወቀ ይርዳውን " ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል፤ የተለያዩ ሴቶችንም በስልክ ታናግራለህ " በሚል ምክንያት ሶፋ ላይ በተኛበት ጭንቅላቱን በመጥረቢያ ደጋግማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጋለች።

ትዕግስት በፈፀመችው ወንጀል በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ ከተጣራባት እና ክስ ከተመሰረተባት በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ መሆኗን በማረጋገጥ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል።

የፖሊስ መልዕክት ፦

በትዳር መካከል አለመግባባቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት በመነጋገር ለመፍታት ከመሞከር እና ይህም ካልተሳካ በሰላማዊ መንገድ ከመለያየት በዘለለ በስሜታዊነት እና በቅናት መንፈስ ተነሳስቶ ወንጀል መፈፀም ከሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት ባሻገር በልጆች እና በቤተሰብ ላይ የሚያሳድረው ስነ ልቦናዊ ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ነገሮችን በሰከነ ሁኔታ ማመዛዘን ይገባል።

Via Addis Ababa Police

@tikvahethiopia
#ውብ_አረቢያን_መጅሊስ

ከአውሮፓና ከእስያ በሚመረቱ ጥሬ እቃ በብቁ ባለሞያ በዘመነ ማሽን ውብ አረቢያን መጅሊስ የሚያመርታቸውን ውብ እና ማራኪ የሆኑ መጅሊሶቻችን እና ሶፋዎችን እንካቹ ስንል 👉 በ9 ቅርጫፎቻችን ስንጠበቅዎ በታላቅ ደስታ ነው 0910222244 / 0954111133 / 0954111100
ተጨማሪ ፎቶ ለመምረጥ ሊንኩን የጫኑት https://yangx.top/wubeare
#ቻፓ

ቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጅዎች አ.ማ (ቻፓ) ለአለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ የኦንላይን ክፍያ መቀበያ አገልግሎቱን መጀመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ለንግድ ተቋማትም ሆነ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀጥታ ክፍያ ለመፈጸም አስቻይ ሁኔታዎች ብዙ የተመቻቹ ባለመሆናቸው በእጅ አዙር የሚደረጉ ክፍያዎችን መጠቀም አስገዳጅ ነበር።

አሁን ላይ " ቻፖ " ከብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተር ፈቃድ በማግኘት ወደ ገቢያው ይዞት የገባው ሥርዓት ተጠቃሚዎች መግዛት የሚፈልጉትን እቃ/ የአገልግሎት ክፍያ በቀጥታ እዛው ላይ በሀገሪቱ ባሉ 9 ባንኮች እንዲሁም ቴሌብርና አለምአቀፍ የክፍያ መንገዶችን በመጠቀም መፈጸም ያስችላቸዋል።

ይህንን ለማድረግ የንግድ ድርጅቶች 6 መስመር ኮድ በራሳቸው ድረገጽ/መተግበሪያ ላይ በማስገባት (API Integeration) መገልገል የሚችሉ ሲሆን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት ደግሞ በቀላል መንገድ ከለጋሾች ድጋፍ መቀበል ያስችላቸዋል።

በቻፖ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ህብረት ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክን በመጠቀም ክፍያ መፈጸም ይቻላል።

ከአለምአቀፍ የክፍያ መንገዶች ደግሞ Visa፣ Mastercard፣ American Express፣ UnionPay፣ Discover፣ Diners Club፣ JCB እና PayPal በአገልግሎቱ የተካተቱ ናቸው።

@tikvahethiopia
" ከፍተኛ የውሀ እጥረት ተከስቷል " - የአ/አ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን

የአዲስ አበባ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፤ በአቃቂ ከርሰ ምድር የውኃ ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ አምስት የውኃ ጉድጓዶች በጎርፍና ደለል በመሞላታቸው ምክንያት በከተማዋ ከፍተኛ የውኃ እጥረት መከሰቱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በቀን 20 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ውኃ የማምረት አቅም ያላቸው አምስቱ የውኃ ጉድጓዶች ንፋስ ስልክና ቂርቆስ ክ/ከተሞችን ጨምሮ በርካታ የከተማዋን አካባቢዎች የሚሸፍኑ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ማምረት አቁመዋል ብሏል።

በዘንድሮው የክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ የጎርፍ ፍሰት በመኖሩ ምክንያት የውኃ ጉድጓዶችን ከመሰል ችግሮች ለመጠበቅ በተሰራው የመከላከያ ግንብ መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።

የውኃ እጥረቱን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ቀን ውኃ ያገኙ ከነበሩ አካባቢዎች በመቀነስ እጥረቱ ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች እየተላከ እንደሆነ ተገልጿል።

የተፈጠረው ወቅታዊ ችግር እስኪፈታ ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ባለስልጣኑ ጥሪ ማቅረቡን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

Via AMN

@tikvahethiopia