• ሴቶች በቤት ውስጥ ስራ 5 ሰዓታትን ያሳልፋሉ
• ወንዶች በቤት ውስጥ ድር 1 ሰዓት ብቻ ይቆያሉ
በኬኒያ በኦክስፋም አማካኝንት የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በገጠራማ ቦታዎች አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ለገቢ ምንጭ ከሚጠቀሙበት ስራ በተጨማሪ በቀን አመስት ሰዓታትን የቤት ውስጥ ስራ በመስራት ሲያሳልፉ፤ በአንጻሩ ወንዶች ደግሞ አንድ ሰዓት ብቻ እንደሚሰሩ ነው ጠቁሟል፡፡
ጥናቱ በቤት ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ልጆችን መንከባከብ፣ ምግብ ማብሰል፣ ውሃ መቅዳትና የመሳሰሉትን ተግባራት ያካተተ ነው፡፡
ክፍያ በሌለው የቤት ውስጥ ስራዎች ሴቶች ከወንዶች ይልቅ አራት ሰዓታትን እንደሚያጠፉ ያሳየው መረጃው፣ ይህም ለጥናቱ ግብዓት ከሆኑት ስራዎች ውጪ ያሉት ተግባራት እንዳላካተተ አመልክቷል፡፡
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ስብሰባ ተቀምጧል!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በመሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስብሰባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በስብሰባው÷ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉና ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ በመጨረሻም ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል፡፡
[Hawassa University]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Ameen
አቢሲኒያ ባንክ ‘አሚን’ የተሰኘ እና የሸሪዓ ህግጋትን የተከተለ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ዛሬ አስመርቋል። በሰሜን ሆቴል አካባቢ የተከፈተው አሚን ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎትን ለሚሹ ደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ የሚደርግ መሆኑን የአቢሲኒያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር አብዱልቃድር ሬድዋን ገልጸዋል፡፡
#waltatv

#UPDATE
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት የዱባይ ኤክስፖ 2020 ቅድመ ዝግጅትን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት በዱባይ ኤክስፖ የግንባታ ሥራዎች ላይ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንዲሳተፉ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የስራ ኃላፊዎች ጋር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በአክሱም ከተማ ዘመናዊ ሆቴል ተመረቀ...
በአክሱም ከተማ አንድ ባለሀብት 273 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ያስገነቡት ዘመናዊ ሆቴል ዛሬ ተመርቋል።
የሆቴሉ ባለቤት አቶ ሰለሞን ተክላይ በሆቴሉ ለ200 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውንም ተናግረዋል።
ከ80 በላይ ዘመናዊ መኝታ ቤቶች ያሉት ሆቴሉ ደረጃቸውን የጠበቁ መዝናኛ፣መሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ ሲኒማ ቤትና ሌሎችን መገልገያዎች አካቶ የተደራጀ መሆኑን አመልክተዋል።

#አክሱም
የትግራይ ክልል የንግድ፣ ኢንዱስቱሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዛሬው የሆቴል በምረቃ ወቅት የተናገሩት፦
"እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማስተናገድ የሚያስችል የአሰራርና አደረጃጀት ሪፎርም እየተከሄደ ነው። አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች መከፈት ለቱሪዝም ፍሰትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው። በአክሱም ከተማ ዛሬ የተመረቀው ሆቴል ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ቱሪዝም ፍሰት መጨመርና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ይኖረዋል።"

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተባበሩት ኤመሬትስ አመራሮች ጋር ተወያይተው ስምምነት ከተደረሱባቸው ጉዳዮች መካከል፦
- የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ሕጋዊ ለመሆን እንዲችሉ ፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በወንጀል ተጠርጥረው በእስር ቤት የሚገኙ ዜጎች ምህረት እንዲደረግላቸው እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
- ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የቀረበው የትምህርት ቤት ግንባታ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው የተፈቀደ ሲሆን፣ የፕሮቴስታንት ክርስትና እምነት ተከታዮችም የአምልኮና የጸሎት ቦታ ችግር እንዲፈታ ስምምነት ተደርጎዋል፡፡
- በተጨማሪ ዱባይ ኤክስፖ የግንባታ ሥራዎች ላይ አስር ሺህ [10,000] ወጣቶች እንዲሳተፉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች እና ኮሮና ቫይረስ!
'CHEER UP CHINA' የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች ከነገው የሴልታ ቪጎ ጨዋታ ጅማሮ በፊት የሚለብሱት የማልያ መልእክት ነው፡፡ የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ ጉዳት ለደረሰባቸው ጉዳተኞች የድጋፍ መልክቶችን ያነገበ መለያ ከጨዋታው በፊት ለብሰው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፦
ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ጉዳዮችን አጫጭር መረጃዎችን ለማግኘት የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ መሆን እንደምትችሉ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን https://yangx.top/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
@tikvahethiopiaBot @tikvahethsport

በዛሬው ዕለት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውይይት ላይ የተገኙ 41 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ትናንት ይፋ በተደረገው የምርጫ ሰሌዳ መሰረት አይካሄድ ሲሉ ድምፅ ሰጥተዋል።
በውይይቱ ላይ ምርጫው በተያዘለት የግዜ ሰሌዳ ይካሄድ አይካሄድ ከሚሉት ሀሳቦችም ባሻገር የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚሉ ሀሳቦችም ተነስተውበታል።
በውይይቱ ማጠቃለያም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በምርጫው የግዜ ሰሌዳ ላይ ፓርቲዎቹ አቋማቸውን በድምፅ እንዲሰጡ ጠይቋል።
በተሰጠው ድምፅ መሰረትም 41 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው በተያዘለት የግዜ ሰሌዳ አይካሄድ ብለዋል። ምርጫው በግዜ ሰሌዳው ይካሄድ በማለት ድምፅ የሰጡት 6 ፓርቲዎች ብቻ ናቸው። ከእነዚህም መካከል አንዱ ብልፅግና ፓርቲ ነው። ሌሎች 6 ፓርቲዎች ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።
የጋራ ምክርቤቱ ሰብሳቢዎችም የፖለቲካ ፓርቲዎቹን አቋም ለምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርቡ እና ከምርጫ ቦርድ ጋር የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት እንደሚሞክሩ አስታውቀዋል።
[አሻም ቴሌቪዥን]

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ቅሬታ ምን ነበር?
ዛሬ በኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል በተካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የውይይት መድረክ ላይ ሀሳባቸውን ያቀረቡት ፓርቲዎች ያሰሙት ቅሬታ፦
- ምርጫው በክረምት መሆኑ ፓርቲዎቹን ቅስቀሳ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሚያደርግባቸው ተናግረዋል።
- ያልተሟላ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለበት ሁኔታ፣ የክረምቱ ዝናብ እና ጎርፍ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አባሎቻቸው ጋር ለመድረስ እና ቅስቀሳ ለማድረግ የማያስችል ሁኔታ ውስጥ ይከታቸዋል።
- ምርጫው እንዲደረግበት የተወሰነበት ነሀሴ ወር አብዛኛው የገጠሩ ማህበረሰብ የእርሻ ስራውን የሚያከናውንበት በመሆኑ ህዝቡን ምርጫው ላይ ከመሳተፍ ያግደዋል።
በነገራችን ላይ...
በውይይቱ ላይ ምርጫው ይራዘም የሚል ሀሳብ ያነሱ ነበሩ ለዚህ እንደምክንያት ያቀረቡት ምርጫው መካሄዱ የሀገሪቱን ደህንነት አደጋ ውስጥ ይከታል እና ለምርጫ ዝግጅት የሚሆን በቂ ጊዜ አለመኖሩ የሚሉ ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲስ ምን አለ?
ብልፅግና ፓርቲን በመወከል በውይይቱ ላይ ሀሳባቸውን ያቀረቡት አቶ መለስ አለሙ ፓርቲያቸው ምርጫው በተቀመጠው የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ይካሄድ የሚል አቋም እንዳለው አስታውሰዋል። ምርጫው የሚራዘም ከሆነ አሁን ላይ ያለው ፓርላማ ህጋዊነቱን ያጣል ብለዋል።
ምንጭ፦ አሻም ቴሌቪዥን

#Election2012
በ2012ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከዚህ በፊት የነበሩ አስፈፃሚዎች አይሳተፉም!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እንደተገለጸው፤ ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ላይ አመኔታ ስለሌለ በነሃሴ ወር በሚካሄደው ምርጫ እንዳይሳተፉ ተወስኗል።
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ፦
- ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ጥፋተኛ ናቸው ማለት አይደለም፤ እንዳይሳተፉ የተደረገው ግን ጥርጣሬን ለማስወገድ ነው።
- በምርጫ መራጩ ማህበረሰብ ውስጥ አስተማሪ የነበሩ እና በገለልተኝነታቸው የሚታወቁ ሰዎች የምርጫ አስፈፃሚዎች ይሆናሉ። ለህዝብና ቤት ቆጠራ ሥልጠና ወስደው የነበሩም በተመሳሳይ ለአስፈፃሚነት ይመለመላሉ።
- ኢትዮጵያ ውስጥ ገለልተኝነትን ሊያረጋግጥ የሚችል ዘመናዊ አሰራር ያለው ተቋም ስለሌለ ያለው አማራጭ ገለልተኝነታቸው የሚጣራው በማህበረሰቡ ነው።
- በምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኝነት ላይ ጥርጣሬ ያለው ፓርቲ ተጨባጭ መረጃ ካለው ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል። ፓርቲዎች እስከ ወረዳ ድረስ ወርደው ከህብረተሰቡ ጋር መገናኘትና መረጃ መሰብሰብ አለባቸው።
- የትኛው የምርጫ አስፈፃሚ ችግር እንዳለበትና የትኛው እንደሌለበት ወርደው ማጣራት አለባቸው። የምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኛ ካልሆኑ የሚደረገው ምርጫ ከንቱ ይሆናል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ አንድ ግዙፍ መርከብ ውስጥ ተገልለው የሚገኙ ዜጎቿን ወደ ሀገሯ ልትመልስ ነው።
ቶኪዮ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው አንድ አይሮፕላን ወደ ጃፓን በመላክ ዜጎቹን ወደ ካሊፎርኒያ እሁድ ዕለት ለመመለስ አቅዷል።
ዲያመንድ ፕሪንሰስ የተባለችው ትልቅ መርከብ ውስጥ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ አንስቶ መርከቧ ፎኮሹማ ወደብ አቅራቢያ ካለፈው ወር አንስቶ እንዳንትቀሳቀስ ታግታ ትገኛለች።
የበርካታ አገር ጎብኚዎች በተሳፈሩባት መርከብ ውስጥ ዛሬ ብቻ 67 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዚህም የተነሳ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 285 አሻቅቧል።
በመርከቧ ላይ በጠቅላላው 3,500 የሚሆኑ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 380 የሚሆኑት የአሜሪካ ዜጎች ናቸው።
[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ]

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012
አቶ ወሰን አለሙ ይባላሉ የህግ ባለሞያና የኢትዮጵያ አይነ-ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ መጪውን ምርጫ በተመለከተ ጠይቀናቸው ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡-
- ሥልጠናዎች አካል ጉዳተኞችን ያማከሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሥልጠናውም በራሳቸው በአካል ጉዳተኞቹ ሊሰጥ ይገባል፡፡
- የምርጫ ጣቢያዎቻችን ተደራሽ መሆን አለባቸው ዊልቸር ተጠቃሚዎች ሊቸገሩ አይገባም፣ አይነ ስውራን ሊቸገሩ አይገባም ወደፊት ደግሞ ኤሌክትሮኒክ አድርገን ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ መቻል አለብን፡፡
- ፓርቲዎች አካል ጉዳተኛን በበቂ ደረጃ ማካተት አለባቸው ያለበለዚያ ማንም እንደማይመርጣቸው ማወቅ አለባቸው፡፡ አካል ጉዳተኛን የማያካትት ፓርቲ ለሀገር አይጠቅመንም፡፡

ያየነውን እንመሰክራለን!
ባለፉት ዓመታ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ሜዳዋች ሲፈጠሩ የነበሩትን ክስተቶች ሁላችንም የምናውቀው ነው። በየጊዜው ተስፋ ሲያስቆርጡን፣ በሀዘን ውስጥ ሲከቱን የነበሩ ክስተቶች ነበሩ። እዚህ መዘርዘር አያስፈልግም።
ዘንድሮ ግን በእግር ኳስ ሜዳዎቻችን ላይ ያየነው ለውጥ እጅግ ድንቅና ሊበረታታ የሚገባው ነው። ይህ ነው የሚባል ችግር ሳንሰማ ዛሬም በአስደማሚ የሜዳ ላይ ትዕይንቶች እየተገረምን ፣ ተስፋችን እየለመለመ ነው ፤ እውነትም እግር ኳስ የፍቅር እና የሰላም ፣ የህዝብ አቀራራቢ መሆኑን የመሰከርንበት ነው።
ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ዘውትር የሚጠመዱት ግጭትን በማያባብሱ ጉዳዮች፣ በስድብ፣ በጥላቻ፣ በክፋት በመሆኑ ሁሉም ነገር ጨለማ ሆኖ እንዲታየን ያደርጉታል።
በሀገራችን መልካም ስራዎች እንደ ክፉና መጥፎ ድርጊቶች ጎልተው አይደመጡም ሽፋን አያገኙም። ግጭቶች ፣ አለመግባባቶች ግን ሰፊ ሽፋን ይሰጣቸዋል።
እኛ የቲክቫህ ቤተሰቦችን ያየነውን እንመሰክራለን። ዘንድሮ በእግር ኳስ ሜዳዎች፣ በደጋፊዎች ፣ በተጫዋቾች ያየነው ለውጥ ልባችንን በተስፋ ሞልቶታል!
በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ፣ ተጫዋቾች ፣ አሰልጣቾች ፣ የፀጥታ አስከባሪዎች ፣ የስፖርት አመራሮች ላሳያችሁን መልካም ስራ ፣ ለሰጣችሁን ትልቅ ተስፋ እናመሰግናለን።
መልዕክቶቻችሁን @tikvahethiopiaBot
[PHOTO : ትግራይ ስታድየም #TIMOTIOS]

TIKVAH-ETHIOPIA
#Solve_IT_2020 ' Solve IT ' ባለፉት አመታት የቴክኖሎጂ አቅማቸውን ተጠቅመው ችግር ፈቺ ግኝቶችን ለፈጠሩ ወጣቶች ከ100,000 አስከ 25,000 ብር መነሻ ገንዘብ አበርክቷል፡፡ ዘንድሮም ኃሳብ ላላቸው ወጣቶች ኃሳባቸውን በእውቀትና በገንዘብ ለመደገፍ ወደ 15 የተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመንቀሳቀስ ግንዛቤ ማስጨበጫና ምዝገባ በማድረግ አወዳድሮ ይሸልማል፡፡ ከየካቲት 2 እስከ የካቲት…
ለጥያቄያችሁ መልስ..
በSolve IT በኦላይን ምዝገባ ላይ በርካቶች የማረጋገጫ መልዕክት አልደረሰንም የሚል ቅሬታዎችን ተቀብለናል፡፡ ይህንንም ለአዘጋጆቹ አሳውቀን በደረሰን ምላሽ መሰረት ችግሩ የሚከሰተው የኢሜል አድራሻቸውን በትክክል ሳያስገቡ ሲቀርና ፎርሙን በትክክል ሳይሞሉ ሲቀር እንዲሁም ኢሜሉ "Spam" ውስጥ ስለሚገባ ነው። Gmail የሚጠቀሙ ተመዝጋቢዎች "All mail" የሚለው አማራጭ ውስጥ ቢገቡ የማረጋገጫ መልእክቱን ያገኙታል። የኢሜል አድራሻችሁንና መረጃዎችን በአግባቡ በማስገባት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
https://www.icog-solveit.com/register/participant

#BURAYUU
ዛሬ ማምሻውን በቡራዩ በነበረ የሆቴል ምርቃ ላይ የተገኙ ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል። በፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ከተፈፀመባቸው ሰዎች መካከል እውቋ አርቲስት ሀዊ ቀነኒ እና ሌሎች ይገኙበታል።
አርቲስት ሀዊ በተፈፀመባት ድብደባ ሆስፒታል ገብታ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው። የፀጥታ ኃይሎች ድምፃዊ ደሳለኝ ቤከማ እና አርቲስት ልጅ ያሬድን በቁጥጥር አውለው ነበር የተባለ ሲሆን ከሰዓታት በፊት ልጅ ያሬድ መለቀቁን ሰምተናል።
ልጅ ያሬድ በፌስቡክ ገፁ "የኦነግ ሸኔ ደጋፊ ነህ ተብዬ መሬት ላይ አከባለውኛል፤ ጭስ ቦንብም ወርውረዋል" ብሏል።
በቡራዩ ከተማ ስለተፈጠረው ክስተት OMN [ኦ ኤም ኤን] ከከተማው ከንቲባ ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት እንዳልቻለ አሳውቋል።
በቡራዩ ከተማ የተፈጠረው ምንድነው? ለምን ሰዎች ተደበደቡ? ስለጉዳዩ የፖሊስ ምላሽ ምንድነው? ዘርዘር ያለና የመንግስት ምላሽ የተካተተበት መረጃ ስንመለከት እንድታነቡት እናደርጋለን።