#update የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት የ3ኛ ተከሳሽ ኢሳያስ ዳኘው እና የ4ኛ ተከሳሽ አብዱል ሀፊዝ አህመድ የክስ ዝርዝር በዛሬው እለት በችሎት ተነበበ፡፡
ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/FD-07-15
ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/FD-07-15
#udate ህንድ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስፔስ ልታደርግ የነበረውን ጉዞ ከአንድ ሰዓት በታች ጊዜ ሲቀረው በቴክኒክ ችግሮች አማካኝነት ሰርዛለች፡፡ ሳተላይቱ በምስራቃዊ ህንድ ስሪሃሪኮታ ስፔስ ሰኞ 2፡51 ለመንቀሳቀስ ፕሮግራም እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ገልጿል፡፡ የተሰረዘው የስፔስ ጉዞ መቼ እንደሚደረግ በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑም ተገልጿል፡፡
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት በአዴፓ እና በህወሐት መካከል ሰሞኑን የታየው አለመግባባት #በሰከነ መንገድ ሊፈታ ይገባል ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አባላት ገለጹ። ችግሩ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የዓላማ አንድነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴው በክልሉ ወቅታዊ እና በለውጥ ስራዎች ላይ ሲመክር ሰንብቶ ዛሬ ሐምሌ 08/2011 ዓ.ም መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADP-07-15
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ADP-07-15
#መቐለ
ሕወሃትን ከኤርትራው ሕግዴፍ ጋር ለማስማማት ያለመ ምክክር መድረክ መቐለ ላይ ተጀምሯል፡፡ መድረኩን ያዘጋጀው ሰለብሪቲ ኤቨንትስ የተባለ የግል ተቋም ሲሆን ከሁለቱ ሀገራት ምሁራን፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የማቀራረቡ ጥረት ከሁለቱ ፓርቲዎች በጎ ምላሽ እንደተቸረውም DW የመድረኩን አዘጋጅ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በቀጣይነት የሁለቱን ድርጅቶች የቀድሞ ታጋዮች፣ የጦር ጉዳተኞች፣ የቀድሞ አመራሮች የሚሳተፉበት ውይይት በአዲስ አበባና አሥመራ ለማድረግ አቅዷል፡፡
Via #wazemaradio/#DW/

#NewsAlert ኮንጎ ውስጥ የኢቢላ ወረርሽኝን በማጥፋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁለት የማኅበረብ ጤና ሠራተኞች፣ ምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ክፍለ-ሀገር ኬቬዮ ውስጥ #መገደላቸውን፣ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታወቀ። ሠራተኞቹ ለወራት ያህል ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበርም፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በአማራ ክልል በጥረት ኮርፖሬት ስር የሚተዳደሩ ከአስር በላይ ኩባንያዎች በአክሲዮንና ሙሉ በሙሉ በሽያጭ ወደ ግል እንዲዛወሩ መወሰኑን የኮርፖሬሽኑ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ #አባተ_ስጦታው አስታውቀዋል። በአክሲዮንና በሽያጭ ወደ ግል ከሚዘዋወሩት ኩባንያዎች መካከል አምባሰል ንግድ ስራዎች ድርጅት፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣የባህር ዳርና ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፉብሪካዎች ይገኙበታል።
Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ #etv ዜናን ይከታተሉ #tikvahethiopia
#ከደኢህዴን_መግለጫ ~የክልል ጉዳይ❓
በክልል የመደራጀት ጥያቄን በተመለከተ የህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ድርጅታችን ይገነዘባል። በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሲነሳ የነበረው ከአንድ አካባቢ ብቻ ባይሆንም ጥያቄውን በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ድርጅቱ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በወሰደው አቋም መሰረት በዝርዝር ህዝቡን ያሳተፈ ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። በጥናቱ የቀረቡ አማራጮችን በጥልቀት በመመርመር የህዝቡን የጋራና ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ አማራጭ በመውሰድ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች በሚመለሱበት አግባብ ላይ አቋም ተወስዷል። በክልላችን መላው ህዝብ ምክክርና ውይይት የሚደረግበት ሆኖ በአንድ በኩል በጥናቱ የተገኘውን የክልሉ ህዝቦች አብሮ የመቀጠል ፍላጎትን ባከበረ፤ በሌላ ጎኑ ደግሞ የጉባኤውን ውሳኔ ተግባራዊ ባደረገ መንገድና ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ የመምራት ሃላፊነት ለመወጣት ማዕከላዊ ኮሚቴው ተስማምቷል። #TIKVAH_ETHIOPIA

😢#የመን Yemen is seeing the world's worst humanitarian crisis, according to the #UN.
https://telegra.ph/Yemen-07-15
https://telegra.ph/Yemen-07-15
#EBOLA ጎማ ከተማ ውስጥ #ለመጀመሪያ ጊዜ የኢቦላ በሽታ መገኘቱ ዛሬ ተሰምቷል። በነገራችን ላይ #ጎማ ምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምትገኝ ከተማ ስትሆን #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ በሳምንት 7 ጊዜ ወደ ከተማይቱ ይበራል።
Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦
እናስተውል!
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
አሁን ላይ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ በእርግጥ በጣም ወደ #ከፋ ሌላ መንገድ ሊወስደን እንደሚችል በዚህ ወቅት መገንዘብ ካልቻልን ችግር ውስጥ ነን። #የመበታተን እና #የመጠፋፋት ምልክቶች እያየን ነው። ቤተሰብ ያለው ስለቤተሰቡ ያስብ፣ ሀገሩን የሚወድ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨንቀው፣ ህይወቱን የሚወድም እንዴት እሆናለው ብሎ ያሰላስል።
በስሜታዊነት እና በደመ ነፍስ የሚደረጉ ድርጊቶች እና የሚወሩ ጉዳዮች እዚህ አድርሰውናል። እነዚህ ነገሮች አሁኑኑ ካልተገቱ ሀገራችንን በምናውቃት መልኩ #በቅርቡ ላናገኛት እንችላለን።
ፖለቲከኞች ህዝብ ላይ #አትቆምሩ፣ ህዝቤ ፖለቲካ ቀነስ አርገህ ስራህ ላይ አተኩር፣ አክቲቪስቶች አደብ ግዙ፣ እኔን ጨምሮ ጋዜጠኞች ለማንም ሳንወግን ስራችንን እንስራ።
አሜን!
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!!
🗞ቀን ሃምሌ 8/2011 ዓ/ም

#update የመቀሌ 70 እንደርታ እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ቀጣይ ሐሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ እንዲካሄድ ተወስኗል።
በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከመቀሌ 70 አንደርታ ማገናኘቱ የሚታወስ ነው። ሁለቱን ቡድኖች ያገናኘው ጨዋታ የት ይካሄዳል የሚለው ጥያቄ ትኩረት ስቦ ቆይቶ ነበር።
ሁለቱ ቡድኖችም የሚጫወቱበት ሜዳ የት እንደሚሆን ከፌደሬሽኑ የሚወሰነውን ሀሳብ ይጠባበቁ ነበር። በመጨረሻም የውድድሩ አዘጋጅ ከሁለቱም ቡድኖች ጋር በመምከር ጨዋታው የፊታችን ሀሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደረግ ወስኗል።
ጨዋታው ቀጣይ ሐሙስ በዝግ ከረፋዱ 4:00 ላይ ይጀመራል። ከሁለቱ ቡድኖች አሸናፊው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ተወዳዳሪ ይሆናል።
Via EPA

5 ሚልየን ብር የወጣበት የአመልሰት ሙጬ ፊልም ትላንት ምሽት በብሔራዊ ቲያትር ቤት በድምቀት ተመረቀ።
ትላንት ጠዋት ላይ በኤልያና ሆቴል በተሰጠው መግለጫ ላይ የፊልሙ ፅሐፊ እና ዳሬክተር የሆነችው አምልሰት ሙጬ በመግለጫው ላይ እንደተናገረችው የፊልሙ ሐሳብ ወይም ጭብጥ መርካቶ አካባቢ ተወልዳ አድጋ ራሳን ለመለወጥ ጥረት የምታድርግ አንዲት ሴት ልጅ ሯጭ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ የያዘ ፊልም እንደሆነ ገልፃለች።
አትሌት ሻለቃ ሐይሌ ገ/ስላሴን ጨምሮ በፊልሙ ላይ ከ 400 የሚደርሱ ተዋንያን በዚህ ፊልም ላይ ተሳትፈውበታል።
Via @AccessAddis

#update የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ሀገራቸው ከሩሲያ የገዛቻቸው የኤስ-400 የሚሳኤል መቃወሚያዎችን በመጪው የፈረንጆቹ 2020 ሚያዚያ ሙሉ ለሙሉ እንደምትረከብ ገልጸዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመጪው ሀምሌ 22/2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን ለመትከል እቅድ ተይዞ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ በአማራ ክልል በዚህ ክረምት ወራት 2 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 100 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከልም ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በደቡብ ክልልም ሐምሌ 22 ቀን 50 ሚሊዮን ችግኝ ይተከላል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ በደረሰ ጥቃት የተሰዉ አመራሮችን ቦታ ክፍተት ለመሙላት የተደረገው ምርጫ የአማራን ሕዝብ ካጋጠሙት ችግሮችና ክስተቶች በማውጣት ወደተሻለ ደረጃ እንደሚያሻግር ተገለጸ፡፡ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድርነት በዕጩነት፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ደግሞ ለአዴፓ ምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡
የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የአመራር ማሟላት ሥራው በማዕከላዊ ኮሚቴው በተካሄደ ምስጢራዊ ምርጫ መሠረት ዕጩ ርዕሰ መስተዳድርና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ተመርጠዋል። በጥቃቱ በተሰዉት እና የአዴፓ እና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚዎች በነበሩት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ምትክ አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አገኘሁ ተሻገርን የመተካት ሥራ እንደተሰራም አቶ አብርሃም ገልጸዋል፡፡
Via #EPA