#update የኦሮሞ ህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ ገለጹ።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ከጅማ ዞንና እና ከጅማ ከተማ አስተዳድር ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።
በውይይት መድረኩ በመልካም አስተዳደር፣በልማትና ተጠቃሚነት ላይ ለተነሱ ጥያቄች አቶ ሽመልስ አብዲሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በምላሻቸውም መንግስት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ከአመራሩ ጎን በመቆም በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የተገኘውን ሰላም፣ መረጋጋትና ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሰሩ ሃይሎችን በጋራ በመከላከል የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ማሳካት እንደሚገባም ማንሳታቸው ተዘግቧል።
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር👆
የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር የደርግ ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ልደትና የምስጋና ፕሮግራም በመጪው ሰኞ ሊያሰናዱ መሆናቸውን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ መርጊያ ለቢቢሲ ገለፀዋል።
ከዚህ በፊት ልደታቸውን በይፋ አክብረን አናውቅም የሚሉት አቶ ጆኒ ዘንድሮ ለማክበር የማህበሩን አባላት ያነሳሳውን ጉዳይ ይገልፃሉ።
ነገሩ ወዲህ ነው፤ ከወር በፊት በህፃናት አምባ ያደገና የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ኮሎኔሉን ለማግኘት እርሳቸው በስደት ወደ ሚኖሩበት ዚምባብዌ ለማቅናት ይነሳል። ግለሰቡ ስሙ እንዲጠቀስ ባይፈልግም አካሄዱ ግን እርሳቸውን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ነበር።
እርሳቸውን ለማግኘት ቁጥጥሩና ጥበቃው ጥብቅ ቢሆንም በወንድማቸውና እዚያው ዚምባብዌ በሚኖር አንድ የህፃናት አምባ ልጅ አማካኝነት ፈቃድ ማግኘት እንደቻሉም ገልፀውልናል።
ታዲያ ማህበሩ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ለእርሳቸው የሰላምታ ደብዳቤ ለመላክ አሰበ። በደብዳቤያቸው ላይም እንዲሁ በትክክል የተወለዱበትን ቀን እንዲነግሯቸው ጠይቀዋቸዋል።
አቶ ጆኒ ምክንያታቸውን ሲያስረዱም የኮሎኔሉ የልደት ቀንና ከአገር የወጡበት (ግንቦት 13) ተመሣሣይ ነው የሚሉ መረጃዎች ይወጡ ስለነበር ትክክለኛ የልደት ቀናቸውን ለማወቅ ነው ብለዋል።
የማህበሩ ኮሚቴ የፃፉላቸው ደብዳቤ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት የለውም የሚሉት አቶ ጆኒ ደብዳቤው ልጅ ለአባቱ የሚፅፈው ዓይነት ነው ብለዋል።
በመሆኑም ደብዳቤው ስለ ደህንነታቸው፣ ስለ ልጆቻቸው ሁኔታ የጠየቁበት፣ ቤተሰባዊ ሰላምታ ያቀረቡበትና የልደት ቀናቸውን የጠየቁበት እንደሆነ ይናገራሉ።
"ልደታቸውን ስናከብር እናስታውሳቸዋለን ብለን እንጂ ለምርምር ፈልገነው አይደለም" ሲሉም የልደት ቀናቸውን የጠየቁበትን ምክንያት ያስረዳሉ።
አቶ ጆኒ እንደገለፁልን ከደብዳቤው ጋር ባህላዊ የአልጋ ልብስ፣ ግድግዳ ላይ የሚሰቀል የመስቀል ቅርፅ ያለበት ጌጥ እና ለባለቤታቸው ውብ አንችና ለእርሳቸው የሚሆን ባህላዊ ፎጣ ስጦታም ልከውላቸዋል። እርሳቸውም እንደ አባት ምላሻቸውን እንደላኩላቸው አቶ ጆኒ ገልፀዋል።
በምላሹ በላኩላቸው ደብዳቤ ላይም በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳሉ፣ የተጋነነ የጤንነት ችግር እንደሌለባቸው፣ በልጆቻቸው እንደተባረኩ፣ አምስት የልጅ ልጆች እንዳዩ፣ ሁል ጊዜ ስለ ሃገራቸው እንደሚያስቡና ሃገራቸውን እንደሚናፍቁ በመግለፅ መጨረሻ ላይ የተወለዱበትን ቀንና ዓመተ ምህረት የሰፈረበት አጭር ደብዳቤ ፅፈውላቸዋል።
"የተወለድኩት፡ በአዲስ አበባ ፡ እንደኢትዮጵያ፡ አቆጣጠር፡ በ1933.ዓ.ም፡ ግንቦት አስራዘጠኝ ቀን፡ነው።" ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ እንዳሰፈሩ አቶ ጆኒ ገልፀዋል።
ማህበሩም ቢሮ እንዳለውና እንደሌለው በመጠየቅም ቢሯቸው ላይ የሚያስቀምጡት የአፍሪካ ካርታ ያለበት ሰዓት ልከዋል።
ይህ ብቻም ሳይሆን የእርሳቸው ፊርማ ያረፈበት፣ 'ለህፃናት አምባ ልጆች'፤ መልካም ንባብ' የሚል ፅሁፍ ያለበት የመጀመሪያ መፅሃፋቸውን ልከውላቸዋል።
"በዋነኛነት እንደ ልጆች የሚሰሙን ነገሮች አሉ፤ በእርሳቸው ጊዜ በነበረው ሥርዓት ያልተገቡ ነገሮች ተከናውነዋል፤ ነገር ግን በዘመኑ በጣም ጥሩ ሥራዎችንም ሰርተዋል" የሚሉት አቶ ጆኒ ባለፈው ሥርዓት በአጠቃላይ ደርግ በሚል መንፈስ የእርሳቸው ሥራ መጥፎነት ነው የተሳለው ይላሉ።
በመሆኑም የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር እርሳቸው በዘመኑ ከሰሯቸው በጎ ሥራዎች መካካል አንዱ የህፃናት አምባን ማቋቋም መሆኑን በመጥቀስንና መሰል ሥራዎችን በማንሳት የልደትና የምስጋና ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቧል።
ግንቦት 18/2011 ዓ.ም የተወሰኑ የህፃናት አምባ ልጆች በግል በነበራቸው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የኮሎኔሉን ልደት እንዳከበሩ ገልፀውልናል። ይሁን እንጂ ዋናው ማህበር በመጭው ሰኞ ሰኔ 2 ቀን/2011 ዓ.ም ፕሮግራሙን ለማካሄድ እንዳቀደ አቶ ጆኒ መርጊያ ነግረውናል።
"በፕሮግራሙ ላይ እንደማንኛውም ልደት ኬክም ዳቦም ይኖራል፤ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችንና ሌሎች እንግዶችን ጋብዘን ሞቅ አድርገን ለማክበር ነው ያሰብነው" ብለዋል።
ፕሮግራሙ የሚካሄድበትን ሰዓትና ቦታ ጊዜው ሲቃረብ እንደሚገልፁ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በህፃናት አምባ ያደጉ ልጆች ቁጥራቸው ከ7 ሺህ በላይ ሲሆኑ አዲስ አበባ የሚገኙና የማህበሩ አባል የሆኑ ልጆች ቁጥር ስድስት መቶ እንደሚሆን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የህፃናት አምባ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጂራ አውራጃ፤ አላጌ በሚባል አካባቢ የተቋቋመ ሲሆን ወላጆቻቸውን በጦርነትና በሌሎች ምክንያቶች ያጡ ህጻናትን ተቀብሎ የማሳደግ ዓላማ ነበረው።
ህፃናት አምባው 'ሰብለ አብዮት'፣ መስከረም ሁለት ኦጋዴን፣ ዘርዓይ ደረስ እና መንግሥቱ ኃይለማሪያም የተባሉ 5 መንደሮችም ነበሩት።
Via #BBC
ፎቶ፦ ማርታ

ሂሳብ ተከፍሏል...
"ሰላም ፀግሽ! ይህ ምትመለከተው ከአጎና ደምበል መስመር የሚሰራ #ታክሲ ውስጥ ተለጥፎ ያየሁት ነው።" አብዱልፈታ መሃመድ
| ሂሳብ ተከፍሏል፦
√ለአቅመ ደካማዎች
√ለሃይኖት አባቶች
√የሚሊተሪ ዩኒፎርም ለለበሱ

ዶ/ር አብይ አህመድ...👆
"ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ አገር መሪነት ሀላፊነት ከመጡ በሗላ #የመጀመሪያ የሆነውን የአንድ ለአንድ የአማርኛ ቃለመጠይቅ ትላንት እካሂደዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዬ ጋር ባካሄዱትና በቪዲዬ ካሜራ ጭምር በተቀረፀው ቃለ መጠይቅ የአንድ አመቱ የለውጥ ጉዞ #ስኬቶችና #ፈተናዎች ተዳሰዋል። ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ድምፅ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።"
Via #እስክንድር_ፍሬው

ግንቦት ሃያ ~~ አክሱም👆
28ኛ ዓመት የግንቦት 20 የድል በዓልን በክልል ደረጃ ‘‘ግንቦት 20 የጽናት፣ የአይበገሬነትና የአሸናፊነት አርማ ነው‘‘በሚል መሪ ቃል በአክሱም ከተማ #በደማቅ ስነ-ስርአት ዛሬ ተከብሯል።

“ፊቼ ጫማባላላ”ን #በሰላም ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል!
.
.
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ”ፊቼ ጫማባላላ” በዓል ባህላዊ ይዘቱ ተጠብቆ በሠላም እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን አዘጋጆቹ ገለጹ፡፡
የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ከከተማው ፖሊስ መምሪያ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ተፈራ እንዳስታወቁት በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል።
በዓሉ የሲዳማ ብሔር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን መገለጫ የዓለም ቅርስ እንደመሆኑ በከተማው በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ተዋቀሮ በመስራት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።
እንደ አቶ መልካሙ ገለፃ የበዓሉን አከባበር የሚያውኩ ችግሮች ከተፈጠሩ ጉዳዩን ተመልክተው ብይን የሚሰጡ አራት ተዘዋዋሪ ችሎቶች ተዘጋጅተዋል፡፡
በዕለቱ በከተማዋ በሚገኙ መንደሮች ውስጥ ሁሉም ኅብረተሰቡ የሚሳተፍባቸው መርሐ-ግብሮች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።
ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች የሲዳማ ብሔር የባህል ምግብ ዝግጅትም እንደሚኖርም ገልጸዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በበኩላቸው በዓሉ በሠላም ለማክበር ዝግጅቱ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
እንደ ኮማንደር መስፍን ገለፃ ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ ሥጋቶችና ያልተጨበጡ የማደናገሪያ ወሬዎችም ከህዝብ ጋር ከተደረገው ውይይት በኋላ መቃለላቸውን ተናግረዋል፡፡
የዘንድሮው የ”ፊቼ ጫማባላላ” በዓል የሚከበረው የፊታችን #ሐሙስና #ዓርብ ነው።
Via #ENA