TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እኛ በሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን። ይኸው ሱዳን ውስጥ ስቃያችንን እያየን ነው።

በተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን ተሰብስበው እንዲታሰሩ እና ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ሆኗል።

ለአመታት በኖርንበት ሀገር ምንም በማናውቅበት ሁኔታ ሰብሰው አስረውናል።

30 እና 40 ዓመት በላይ የኖሩ ጭምር ታስረዋል። ምክንያት ስንጠይቅ ' ከላይ ነው ትዕዛዙ ' ይሉናል። ሰዎቹ የሌ/ጄነራል አልቡርሃን ናቸው።

ጭራሽ ' ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF ለሚባለው) መረጃ  ትሰጣላችሁ ' የሚል ነገር ያወራሉ የጄነራሉ ሰዎች።

እስካሁን ያለው የታሳሪ ብዛት ከ600 በላይ ይሆናል። 

ህጻናት እና ሴቶች በብዛት አሉ ፣ ነፍሰጡሮች ፣ አዛውንቶች፣ ህመም ያለባቸው ሰዎችም አሉ።

ምቹ ባልሆነ ስፍራ ፣ በየሜዳው ነው ያለነው ፤ ከሙቀቱ ተደምሮ እጅግ ስቃያችንን እያየን ነው።  ራሳቸውን ስተው የነበሩ ሴቶችም አሉ። ወደ ህክምና ተብሎ ከተወሰዱ በኃሏ የት እንደደረሱ አይታወቅም።

' እዚህ መኖር አትችሉም ' ከተባልን የለፋንበትን ንብረት ይዘን ወደ ሀገራችን እንዲመልሱን ይደረግ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጩኸታችንን ይስማንና ካለንበት ስቃይ ያሶጣን።
" - በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

#TikvahEthiopiaSUDAN

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ ከእገታው የወጡት ኢትዮጵያዊያንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል ” - ቤተሰብ 🔵 “ እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም? ” - ኢትዮጵያዊ በታይላንድ ➡️ “ ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው ” - የወላጆች ኮሚቴ ሰርተው ለመለወጥ ሲሉ ተታለው ወደ ታይላንድ…
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ

“ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር

ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር ላይ ያለ ቦታ እንደሆነ፣ የድረሱልን ተማጽኖ ቢያስሙም የሚደርስላቸው ባለመገኘቱ ራሳቸውን እስከማጥፋት ሙከራ እያደረጉ እንዳሉ ታውቋል።

በአካባቢው ባሉ ካምፓች የነበሩ ሌሎች ሰዎች ከእገታ እየወጡ እንደሆነ፣ " ዋልዋይ " ካምፕ የሚገኙትን ታጋቾች ግን እንዳይወጡ አጋቾቹ በድብቅ እንደያዟቸው ተመልክቷል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ ምን አሉ ?

“ በማይናማር ካምፕ የነበሩ 29 ኢትዮጵውያን ካምፓኒው ‘ወደ ሌላ ቦታ ልውስዳችሁ’ ሲላቸው ለደኀነታቸው አስተማማኝ ስላልሆነ እዚሁ ነው መቆት የምንፈልገው ብለው ነበር፡፡

ነገር ግን ካምፓኒው የጸጥታ ኃይሎችን ወዳነበሩበት ካምፕ በማምጣት እጃቸውን በግዴታ እየጎተተ በመኪና አሳፍሮ በማይናማር 'ዋልዋይ' የሚባል ቦታ ወስዷቸዋል፡፡

የተወሰዱት ገና አዲስ በመሰራት ባለ ኮምፓውንድ ነውና በጣም ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እየደረሰባቸው ይገኛሉ፡፡ ኮምፓውንዱ ህግ እና ስርዓት የለውም። በጋንግስተሮች ብቻ የሚተዳደር ነው። ለደኅንነታቸው የሚጮህላቸው የለም።

ሴቶችን ፀጉራቸውን ላጭተዋቸዋል። ወንዶችና ሴቶችን በኤሌክትሪክ ይገርፏቸዋል፤ በጨለማ ክፍል በማስገባት ከሦስት ቀናት በላይ ምግብ በመከልከል በሰንሰለት ያንጠለጥሏቸዋል።

እናም በማይናማር የነበሩ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። እንዲያውም ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ እያደረጉ ነው። በሰጡን መረጃ መሰረት።

እዚያ ከሄዱ በኋላ ይበልጥ ከባድ ችግር እየገጠማቸው ነው። ለካምፓኒው ሥራ ቢሰሩም ባይሰሩም ሁሌም ይቀጠቀጣሉ፡፡ ተስፋ ወደ መቁረጥ ደርሰዋል፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ አድርገዋከል ” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል፥ በማይናማር ታግተው አስከፊ ጊዜ ያሳለፉና ከወር በፊት ከእገታ የወጡ፣ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስትን የቪዛና ሌሎች ጉዳዮች ይሁንታ እየጠበቁ ታይላንድ ከሚገኙ ከ250 በላይ ዜጎች መካከል ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተረጋገጠላቸው ለመመለስ ትኬት ያላቸው 40 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያኑ ነግረውናል፡፡

ሌሎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚችሉት በራሳቸው ሙሉ ወጪ ትኬት ሲቆርጡ መሆኑን እንደተናገሩ፣ የደርሶ መልስ ቪዛና ለትኬት መቁረጫ ገንዘብ የሌላቸው በርካቶች ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ “ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር…
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እዚህ ያለነው ወደ 70 ኢትዮጵያውያን ነን ፤ ያለንበት ሁኔታ አስከፊ ነው ፤ ያናገረን አንድም አካል የለም " - ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በማይናማር / ማይዋዲ KK2 የሚባለው ስፍራ የሚገኙ በቁጥር 70 የሚሆኑ ወጣቶች ከቦታው የሚያስወጣቸውን አጥተው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያሉበት ቦታ በማይናማር ወታደራዊ ሰዎች እየተጠበቀ እንዳለ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያኑ " እኛ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን። 70 እንሆናለን። ማንም መጥቶ የጠየቀን የለም። መቼ እንደምንወጣም አናውቅም። ሁሉ ነገር ጨልሞብናል " ብለዋል።

" የሚሰጠን ምግብ የማይበላ ነው። ማደሪያ የለንም እንጨት ላይ ነው የምንተኛው ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ለመናገር ይከብዳል ስቃይ ላይ ነን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው አንድ ወንድማችን በጣም ታሞ በስንት መከራ ነው ህይወት የዘራው " ሲሉ አክለዋል።

" ያሉትን የMilitary ሰዎች ጠይቀናቸው ነበር አብረውን ካሉት ውስጥ ' የህንድ መንግሥት ዜጎቹን ለመውሰድ accept ስላደረገ እነሱ ይወጣሉ በእናተ በኩል ምንም ምላሽ የለም ' ብለውናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ትወጣላችሁ የሚለን የለ ወይ ስለኛ የሚናገር የለም እባካችሁ ስቃያችንን ስሙን " ሲሉ ተማፅነዋል።

" ህንዶቹ ነገ እና ከነገ ወዲያ ይወጣሉ ዛሬ እየተዘጋጁ ነው ከኛ ሀገር በኩል ያናገረን የለም በጣም ተጨንቀናል " ብለዋል።

እኚህ ወጣቶች ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ ታይላንድ ተብለው ወደ ማይናማር በግዳጅ የተወሰዱና በዛም በማፊያዎች ስንትና ስንት ስቃይ ያዩ ሲሆን ከዛ ስፍራው እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ አሁን ደሞ ሌላ ስቃይ እያዩ እንደሆነ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM