TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" ከዚህ ቀደም ገዝተን ከታጠቅናቸው ድሮኖች የሚለያቸው በከፍተኛ altitude መብረር መቻላቸው፣ በAI የታገዙ በመሆናቸው redundant communication system ያላቸው መሆናቸው ፣ Anti Drone Jammer ስላላቸው ነው " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትላንትናው ዕለት " ስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ " የተሰኘ ኢንዱስትሪ አስመርቀዋል።

ይህ ኢንዱስትሪ ፤ ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርት እንደሆነም ተናግረዋል።

ድሮኖቹ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለመከላከል አቅም እንዲሁም ለማጥቃት እንደሚውሉ ጠቅሰዋል።

" ከፍተኛ የsensor አቅም እና AI ያላቸው ድሮኖች ናቸው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " አንዳንዶቹ suicide እንዳንዶቹ አጥቅተው የሚመለሱ ናቸው " ሲሉ አብራርተዋል።

ድሮኖቹ ከዚህ ቀደም ከተገዙት የሚለያቸው ነገሮችም እንዳለ ተናግረዋል።

" ከዚህ ቀደም ገዝተን ከታጠቅናቸው የሚለያቸው አንኳር ነገሮች አሉ። አንዱ ከዚህ ቀደም የምንገዛው test የሚደረገው sea level ላይ ስለሆነ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ከፍተኛ altitude ላይ ለመብረር ይቸገራሉ የኛ UAV ተሰርተው test የሚደረጉት ከ2 ሺህ በላይ ስለሆነ በከፍተኛ altitude መብረርስ ስለሚችሉ ዝቅተኛ ቦታ ሲያገኙ የበለጠ functional ይሆናሉ " ብለዋል።

" ሌላው በAI የታገዙ በመሆናቸው redundant communication system ያላቸው ናቸው ሳተላይትም ይጠቀማሉ ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዱ ድሮን anti drone jammer አለው የሚወድቁ jmmer አይደሉም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከውጭ የሚመጡት በኢትዮጵያ altitude ለመብረር ይቸገራሉ ሲሉ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " አቅም አባዢ አዳዲስ የጦር አቅሞችን በገዛ ገንዘባችን ለመታጠቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም " ያሉ ሲሆን " ድሮን ገዝቶ ለመታጠቅ የምንፈልገው አይነት የምንፈልገውን ቅርፅ መግዛት እንዳንችል ሻጮችም ሌሎችም ጫና ያሳድሩብን ነበር በኃላ ድሮን ገዝተን መታጠቅ ስንችል አጠቃቀሙ በፈለግነው ልክ operate ለማድረግ ፈተና ነበር " ብለዋል።

" ዛሬ ግን AI የታገዙ፣ ለማጥቃት የሚውሉ suicide ድሮችን ጭምር በኢትዮጵያ በዚህ ልክ ተመርቶ ማየት ለእንደኛ አይነት ህልመኛ ግለሰቦች አስደማሚ ውጤት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም አለው " ሲሉም ተናግረዋል።

" ገበያ በስፋት ማፈላለግ አለብን " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " በአፍሪካ ገበያ በስፋት እየሸጥን ተጠቃሚው እራሱ ከሚገጥመው ፈተናና ችግር በሚያመጣው ግብዓት መሰረት ማሻሻል ይጠበቅብናል " ብለዋል።

" የድሮን ቴክኖሎጂ ከአቬዬሽን ጋር የሚያያዝ ቢሆንም በውስጡ ከባድ የሚባሉ component አሉት አንዱ AI ነው የስማርት sensors በሌላ ተቋምም ቢሆን ማምረት ማጠናከር ያስፈልጋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ አሁን ተመረቀ ከተባለው ኢዱንስትሪ በተጨማሪ በአየር ኃይል እና በINSA የሚሰሩ ድሮኖች እንዳሉም ተናግረዋል።

ተቋማቱም እንዲናበቡና እንዲደጋገፉ መወዳደር ባለባቸው ሁኔታም ሊወዳደሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

እርስ በእርስ ቴክኖሎጂ መደበቅ እና መከልከል እንደማይገባ ይልቅም ለምርምር በመስጠት ይበልጥ እያደገ እንዲሄድ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንዱስትሪውን ባስመረቁበት ወቅት " መዘጋጀት ካልቻልን ጦርነት በማንኛውም ጊዜ ሊያጋጥምና ሀገር ሊያፈርስ ይችላል " ያሉ ሲሆን " ጦርነት ለማስቀረት በቂ ዝግጅት ማድረግ ይገባል ፣ ጦርነት አሳጥሮ ለመጨረስም በቂ ዝግጅት ያስፈልጋል " ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 “ መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ ከእገታው የወጡት ኢትዮጵያዊያንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል ” - ቤተሰብ 🔵 “ እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም? ” - ኢትዮጵያዊ በታይላንድ ➡️ “ ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው ” - የወላጆች ኮሚቴ ሰርተው ለመለወጥ ሲሉ ተታለው ወደ ታይላንድ…
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ

“ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር

ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር ላይ ያለ ቦታ እንደሆነ፣ የድረሱልን ተማጽኖ ቢያስሙም የሚደርስላቸው ባለመገኘቱ ራሳቸውን እስከማጥፋት ሙከራ እያደረጉ እንዳሉ ታውቋል።

በአካባቢው ባሉ ካምፓች የነበሩ ሌሎች ሰዎች ከእገታ እየወጡ እንደሆነ፣ " ዋልዋይ " ካምፕ የሚገኙትን ታጋቾች ግን እንዳይወጡ አጋቾቹ በድብቅ እንደያዟቸው ተመልክቷል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ ምን አሉ ?

“ በማይናማር ካምፕ የነበሩ 29 ኢትዮጵውያን ካምፓኒው ‘ወደ ሌላ ቦታ ልውስዳችሁ’ ሲላቸው ለደኀነታቸው አስተማማኝ ስላልሆነ እዚሁ ነው መቆት የምንፈልገው ብለው ነበር፡፡

ነገር ግን ካምፓኒው የጸጥታ ኃይሎችን ወዳነበሩበት ካምፕ በማምጣት እጃቸውን በግዴታ እየጎተተ በመኪና አሳፍሮ በማይናማር 'ዋልዋይ' የሚባል ቦታ ወስዷቸዋል፡፡

የተወሰዱት ገና አዲስ በመሰራት ባለ ኮምፓውንድ ነውና በጣም ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እየደረሰባቸው ይገኛሉ፡፡ ኮምፓውንዱ ህግ እና ስርዓት የለውም። በጋንግስተሮች ብቻ የሚተዳደር ነው። ለደኅንነታቸው የሚጮህላቸው የለም።

ሴቶችን ፀጉራቸውን ላጭተዋቸዋል። ወንዶችና ሴቶችን በኤሌክትሪክ ይገርፏቸዋል፤ በጨለማ ክፍል በማስገባት ከሦስት ቀናት በላይ ምግብ በመከልከል በሰንሰለት ያንጠለጥሏቸዋል።

እናም በማይናማር የነበሩ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። እንዲያውም ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ እያደረጉ ነው። በሰጡን መረጃ መሰረት።

እዚያ ከሄዱ በኋላ ይበልጥ ከባድ ችግር እየገጠማቸው ነው። ለካምፓኒው ሥራ ቢሰሩም ባይሰሩም ሁሌም ይቀጠቀጣሉ፡፡ ተስፋ ወደ መቁረጥ ደርሰዋል፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ አድርገዋከል ” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል፥ በማይናማር ታግተው አስከፊ ጊዜ ያሳለፉና ከወር በፊት ከእገታ የወጡ፣ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስትን የቪዛና ሌሎች ጉዳዮች ይሁንታ እየጠበቁ ታይላንድ ከሚገኙ ከ250 በላይ ዜጎች መካከል ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተረጋገጠላቸው ለመመለስ ትኬት ያላቸው 40 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያኑ ነግረውናል፡፡

ሌሎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚችሉት በራሳቸው ሙሉ ወጪ ትኬት ሲቆርጡ መሆኑን እንደተናገሩ፣ የደርሶ መልስ ቪዛና ለትኬት መቁረጫ ገንዘብ የሌላቸው በርካቶች ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ “ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር…
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እዚህ ያለነው ወደ 70 ኢትዮጵያውያን ነን ፤ ያለንበት ሁኔታ አስከፊ ነው ፤ ያናገረን አንድም አካል የለም " - ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በማይናማር / ማይዋዲ KK2 የሚባለው ስፍራ የሚገኙ በቁጥር 70 የሚሆኑ ወጣቶች ከቦታው የሚያስወጣቸውን አጥተው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያሉበት ቦታ በማይናማር ወታደራዊ ሰዎች እየተጠበቀ እንዳለ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያኑ " እኛ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን። 70 እንሆናለን። ማንም መጥቶ የጠየቀን የለም። መቼ እንደምንወጣም አናውቅም። ሁሉ ነገር ጨልሞብናል " ብለዋል።

" የሚሰጠን ምግብ የማይበላ ነው። ማደሪያ የለንም እንጨት ላይ ነው የምንተኛው ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ለመናገር ይከብዳል ስቃይ ላይ ነን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው አንድ ወንድማችን በጣም ታሞ በስንት መከራ ነው ህይወት የዘራው " ሲሉ አክለዋል።

" ያሉትን የMilitary ሰዎች ጠይቀናቸው ነበር አብረውን ካሉት ውስጥ ' የህንድ መንግሥት ዜጎቹን ለመውሰድ accept ስላደረገ እነሱ ይወጣሉ በእናተ በኩል ምንም ምላሽ የለም ' ብለውናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ትወጣላችሁ የሚለን የለ ወይ ስለኛ የሚናገር የለም እባካችሁ ስቃያችንን ስሙን " ሲሉ ተማፅነዋል።

" ህንዶቹ ነገ እና ከነገ ወዲያ ይወጣሉ ዛሬ እየተዘጋጁ ነው ከኛ ሀገር በኩል ያናገረን የለም በጣም ተጨንቀናል " ብለዋል።

እኚህ ወጣቶች ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ ታይላንድ ተብለው ወደ ማይናማር በግዳጅ የተወሰዱና በዛም በማፊያዎች ስንትና ስንት ስቃይ ያዩ ሲሆን ከዛ ስፍራው እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ አሁን ደሞ ሌላ ስቃይ እያዩ እንደሆነ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ብርሃን_ባንክ
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_2%_ #እና_ልዩ_ስጦታ_ያገኛሉ

ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ባንክ ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የምንዛሬ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " - የወላጆች ኮሚቴ

➡️ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " - ተመላሽ ኢትዮጵያዊ

ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ታይላንድ ካምፕ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 32 የሚሆኑት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የወላጆች ኮሚቴና ተመላሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " ብሏል።

ልጆቹን ለሀገራቸው እንዲበቁ ላደረጓቸው ምስጋና አቅርቦ፣ ከእገታ ወጥተው በታይላንድ ያሉ፣ በማይናማር ገና ከእገታ ያልወጡና ወጥተው ወደ ታይላንድ ያልተሻገሩ፣ ጭራሹንም ያሉበት የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያንን መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

ከተመላሾቹ መካከል አንዱ፣ 32 ልጆች መምጣታቸውን አረጋግጦ፣ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ 32 ልጆች እንደመጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት አረጋግጧል። 

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያ መካከል 32ቱ ዛሬ ወደ አገራቸው ገልጾ፣ " 43  ኢትዮጵያውያንን ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል " ብሏል።

" ቀሪዎቹ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ኤምባሲው ጥረት እያደረገ ይገኛል " ሲልም አክሏል።

ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ  አገራቸው ለመመለስ  ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#USAID

ከስድስት ሳምንት ግምገማ በኋላ አሜሪካ 83 በመቶ የሚሆነውን የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት
(USAID) ፕሮግራሞችን መሰረዟን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በX ገጻቸው አስታውቀዋል።

" በቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግባቸው የነበሩ 5,200 ኮንትራቶች ተቋርጠዋል " ያሉት ሚኒስትሩ " እነዚህ ለብሔራዊ ጥቅማችን ምንም የማያገለግሉ አንዳንዶቹ እንደውም የሚጎዱ ጭምር ናቸው " ሲሉ ነው የገለጹት።

ቀሪ 18 በመቶ የሚሆኑት ፕሮግራሞች (1000 የሚጠጉ) በስቴት ዲፖርትመንቱ በአግባቡ እየተመራ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

Via
@tikvahethmagazine
" ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት እርምጃ ይውሰዱ " - ጠቅላይ ም/ቤቱ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይ ደግሞ በቲክቶክ ላይ አንድ ግለሰብ ነብዩ ሙሀመድ " ﷺ " እና እስልምናን መዝለፉ በርከቶችን አስቆጥቷል።

ጉዳዩን በተመለከተም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መግለጫ ልኮልናል።

በዚህም መግለጫው የጥላቻ ንግግር በማድረግ ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ አጥብቆ አሳስቧል።

የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የገለጸው  ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል እንደቆየ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ መሆኑን ጠቁሟል።

የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራም አሳውቋል።

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ አሳስቧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፦

➡️ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመካረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን፤

➡️ ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

➡️ የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤

➡️ ወቅቱ በሙስሊሞችና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የጾም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ም/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia