#AddisAbaba
" አባታችንን አፋልጉን ! "
አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።
እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።
በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።
መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።
ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው
@tikvahethiopia

ብልህ ለራሱ ያውቃል ... በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ህይወትን ቀለል አድርጎ ይመራል።#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#እንድታውቁት
አዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ :-
1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ ፤
2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤
3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸውን እና ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሰ የአዲስ አባባ ከተማ አስታዳደር አሳውቋል።
#AU #ADDISABABA

የኢትዮጵያ እና አፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች።
በርካታ እንግዶች ለ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።
ዛሬ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዲሁም የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገብተዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #ADDISABABA
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታውቋል።
የፀጥታና ደኅንነት ጥምር-ኃይሉ " የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ በማጠናከር የኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ ሳይገታ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ በማድረግ በቅንጅት በመሥራቱ ጉባኤው በስኬት ተጠናቋል " ሲል ገልጿል።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል " ብለዋል።
" ጉባኤው እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው የተለየ ሁኔታ የተካሄደ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
እንግዶች ወደየሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

“ እግዱ እንዲሰጥ መደረጉ ተገቢነት ስለሌለው እግዱ ሊነሳ ይገባል ”- እናት ፓርቲ ይግባኝ ባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያሰራጨው የቤት ግብር ግምት ማሻሻያ የጥናት ሰነድን በተመለከተ ያቀረበው የእግድ ማመልከቻ እንዲነሳለት እናት ፓርቲ ጠየቀ። ቢሮው፣ “ከሕግ ውጪ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ለከተማው የግብር ሰብሳቢ አካላት የበተነው” ሰነድ ከፍተኛ ግብር የሚጥል፣ የቤት ግብር…
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ ስልጣን ያለው መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ያለው ሲሆን፣ ይህን ግብር ከመሰብሰብ የሚከለክል ምንም አይነት ህጋዊ አካል እንደሌለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።
ከንቲባዋ የጣራና የግድግዳ ግብርን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ የጣራና የግድግዳ ግብር አዋጅ በ1968 ዓ.ም የወጣ አዋጅ መሆኑን አስታውሰዋል።
በወቅቱ የነበረው አሰራር አሁንም እንደቀጠለ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ነገር ግን የተለወጠው ወቅቱን ያገናዘበ የዋጋ ተመን ብቻ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም አዋጁ ሲወጣ የነበረው የኪራይ ዋጋ እና አሁን ያለው የኪራይ ዋጋ እኩል ባለመሆኑ አሁን የጨመረው ኪራዩ መሆኑን ጠቁመዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የሚያስከፍለው ግብር ግን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን ለመኖሪያ ቤት የዋጋውን ግማሽ እንዲሁም ለንግድ ቤቶች 75 በመቶ ብቻ እንደሆነ ከንቲባዋ አብራርተዋል።
በከተማዋ በግብር ስርዓት ውስጥ ያልነበሩ በርካታ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች፣ በከተማዋ ካሉ 800 ሺህ ህንጻዎችና ቤቶች ግብር ይከፍሉ የነበሩት 120 ሺህ ብቻ እንደነበሩ ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

🚨" ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ ተቀጥተዋል !! "
እንደ ሸገር ሬድዮ ዘገባ ፥ በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ።
ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም።
ባለፉት በ6 ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ ተቀጥተዋል፡፡
ይህም በየቀኑ 7,183 አሽካርካሪዎች መቀጣታቸውን ያሳያል፡፡
በሌላ በኩል " የታጠፈ የደበዘዘ የተፋፋቀ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አደርጋለሁ " ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡
ባለፈው በጥር ወር ብቻ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ2,100 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየተባባሰ ለመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ልዩ ልዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች እንደ ምክንያትነት የሚገለጹ ቢሆንም ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች መበራከት ለአደጋ ብቻ ሳይሆን የወንጀል ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል፡፡
በየጊዜው የታጠፈ የደበዘዘ እና የተፋፋቀ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ያለው ፖሊስ አሁንም ጠንካራ የቁጥጥርና አደርጋለሁ ብሏል፡፡
ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥፋቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ 1500 ብር ያስቀጣል፡፡
መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ወደ አቢሲንያ ፖስ ማሽን ስልክዎን ጠጋ ብቻ በማድረግ ይክፈሉ !
ፈጣንና አስተማማኝ የሆኑት የአቢሲንያ ባንክ ፖስ ማሽኖች ሁሉንም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶች የሚቀበሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የተለያዩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ያስተናግዳሉ። እርስዎ ብቻ ይፈልጉን - በየቦታው አለን! የሁሉም ምርጫ መሆናችን በምክንያት ነው!
#BankOfAbysinia #POSMachine #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ዓመት / 2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርት ለመመዝገብ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ወይንም ፋይዳ መያዝ አስገዳጅ ሆነባቸው፡፡
የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
ተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ አንዲያካሂዱ በዘመቻ መልክ ለመሰራት የታሰበ ሲሆን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናትን ምዘገባ በዘመቻ እንደሚከናወን መነገሩን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

#እንድታውቁት #AddisAbaba
ከዛሬ ለሊት 6:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ ነገ 7:00 ሠዓት ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።
129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ነገ ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይከበራል።
ይህን ተከትሎ ፦
- በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት
- ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር
- ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ
- ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት
- ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ
- ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት የሚወስዱት መንገዶች ከዛሬ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከለሊቱ 6፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ህብረተሰቡም ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbaba 🚨" ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊየን 293 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ ተቀጥተዋል !! " እንደ ሸገር ሬድዮ ዘገባ ፥ በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ። ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም። ባለፉት በ6 ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ…
#AddisAbaba
በተደመሰሰ፣ በታጠፈ እና በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር ሲገለገሉ የተገኙ ከ1,000 በላይ አሽከርከሪዎችን ቀጥቻለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አሽከርካሪዎች የተቀባ፣ የታጠፈ ፣ የተፋፋቀ፣ የተቆራረጠ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ ቆይተዋል ሲል ፖሊስ አስታውሷል፡፡
አንዳንዶቹ እንደውም ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው ብሏል፡፡
ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ ቁጥጥር 1,587 ተሽከርካሪዎች ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን ለጥፈው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡
የተፋፋቀ፣ የደበዘዘ፣ የታጠፈ እና የማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር መጠቀም፣ ከሰሌዳ መብራት ውጪ ሌሎች ዓይነቶችን አብረቅራቂ መብራቶችን መጠቀም፣ ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ መለጠፍ እና ሆን ብለው ሰሌዳን አጥፎ መንቀሳቀስ በቁጥጥሩ ወቅት የተገኙ ጥፋቶች ናቸው ሲል ፖሊስ አስረድቷል፡፡
በጥፋት ውስጥ ከተገኙት ውስጥ ኮድ-1 ወይም ታክሲ 216፣ ኮድ-2 ወይም የቤት መኪና 320፣ ኮድ-3 የሆኑ 1,037 እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች 14 መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ጠቅሷል፡፡
ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል አብዛኛዎቹ የፊት ወይም የኋላ ሰሌዳ ሳይኖራቸው የተገኙ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 633ቱ ደግሞ የተቆረጠ ወይም ለዕይታ ግልጽ ያልሆነ ሰሌዳ ሲጠቀሙ የተገኙና ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ ያሰሩ፣ የተሸፈኑና የተለያየ ቀለም የተቀቡ ሰሌዳዎች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
#AddisAbabaPolice #ShegerFM