TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ። 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአህጉሪቱ መዲና በሆነችሁ በአዲስ አበባ ዛሬ በይፍ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ከ35 በላይ የሀገር መሪዎች፣ አንድ ንጉስ፣ 19 ቀዳማዊት እመቤቶች፣ ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዲስ…
#AU

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጠናቋል።

በጉባዔው ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሕብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች አመራሮች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው ፦
➡️ የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣
➡️ የማካካሻ ፍትህ፣
➡️ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣
➡️ አህጉራዊ ሰላምና ደህንነት፣
➡️ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፈጻጸምና አህጉራዊ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር፣
➡️ ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥ፣
➡️ ሰብዓዊ መብቶች፣
➡️ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማትና አደረጃጀቶች ምርጫ ውይይት ከተደረገባቸው ዋንኛ አጀንዳዎች መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተቋማት አመራሮች ጋር መክረዋል።

ባለፉት ቀናት እጅግ በርካታ አህጉር አቀፍ መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችን ፣ እንግዶችን ስታስተናግድ የቆየችው የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እንግዶቿን እየሸኘች ትገኛለች።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ብርሃን ልዩ ካርድን በመጠቀም በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብዎን ወጪ ያድርጉ፣ በፖስ ማሽኖች ክፍያዎችን በቀላሉ ይፈጽሙ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#berhanatm #berhanpos #payment #cashout #liyucard #berhanliyucard #berhanbank
#bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #ADDISABABA

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታውቋል።

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር-ኃይሉ "  የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ በማጠናከር የኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ ሳይገታ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ በማድረግ በቅንጅት በመሥራቱ ጉባኤው በስኬት ተጠናቋል " ሲል ገልጿል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል " ብለዋል።

" ጉባኤው እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው የተለየ ሁኔታ የተካሄደ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

እንግዶች ወደየሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

@tikvahethiopia
“ ይሳቅ ህሩይ የትግራዋይ ነው። ከፋኖ ጋር ሊያገናኘው የሚችል አንዳችም ነገር የለም።  ” - ኢሕአፓ ስለታሰረው አመራሩ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባሉ አቶ ይሳቅ ወልዳይ እንደታሰሩበት ገልጿል።

ፓርቲው አመራሬ “በሐሰተኛ ፍረጃ ነው” የታሰሩብኝ ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ፕሬዜዳንት መጋቢብሉይ አብርሃም ሃይማኖት በሰጡት ቃል ፥ "  የካቲት 6/2017 ዓ/ም ከቤታቸው በፓሊስ ተወስደው ነው የታሰሩት።  ' ፋኖ ይደግፋል '  በሚል ሐሰተኛ ውንጀላ ነው የተወነጀለው " ሲሉ
ገልጸዋል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ፕሬዜዳንት በዝርዝር ምን አሉ ? 

“ ሰላማዊ ታጋዮችን በሐሰተኛ መረጃ እያሸማቀቁ እያሰሩ፤ ጋዜጠኞችን እያሳደዱ ሀገር ሰላም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ ሰላም ጠሉ ራሱ መንግስት እንደሆነ ነው እያረጋገጠልን ያለው።

አቶ ይሳቅ ከተባለበት ጉዳይ ጋር የሚያያይዘው አንዳችም ነገር የለም። መንግስት ሕግ ማክበር እንዳለበት የዘነጋው ይመስለኛል። መንግስት ሕገ መንግስቱን አክብሮ ነው የሚያስከብረው፤ ራሱ እየደፈጠጠ መሆን የለበትም።

ይሳቅ ህሩይ የትግራዋይ ነው። ከፋኖ ጋር ሊያገናኘው የሚችል አንዳችም ነገር የለም። ግን ‘የአፍሪካ ህብረትን ለመበጥበጥ፣ መሪዎችን ለመግደል’ የሚል ሐሰተኛ ፈጠራ ሲያቀናብሩ አእምሯቸው እንዴት አቀናበረው ? ብለን እንድንጠይቅ አድርጎናል።

ከዚህ በፊት ዓርዓያ ተስፋማርያም በሚባል ጋዜጠኛ ነኝ በሚል ግለሰብ ይሄው አባላችን ታስሮ በጩኸት ወጥቷል። አሁንም በሐሰተኛ ቅንብር፣ ከመንግስት አካላት ጋር ያላቸው ግንኙነትን በመጠቀም ታስሯል ” ብለዋል።

አመራሩ ከ“ፋኖ” ጋር በተገናኘ የተጠረጠሩት ፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን ከምን ጋር አገናኝቶት ነው ? ለሚለው ጥያቄ በምላሻቸው፣ በኮሪደር ልማት አዲስ አበባ ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ካሳ እንዳልተከፈላቸው በማጋለጣቸው ነው ሲሉ ጠቅሰዋል። 

አክለው፣ “ ያንን ተከትሎ ኢሕአፓን ለማሸማቀቅና ቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጠንካራ ሰላማዊ ትግል እንዳያደርግ ሆን ተብሎ ለማስፈራራት የተቀናበረ ቅንብር ነው ” ብለው፣ ፓርቲው በዚህ እንደማይሸማቀቅ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የፌደራል ፓሊስ የምርመራ ጊዜ ማጣሪያ የጠየቀበት ደብዳቤ፣ ከአቶ ይሳቅ ጋር 13 ግለሰቦችን ጠቅሶ " በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሰው " ቡድን ግንኙነት አላቸው በሚል ይወነጅላል።

ፓሊስ፣ “ ምርመራውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት ” የ14 ቀናት የቀጠሮ ጊዜ እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቡን ደብዳቤው ያትታል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ከንቲባ በበኩላቸው፣ “ ሰኞ ፍርድ ቤት ለኛ ቀጠሮ ሰጥቶናል የፌደራል ፓሊስ የ14 ቀን ቀጠሮን ውድቅ በማድረግ ‘ተጨባጭ መረጃ ካላችሁ አምጡ’ በማለት” ብለዋል። 

“ ፍርድ ቤቱም ‘እንደዚህ አይነት ሐሰተኛ ቅንብሮች እየተለመደ ስለመጡ ተጨባጭ ነገር ካለ አምጡ አለዚያ ጊዜ ቀጠሮ አልሰጣችሁም’ ብሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል ” ነው ያሉት።

13ቱም “ተጠርጣሪዎች” የፓርቲው አካላት ናቸው ? ስንል የጠየቅናቸው ተቀዳሚ ፕሬዛዳንቱ፤ ከአቶ ይሳቅ ውጪ ያሉት 12 ተጠረጠሩ ተብለው የታሰሩ ግለሰቦች ከፓርቲው ጋ ግንኙነት እንደሌላቸው አስረድተዋል።

“ ነጋዴዎች አሉ ምንም ፓለቲካ ውስጥ የሌሉ። በተጨባጭ መረጃ ያለን አንድ ካድሬ ከጠላ ይፈርጅህና ለወራት ታሽተህ ትለቀቃለህ። ዜጎችን ማሸማቀቂያ፣ ማሰቃያ ሆኗል የፍትህ ስርዓቱ ” ሲሉ ወቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “ የተሰጠው መልስ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው ” - አርሶ አደሮች

➡️ “ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል ” - ግብርና ሚኒስቴር 


ሀዋሳ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና በበቆሎ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ከአምናው እጥፍ በላይ በመጨመሩ ማምረት እንደማይችሉ ሰሞኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም።

“ አምና 3,600 ብር ስንገዛው የነበረውን ማዳበሪያ ዘንድሮ 8,400 ብር ለመግዛት ተገደናል። አምና 1,800 ብር  የነበረው የአንድ ፕሎት ምርጥ ዘር በቆሎ ዘንድሮ 4,600 ብር ገብቷል ” ሲሉ ነበር ያማረሩት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ምላሽ የጠየቀው የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ፣ “ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። የጨመርነው ነገር የለም። የትራንስፓርት ብቻ ነው የጨመርነው ” ብሎ፣ የምርጥ ዘር በቆሎ ዋጋም ከትራክተር፣ ከነዳጅ ዋጋ ጋር በተያያዘ መጨመሩን ቢሮው አልደበቀም።

አርሶ አደሮቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ የሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮ የሰጠው ምላሽ አጥጋቢ ካለመሆኑም አልፎ ከእውነት የራቀና በህዝቡ ስቃይ እንደመሳለቅ የሚቆጠር ነው። ምላሹ ‘ማዳበሪያ ላይ  የተደረገው ጭማሪ የትራንስፖርት ብር ብቻ ነው’ ብሏል።

የትራንስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ለማዳበሪያ በአመት 4,000 ብር መጨመር ዝርፊያ እንጂ ጭማሪ አይባልም። የበቆሎውን በተመለከተም ቢሮው፣ የትራክተርና የነዳጅ ጭማሬን በመጥቀስ ነው ምላሽ የሰጠው።

ለህዝቡ ማሳውን የሚያርሰው መንግስት አይደለም ህዝቡ በራሱ ገንዘብ እንጂ። ስለዚህ የማይገናኝ ነገር አገናኝቶ ህዝቡን ማሰቃየት አግባብ አይደለም። 

በቆሎ የሚዘራው ከታህሳስ 15 ጀምሮ ነው። የሻመና ህዝብ ለአንድ ፕሎት እስከ 17,000 ብር በላይ አውጥቶ እንዴት ሊገዛ ይችላል ? ምንስ ሊያተርፍ ነው ? በዚህ ኑሮ ውድነት ገንዘቡንስ የት ነው የሚያመጣው ? ነው ወይስ ህዝቡን ነገ በረሃብ መቅጣት ነው የተፈለገው ? 

በአንድ በኩል ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ የማይጠቀም አርሶ አደር እንዳይኖር ያስገድዳሉ፣ በሌላ በኩል ዋጋ በማናር እንዳይጠቀም ማድረግ አይጋጭም ? አርሶ አደሩ ዘንድሮ ምርት አያመርትም። መንግስት ችግሩን ይፍታልን ”
ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሩ ሲከፋፈል ዋጋው ምን ያክል ነው ? አርሶ አደሮች ዘንድሮ የተጋጋነ ዋጋ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል። ጭማሬው ከላይ ነው ከታች ? ኩንታል ማዳበሪያ (ለምሳሌ ዳፕ) ዋጋው ስንት ነው ? ሲል ለግብርና ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ምን መለሱ?

“ አንድ ኩንታል እንደዬአካባቢው ስለሚለያይ ይህን ያክል ነው ብለን ለመግለጽ ያስቸግረናል። ምክንያቱም በርቀቱ ስለሚወሰን። በትራንስፓርት ነው የሚለያዩት። 

ከዚያ ውጪ በሁሉም የአገራቷ ክፍል የሚሰራጨውን ማዳበሪያ ሴንትራሊ ዋጋ አውጥቶ የሚልከው ግብርና ሚኒስቴር ነው። ዋጋ ስናወጣ በግብርና ሚኒስቴር በኩል የሚጨመር ምንም አይነት የፕሮፊት ማሪጅን የለም። 

ማዳበሪያው የተገዛበት፣ የትራንስፓርትና ሌሎች እንዲሁም ወጪዎች ተደርገው የአንድ ኩንታል ዋጋ ተሰልቶ ነው ወደ ታች የሚወርደው። መንግስት 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል።

ማዳበሪያ ከአምናው አንጸር ሲወዳደር ዋጋ በተወሰነ መንገድ ጨምሯል። ስለዚህ ታች የጨመረ ዋጋ ሳይሆን ማዳበሪያው የተገዛበት፣ ከሪፎርሙ ጋር የተወሰነ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ ስላለ፣ በዚያ ምክንያት የማዳበሪያ ዋጋ ጨምሯል። 

ማዳበሪያ በዶላር ከውጪ ነው የሚገዛው። ታች ሊጨመር የሚችለው ትንሽዬ ወይ 100 ብር ወይ 50 ብር የዩኒየን ማሪጅን፣ ወደ ታች ደግሞ ሲወርድ እኛ እስከ ማዕከላዊ መጋዘን ነው የምናቀርበው። 

ከማዕከላዊ መጋዘን ወደ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማኀበር ሲያወርዱ ሁሉም ክልሎች እንደየርቀቱ የትራንስፓርት ዋጋ ልዩነት ይኖራል። 

ስለዚህ አንድ ኩንታል ዋጋ ይሄን ያክል ብር ነው ብልህ ሀገራዊ ዋጋን ሪፕረሰንት ስለማያደርግ እንደዬ አካባቢው የተለያዬ ነው የሚሆነው። ግን ሴንትራሊ ለሁሉም የተገዛበትም ድጎማውም እኩል ነው የሚሰራው ”
ብለዋል።

በአጠቃላይ ያለውን አቅርቦት ሲያስረዱም፣ “ 24 ሚሊዮን ኩንታል ነው የምናቀርበው። እስካሁን የ13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ ፈጸመናል ” ነው ያሉት።

(ማዳበሪያን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
አፖሎ ከአቢሲንያ ባንክ የቀረበ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጀታል ባንክ መተግበሪያ ሲሆን በቅድሚያ እርስዎ ተመዝግበው ለወዳጅ ዘመዶችዎ የተመዘገቡበትን መለያ ስልክ ቁጥር በመላክ እነሱንም ያስመዝግቡ።                                                                                                                                                                                   የሽልማቱ ዕጣ አሸናፊ ለመሆን አዲስ አካውንት መክፈትና ከ1000 ብር ጀምሮ መቆጠብ ይኖርብዎታል።
ወዳጅ ዘመዶችዎንም ወደ አፓሎ በመጋበዝ  የዕጣ ቁጥሮችን በመሰብሰብ ባንኮክን የማየት ህልምዎን እውን ያድርጉ ። በተጨማሪም አይፎን 16 ፣ ሳምሰንግ S24 እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች በዕጣዎቹ ተካትተዋል።  መልካም ዕድል! 
አፖሎ ዲጅታል ባንክ  መተግበሪያውን ለማውረድ https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo   ይጫኑ! 
ደንብ እና ግዴታዎች https://yangx.top/apollodigitalproduct/248
#ApolloReferral #መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewards
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የካቲት 11 በዓል ምን አሉ ?

" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) 50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል በማስመልከት በትግርኛ ቋንቋ ለመላው የትግራይ ህዝብ " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።

በአገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙት የትግራይ ተወላጆች እና ወዳጆች " ለ50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል እንኳን አደረሳችሁ " በሚል መልዕክታቸውን ያስቀደሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፥ የትግራይ ህዝብ ባለፉት ዘመናት ተጋድሎ ለአገር  ሉአላውነት እና ዳር ደንበር መከበር የከፈለውን መስዋእትነት በታላቅ ክብር አስታውሰዋል። 

በአገራችን ታሪክ ፓለቲካዊ ልዩነቶች በህግ ወይ በመግባባት የመፍታት የዳበረ ልምድ እንዳልነበረ ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ማህበረሰቡ በየብሄሩ እና አከባቢው የሚፈጠሩት ልዩነቶች በእርቅ እና ሽምግልና መፍታት በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች የተዘወተረ ነው ብለዋል። 

" ይህ ሆኖ እያለ ፓለቲካው ከባህል አፈንግጦ ሁሉም ልዩነቶች በግጭት ብቻ መፍታት ፓለቲካዊ ባህል ሆኖ ለዘመናት ቆይተዋል አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ፓለቲካዊ ልዩነት በውይይት ፣ በእርቅ እና መግባባት ብሎም በህገ -መፈታት አለበት የሚለው አቋም ከለውጡ በኋላ እንደ መንግስት የተያዘ አቋም ነው  ጠቅላአቋመያዝ በዘለለ ሕጋዊ እና ተቋማዊ አሰራር ተበጅቶለት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ " ገልፀዋል። 

" አሰራሩ ጅምር ላይ መሆኑ ልብ ማለት ይገባል " ያሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ጭቆና በምክክር እና ህጋዊ አሰራር መፈታት በማይችልበት ወቅት የነበረው ብቸኛ አማራጭ ጠብመንጃ በማንሳት ዴሞክራሲ እና እኩልነት ለማስፈን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማበር የየካቲት 11 ትግል ለማካሄድ መገደዱን አስታውሰዋል። 

" ጠበመንጃ በማንሳት የሚካሄድ የግጭት መንገድ በመሰረቱ የሚደገፍ ባይሆንም በወቅቱ የነበረው ፓለቲካዊ እና ህጋዊ ሁኔታ ግን ጠብመንጃ ለማንሳት የሚያስገድድ ነበር " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " የካቲት 11 የተቀጣጠለው በጠብመንጃ የታገዘ ፓለቲካዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማቆም ልየነቶች በውይይት ለመፍታት ያለመ በመኖሩ ከሱ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩት ትግሎች ሲነፃፀር ይለያል " ብለዋል።  

ስለሆነም ማንኛውም ልዩነት በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት እና በህጋዊ መንገድ መፍታት የየካቲት 11 ፍሬዎች መሆናቸው መገንዛብ ያሻል ሲሉ አክለዋል።

" ባለፉት የቅርብ ዓመታት ያጋጠሙን መቃቃሮች ለመፍታት የተከተልነው የግጭት  መንገድ ፤ ከየካቲት 11 ዓላማዎች የወጣ መሆኑ ግልፅ ነው ፤ ይሁን እንጂ ከባድ ዋጋ ከፍለንም ቢሆን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚደነቅ እርምጃ ነው ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ፓለቲካዊ ልዩነት በጠንጃ ለመፍታት የመፈለግ ዝንባሌ መታየቱ አልቀረም " ብለዋል።

" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ አመራሮች መካከል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለውጤት እንዲበቃ ያላቸው መልካም ምኞት ገልፀዋል።

ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ፣ የተስተጓጎለው ልማት ተጠናክሮ በህዝብ ወደ ተመረጠ መንግስት ሽግግር እንዲደረግ  ከልብ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።  

የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በተገለፀው የውውይት መንፈስ ማሰብ ከጀመሩ ፤ ትግራይ ወደ መደበኛ የህገ-መንግስት ስርዓት በመመለስ በሃገረ መንግስቱ ያላትን ተሳትፎ  አጠንክራ  የምትቀጥልበት ጊዜ በጣም አጭር እና ተጨባጭ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

መልካም የየካቲት 11 በዓል እንዲሆንም በፅሁፋቸው ተመኝተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል ! "

የ17 አመት ታዳጊ በሆነችው አዶናይት ይሄይስ ላይ የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተወሰነበት።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ክልል ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

የወንጀሉ ሰለባ የሆነችው የ17 አመት እድሜ ያላት አዶናይት ይሄይስ የተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የፍቅረኛው ልጅ ነበረች።

መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰአት ሲሆን ታዳጊ አዶናይት ይሄይስ መኖሪያ ቤቷ እያለች ተከሳሽ " ለምን አስገድዶ ደፈረኝ ብለሽ ለፖሊስ ክስ መሰረትሽ " በሚል ሰበብ በቢላዋ የተለያየ የሰውነት ክፍሏን 16 ቦታ በመውጋት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ ልብሱን በመቀየር ሊሰወር ሲሞክር በአካባቢው ማህበረሰብ እና በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም በተያዘው ተከሳሽ ላይ ባደረገው ምርመራ ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ባልታወቀ ጊዜና ሰዓት ታዳጊዋን " ነይ ሱቅ ልላክሽ " እና ሌሎች ማታለያዎችን እየተጠቀመ በመኖሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት የቆየ መሆኑንና በወቅቱ እድሜዋ በግምት 10 አመቷ እንደነበረ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ የእናቷ የፍቅር ጓደኛ የነበረ ሲሆን ይህንን አፀያፊ ድርጊት ለአንድ ሰው ብትናገሪ እናት እና አባትሽን እገላለሁ እያለ ሲያስፈራት የቆየ ስለመሆኑ የሚዘረዝረው የምርመራ መዝገቡ በተጨማሪም ሟችን " በሞባይል ካሜራ ቪዲዮ ቀርጬሻለሁ በሚዲያ እና በቴሌግራም እለቀዋለሁ " እያለ ለአመታት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት መቆየቱንና በዚህም ታዳጊዋ ከተከሳሽ በመፀነሷ ፅንሱን እንድታስወርድ ማድረጉን የተከሳሽ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

ፖሊስ ባከናወነው ተጨማሪ የምርመራ ስራ ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ቦታው ድረስ በመሄድ መርቶ ያሳየ ሲሆን የምርመራ መዝገቡን በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለዓቃቤ ህግ በመላክ ክስ ተመስርቶበታል።

የወንጀል መዝገቡን ሲከታተል የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ
#የሞት_ቅጣት እንዲቀጣ እና የዘወትር ህዝባዊ መብቶቹ እንዲሻሩ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ። ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ…
#Update

" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።

በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia