TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Breaking : የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሚኒስትሩ አብረዋቸው ለውድድር የቀረቡትን የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁም የማዳጋስካሩን ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው የተመረጡት። @tikvahethiopia
#Update

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ 6 ዙር ከፈጀው የድምጽ አሰጣጥ በኋላ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው መመረጥ ችለዋል።

የምርጫ ሂደቱ ምን ይመስላል?

በምርጫው የሚያሸንፈው ተመራጭ ድምጽ መስጠት ከሚችሉት 48 አባል ሀገራት ሁለት ሶስተኛውን ድምጽ (33 ድምፅ) ማግኘት ይጠበቅበታል።

በሚደረገው ምርጫ ለማሸነፍ የሚያስፈልገውን 33 ነጥብ ማግኘት ካልተቻለ ተከታታይ ምርጫዎች የሚካሄዱ ሲሆን ዝቅተኛ ድምጽ ያገኘው ከውድድሩ ተሰናብቶ ቀሪ ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ የሚያስችላቸውን ነጥብ እስኪያገኙ ይወዳደራሉ።

በዚህም ለ7ኛ ጊዜ በተደረገው በዚህ ውድድር አሸናፊውን ለመለየት 6 ዙሮች ፈጅቷል።

በመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዙሮች የኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መምራት ቢችሉም የማሸነፊያ ነጥብ ሳያገኙ ቀርተዋል።

በስድስተኛው ዙር ድምጽ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን 33 ነጥብ በማግኘታቸው ምርጫውን አሸንፈዋል።

በዚህም ለቀጣይ 4 ዓመታት የቀድሞውን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂን በመተካት 7ኛው የኅብረቱ ሊቀመንበር በመሆን መመረጥ ችለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ እግዱ እንዲሰጥ መደረጉ ተገቢነት ስለሌለው እግዱ ሊነሳ ይገባል ”- እናት ፓርቲ

ይግባኝ ባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያሰራጨው የቤት ግብር ግምት ማሻሻያ የጥናት ሰነድን በተመለከተ ያቀረበው የእግድ ማመልከቻ እንዲነሳለት እናት ፓርቲ ጠየቀ።

ቢሮው፣ “ከሕግ ውጪ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ለከተማው የግብር ሰብሳቢ አካላት የበተነው” ሰነድ ከፍተኛ ግብር የሚጥል፣ የቤት ግብር ክፍያን የሚለውጥ በመሆኑ ‘ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም’ ተብሎ በመመሪያ እንዲሻር በሙሉ ድምፅ” የተሰጠውን ውሳኔ እግድ እንዲሰጠው ማመልከቱን እንደተገነዘበም ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው ይህን ያለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከውና ጉዳዩን በተመለከተ የተቃውሞ ባወጣው መግለጫ ነው።

ፓርቲው በመግለጫው፣ ይግባኝ ባይ የፌራሉ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እና አፈጻጸሙ እንዲታገድለት ለእግዱ የተለያዩ ምክንያቶች ማቅረቡን በበደረሰው የእግድ ትዕዛዝ እንዳወቀና ምክንያቶቹን እንደማይቀበላቸው ገልጿል።

በዚህም ፓርቲው፣ ፍርድ ቤት ጥር 9/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት፣ “የይግባኝ አቤቱታው ተመርምሮ የዚህ ችሎት ውሳኔ ውጤት ከመታወቁ በፊት እንደስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢፈጸም ሊካስ የማይችል ጉዳት እንደሚደርስባቸው ስለገመትን” በሚል የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ አዟል” ብሏል።

አክሎ፣ “ይሁን እንጂ ይግባኝ ባይ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊታገድለት እንደሚገባ በምክንያትነት ያቀረባቸው ነጥቦች በሙሉ መሠረተ ቢስ” መሆናቸውን በመጥቀስ የእግድ ትዕዛዙ እንዲነሳ ተቃውሞ አቆርቧል።

ፓርቲው፣ ይግባኝ ባይ፣ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲታገድለት፣ “ውሳኔው ቢፈጸም የከተማ አስተዳደሩን መብትና ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ በመሆኑ” ሲል ምክንያት ማቅረቡን ጠቅሶ፣ የነበረው ክርክር ለከተማ አስተዳደር ተብሎ በተጠበቀለት መብትና ጥቅም ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ድሮም በነበረ የግብር ክፍያ መሰረት መሆኑን ገልጿል።

“ይግባኝ ባይ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ከከተማው ነዋሪዎች ላይ በስራ ላይ ባለው አዋጅና ደንብ በተደነገገው መሠረት ግብሩን ለመተመንንና ለመወሰን የፈጠረበት ደንቃራና የአፈጻጸም ችግር በሕግ የተደገፈ ምንም አይነት ምክንያት ዘርዝር” አለማቅረቡን ፓርቲው አስረድቷል።

የእግዱ መነሳት የሚያስገኘውን ጥቅም በገለጸበት አውድ ፓርቲው፣ “የሕግ መሰረት የሌለውንና ከአገራችን ህግ ሥርዓት ውጪ በጥናት ሰነድ ላይ በመመስረት የሚጣል የግብር አተማመንና አሰባሰብ የአገሪቱን የግብር ሥርዓት የሚያናጋ የዘፈቀደ እርምጃ በመሆኑ በፍትህ ስርዓቱ በመጠቀም ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲገባ ያደርጋል” ብሏል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
“ ድግግሞሹ ቀንሷል፤ እንደድሮው አይደለም። ግን የነበረውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል ነው ” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ከዚህ ቀደም ካጋጠሙ ክስተቶች አንጻር በከፍተኛ ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመተሃራ በቅርበት ላይ አርብ ሌሊቱን ተከስቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አርብ ሌሊት መተሃራ አካባቢ 6.0 ሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉን ተመራማሪ ጠይቋል።

በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥበጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር)፣  በሰጡት ምላሽ፣ “ አዎ። ልክ ነው ተፈጥሯል። ሌሊት 5 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ገደማ ከምሽቱ ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ ነገር ግን ሰው አልሰማውም እንደድሮው ” ሲሉ አክለው፣ “ እንደዚያ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ ስለሆነ ነው እንጂ እንደዛ ባይሆን ኑሮ በጣም ብዙ ጉድ ይሆን ነበር ” ብለዋል።

የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ነው መባሉ ልክ ነው ? ስልን ላቀረብንላቸው ጥያቄ፣ “ እውነት ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ የሚያመላክተው ስኬሉ እየጨመረ እንደመጣ ነው፤ ሰሞኑን ትንሽ ቆም ሲል ጠፋ የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር፤ አሁንም እንቅስቃሴው አለ ማለት ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም ለተመራማሪው አቆርበናል።

“ እንደዛ ሆነ ማለት ይቀንሳል ማለት አይደለም። እየቀጠለ ነው ያለው ነገርየው። ሙሉ ለሙሉ ቆመ፣ ሞተ ለማለት አያስደፍርም። እንቅስቃሴው እንዳለ ነው ” ብለዋል።

“ ከመስከረም ጀምሮ እስካሁን አቅም በፈቀደ ሁሉም ሰው ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለማድረግ እየተሞከረ ነው። አሁንም ያው ከመሬት ወለል በታች ጥልቅ መሆኑ ነው የበጀን ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ድግግሞሹ ቀንሷል፤ እንደድሮው አይደለም። ግን የነበረውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል ነው። ጨርሶ ቆመ ማለት እንደማይቻል ነው ዋናው መልዕክት ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ሌሎች ምን እንማር ? "

በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ " ሌሎች ምን እንማር ? " በሚል ርዕስ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት " የዛሬው መድረክ እስካሁን የሄድንበት ርቀት መገምገም ነው። ከጀመርነው ፍጥነት አንፃር ገና ያላለቁ ነገሮች አሉ። ግን በተሻለ ፍጥነት መጨረስ የምንችልበት እድል ለማግኘት ነው የመጣነው " ብለዋል።

አክለውም ሰላምን ከመስበክ ፣ ሰላምን ከመተግበርም ሆነ ከምንም ነገር በላይ ግን ተፈናቃዮች ወደወትሮ ህይወታቸው የሚመለሱበትና ህገመንግስቱ በሚያስቀምጠው መሰረት የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጉዳይ ላይ ነው ሀሳብ የተለዋወጥነው። በቀጣይም በዚህ መሰረት የምንቀጥል ይመስለኛል" ብለዋል።

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ፎቶ ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (መስፍን ሰለሞን)

@tikvahethiopia
“የባለስልጣናት ያልተገሩ ንግግሮችና የመንግስትም ተቀዳሚ ተግባሩን ፍጹም መርሳት ሕዝብን ለእልቂት እየዳረገ ነው”- ፓርቲው

እናት ፓርቲ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣውና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ፣ “መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ መላ ኢትዮጵያውያንን የደኅንነት ዋስትና ያሳጣው ሀገራዊ እልቂት አሁን አሁን ወደ ሀገራዊ ቀውስነት እያደገ ነው ለማለት ያስደፍራል” ሲል ተችቷል።

አክሎ፣ “ለዚህ ደግሞ ብዙ የተጠራቀሙና ያልተፈቱ የችግር ቋጠሮዎች ቢኖሩም በዋናነት ባለስልጣናት የሚያደርጓቸው አደገኛ የእልቂት ጠመቃ ንግግሮች ዋነኞቹ ናቸው” ብሏል።

“መንግስት በተደጋጋሚ ቢነገር ችላ ያለውን የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ አለመስራት አሁን ያለንበት ሁኔታ ምን አልባት ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ እያደረሰው ይገኛል” ሲል ወንጅሏል።

በዚህም ሰሞኑን በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ቀበሌዎች በአንድ ግለሰብ ግድያ ምክንያት የተስተዋለውን “ቀውስ” ያወሳው ፓርቲው፣ ግድያውን አውግዞ፣ “ድርጊቱም በውል ተጣርቶ አጥፊዎች ከሕግ ፊት እንዲቀርቡ እናሳስባለን” ሲል ጠይቋል።

የስፍራው ነዋሪዎች ዘርፈ ብዙ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹለት ያተተው መግለጫው፣ በጅማው “ቀውስ” “በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለዋል። ወፍጮ ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ሱቆች እየጋዩ ነው። ‘ይህም ማንነት ተኮር ነው’፣ ‘አማራ ነው ያሉትን ንብረት እየመረጡ ነው የሚያቃጥሉት’ ብለዋል” በሚል ተጠናቅሯል።

“ብዙ ሺህ ሰው አካባቢውን ለቆ ከፋ ዞን ተጠልሏል። በተለይ የአቅመ ደካሞች፣ ሕጻናትና ነብሰ ጡሮች ስቃይ አሳዛኝ ነው፤ በሽሽት ላይ ሳለች የወለደች እናት እንዳለችም ይናገራሉ” በማለት የነዋሪዎቹን እሮሮ ጠቃቅሷል።

የከፋ እለቂት ሳይደርስ መንግስት ድርሻውን እንዲወጣ፣ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ እንዲደረግ፣ ገዳዮችና አሳዳጆች ለፍትህ እንዲቀርቡ፣ ‘የሰባብረናቸዋል’ ዓይነት ንግግሮች እንዲቆሙና ማስተባበያዎች ይቅርታ እንዲጠየቅባቸው ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫም ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia