#Ethiopia #USA #Starbucks
የአሜሪካው ' ስታርባክስ / Starbucks ' ኤክስኪዩቲቭ ቫይስ ፕሬዝዳንት ሚሼል በርን ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ እና የUSAID ዳይሬክተር ሆክላንደር ለበርን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል የስታርባክስን አመራር " እንኳን ወደ ኢትዮጵያ፤ ወደ ቡና መገኛዋ ሀገር በደህና መጡ " ብላለች።
የስታር ባክስ አመራር ሚሼል በርን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላለው አስደናቂ እድገት፣ በምርታማነት ላይ ስላሉ ኢንቨስትመንቶች ይመክራሉ ተብሏል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ በተመለከተ ይወያያሉ።
ስታር ባክስ (starbucks) በቡና አቅርቦቱ በመላው ዓለም የሚታወቅ ከፍተኛ ሃብት ያለው ኩባንያ ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA
በአሜሪካ ሀገር በደቡባዊ ካሊፎርኒያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
19 ሰዎችም ተጎድተዋል።
አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ፉለርተን በተሰኘ ከተማ በአንድ የፈርኒቸር ውጤቶች ማምረቻ ህንጻ አናት ላይ ነው።
በህንጻው ውስጥ 200 የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ ላይ ነበሩም ተብሏል።
የሞቱት ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካካል እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በህንጻው ውስጥ ስራ ላይ የነበሩት ናቸው።
አውሮፕላኑ ፉለርተን ከተባለ ኤርፖርት በተነሳ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው በህንጻው አናት ላይ የተከሰከሰው።
መንስኤው እየተጣራ መሆኑን የኤፒ መረጃ ያሳያል።
ሰሞኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ አደጋዎች ተደጋግመው ተሰምተዋል።
በደቡብ ኮሪያ ሙዋን ሲያርፍ የነበረ አውሮፕላን ላይ አደጋ ደርሶ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 179 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
ሌላው ምንም እንኳን የተመዘገበ እጅግ የከፋ ጉዳት ባይኖርም በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ 71 መንገደኞችን የጫነ አውሮፕላን በእሳት መያያዙና በሚያስደነግጥ ሁኔታ መቆሙ ሰሞኑን ከተሰሙት ክስተቶች መካከል ነው።

#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል።
እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል።
የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።
በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም።
1. ፓሊሳድስ
ፓሊሳድስ የተሰኘ መጠሪያ የተሰጠው ሰደድ እሳት በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰው ማክሰኞ እለት ሲሆን በግዛቲቷ ትልቁ ነው። የፓስፊክ ፓሊሳድስ አካባቢን ጨምሮ ከ17 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ግዛት አውድሟል።
2. ኢቶን
ኢቶን የተሰኘው ደግሞ በሰሜናዊ የሎስ አንጀለስ እን አልታዴና ባሉ ከተሞች እየተዛመተ የሚገኝ ሲሆን 10 ሺህ 600 ሄክታርን መሬት በመሸፈን በግዛቲቷ ሁለተኛው ትልቁ እሳት ሆኗል።
3. ኸረስት
ኸረትስ የተሰኘው ሰደድ እሳት ማክሰኞ እለት ተከስቶ ከሳን ፈርናንዶ በስተሰሜን በኩል እየተዛመተ ይገኛል። ይህም እሳት 855 ሄክታርን ይሸፍናል።
4. ሊዲያ
ይህ ደግሞ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በሎስ አንጀለስ በስተሰሜን ተራራማዋ አክቶን አካባቢ ተቀስቅሶ ወደ 350 ሄክታርን መሬት በመሸፈን ተዛምቷል።
5. ሰንሴት
ይህ ሰደድ እሳት ረቡዕ ምሽት ላይ በሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች የተከሰተው ሰደድ እሳት ሲሆን ከሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ 20 ሄክታር እያደገ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ወደ 43 ሄክታር ተዛምቷል።
ውድሌይ እና ኦሊቫስ የተሰኙት ሰደድ እሳቶች በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአካባቢው የእሳት አደጋ ባስልጣናት ገልጸዋል።
የመረጃው ምንጮች ፦ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን ናቸው።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለመሀላ ፈጸሙ።
ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮ እንደገቡ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፊርማቸውን ከሚያኖሩባቸው ትዕዛዞች መካከል ፦
- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከአሜሪካ ማባረር ፤
- ጾታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ ማድረግ ፤
- ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ከጦር ሠራዊቱ ማስወገድ ዋነኞቹ ናቸው።
ትዕዛዞቻቸው በፍ/ቤት ሙግት ሊቀርብባቸው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

#USA ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለመሀላ ፈጸሙ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ቢሮ እንደገቡ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተናግረዋል። ፕሬዜዳንቱ ፊርማቸውን ከሚያኖሩባቸው ትዕዛዞች መካከል ፦ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከአሜሪካ ማባረር ፤ - ጾታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ ማድረግ ፤ - ብዝሀነት፣ እኩልነትና…
" ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም #ወንድ እና #ሴት ናቸው " - ፕሬዝዳንት ትራምፕ
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ ከሚሰሯቸው ዋነኛ ስራዎች አንዱ በሀገሪቱ ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እውቅና መስጠት ነው።
ይህም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን የመልቀቂያ ጊዜ ለትራንስጀንደር / ፆታቸውን ለሚቀይሩ ሰዎች የሚሰጠውን ከለላና ጥበቃ የሚሽር ነው።
ለወንድ እና ለሴት ብቻ እውቅና መስጠት ትራፕም ከሚያስተላልፏቸው ትዕዛዛት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ታውቋል።
ትራምፕ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ / ከእንግዲህ ወዲህ / የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ እውቅና የሚሰጠው ለሁለት ፆታ ብቻ ነው እነሱም ወንድ እና ሴት " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።
የአሜሪካ መንግሥት ከአሁን በኃላ እውቅና የሚሰጠው ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እንዳሆነ የገለጹት ትራፕም ፤ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ለማስወገድ የአፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፤ ፆታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ትዕዛዝም ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትራምፕ " ሰዎች ተፈጥሯዊ ፃታቸውን መቀየር የለባቸውም " ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም ፆታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መነገሩ ይታወሳል።
15 ሺህ ፆታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቪድዮው የፎክስ ኒውስ መሆኑን ይገልጻል።
#USA #PresidentDonaldTrump

" ሥራችሁን በፈቃዳቸው ከለቀቃችሁ የ8 ወር ደመወዝ ጉርሻ እንሰጣችኋለን " - የትራምፕ አስተዳደር
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር፣ ፍላጎት ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች በመጪው መስከረም መጨረሻ ሥራቸውን በፈቃዳቸው የሚለቁ ከሆነ የ8 ወር ደመወዝ ጉርሻ እንደሚሰጥ ትላንት ለመንግሥት ሠራተኞች በላከው ኢሜይል አስታውቋል።
ፕሮግራሙ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችንና ሠራተኞችን ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ አካል መሆኑ ተመልክቷል።
ሠራተኞች ፍላጎታቸውን እስከ መጪው ሐሙስ ማለትም እአአ የካቲት 6 ቀን ድረስ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል። ይህን የሚያደርጉ ሠራተኞች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ከቢሮ እንዲሠሩ የሚያዘው ደንብ ላይመለከታቸው እንደሚችል ታውቋል።
በስደተኞችና በብሔራዊ ፀጥታ ጉዳይ ላይ የሚሠሩ እንዲሁም የፖስታ ቤት ሠራተኞች ፕሮግራሙ እንደማይመለከታቸው ተመልክቷል።
የመንግሥት ሠራተኞችን የሚወክሉ የሠራተኛ ማኅበራት የአስተዳደሩን ሐሳብ ተቃውመዋል። ሠራተኞች እንዳይስማሙም መክረዋል።
“ የፌዴራል ሠራተኞች ታማኝ፣ አስተማማኝና በየቀኑ ለመሻሻል የሚጥሩ መሆን አለባቸው ” ብሏል ከትራምፕ አስተዳደር የተላከው መልዕክት፡፡
የአሜሪካ መንግሥት ሠራተኞች ፌዴሬሽን “ ሠራተኞች አዲሱ ፕሮግራም በፈቃደኝነት የሚያደርጉት ጉዳይ አድርገው እንዳያዩት” አሳስቧል።
የአስተዳደሩ ተግባር የሚያሳየው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ጤናማ ያልሆነ አካባቢን መፍጠርና ሠራተኞች መቆየት ቢሹ እንኳ ሥራቸውን መቀጠል እንዳይችሉ ለማድረግ ነው ብሏል።
#VOA

በአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን እና የወታደራዊ ሂሊኮፕተር በአየር ላይ ተላትመው ተከሰከሱ።
አደጋው ያጋጠመው በዋሽንግቶን ዲሲ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 3:00 ላይ ነው።
የፒኤስኤ ንብረት የሆነው የበረራ ቁጥሩ 5342 የሆነና 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘው አውሮፕላን ሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ ኤርፖርት ለማረፍ በተቃረበበት ሰዓት ነው 3 የአሜሪካ ጦር አባላትን ከያዘ ወታደራዊ ሂሊኮፕተር (ብላክ ሀውክ) ጋር የተላተመው።
አውሮፕላኑ እና ሂሊኮፕተሩ ' ፖቶማክ ወንዝ ' ላይ ነው የተከሰከሱት።
አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አንድ ስራ እየተሰራ ሲሆን የሬገን ኤርፖርት ለጊዜው የአውሮፕላን በረራ ማድተናገድ አቁሟል።
የዲሲ ፖሊስ እስካሁን ስለ ሞቱ ሰዎች የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለና የነፍስ አድን ስራ ላይ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።
የአይን እማኞች ግጭቱ ሲፈጠር ከፍተኛ ብርሃን በአካባቢያቸው ታይቶ እነበር ጠቁመዋል።
የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ " አሰቃቂ አደጋ " ሲሉ ገልጸው የተሰማቸውን ሀዘን አካፍለዋል።
ምክትል ፕሬዜዳንት ጄዲ ቫንስ ከአሰቃቂው አደጋ ሰዎች እንዲተርፉ ሁሉም በፀሎት እንዲተጋ ጥሪ አቅርበዋል።
የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት በኤክስ ገጻቸው ላይ " እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር " ብለዋል።
መረጃው ከኤስቢኤስ፣ ኒውስኤክስ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።
ቪድዮ ፦ avgeekjake

#Update " እስካሁን በህይወት የተገኘ የለም " በአሜሪካ ፤ ዋሽንግቶን ዲሲ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ በ " ፖቶማክ ወንዝ " ውስጥ ከተከሰከሰበት አደጋ የነፍስ አድን ሰራተኞች እስካሁን አንድም ሰው በህይወት አላገኙም። የነፍስ አድን ስራው ግን መቀጠሉ ተነግሯል። አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነው 3 ሰው ከያዘው የጦር ሂሊኮፕተር ጋር…
#USA
" ታዳጊዋ በሕይወት ለመትረፍ ብዙ ታግላለች፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ቤቷ ስትሄድ ነው ይህ ገጠማት " - ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ
በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ በፊላደልፊያ ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከሰከሰ።
የሕክምና አውሮፕላኑ ድርጅት-ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ በሰጠው መግለጫ ፤ ጄቱ አርብ ምሽት አንድ ታማሚ ሕፃንና አስታማሚዋን እናቷን እንዲሁም 4 የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ እየተጓዘ ነበር ።
በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍራ የነበረችው ሕፃን ሕይወቷን አደጋ ላይ በሚጥል የጤና እክል የነበረባት ሲሆን በአሜሪካ ሕክምና አድርጋ ወደ ሜክሲኮ ቲጁዋና እየተጓዘች እንደነበር የአየር አምቡላንስ ድርጅቱ ለኤንቢሲ ኒውስ ተናግረዋል።
ከእናት እና ልጅ በተጨማሪም አብራሪው ፣ረዳት አብራሪው ፣ ዶክተር እና የመድሃኒት ባለሙያ በአውሮፕላኑ ውስጥ ነበሩ።
ድርጅቱ " ታዳጊዋ በሕይወት ለመትረፍ ብዙ ታግላለች፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ቤቷ ስትሄድ ነው ይህ ገጠማት " ብሏል።
አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት አካባቢም ቤቶች እና ተሽከርካሪዎች በእሳት የተያያዙ ሲሆን መሬት ላይ የነበሩ ሰዎችም ለጉዳት መዳረጋቸው ተገልጿል።
የግዛቷ አስተዳዳር " የሕይወት መጥፋት እንደሚኖር እናውቃለን፤ አደጋው አሳዛኝ ነው " ብሏል።
የፊላደልፊያ ከንቲባ ቺርል ፓርከር የከተማዋ ባለስልጣናት በአደጋው የደረሰው ጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አለማወቃቸውን ገልጸው ፤ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በፀሎት እንዲታሰቡ ጠይቀዋል።
እስካሁን በህይወት ያለ ሰው ስለመኖሩ ማረጋገጥ አልተቻለም።
ከቀናት በፊት በዋሽንግቶን ዲሲ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ ወንዝ ላይ ከተከሰከሰ በኃላ በህይወት የተረፈ ሰው አልተገኘም።
መረጃው ከቢቢሲ እና ኤንቢሲ ኒውስ የተውጣጣ ነው።
ቪድዮ ፦ ፌርበክ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።
ትራምፕ " በአሜሪካ እና የቅርብ አጋሯ እስራኤል ላይ ቅቡለነት እና መሠረት የሌለው ተግባር እየፈጸመ ነው " ሲሉ የከሰሱትን የዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ የጣሉበት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ላይ ፈርመዋል።
ትራምፕ ICC ላይ የጣሉት ዕቀባ እና ቪዛን የሚያጠቃልል ነው።
የቪዛ ዕቀባው የአሜሪካ ወይም የአጋሯቿ ዜጎች ላይ ምርመራ የሚያደረጉትንና የሚረዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻችን ዒላማ ያደረገ ነው።
ታራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ዋሽንግተንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው።
ባለፈው ጥቅምት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ኔታኒያሁ በጋዛ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
አሜሪካ የዚህ ዓለም አቀፍ ተቋም አባል አይደለችም። በተደጋጋሚም በአሜሪካ ዜጎች ላይ በፍርድ ቤቱ የሚተላለፍ ውሳኔዎችን ውድቅ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል።

አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን አፍና ገደለች።
አሜሪካዊው የ52 ዓመቱ ድሜትሪስ ፍሬዘር በአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ግለሰቡ በአላባማ በርሚንግሀም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፓውሊን ብራውን የተባለች የ2 ልጆች እናትን በመኖሪያ ቤቷ ገብቶ አስገድዶ ከደፈረ በኋላ #እንደገደላት ተገልጿል።
በሌላ ጊዜ የ14 ታዳጊ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙ መረጋገጡን ተከትሎ በተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት ነበር።
ይህንንም ተከትሎ ተከሳሽ ድሚትሪስ ፍሬዘር በሞት ፍርድ እንዲቀጣ የተላለፈበት ሲሆን የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው የሞት ፍርድ የማይተላለፍበት ሚቺጋን ግዛት ውስጥ በመሆኑ ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮለት ነበር።
በአላባማ ወንጀል መፈጸሙ በፍርድ ቤት መረጋገጡን ተከትሎ ወደ አላባማ እስር ቤት ተላልፎ ሊሰጥ ችሏል።
አላባማ ግዛት የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ፍርደኞችን አየር አጥሯቸው እንዲሞቱ የሚያደርግ ህግ ስላላት ይህም ወንጀለኛ በናይትሮጅን ጋዝ ታፍኖ ህይወቱ እንዲያልፍ መደረጉን ሮይተርስን ዋቢ በማድረግ አል አይን ኒውስ ዘግቧል።

#USA " ታዳጊዋ በሕይወት ለመትረፍ ብዙ ታግላለች፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ቤቷ ስትሄድ ነው ይህ ገጠማት " - ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ በፊላደልፊያ ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከሰከሰ። የሕክምና አውሮፕላኑ ድርጅት-ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ በሰጠው መግለጫ ፤ ጄቱ አርብ…
#USA : ከቀናት በፊት በአሜሪካ አላስካ ግዛት 9 መንገደኞችን እና 1 አብራሪን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ደብዛው ጠፍቶ ከቆየ በኃላ በአየር እና ምድር በተደረገ አሰሳ ስብርባሪው ተገኝቷል።
በአደጋው በሕይወት የተረፈ ሰው የለም።
የ3 ሰዎች አስክሬን በነፍስ አድን ሰራተኞች ተገኝቷል።
ይህ አደጋ በአሜሪካ ከ1 ሳምንት ባነሰ ጊዜ የደረሰ 3ኛው የአቬዬይሽን አደጋ መሆኑን የቪኦኤ ዘገባ ያሳያል።
በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከስክሶ በህይወት የተገኘ እንደሌለ ይታወቃል።
ከዚህ አደጋ በፊት ደግሞ በዋሽንግቶን ዲሲ 60 መንገደኞች እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን 3 ሰዎች ከያዘ የጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ አንድም ሰው በህይወት አለመገኘቱ መገለጹ ይታወሳል።

" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው ፤ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር አነሳለሁ " - ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር።
በዚህም ንግግራቸው " አሜሪካ ተመልሳለች " ያሉ ሲሆን የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች " ዩ ኤስ ኤ" በሚል ዝማሬ አጅበዋቸዋል።
ትረምፕ ንግግራቸውን ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በምክር ቤቱ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ሰዎች በተሰማ የስላቅ ድምፅ ንግግራቸው ተስተጓጎሎ ነበር።
የተወካዮች ምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን የምክርቤቱ ሥነ ስርዐት አስከባሪዎች፣ በቴክሳስ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለምክርቤት አባልነት የተመረጡትን አል ግሪን ከምክርቤቱ እንዲያስወጧቸው አዘዋል። ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትም ሥነ-ስርዐት እንዲከተሉ አሳስበዋል።
ግሪን ከምክርቤቱ አዳራሽ ከወጡ በኋላ ትረምፕ ንግግራቸውን ቀጥለዋል።
ትረምፕ በዚሁ ንግግራቸው " የመጀመሪያው ወር የፕሬዝደንትነት ዘመኔ፣ በሀገራችን ታሪክ እጅግ ስኬታማው መሆኑን ብዙዎች ገልጸውታል " ብለዋል።
ገና በጥቂት ሳምንታት አሳካው ያሏቸውን ስኬቶች አብራርተዋል።
ከነዚህ አንዱ በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዱትን እምርጃ ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም የፌደራል ቅጥር ሂደቶች እና የውጭ ርዳታዎች ላይ እግድ መጣላቸውን ገልጸዋል።
የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ፣ በምፅሃረ ቃሉ 'ዶጅ' በመባል የሚጠራ በኢላን መስክ የሚመራ ተቋም መመስረታቸውን የተናገሩት ትረምፕ በቢሊየኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ እያዳነ መሆኑንም አመልክተዋል።
ትረምፕ በንግግራቸው በ48 ዓመት ውስጥ ያልታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል " ወርቃማ ፈሳሽ " ሲሉ የጠሩትን የነዳጅ ጋዝ ቁፋሮ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።
" የወሳኝ እና ብርቅዬ ማዕድናት ምርት ይፋጠናል " ሲሉም ገልጸዋል።
" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው " ያሉት ትራምፕ፣ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር እንደሚያነሱ ተናግረዋል።
ትረምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ ያደረጉትን ኃይለቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋርጣለች።
" አውሮፓውያን ዩክሬንን ከመደገፍ ይልቅ ከሩስያ ለሚገዙት ነዳጅ እና ዘይት የበለጠ አውጥተዋል " ያሉት ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝደንት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደፃፉላቸው አመልክተዋል።
ትረምፕ አክለው " በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ ጋራ ጠንከር ያለ ውይይት አድርገን ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን የሚያሳይ ምልክቶች አግኝተናል " ብለዋል።
መረጃው የቪኦኤ ነው።