TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የአዲስ አበባ ካቢኔ ምን ውሳኔዎች አሳለፈ ?

የአዲስ አበ ባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 4ተኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የመጀመሪያው በከተማዉ አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎችን የሚመለከት ነው።

በዚህም ሆስፒታሎቹ ዘመኑን በዋጀ ህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካከበቱ
#የግል_ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።

ሁለተኛ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል
#ለ3ተኛ_ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በማየት ካቢኔዉ አፅድቋል።

በሶስተኛ ደረጀ የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዲስትሪዎች ባቀረቡት
#የማስፋፊያ_ቦታ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት እና የአተገባበር አቅጣጫ በማስቀመጥ ካቢኔው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

አራተኛ የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብን በመመርመር ማፅደቁን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia