TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" ከ10 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል በቃጠሎ ወድሟል " - የማዜ ብሔራዊ ፓርክ

ከትናትና በስቲያ ማምሻውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የማዜ ብሔራዊ ፓርክ አከባቢ የተነሳዉ እሳት ሌሊቱን ሙሉ ሳይጠፋ ማደሩንና በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዜ ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ጬማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአከባቢው ከፓርኩ አቅራቢያ ከሚገኝ ሞርካ ቀበሌ አንድ አርሶ አደር የማሳ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት እያካሄደ ከነበረዉ ቃጠሎ የወጣ እሳት ምሽት 12 ሰዓት አከባቢ በፓርኩ ዙሪያ የሚገኝን 5 ሄክታር ቦታ ካወደመ በኋላ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ የፓርኩን ክፍል ማዉደም መጀመሩን የገለፁት አቶ መስፍን ከወቅቱ ነፋሻማነትና የሰዓቱ ምቹ አለመሆን የእሳት ማጥፋትን ስራ ፈትኖት እንደነበር አስታዉቀዋል።

የእሳት ማጥፋት ስራዉ ከዛሬ ማለዳ ከ12 ሰዓት ጀምሮ በተደራጀ መልኩ በአከባቢው ነዋሪዎች፣ በፀጥታ መዋቅርና በእሳት አደጋ ብርጌድ ርብርብ ሲደረግበት ቆይቶ ከፓርኩ ዉጪ 5 ሄክታር ከፓርኩ ክፍል ደግም 10 ሄክታር በላይ ካወደመ በኋላ ረፋዱ አራት አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ መስፍን አስታዉቀዋል።

አቶ መስፍን አክለዉም እስካሁን በተደረገዉ ማጣራት ከፓርኩ ስነ ምህደር ዉድመት ባሻገር በአራዊቱ ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልፀዋል።

በእሳት ማጥፋቱ ስራ ከተሳተፉት የአከባቢዉ ነዋሪዎች ፣የፀጥታ መዋቅር አባላትና በሃይለማርያምና ሮማን ፋዉንዴሽን የተቋቋመው የእሳት አደጋ ብርጌድ በተጨማሪ ከወላይታ ወደ ሳዉላ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የግልና ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ሕዝቡን በማጓጓዝ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ምስጋና አቅርበዋል።

የማዜ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ እና ጎፋ ዞኖች መካከል ቁጫ ወረዳ አከባቢ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 460 ፣ከሐዋሳ 235 እንዲሁም ከጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ 196 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 220 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆንበሀገራችን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘዉ የስዋይኔ ቆርኬ ጨምሮ አንበሳ፣አቦሸማኔ፣የቆላና ትልልቆቹ አጋዘኖች፣አምባራይሌና ከርከሮን ጨምሮ 39 የተለያዩ አጥቢ እንስሳቶች፣196 የአዕዋፋት ዝርያዎች እና ከ80 በላይ የእፅዋት አይነቶ እንደሚገኙበት ከማዜ ብሔራዊ ፓርክ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የ6 ወጣቶች ሕይወት አለፈ።

በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ " ሽቆ " ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ቡና ጭኖ ከሳይት ሲወጣ የነበረ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 18766 ኦሮ የሆነ የጭነት መኪና ተገልብጦ የ6 ወጣቶች ሕይወት አለፈ።

ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱም ታእላውቋል።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል ሽንኩራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፥ በመኪናዉ ላይ ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ አስር ሰዎች ነበሩ።

ስምንቱ ገዳ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ የቡና ሳይት የሚሰሩ ታዳጊ ወጣቶች እንደነበሩና በአደጋው ወቅት መኪናዉ ሲገለበጥ ቡናዉ በላያቸዉ ላይ በመጫኑ 6ቱ ወዲያዉኑ ሲሞቱ ሁለቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ የመጀመሪያ ሕክምና በአለታ ወንዶ ሆስፒታል ከተደረገላቸው በኋላ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሀዋሳ መላካቸውን ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል አስታዉቀዋል።

ዋና ኢንስፐክተሩ ሹፌሩና ረዳቱ በአሁኑ ሰዓት በአለታ ወንዶ ወረዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።

በክልሉ በቡና ምርት ወቅት የሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ለትራፊክ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድልን ከፍ እንደሚያደርጉ በትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዙሪያ በሁሉም መዋቅሮች ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ ቢሆንም በቸልተኝነትና ከልክ ባለፈ በራስ መተማመን በገጠሪቱ አከባቢዎች አደጋዎች እንደሚከሰቱ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
" ፍትህ እንሻለን ! " - ቤተሰቦች

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል።

" በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ " የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል " ፍትህ እንሻለለን " ብለዋል።

ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የ8 ዓመት ልጅ ስትሆን ገና የአንደኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።

ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ  ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል።

በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡

ሮጣ ያልጠገበች ፤ ክፉ ከደጉን እንኳን የማትለይ ህፃን ለአዕምሮ በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ " እንዳትናገር በሚል " ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል። 

ህፃኗ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ " ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው " ብለዋል።

በወረዳው ኤላ ከተማ በ8 ዓመቷ ልጅ ሲምቦ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።

የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ " የህፃኗ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወጣው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡ ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት " ብለዋል።

2009 ዓ.ም. የተወለደችው ትንሿ ሲምቦ ገና በ8 ዓመቷ ለዚህ እጅግ ለአሰቃቂ ድርጊት ሰለባ መሆኗ ቤተሰቦቿን ቁጭት ውስጥ ከቷል።

" ባለሙያዎች በሰውነቷ ላይ የታየውን ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ እያደረጉ ነው " ያሉት የቤተሰብ አባል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ  አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ተኩል  የተገኘው የህፃኗ ሲምቦ አስክሬን በትናንትናው እለት ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ላለፉት አምስት አመታት ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የሚመጣ ግለሰብ፣ቡድን እና ፓርቲ አላየንም " - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከትላንትና በስቲያ የተጀመረው የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን ዛሬ እሁድ ማጠቃለያውን ያገኝቷል። ጠቅላላ ጉባኤው በፓርቲው ፕሬዜዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በጉባኤው የሃገር ውስጥ…
ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የፓርቲው ፕሬዜዳንት አድርጎ በከፍተኛ ድምጽ እንደመረጣቸው ፓርቲው አሳውቋል።

ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ እንደፈጸሙ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መምረጡ ተነግሯል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
“ዶክተር አንዷለም ተተኩሶበት ተመትቶ ተገኘ መኪናው ውስጥ። አንድ ሀኪማችንም ተተኩሶበት መኪናው ሁለት፤ ሦስቴ ተመትቶታል” - ጤና ሳይንስ ኮሌጁ

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥበበ ግዮን ግቢ ስፔሻላንስድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ዳኘ በተተኮሰባቸው ጥይት መገዳላቸውን ዩኒቨርሲቲውና ኢንተርን ሀኪሞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸው ሲባል ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ዶክተር አንዷለም ተተኩሶበት ተመትቶ ተገኘ መኪናው ውስጥ። አንድ ሀኪማችንም ተተኩሶበት መኪናው ሁለት፤ ሦስቴ ተመትቶበታል ” ሲሉ አስረድተዋል።

ተኩሱ ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃዎች በፊት በአካባቢው እንዳለፉ የገለጹት እኝሁ አካል ስለ ዶክተር አንዷለም ሲገልጹ፣ “ ከሥራ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት ቆሸ የሚባለው ሰፈር ተኩስ ተከፈተበት ” ነው ያሉት።

“ አንዷለምን የምናውቀው ደግ፣ ሩህሩህ፣ የሁላችንም ምሳሌ አድርገን ነው። ሰው ነው ከሰውም ሰው ” ሲሉ እያለቀሱ ተናግረዋል።

የገዳዮቹ ማንነት ታውቋል ? የለበሱት ልብስ ምን አይነት ነበር ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ “ እርግጠኛ ሆኖ አሁን መናገር አይቻልም ” ብለዋል።

አክለው፣“ አንድ ከዶ/ር አንዷለም በፊት ሲጓዝ የነበረ ሀኪም ተተኩሶበት ተርፏል። ‘ሦስት የሚተኩሱ ሰዎች ነበሩ፤ የምን እንደሆነ አላውቅም ዩኒፎርም ነገር ለብሰዋል’ ብሎናል ” ሲሉ አስረድተዋል።

በጥበበ ግዮን ግቢ ህክምና ጤና ሳይንስ ኢንተርን ሀኪሞች በበኩላቸው፣ “ ዶክተር አንዷለም ከከተማ ከሥራ ውሎ ሲመለስ ምሽት ላይ ነው የተመታው። ግን ማን እንደመታው የተረጋገጠ ነገር የለም ” ሲሉ ነግረውናል።

“ አስከሬኑም ለፓሊስ ተደውሎ ነው ማታ የተነሳው ” ያሉት ኢንተርን ሀኪሞቹ፣ “ አሁን ሀኪሞቹም፣ ሬዚደንቶቹም ሁሉም የባሕር ዳር ዩኑቨርሲቲ ተማሪዎችና ሠራተኞች ሀዘኑን እየተካፈልን ነው ያለነው ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶክተር መንገሻ ከሰዓታት በፊት በሰጡን ቃል “ አስከሬን ይዘን ከቤት ወደ ቤተክርስቲያን እየወጣን ነው ” የሚል አጭር ማረጋጠጫ ብቻ ሰጥተዋል።

ስለገዳዮቹ ማንነት የታወቀ ነገር እንዳለ የጠየቅነው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጸጥታ ክፍል በሰጠን ምላሽ፣ “ ግድያው ከግቢ ውጪ ስለተፈጠረ ምንም ያወቅነው ነገር የለም ” ብሏል።

“ ያወቅነው መረጃ የለንም። እኛም እንደማንኛውም ሰው መሞቱን ብቻ ነው የሰማነው ” ሲል አክሏል።

የሚመለከታቸውን የከተማውን የጸጥታ አካላት ለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ የምናቀርብ ይሆናል።

ዶክተር አንዷለም ዳኘ የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስፔሻሊስት፤ የጉበት፣ የቆሽት፣ የሀሞት ጠጠር መስመር ሰብ ስፐረሻሊስት ሀኪም፣ እንዲሁም የልጆች አባት እንደነበር ኢንተርን ሀኪሞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በወጋገን ካርድ በፖስ ማሽኖቻችን ክፍያ ሲፈፅሙ ተመላሽ እንዳለው ሰምተዋል

በወጋገን ክፍያ ካርድዎ ለአጠቃቀም ምቹ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ በሆኑት የወጋገን ክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) ተጠቅመው እስከ ጥር 30 ክፍያ ሲፈፅሙ ተመላሽ ያገኛሉ፡፡

ዛሬውኑ ከሚቀርብዎ ቅርንጫችን የወጋገን ክፍያ ካርድዎን በመውሰድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆኑ፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል በ866 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ! በተጨማሪም ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀላሉ https://linktr.ee/WegagenBank
Addis Ababa University
Software Engineering and Computing Department
Python programming, Data Analytics and Machine Learning Training Program

Registration Date: January 28 to February 28, 2025
Class start Date: March 1, 2025
Class mode: Fully live online
Certification: You will earn three certificates in this training.
Register Here: https://formurl.com/to/AAUTraining

Join Our telegram channel: @DataScience_AAU
For more information contact us: Mobile: 0979724497 | 0902340070
                                                             Office: 011-1-260194
#Update

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።

ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የመረጠ ሲሆን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን በርሀ (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብ የክልሉ ምክር ቤት የሚያፈርሰው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋምያ ሰነድ ጥር 2015 ዓ.ም ሲፀድቅ የተነሳ ሃሳብ ነው።  

ሃሳቡ በድጋፍ እና በተቃውሞ ለሁለት አመታት ያህል ሲናጥ ቆይቶ ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በይፋ ተመስርቶ መሪዎቹ መርጠዋል። 

በምስረታ ካውንስሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ የሚገኙ የኢሮብ እና ኩናማ ብሄረሰቦች የተወከሉበት ካውንስሉ ዘግይቶም ቢሆንም መመስረቱ መልካም ሆኖ አቃፊ ፣ አሳታፊ እና የሃሳብ ብዙህነት የሚንሸራሸሩበት መድረክ መሆን ይገባዋል ብለዋል። 

የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቀመጡት የትግራይ ህዝብ ጥቅሞች በተሻለ እና በአስተማማኝ እንዲመለሱ አጋዥ ሃይል ለማሰባሰብ አልሞ መቋቋሙን የጠቆሙት ፕሬዜዳንቱ " ልዩነቶቻችን በማጠበብ ለተሻለ ነገ በጋራ መስራት ወቅታዊ የትግራይ ጥያቄ ነው "  ብለዋል። 

የካውንስሉ እድሜ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ መሆኑ ያስረዱት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ይህንን ታሳቢ በማድረግ የትግራይ ፓለቲካዊ ምህዳር ማስፋት እና ለነገ ማመቻቸት ዋነኛ ስራው መሆን እንደሚገባ አክለዋል።   

ካውንስሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች መሬት ላይ እንዲወርዱ አጋዥ ሚና ከመጫወት በተጨማሪ የትግራይ ተደማጭነት እና የመደራደር አቅም የሚያጠናክር አቅጣጫ መከተል ይገባዋል ብለዋል ፕሬዜዳንቱ። 

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት ለመምራት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ቃለ ማህላ ፈፅሟል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት መመስረት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ እና ሌሎች ተቃውሞውታል

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia