TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

⚫️ " ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም " - ቅሬታ አቅራቢ

🔴 " ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ፍርድ ቤት፣ ሰሚት ሳፋሪ፣ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ፣ ፍየል ቤት ፣ ወጂ ሰፈር፣ ሰንራይዝ ሪል ስቴት፣ ፊሊንት ስቶን ሆምስ እና ጎሮ ሚካኤል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የሃይል መቆራረጥ ከፍተኛ የሆነ ምሬት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚገኙ በተለይም የፍሊንት ስቶን ትዊን የጋራ መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች " ከህዳር 02/03/17 ዓ/ም ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ቀንም ለሊትም ሳናገኝ በችግር ላይ እንገኛለን " ሲሉ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በደብዳቤ ጭምር ቢያሳውቁም " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተናል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ በአካባቢው ለሃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆነው በመሬት ውስጥ በሚቀበሩ የሃይል መስመሮች ላይ የሚያጋጥም የመሰረት ልማት ጉዳት እና ስርቆት ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ደንበኞቹ የሃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የሚጠይቅ ጽሁፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ነዋሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?

" ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም መብራት አይመጣም ከመጣም ለሊት ነው ከዛ ተመልሶ ይጠፋል መኖር ከብዶናል።

ህመምተኞች አሉ ፤ ፍሪጅ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ ከዚህም በላይ በዚህ ኑሮ ውድነት ምግብ ለመድፋት ተገደናል።

ከህዳር 18 እስከ ታህሳስ 9 ባለው ጊዜ አምስት ጊዜ በተደጋጋሚ በመንገድ ስራ ምክንያት በመሬት ውስጥ ያለ መስመር በኤክስካቫተር እየተመታ ሃይል ተቋርጧል።

መፈጠር አልነበረበትም ቅድመ መከላከል ስራዎች ሊሰሩ ይገባ ነበር ከሆነ በኋላ ግን በተደጋጋሚ መፈጠር አልነበረበትም ተጠያቂነትም ሊኖር ይገባ ነበር።

ከታህሳስ 10 በኋላ ግን አንድ ጊዜ ሲመታ ከ18 ሰዓት እስከ 3 ቀን መብራት ይጠፋ ጀምሯል ከዛ በኋላ መቆራረጡ በከፍተኛ ሁኔታ ባሰ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ለ25 ደቂቃ ብቻ ሃይል የምናገኝበት ጊዜ ሁሉ አለ።

ትልቁ ቆየ ከተባለ 4 ሰዓት ነው ይህም ከእኩለ ለሊት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ሰው ከተኛ በኋላ ለምንም አገልግሎት መዋል በማይችልበት ሰዓት ነው ከሚመጣው።

የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን በሚል በወጣው ዝርዝር ውስጥ አካባቢያችን የሃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የሚገልጸው ከ 3 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ቢሆንም እኛ ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መብራት አናገኝም።

ችግሩን ማስቆም ሲችሉ ማህበረሰቡ በመሃል እየተቀጣ ነው ልጆች ከትምህርት ቤት መጥተው ማጥናት አልቻሉም ፣በተደጋጋሚ በመጥፋቱም ምክንያት ነዋሪው ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እየተዳረገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ቀን ቀን የፕሮጀክት ስራ አለ በስራው ምክንያት ይቋረጣል ማታ ማታ ይለቁላቸዋል ሙሉ ቀን የማይበራላቸው ብልሽት ሲኖር ነው እንደዛ የሚሆነው ሁሌ አይደለም።

ከሰሚት ጀምሮ እስከ ወረገኑ ድረስ እዛ መስመር ላይ መሰረተ ልማት ስራ እየተሰራ ነው ስራዎች በቅንጅት ነው የሚሰሩት አንዳንዴ ብዙ ስራ ስለሆነ እየተሰራ ያለው ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ችግሮች ይከሰታሉ።

ለዘለቄታው ለመገልገያ (Utility) የሚሆን ኮሪደር አብሮ እየተሰራ ነው ለተወሰነ ጊዜ ነው የተጠቀሰው አይነት ችግር የሚኖረው በቀጣይ በጣም አስተማማኝ የሆነ መሰረተ ልማት እየተሰራ ነው።

መንገድ በሚሰራበት ጊዜ ከእግረኛና ከአስፋልት መንገድ ጎን የውሃ ፣ የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ መስመር (Utility Corridor) አብሮ እየተገነባ ነው።

ቀደም ሲል የነበረው አካሄድ ብልሽት በሚኖርበት ጊዜ አስባልት ተቆፍሮ ነበር የሚሰራው በአሁኑ አሰራር ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ብልሽት ሲኖር መቆፈር እና ማፍረስ ሳያስፈልግ ገብቶ ለመስራት ያስችላል ፣ የመቀየር እና የማሻሻል ስራ ሲያስፈልግ ማሟላት የሚችል የአቅም ማሳደግ ስራ እየተሰራ ነው።

ይህ አይነት ቅንጅት ባለመኖሩ ብዙ ችግሮች ሲከሰቱ ነበር አሁንም የምናየው ችግር የተከሰተው ቀደም ሲል ይህ አይነት ቅንጅት እና የUtility corridor ባለመኖሩ ምክንያት የተከሰተ ነው ።

ይሄንን ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ችግሩን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው።

የተወሰነ ጊዜ መታገስ ነው ለዘመናት የሚያገለግል ስራ ነው የሚሰራው ስራው እስከ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው ከክረምቱ በፊት ያልቃል" ብለዋል።

እስከዛ አሁን ባሉበት አይነት የመብራት ችግር ውስጥ ይቆያሉ ወይ ? ስንል ለዋና ስራ አስፈጻሚው ጥያቄ አንስተናል።

ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ

" ሲሪየስ በሆነ ነገር ውስጥ ላይቆዩ ይችላሉ ብዙ ነገር እየተሻሻለ ነው የሚሄደው ብዙ ቁፋሮ አለ ቁፋሮ ካለቀም በኋላ መሰረተ ልማቱ ቦታውን ይይዛል ለስራ ሲባል ሃይል መቆራረጥ ይኖራል ነገር ግን እየተሻሻለ ይሄዳል።

ከመገናኛ ሰሚትም ሲሰራ እንደዚህ አይነት ችግሮች ነበሩ አሁን CMC አካባቢ እንደዚህ አይነት ችግር የለም ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ችግሮች አይኖሩም የሁሉም ስራ ያልቃል ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ችግሩን በማቃለል እስከዛ በተሻለ መንገድ ሃይል የሚያገኙበት እድል ይኖራል ወይ ? የሚል ጥያቄም ያነሳንላቸው ሲሆን በምላሻቸውም " እንደዛ እናደርጋለን ከባድ ችግር ስለነበር አንድ ጊዜ ነው እስካሁን ለቀናት በሚባል ደረጃ የተቋረጠው ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይኖር ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል። የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን 36 ኪ/ሜ በኩል ነው የተመዝገበው። የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ እና ቦታዎችም የተሰማ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ንዝረቱ በደንብ ይሰማ ነበር። አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ " የመሬት ንዝረት እየተሰማ ነው…
#Earthquake

ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል።

እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል።

ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው።

ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ነው።

ንዝረቱ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል። እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል። ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው። ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ…
ለመሆኑን በሀገራችን የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች የትኞቹ ናቸው ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ፦

" ... ከላይ ከነ መቐለ ጀምሮ ወልዲያ፣ ደሴን እያካተተ የሚመጣው በአዲስ አበባ አድርጎ እስከ አርባ ምንጭ የሚዘልቀው ደጋማው የሀገሪቱ ክፍል ነው። ስምጥ ሸለቆ መሃሉ ላይ አለ።

ከዛ ወደ ማዶ ስንሻገር ከድሬዳዋ ጀምሮ ጎባን ባሌን፣ አካባቢ አድርጎ አሰላን ጨምሮ አሰላም በስምጥ ሸለቆ ጫፍ ላይ ነው።

በጣም ትልቅ የሆነ ቆላማ ክፍል ከአፋር ጀምሮ ከዳሎልና ከኤርታሌ አካባቢ አንስቶ ድሬዳዋን እያካለለ ሰመራን መሃል አድርጎ በአዳማ ፣ ቢሾፍቱ አድርጎ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ ድረስ የሚዘልቀውን ስምጥ ሸለቆ እየነካካ ነው የሚሄደው።

በተገለጹት ቆላማ አካባቢ በተባሉት / ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ባሉት ወይም ለነሱ አዋሳኝ በሆኑት ቦታዎች ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ ናቸው አዲስ አበባን ጨምሮ።

አዲስ አበባን ሰው ላይገነዘብ ይችላል የሰላሌን ሜዳ ጨርሰን እንጦጦ ቁልቁለቱን ወደዚህ ስንይዝ ስምጥ ሸለቆን ያዝን ማለት ነው። ስለዚህ አዲስ አበባ ያለችው ከስምጥ ሸለቆ ኮርቻ ላይ ናት።

እነዚህ ከተሞች የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጠር በሚችልበት አካባቢ የተገነቡ ናቸው።

ለምሳሌ ፥ ህዳሴ ግድብ ያለበት በቅርብ ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያሰጋው አይደለም። ምናልባት ከ60 ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚያሰጋው አይደለም።

ቁም ነገሩ እሱ አይደለም። ምን ያክሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የተባለ ኢኮኖሚ የያዙ ናቸው በየት አካባቢ ይገኛሉ ከተሞችስ ስንት ናቸው ? ከተባለ ከስምጥ ሸለቆ ተፅእኖ ውጭ ያሉት ከተሞች በጣም ጥቂት ናቸው።

በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ወይም አዋሳኝ ውስጥ ያሉትን ከደመርን ከ80 እስከ 90 ፐርሰንት ሁሉም በሚባል ደረጃ አንድም በስምጥ ሸለቆ ውስጥ አልያም ጫፍ ላይ ናቸው። ስለዚህ ከመሬት መንቀጥቀጥ ተፅእኖ ውጭ ናቸው ማለት አይቻልም። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል። እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል። ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው። ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ…
#Earthquake 

ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል።

የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ።

በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም መንቀጥቀጡ ካየለበት ስፍራ ሸሽተው ለመውጣት ተገደዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተትና ተከትሎ የሚመጣው ንዝረት ድግግሞሹ የቀጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ " ምንም ነገር አይፈጠርም ፤ ለምደነዋል " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እንላለን።

አያድርገውና እጅግ የከፋ ነገር በሚመጣበት ጊዜ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዘውትር አስታውሱ።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works

ከመጀመሪያዎቹ መሀል ይሁኑ ! ውጭ ሀገር ያዩት እርሶ ቤትም አይቀርም በሀገራችን የመጀመሪያው የሆኑ የአልሙኒየም ፍሬም መስታዎት በሮችን የተላበሱ የእንጨት ስራ ውጤቶችን ለእናንተ ለደንበኞቻችን ፤ይዘን መተናል
" ልዩ ውበት ይገባዎታል! "
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works
Closet / Cupboard
Kitchen cabinet
TV Unit
Dressing

📍አድራሻ፦ ጀሞ 1 የተባበሩት ማደያ ውሰጥ
- 22 ከጎላጎል አጠገብ ኖህ ሪልስቴት 3ኛ ፎቅ
📲 0929414154
📲 0983915600
📲 0954777788 /99
ቴሌ ግራማችንን ይቀላቀሉ
https://yangx.top/webnewood
ሕብረት ባንክ !

በየቀኑ ስጦታዎን ይውሰዱ!

ባንካችን  ከታህሳስ 23 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም  ዘወትር ከቀኑ  5፡30 ጀምሮ የጥያቄና መልስ ውድድር  በቴሌግራም ገፃችን ላይ የሚያካሄድ ሲሆን፤ ቀድመው ለመለሱ አስር ተሳታፊዎች ልዩ የገና ስጦታ አዘጋጅቷል፡፡
በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለመሆን እና ለመሸለም  በቅድሚያ  የባንካችንን የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች ይቀላቀሉ፡፡

የቴሌግራም ገፃችን- https://yangx.top/HibretBanket
የፌስቡክ ገፃችን- https://web.facebook.com/HibretBank

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#quiztime #telegramquiz #winprizes #hibretbank
TIKVAH-ETHIOPIA
" መልሼ አጤነዋለሁ " - ሶማሊያ የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ " መልሶ ለማጤን " ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ " የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል " ሲሉ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ…
#Ethiopia #Somalia

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ።

በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ከኢፌዴሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንቱ የተላከ መልዕክትን አድርሰዋል።

" በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶማሊያ እና በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል " ያለው ሚኒስቴሩ " ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የAUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል " ሲል ገልጿል።

በቅርቡ የሶማሊያ ከፍተኛ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ ውይይት ለማካሄድ መስማማታቸውም ተመላክቷል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብድርቋድር ኑር ጃማ ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሶማሊያን ሰላም ለማረጋገጥ ለከፈለው መስዋትነት እና ላበረከተው አስተዋጽዖ ያላቸው አክብሮት እና ምስጋና ማቅረባቸው ተነግሯል።

#MinistryofForeignAffairsofEthiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት…
#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና የ " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ " ስልጠናዎችን ለመሰልጠን ላሰቡ ጥሩ እድል መመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናዎቹን ለመውሰድ ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል።

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ የመንግስትና የግል ሰራተኞች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ ስልጠናዎችን መሰልጠን ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠና ቀናት
#ቅዳሜ እና #እሁድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30 እንደሆነ ተመላክቷል።

የስልጠና ቦታው አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ ሲሆን ለመመዝገብ ይህን ሊንክ 
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

በአሜሪካ ሀገር በደቡባዊ ካሊፎርኒያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

19 ሰዎችም ተጎድተዋል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ፉለርተን በተሰኘ ከተማ በአንድ የፈርኒቸር ውጤቶች ማምረቻ ህንጻ አናት ላይ ነው።

በህንጻው ውስጥ 200 የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ ላይ ነበሩም ተብሏል።

የሞቱት ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካካል እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በህንጻው ውስጥ ስራ ላይ የነበሩት ናቸው።

አውሮፕላኑ ፉለርተን ከተባለ ኤርፖርት በተነሳ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው በህንጻው አናት ላይ የተከሰከሰው።

መንስኤው እየተጣራ መሆኑን የኤፒ መረጃ ያሳያል።

ሰሞኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ አደጋዎች ተደጋግመው ተሰምተዋል።

በደቡብ ኮሪያ ሙዋን ሲያርፍ የነበረ አውሮፕላን ላይ አደጋ ደርሶ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 179 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

ሌላው ምንም እንኳን የተመዘገበ እጅግ የከፋ ጉዳት ባይኖርም በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ 71 መንገደኞችን የጫነ አውሮፕላን በእሳት መያያዙና በሚያስደነግጥ ሁኔታ መቆሙ ሰሞኑን ከተሰሙት ክስተቶች መካከል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum " በአሁኑ ሰዓት የተለየ አዲስ መመሪያና ክልከላ ባልወጣበት ፤ የነበረውን የአለባበስ ስርዓት የሚቀይር አዲስ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም " ሲል የትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። ቢሮ ለአክሱም የትምህርት ፅህፈት ቤት በፃፈው ደብዳቤ ፤ " ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ምን ዓይነት አለባበስ መከተል እንዳለባቸው የሚያዝ የቆየ መመሪያ…
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን "  - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚሁ መግለጫ " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ብሏል።

" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወስዳለን " ሲልም ገልጿል።

መግለጫውን የተከታተለው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጫው " ጠንከር ያለ ነበር " ብሏል።

ዝርዝሩ እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake  ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል። የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ። በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ።

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው " የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር " ብለዋል፡፡

መረጃው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (FMC) ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን "  - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ " የፌደራል…
#Update

" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃዎችን እንስወዳለን "   - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ 160 የያዝነው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ ጠቅሷል።

ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።

ምክር ቤት ባወጣው የ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ፦

1. የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው።

2. የትምህርት ቤቶች ህግ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች የሚፃረር መሆን የለበትም። በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ ተደንግጓል ስለሆነም ጥያቄያችን በዚሁ ደንብ በአስቸኳይ እንዲመለስ እንጠይቃለን።

3. ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን።

4. በጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን።

5. ጉዳዩ በማንኛውም መልኩ ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀምያ ማዋል ስለማይገባ ጉዳዩ እንዳይፈታ የሚያወሳስቡት ግለሰቦች ወይም አካላት መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ እናቀርባለን።

6. ኢ-ህገመንግስታዊ  ተግባሩን የሌሎች እምነት ተከታዮች እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች እንዲያወግዙት ጥሪ እናቀርባለን።

7. ከትምህርት ገበታ የተስተጓጎሉት ተማሪዎች የትምህርት ሚንስቴር ያወጣው ሁሉም ትምህርት ቤቶች መፈፀም የሚገባቸው የአለባበስ ሁኔታ የሚመለከት ህግና ደንብ ያልጣሱ ስለሆነ ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን።

8. ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ እየተደረገ ያለው ተግባር ሰብአዊ መብቶች ፣ ክልላዊ ፣ አገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ህጎች የሚፃረር በመሆኑ በጥብቅ እንኮንነዋለን።

9. ከትምህርት ሚንስቴር መመሪያ እና ደንብ ባፈነገጠ መልኩ በግል ፍላጎት ብቻ በመመራት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ህገ-ወጥ ተግባር የፈፀሙት ግለሰቦች እና አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጥሪ እናቀርባለን።

10. የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲወገዝ ድጋፍ የቸራችሁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ምክር ቤቱ ምስጋና ያቀርባል።

11. ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች ለህዝባችን እናሳውቃለን።

... ብሏል።

መረጃውን የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia