ከ600 በላይ ተሳታፊዎች የሚኖሩት የምልክት ቋንቋ ጉባዔ በቅርቡ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
የራሷን የምልክት ቋንቋ የምትጠቀመው ኢትዮጵያ 15ኛውን የምልክት ቋንቋ ዓለም-አቀፍ የምርምር ጉባዔን (TISLR) ከመጪው ጥር 6 እስከ 9 በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች።
ከዚህ ቀደም በነበሩት ጉባኤዎች ተሳታፊ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተወዳድሮ የዘንድሮውን ጉባዔ እንዲያዘገጋጅ መመረጡን ተከትሎ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ጉባዔውን አዘጋጅቷል።
ይህ በየ 3 ዓመቱ የሚካሄደው የምርምር ጉባኤ በአፍሪካ ሲዘጋጅ የመጀመሪያው መሆኑንና ዓለም አቀፍ የዘርፉ ምሁራንን ጨምሮ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት እንደሚሆን ዛሬ በነበረው የቅድመ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የምልከት ቋንቋን የብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር ምን እየሰራች ትገኛለች ?
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚ/ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ "የቋንቋ ፖሊሲው ለምልክት ቋንቋ እውቅና ይሰጣል ይህንን ሥራ ማድነቅ ያስፈልጋል፤ የብሔራዊ ቋንቋ ለማድረግ ግን ሰፊ ጥናቶች መስራት ይጠበቅብናል።" ብለዋል።
ይሄም ጉባዔም የምልክት ቋንቋዎችን እንደ ህጋዊና አስፈላጊ ቋንቋዎች እውቅና ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ ይሆናል ነው ያሉት።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በመግለጫው ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምልክት ቋንቋ በማስተማር 15 ዓመታትን ማስቆጠሩን ጠቅሰው በጉባዔው በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተሰሩ ሥራዎች የሚቀርቡበት ነው ብለዋል።
አክለውም፥ የዩኒቨርስቲው ተመራማሪዎች፣ መምህራን፤ ተማሪዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ከዓለም አቀፍ አቻዎቻቸው እንዲማማሩ እድል ይሰጣል ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል "የምልክት ቋንቋ እውቅና እንዲኖረው የበኩላችንን አስተዋጽኦ የምናበረክትበት ይሆናል" ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ ጉባዔ ኢትዮጵያ ምን የምታቀርበው ነገር አዘጋጅታለች ?
ዶ/ር ኤርጎጌ በዚህ ጉባኤ ከሚቀርቡ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በተጨማሪ የተሰሩ ሥራዎችን እንድናቀርብ እድል ይሰጠናል ያሉ ሲሆን፤ በተለይም የመጨረሻ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የአካል ጉዳተኞች መብቶች የተጠቃለለ አዋጅን ጠቅሰዋል።
የአካል ጉዳተኞች መብቶች የተጠቃለለ አዋጅ ምን ይዟል?
በዚህ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አመዲን፥ አዋጁ ተበታትኖ የነበሩትን መብቶች ወደ አንድ በማሰባሰብ በተለይም ተጠያቂነትን የሚያሰፍን እንደሆነ ገልጸውልናል።
ከ90 ያላነሱ አንቀጾችን ይዟል በተባለው በዚህ የተጠቃለለ አዋጅ፥ የምልክት ቋንቋን በተመለከተ መጠቀሱን ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ "የምልክት ቋንቋ እንደ አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ እውቅና እንደተሰጣቸው ቋንቋዎች ታስቦ ተግባራዊ መደረግ አለበት የሚል ተካቶበታል" ብለዋል።
የምልክት ቋንቋን መጠቀም በኢትዮጵያ አስገዳጅ ነው ?
ይህንን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ "በተለይም የመስማት የተሳናቸው ተሳታፊዎች ባሉባቸው መድረኮች እንዲሁም በሚዲያ አዋጁ በግልጽ እንደተቀመጠው የመገናኛ ብዙኃን የምልክት ቋንቋ የመጠቀም ግዴታ ተጥሎባቸዋል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የጉባዔው አዘጋጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉባዔው መሳተፍ የሚፈልጉ በዚህ http://tislrethiopia.org/registration/ ሊንክ ተጨማሪ መረጃዎችን መውሰድና መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopia
#SignLanguage
#EthSL
@tikvahethiopia