TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Berbera

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ መጀመሩን ገልጿል።

የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ " የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ አስጀምሯል " ሲሉ ይፋ አድርገዋል።

" ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝንተ ያሳያል ሲሉ አክለዋል።

ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በይፋዊ ማስጀመሪያ ስርዓቱ ላይ ወደቡን የሚያስተዳድረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World በርበራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው እንደነበር ገልጿል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ " ይህ ቢሮ ወደቡ ላይ የሚራገፉ የተለያዩ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው " ብለዋል።

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስትሩ ሳድ (ዶ/ር) " ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ግንኙነታቸው የተጠናከረ ነው ፤ 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን መጠቀም ትችላለች " ማለታቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Photo Credit : #SomalilandFinanceDevelopment

@tikvahethiopia