TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ምን አሉ ? 🔵 " ሕገ-መንግሥቱ ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም " - የኤርትራው ፕሬዝዳንት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በመንግሥታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ስለወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንቱ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ ክልል ስላለው…
#ኤርትራ

🚨 " አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው ! " - የፋና ቴሌቪዥን ዘገባ

🔴 " አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ምርጫንም ሆነ የህግ የበላይነትን እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል ! "


ፋና ቴሌቪዥን በኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ " የአስመራው መንግሥት ነገር - የራሷ አሮባት " በሚል የሰራው ጠንከር ያለ ዘገባ መነጋገሪያ ሆኗል።

" የገዢውን ፓርቲ አቋም ያንጸባርቃል እንዲሁም የመንግሥት ልሳን ነው " እየተባለ የሚነገርለት ፋና ቴሌቪዥን ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በዚህ ልክ ኢሳያስን እና አስተዳደራቸውን አምርሮ የሚተች ዘገባ አውጥቶ አያውቅም።

በትግራይ ጦርነት ወቅት እንኳን ስለ ኤርትራው ገዢ ኢሳያስ ብዙ ሲባል የነበረ ቢሆንም የሻዕቢያ ሰራዊት የሰራቸውን የግፍ ተግባራት በይፋ ተናግሮ አያውቅም ነበር።

በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም እና ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት የግድ እንደሚገባ በግልጽ አቋሟን ይፋ ካደረገች በኃላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የነበረው ግንኙነት ሻክሯል በሚባልበት በዚህ ወቅት ጠንካራ እና ድፍረት የተሞላበት ዘገባ ሰርቶ ወጥቷል።

የዘገባው መነሻ ሰሞነኛው የኢሳያስ ቃለ ምልልስ ነው።

የፋና ዘገባ " በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን እጅግ የሻከረ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያል " ተብሏል።

ፋና በሰራው ዘገባ ስለ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ምን አለ ?

በቡዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ የተዘፈቀችውን የራሳቸውን ሀገር ረስተው ስለ ሌሎች ሀገራት እና ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሲፈተፍቱ ነበር።

ኤርትራ በህገመንግስት መስተዳደር ብርቅ የሆናባት ሀገር ናት። ይህ ሆኖ እያለ ህገመንግስት ያላትን ኢትዮጵያን መተቸታቸው አስገራሚ ነው።

ላለፉት 30 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ኤርትራን የገዙት ኢሳያስ መንግሥታቸው ህገመንግስት ፣ ምርጫ ፣ ነጻና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት የሚባል ነገር አያውቅም ፤ ፍላጎትም የላቸውም። ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይህንኑ ይናገራሉ።

ምርጫም ሆነ ተቀናቃኝ እንዳይኖር ለሶስት አስርት ዓመታት አፍነው እያስተዳደሩ ፣ በኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካም ከዓለም ስለራቀች ሀገራቸ ኤርትራ ለመናገር ነውር አስመስለውታል።

ለቀጠናዊ ሰላም እና ትብብር ጆሮ የማይሰጡት ኢሳያስ በቀጠናው ሰላም መደፍረስ ጣታቸውን ኢትዮጵያ ላይ ቀስረዋል።

የህገመንግስት አስተዳደር የሌላቸው ኢሳያስ የኢትዮጵያን ህገመንግስት ለመተቸት ደፍረዋል።

ኤርትራ ህገመንግስት ካፀደቀች ሩብ ክፍለዘመን ቢሆናትም አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ከመሳቢያቸው ስር ሽጉጠው ምርጫንም የህግ የበላይነትንም እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል።

ህገመንግስት የሌላቸው ሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ አስተያየት መስጠታቸው ስላቅ ይሆናል።

አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው።

አምባገነኑ ኢሳያስ  የጎረቤቶቻቸው በህግ መመራት የራሳቸውን ድካም የሚያጋልጥባቸው ይመስላቸዋል።

ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያደረጉ የጎረቤት ሀገራትን አይወዱም።

ኢሳያስ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለማወክ ከጀርባ ታጣቂ አሰልጥነው የሚልኩ መሆናቸውን ቴሌቪዥን ላይ ሲቀርቡ ይረሱታል።

እራሳቸውን የቀጠናው ጠበቃ የሀገራቱ ሰላም ወዳድ አድርገው የብልጣ ብልጥ ጨዋታ ይጫወታሉ።

ኤርትራን እንደ ሲንጋፖር አደርጋለሁ የሚለው ቅዠት ወደ ተግባር መለወጥ ሲያቅታቸው የናቋት ጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በየአመቱ 8% በላይ እድገት እያስመዘገበች በኢኮኖሚ የቀጠናው ቁንጮ መሆኗ ቅናት ውስጥ ከቷቸዋል።

ኢትዮጵያ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አልፋ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የአፍሪካን ሁለተኛ ኢኮኖሚ ገንብታለች።

ኢሳያስ ድፍን 30 ዓመታት የመሯት ሀገር ከ30 ዓመታት በፊት በተገነባ መሰረተ ልማት እየኖሩ ነው።

በኤርትራ ኢንተርኔት እና ስልክ በቤተሰብ ኮታ ነው የሚሰጠው። ገንዘብ በATM ማውጣት ብርቅ የሆነባት ሀገር ናት። ዜጎች ሰርግ እንኳን ለመከወን የሚያወጡት ወጪ ኦዲት የሚደረግባት ሀገር ናት።

ኤርትራውያን ነገን ያለ ተስፋ ኑሮን በጨለማ ለመግፋት ተገደዋል።

ጉባ ላይ በተለኮሰው የብርሃን ችቦ (GERD) ዜጎቿን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር እየተጣደፈችን ያለችውን ጎረቤታቸውን (ኢትዮጵያን) ለመተቸት አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ምንም የመሸማቀቅ ስሜት አይታይባቸውም።

ኢሳያስ የሚመሩት መንግሥት የጀርባ እቅዱ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለመግዛት እንደነበር በተደጋጋሚ ከሚያሰሙት ንግግራቸው ተስተውሏል።

ከግብፅ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ' ቀጠናዊ ሰላም ለማምጣት ' በሚል የዳቦ ስም በሰጡት መርዛማ ቀጠናውን የማተራመስ ሃሳብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ስጋት የደቀነ ስምምነት አስመራ ላይ ሲፈራረሙ ታይተዋል። ' ነገሩ ሆድ ሲያቅ .. ' መሆኑን ከ30 ዓመቷ ወጣት ሀገር መረዳት ይቻላል።

አንድ አምስተኛውን ህዝባቸውን ስደተኛ ያደረጉ ኢሳያስ በሰው ሀገር ጉዳይ በመፈትፈት የሚስተካከላቸው አይገኝም።

ኢሳያስ አምርረው የሚጠሉት ለኢትዮጵያውያን የሰንደቅ አላማ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድብ ሪቫን ሊቆረጥ መቅረቡ እረፍት ነስቷቸዋል።

ይህንን ዘገባ የተመለከቱ በርካቶች ዘገባው " ወቅታዊውን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን ቁርሾ / ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ያሳያል " የሚል ሃሳባቸውን ሰጥተውበታል።

https://youtu.be/UdzP3vtR4DI?feature=shared

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
"  ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም " - የፌደራል ዋና ኦዲተር

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር የህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ የሥራ ሀላፊዎች፣ ከፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከተሪሸሪው የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማስመልከት በኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምናና  የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ የሚውል በየክልሎች ፣በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ የተሰራጨው 9.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኩፖን ትኬት ጠፍቷል። የሥራ አመራር ቦርዱ አጠቃላይ 17 ሚሊዮን የእዳ ሥረዛ ማድረጉ በኦዲት ሪፖርት ተረጋግጧል።

በህብረተሰቡ ተነሳሽነት የተሰበሰበው ገንዘብ ያለ አግባብ ሲባክንና ለፕሮጀክቱ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል መቅረቱ ተገቢ አይደለም።

ሆስፒታሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ለምስራቅ አፍሪካ ተስፋ ለነበረው ፕሮጀክት የሚሆን በኢምባሲዎች የተበታተነው የሎተሪ ዕጣዎችም የት እንደደረሱ አልታወቀም።

የኦዲት ግኝቱ መነሻ ህዝቡ ያነሳው ቅሬታ ስለሆነ ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል መጠየቅ አለበት።

እስካሁን ባንክ ያልገባው ገንዘብ በማን እጅ እንዳለና ለምንስ ባንክ ገቢ እንዳልተደረገ እንዲሁም የተሸጡ ትኬቶችና ቦንዶች ባንክ ገቢ አልተደረጉም።

የሲቪል ማህበራት እንደገና ሲቋቋም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እንደገና መመዝገብ ቢኖርበትም አልተመዘገበም። ወሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔዎችን መቀበል አለበት።

ቦርዱ ውሳኔ ከወሰነ በኋላ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረገ ነበር። ቦርዱ ስልጣን ሳይኖረው 17 ሚሊዮን ብር የእዳ ስረዛ አድርጓል። የተወሳሰቡ ችግርች ናቸው ያሉት።


የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ምን አሉ ?

🔴 ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም። ቦርዱ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኩፖን ትኬቶችን የጠፉ በሚል ሰርዟል።

🔴 ባንክ ያልገባው ገንዘብ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከሚፈልገው አካል ጋር በመሆን ገንዘቡን ለህዝቡ ይፋ ለማድረግ ወደ ባንክ መግባት አለበት።

🔴 ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፕሮጀክቱ 9.1 ሚሊዮን ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች ተብሎ የወጣ ገንዘብ አለ ይህ መውጣት አልነበረበትም።

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሚናስ ህሩይ ምን አሉ ?

🟠 ለፕሮጀክቱ የታቀደው ገንዘብ 3.5 ቢሊዮን ብር ነበር። የተሰበሰበው ግን 50 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።

🟠 በተለያዩ አካባቢዎች የተበተነው የተንቦላ ሎተሪ ገንዘብ በቸልተኝነት ተረስቷል። ቀጣይ አቅማችን በሚችለው መንገድ ለማስመለስ እንሰራለን።
#HoPR

@tikvahethiopia
#Alert🚨

ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወሰደው ዋና የመኪና መንገድ አጉላዕ በተባለ ቦታ መዘጋቱ ተጓዦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" መንገዱ ከዲሞብላይዜሽን (DDR) ጋር በተያያዘ ጥያቄ ባነሱ የቀድሞ የትግራይ ታዋጊ አባላት ነው የተዘጋው " ብለዋል።

ጥያቄው በዝርዝር ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።

መንገዱ ከዛሬ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከወጣበት ከቀኑ 7:00 ድረስ ተዘግቷል።

መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ከመቐለ የተነሱ መኪኖች 40 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ አጉላዕ ከተማ ደርሰው ወደ ውቕሮ ዓዲግራት እና ሌሎች ቦታዎች ማለፍ አይችሉም።

ከዓዲግራት ፣ ወቕሮ እና ሌሎች ከተሞች የመጡት ደግሞ አጉላዕ ደርሰው ወደ መቐለ ከተማ ማለፍ አይችሉም ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ መንገደኞች።

ተጓዦች መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸው ገልፀው ፤ እስካሁን መንገዱን የዘጉትን የቀድሞ ተዋጊዎች አባላትን ጥያቄ ሰምቶ መልስ የሰጣቸው የለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያለውን መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይጠቁማል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት ይኖረዋል " - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ይስተዋላል።

የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በጥቂት የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ይሆናል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ፣ በደቡም ምዕራብ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ።

@tikvahethiopia
🪪 የዲጂታል መታወቂያ ካርድ ኅትመት በቀላሉ በቴሌብር ሱፐርአፕ ይዘዙ!!

💁‍♂️ ቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ ‘’NID (Fayda) Printing’’ በሚለው ሚኒ መተግበሪያ ተጠቅመው የፋይዳ ቁጥርዎን በማስገባትና ክፍያዎን በመፈጸም እንደምርጫዎ በ6 የሥራ ሰዓታት፣ በ2 ቀናት ወይም በ7 ቀናት ውስጥ በመረጡት የመረከቢያ ቀንና ቦታ ይደርስዎታል፡፡

📍 በመዲናችን የሚገኙ የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/3UT6rY3

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የተዘጋው የመኪና መንገድ ከ10 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ተከፍቷል።

ከውቕሮ ዓዲግራት በሚወስድ ከመቐለ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አጉላዕ በምትባለው ከተማ መንገዱ የተዘጋበት ምክንያት ምንድን ነው ?

መንገዱ ከጥዋት እስከ 10:00 ከሰዓት በኋላ የዘጉት በይፋ በዲሞብላይዜሽን (DDR) ወደ ህብረተሰቡ ያልተቀላቀሉ የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች ናቸው።

የቀድሞ ተዋጊዎቹ ከዲሞብላይዜሽን  (DDR) አጀማመር እና አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ፦

1ኛ. የዴሞብላይዜሽን (DDR) አሰራርና መመሪያ ሴት ተዋጊዎች ፣ በጦርነቱ የተጎዱ ታጣቂዎች ቀጥሎ በሙሉ ጤንነት ያሉ እየለ በየደረጃው እንዲፈፀም የሚፈቅድና የሚያዝዝ እያለ በጦርነቱ የተጎዳን ትቶ ጤነኞቹ ለምን አስቀደመ ?

2ኛ. ዴሞብላይዜሽን (DDR) የማይመለከታቸው አንዳንድ ግለሰቦች በወጣው ዝርዝር ስማቸው ተካተዋል ለምን ? ... የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች አንስተዋል።  

ያነሱዋቸው ጥያቄዎች አስመልክተው ከሚመለከታቸው የፀጥታ እና የፓለቲካ አመራሮች ከተወያዩ በኋላ መንገዱ ሊከፈት እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ሶሪያ በቀጣይ ወዴት ?

የ24 ዓመታት የበሽር አላሳድ አገዛዝ አክትሟል።

ቤተሰባቸውን ይዘውም ሩስያ ገብተዋል። ጥገኝነትም ተሰጥቷቸዋል።

አሁን ላይ የታጠቁ ተቃዋሚዎች መንበሩን ይዘዋል።

አላሳድን አንባገነን እንደሆኑ የሚገልጹ በርካቶች ክስተቱን ለሶሪያ ዘላቂ ሰላም እድል ያመጣል ይላሉ።

ከዚህ በተቃራኒ በሀገሪቱ ብዙ ታጣቂዎች ነፍጥ ስለያዙ  ለስልጣን ሲባል ወደ 2ኛው ዙር የእርስ በእርስ እልቂት ሊገባ ይችላል የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ሶሪያ ከፊቷ ተስፋ እና ስጋት ተደቅኗል።

ሶሪያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት እነማን ናቸው ?

እ.ኤ.አ 2011 ነው የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት የጀመረው።

የተሳታፊው ብዛት በርካታ ነው። እነዚህ የየራሳቸው ተሳትፎ፣ አመለካከት፣ ዓላማ ያነገቡ ናቸው።

ጉዳዩ ወስብስብ ያለ ነው።

👉 የአሳድ መንግሥት ኃይሎች

የሶሪያ አረብ ጦር (SAA) እና የብሔራዊ መከላከያ ኃይል (NDF) እኚህ የአላሳድ የጀርባ አጥንት ናቸው። SAA ኦፊሴላዊ የሆነው የሶሪያ መከላከያ ነው። NDF በመንግሥት የሚደገፍ ሚሊሻ ነው። SAA በኢራን እና ሩስያ ይደገፋል። በቀጣዩ መንግሥት ምስረታ ዕጣ ፋንታቸው ምን ይሆን ? የሚለው ምናልባትም በነ ሩስያ እና ኢራን ተፅእኖ ስር የወደቀ ሊሆን ይችላል።

👉 ነጻ የሶሪያ ጦር (FSA)

ቡድኑ መጀመሪያ የተቋቋመው ከሶሪያ ጦር ከድተው በወጡ አካላት ነው። ከዛም ወደ ተለያዩ አንጃዎች እና ጥምረት ተለውጣል። ብዙ ጊዜ ከምዕራባውያን እና ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ድጋፍ ያገኛል። በብዙ የሶሪያ ክፍሎች ይንቀሳቀሳል ነገር ግን በተለይ በሰሜን የአሳድን ጦር ሲዋጋ ነበር። በኃላም ISISን ሲዋጋ ነበር።

👉 ሀያት ታህሪር አል-ሻም (HTS)

ይህ በመጀመሪያ የሶሪያ የአልቃይዳ ክንፍ ነበር ፤ አልኑስራ በሚል ነበር ይንቀሳቀስ የነበረው። 2017 ላይ ግን በኢድሊብ እና ከፊል አሌፖ ፈርጠም ብሎ ወጥቷል። አላማው እስላማዊ መንግሥት መመስረት እንደሆነ ይነገርለታል። በቅርቡ አሳድን በመገርሰስ ጥቃት ላይ ቁልፍ ሚና ነበረው። በአዲሱ መንግሥት መመስረት ውስጥ የራሱን አላማ ለማስረጽ ግፊት ሊያደርግ ይችላል በዚህም ሴኩላር ከሚባሉት እና መሃከል ላይ ካሉት ጋር ሊጋጭ ይችላል። በኢድሊብ ከነበራቸው የመንግሥት አስተዳደር ጥብቅ የሸሪያ ህግ ለመተግበር ሊሰራ ይችላል።

👉 የሶሪያ ብሔራዊ ጦር (SNA)

እኚህ በቱርክ የሚደገፉ ናቸው። በዋነኝነት በሰሜናዊ ሶሪያ ነው የሚንቀሳቀሱት። የኩርዲሽ ኃይሎችን በመዋጋት የቱርክን ተፅእኖ ለማስረጽ ይንቀሳቀሳሉ ይባላሉ። በአዲሱ መንግሥት የቱርክን ፍላጎት የያዘ ሃሳብ ይዘው ሊቀርቡ ይችላሉ።

👉 የሶሪያ ዴሞክራቲክ ኃይል (SDF)

እኚህ በኩርዲሽ ዋይፒጂ ነው የሚመሩት። በአሜሪካ ድጋፍ ISISን በማሸነፉ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል። እኚህ ቡድኖች ሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያን ተቆጣጥረው የያዙ ናቸው። ራዕያቸው የፌዴራል፣ ያልተማከለ ሶሪያ እንድትኖር ነው። በማንኛውም አዲስ መንግስት ውስጥ፣ የኩርድ የራስ ገዝ አስተዳደር ወይም ፌደራሊዝም እንዲሰፍን ግፊት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ እንደ SNA ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር ሊያጋጫቸው ይችላል።

እንግዴ እኚህ ሁሉ አላማቸው የሚለያይ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ናቸው ሶሪያ ውስጥ ያሉት።

ከአሳድ አገዛዝ ወደ አዲስ መንግሥት ለሚደረገው ሽግግር ምናልባትም እጅግ ወሳኝና ጥልቅ ድርድር አልያም የእርስ በእርስ ግጭት በቡድኖቹ መካከል ሊፈጠር ይችላል።

🚨 SAA እና የአሳድ ደጋፊ ሚሊሻዎች ለውጡ ለነሱ ወይም አጋሮቻቸው ምቹ ሁኔታ ካልፈጠረ ሊቃወሙ ይችላሉ።
🚨 HTS ይበልጥ ሃይማኖታዊ የመንግሥት አስታዳደር ለመመስረት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ።
🚨 FSA እና ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ቡድኖች ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ይደግፋሉ ነገር ግን ጉልህ ተፅእኖ እንዲኖራቸው በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር መጠቃለል አለባቸው።
🚨 SDF ፌዴራሊዝም (ክልላዊ ራስን በራስ የማስተዳደር) እንዲተገበር ግፊት ሊያደርግ ይችላል። ይህን ሞዴል ሌሎች ከተቃወሙት ግጭት መቀጠሉ አይቀሬ ነው።
🚨 ቱርክ በSNA በኩል በምታደርገው ተፅእኖ ጠንካራ ፣ የተማከለ የኩርድ አካል እንዳይፈጠር ለመከላከል በመሆኑ ይህ ወደ ቀጣይ ውጥረት ሊያመራ ይችላል።


በአዲሱ የሶሪያ መንግሥት መስረታ የኃይል መመጣጠን ፣ በቡድኖቹ መካከል ያለው የአስተሳሰብ ልዩነት እና የውጭ ኃይሎች ተፅእኖ ትልቅ ፈታና ይሆናል። የእያንዳንዱ ቡድን ወታደራዊ ጥንካሬ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ እና በውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተቀረጸ በመሆኑ ሰላማዊ  ሽግግር ይኖር ይሆን ? የሚለው አሳሳቢ ነው።

አንዳንዶች ለውጡን በአግባቡ መያዝ ካልተቻለ ሀገሪቱ የመበታተን አደጋ እና ከበፊቱም የባሰ ሰቆቃ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ እየገለጹ ነው።

እኚህ ሁሉ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ወደ አንድነት መጥተው ጠንካራ ሶሪያን ይመሰርቱ ይሆን ? ወይስ ሁለተኛው ዙር የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት ይቀጥላል ? ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል !

🛑 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ፅሁፍ ለማዘጋጀት በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚተነትኑትን ቻክ ፈረን ጨምሮ የተለያዩ ድረገጾችን ተጠቅሟል።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ArbaMinch

🔴 የእሳት አደጋ መድረሱን ተከትሎ የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ እናት ህይወት አለፈ።

በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ረፋድ 4 ሠዓት አከባቢ በተለምዶ ' ቡቡ ሜዳ ' ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሚገኘዉ አዲሱ ገበያ የእሳት አደጋ ተከስቶ በንብረት ላይ ዉድመት ማድረሱን የከተማው አስተዳደር ፖሊስ አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉም የሰዉ ሕይወት መጥፋቱን የሚገልፁ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ማብራሪያ ጠይቋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ ፤ በአከባቢው በሚገኝ አንድ የኤሌክትሮንክስ ሱቅ ዉስጥ በኤሌክትሪክ ኮንታክት ምክንያት በተነሳ የእሳት አደጋ 12 ሱቆች መዉደማቸዉን ገልጸዋል።

በአደጋው ወቅት በገበያው ዉስጥ በተለምዶ መንገድ በጩኸት ይድረሱልን ጥሪ ሲያደርጉ ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዲት እናት ባለባቸው የጤና እክል ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኚህ እናት የልብ ሕመም እንደነበራቸው የገለጹት ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ፤ በጩኸት የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ሳለ በመድከማቸው ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማርተፍ አልተቻለም ነው ያሉት።

ሆኖም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሕይወቷ ያለፈዉ በእሳት አደጋዉ በደረሰ ጉዳት ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል።

በገበያዉ ዉስጥ ያለዉ የሱቆች አሰራር እና አጠቃቀም ለእሳት አደጋ አጋላጭ ነዉ ያሉት አዛዡ ፤ ሕይወቷ ያለፈዉ ግለሰብ በገበያው ዉስጥ ሱቅ እንደነበራቸውና ሱቃቸዉም እሳት አደጋዉ እንዳልደረሰበት ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የእሳት አደጋዉ በተገለፀው አኳሃን መፈጠሩን በገበያው ውስጥ ካሉ ነጋዴዎች የሰማ ሲሆን ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብም በቀጥታ በእሳት አደጋው በደረሰ ጉዳት አለመሆኑን ነጋዴዎች ተናግረዋል።

" ሞች ወ/ሮ አበባየሁ መንገሻ እንደ እናት ያሳደጉኝ እናቴ ናቸዉ፤ የሞቱት በእሳት አደጋዉ አይደለም " ያሉት አቶ አማኑኤል ሰይፉ የተባሉ ነጋዴ አስቀድመው የልብ ሕመምና የሕክምና ክትትል እንደነበራቸው አስረድተዋል።

አክለው በእሳት አደጋዉ ወቅት መደንገጣቸዉና ከሌሎችም ሴቶች ጋር ሆነዉ ለይድረሱልን ብዙ መጮኻቸዉን ተከትሎ መዳከማቸዉንና ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማለፉን ነው የገለጹት።

#TikvahEthiopiaFamilyArbaMinch

@tikvahethiopia