TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#SafaricomEthiopia

📽 😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!

የሳፋሪኮም #1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያው ክፍል ቅዳሜ ምሽት 3 ሰአት በአርትስ ቲቪ እንዲሁም እሁድ ከሰአት 9፡00 ደግሞ በአባይ ቲቪ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
" በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም " - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በኦሮሚያ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ከታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ማህበረሰቡ በአጀንዳ ልዬታ ወቅት የመረጣቸው ከ7 ሺሕ በላይ ተወካዮች እንደሚገኙ፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ በቦታው የተገኙት ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ተናግረዋል።

ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ምን አሉ?

“ ኮሚሽኑ አሁን በአጠቃላይ በአገራቱ ያለውን ሁኔታ ወደ ተሻለ ሰላም ለማድረስ የጸና፣ ዴሞክራሲያዊ፣ የመመካከር ባህልን ያዳበረ ማህበረሰብ እንዲኖረን እየሰራ ይገኛል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በ10 ክሌሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን ስራችንን ስንሰራ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ኦሮሚያም ክልልም እንዲሁም በአማራ ክልል ሥራው ተጀምሯል።

ኦሮሚያ ውስጥ ሆነን መናገር የምንችለው 7,000 የተለያዩ የኦሮሚያ የማህበረሰብ ክፍሎች ከዚህኛው በፊት በተሳታፊ ልዬታ ውስጥ ህዝቡ የመረጣቸው ተወካዮችን እናገኛለን። 

በቀጣዩ ሳምንት የምንሰራቸው ሥራዎች ለሰላም ከፍተኛ  አስተዋጽኦ አላቸው ብለን እናምናለን። በሂደቱ የሚሳተፉ በሙሉ በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርባለሁ።

በትግራይ የተካሄደው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በመሠረቱ እንዲጸና እና ክልሉ ደግሞ ኮሚሽኑ ሥራውን እንዲጀምር ፍላጎቱ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን "
ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት በተመለከተ ተጠይቀው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

° ኮሚሽኑ ሰዎችን አይመርጥም።

° በማህበረሰብ፣ ክልል፣ አገር፣ ከተማ ያሉ ዜጎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አሏቸው። የማህበረሰብ ክፍሎቹን በአሰራር ዜዬ ለይተናል። 

° አርሶ አደሮች፣ አርብቶ  አደሮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሚገፉ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በግጮቶች ምክንያት ከቄያቸው የተፈናቀሉ፣ በሌላ አካባቢ ሰቆቃቸውን የሚያዩ ዜጎችም አሉ። እነርሱም እንዲሳፉ ነው የሚደረጉት።

° ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀሩ። ከዚህ በፊት የፓለቲካ ፓርቲዎች ጥርጣሬዎች ነበሯቸው ከዚያ ጥርጣሬ የወጡ በርካታ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ውስጥ እየተሳተፉ ነው። አሁንም ልዩነት ያላቸው እንዳሉ እናውቃለን። ለእነርሱም ጥሪያችንን እያቀረብን
እንገኛለን።

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን ሁነት በተመለከተ ምን አሉ ?

" ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች (ለምሳሌ በምዕራብ ወለጋ የነበረውን ሁኔታ ሁላትንም የማንስተው ነው) ጅማ ላይ መጥተው ተወካዮቻቸውን መርጠው፣ በሰላም ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል እነርሱ ናቸው የሚሳተፉት።

እየተሟላ ያለ ሂደት እየሰራን ነው። በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ያለውን ሰላም ቸር አምላክ ያጽናልን። ሌሎች ብረት ያነሱ ከመንግስት ጋር ግጭት ያላቸው ወገኖችም ወንድሞቻቸው እንደተመለሱት ሁሉ ሰላምን ተቀብለው ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ እንፍታ።

በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም ብለው የወሰኑ ወገኖች አሉ። ለሌሎችም ይሄንኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Democracy👏

" የህዝቤን ውሳኔ አከብራለሁ " - በምርጫ የተሸነፉት ባውሚያ

አፍሪካ ውስጥ የተረጋጋ ምርጫና የስልጣን ሽግግር ከሚደረግባቸው ሀገራት አንዷ ጋና ናት።

ሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሂዳለች።

ለውድድር የቀረቡትም ተቃዋሚው የናሽናል ዴሞክራቲክ ኮንግረስ ፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ እና የአሁን የገዢው ኒው ፓትርዮቲክ ፓርቲ ዕጩና የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት መሃሙዱ ባውሚያ ናቸው።

ውጤት ?

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ የገዢውን ፓርቲና የአሁኑ ምክትል ፕሬዜዳንት ባውሚያን አሸንፈዋቸዋል።

በምርጫው የተሸነፉት የገዢው ፓርቲ ዕጩ ለተፎካካሪያቸው " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

ምርጫውን የተሸነፉት የገዢው ዕጩ ባውሚያ ህዝባቸውን / ጋናውያንን ለለውጥ የሰጡትን ድምጽ እና ውሳኔ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።

" የጋና ፕሬዜዳንት ሆነው ለተመረጡት የተከበሩ ጆን ማሃማ ስልክ ደውዬ እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ " ሲሉም ገልጸዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ምርጫውን በማሸነፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም እ.ኤ አ. ከሃምሌ 2012 እስከ ጥር 2017 ሀገሪቱን መርተዋል።

የምርጫው ውጤት ለሁለት ስልጣን ዘመን የቆየው የፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ገዢ ፓርቲ ማብቂያ ሆኗል።

ባለፉት የስልጣን ዘመናት ጋና አይታ የማይታውቀው የኢኮኖሚ ቀውስ እንዳጋጠማት ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዲሁም ከፍተኛ ዕዳ ጉድለት እንደተመዘገበ ተገልጿል።

ህዝቡም በተለይ ለተሻለ የኢኮኖሚ ለውጥ ፤ ያለው የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ በማሰብ የገዢውን ፓርቲ ዕጩ በድምጹ በመቅጣት ተቀናቃኙን የቀድሞውን ፕሬዜዳንት ወደ ቢሮ ለመመለስ እንደወሰነ ተመላክቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ትልቁ ማጠንጠኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንደነበሩ ተሰምቷል።

አጠቃላይ የምርጫው ውጤት ግፋ ቢል ማክሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ለምን ምርጫ አልተወዳደሩም ?

በጋና የፕሬዜዳንቱ ስልጣን ገደብ አለው።

ሁለት የስልጣን ዘመን አሸንፎ ሀገር ከመራ ለሌላ የስልጣን ዘመን " ልወዳደር " ቢል አይፈቀድለትም።

በዚህም ሀገር ለመምራት የሚፈቀድላቸው የስልጣን ዘመን ገደቡ ላይ ስለደረሰና መወዳደር ስለማይችሉ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ነው የተወዳደሩት።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ወንበሩን ለሌላ የሀገራቸው ልጅ ያስረክባሉ።

#Ghana
#Democracy #Election

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#TecnoAI

ቴክኖ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው በሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል እጅግ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ከፍ ያሉ የአርቴፊሻል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ይዞ ብቅ ካለው ከቴክኖ ኤ አይ በተጨማሪ አጅግ የተራቀቁ አዳዲስ የቴክኖ የምርት ውጤቶች ለዕይታ ይፋ ይሆናሉ፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ምን አሉ ? 🔵 " ሕገ-መንግሥቱ ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም " - የኤርትራው ፕሬዝዳንት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በመንግሥታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ስለወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንቱ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ ክልል ስላለው…
#ኤርትራ

🚨 " አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው ! " - የፋና ቴሌቪዥን ዘገባ

🔴 " አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ምርጫንም ሆነ የህግ የበላይነትን እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል ! "


ፋና ቴሌቪዥን በኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ " የአስመራው መንግሥት ነገር - የራሷ አሮባት " በሚል የሰራው ጠንከር ያለ ዘገባ መነጋገሪያ ሆኗል።

" የገዢውን ፓርቲ አቋም ያንጸባርቃል እንዲሁም የመንግሥት ልሳን ነው " እየተባለ የሚነገርለት ፋና ቴሌቪዥን ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በዚህ ልክ ኢሳያስን እና አስተዳደራቸውን አምርሮ የሚተች ዘገባ አውጥቶ አያውቅም።

በትግራይ ጦርነት ወቅት እንኳን ስለ ኤርትራው ገዢ ኢሳያስ ብዙ ሲባል የነበረ ቢሆንም የሻዕቢያ ሰራዊት የሰራቸውን የግፍ ተግባራት በይፋ ተናግሮ አያውቅም ነበር።

በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም እና ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት የግድ እንደሚገባ በግልጽ አቋሟን ይፋ ካደረገች በኃላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የነበረው ግንኙነት ሻክሯል በሚባልበት በዚህ ወቅት ጠንካራ እና ድፍረት የተሞላበት ዘገባ ሰርቶ ወጥቷል።

የዘገባው መነሻ ሰሞነኛው የኢሳያስ ቃለ ምልልስ ነው።

የፋና ዘገባ " በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን እጅግ የሻከረ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያል " ተብሏል።

ፋና በሰራው ዘገባ ስለ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ምን አለ ?

በቡዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ የተዘፈቀችውን የራሳቸውን ሀገር ረስተው ስለ ሌሎች ሀገራት እና ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሲፈተፍቱ ነበር።

ኤርትራ በህገመንግስት መስተዳደር ብርቅ የሆናባት ሀገር ናት። ይህ ሆኖ እያለ ህገመንግስት ያላትን ኢትዮጵያን መተቸታቸው አስገራሚ ነው።

ላለፉት 30 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ኤርትራን የገዙት ኢሳያስ መንግሥታቸው ህገመንግስት ፣ ምርጫ ፣ ነጻና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት የሚባል ነገር አያውቅም ፤ ፍላጎትም የላቸውም። ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይህንኑ ይናገራሉ።

ምርጫም ሆነ ተቀናቃኝ እንዳይኖር ለሶስት አስርት ዓመታት አፍነው እያስተዳደሩ ፣ በኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካም ከዓለም ስለራቀች ሀገራቸ ኤርትራ ለመናገር ነውር አስመስለውታል።

ለቀጠናዊ ሰላም እና ትብብር ጆሮ የማይሰጡት ኢሳያስ በቀጠናው ሰላም መደፍረስ ጣታቸውን ኢትዮጵያ ላይ ቀስረዋል።

የህገመንግስት አስተዳደር የሌላቸው ኢሳያስ የኢትዮጵያን ህገመንግስት ለመተቸት ደፍረዋል።

ኤርትራ ህገመንግስት ካፀደቀች ሩብ ክፍለዘመን ቢሆናትም አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ከመሳቢያቸው ስር ሽጉጠው ምርጫንም የህግ የበላይነትንም እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል።

ህገመንግስት የሌላቸው ሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ አስተያየት መስጠታቸው ስላቅ ይሆናል።

አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው።

አምባገነኑ ኢሳያስ  የጎረቤቶቻቸው በህግ መመራት የራሳቸውን ድካም የሚያጋልጥባቸው ይመስላቸዋል።

ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያደረጉ የጎረቤት ሀገራትን አይወዱም።

ኢሳያስ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለማወክ ከጀርባ ታጣቂ አሰልጥነው የሚልኩ መሆናቸውን ቴሌቪዥን ላይ ሲቀርቡ ይረሱታል።

እራሳቸውን የቀጠናው ጠበቃ የሀገራቱ ሰላም ወዳድ አድርገው የብልጣ ብልጥ ጨዋታ ይጫወታሉ።

ኤርትራን እንደ ሲንጋፖር አደርጋለሁ የሚለው ቅዠት ወደ ተግባር መለወጥ ሲያቅታቸው የናቋት ጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በየአመቱ 8% በላይ እድገት እያስመዘገበች በኢኮኖሚ የቀጠናው ቁንጮ መሆኗ ቅናት ውስጥ ከቷቸዋል።

ኢትዮጵያ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አልፋ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የአፍሪካን ሁለተኛ ኢኮኖሚ ገንብታለች።

ኢሳያስ ድፍን 30 ዓመታት የመሯት ሀገር ከ30 ዓመታት በፊት በተገነባ መሰረተ ልማት እየኖሩ ነው።

በኤርትራ ኢንተርኔት እና ስልክ በቤተሰብ ኮታ ነው የሚሰጠው። ገንዘብ በATM ማውጣት ብርቅ የሆነባት ሀገር ናት። ዜጎች ሰርግ እንኳን ለመከወን የሚያወጡት ወጪ ኦዲት የሚደረግባት ሀገር ናት።

ኤርትራውያን ነገን ያለ ተስፋ ኑሮን በጨለማ ለመግፋት ተገደዋል።

ጉባ ላይ በተለኮሰው የብርሃን ችቦ (GERD) ዜጎቿን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር እየተጣደፈችን ያለችውን ጎረቤታቸውን (ኢትዮጵያን) ለመተቸት አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ምንም የመሸማቀቅ ስሜት አይታይባቸውም።

ኢሳያስ የሚመሩት መንግሥት የጀርባ እቅዱ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለመግዛት እንደነበር በተደጋጋሚ ከሚያሰሙት ንግግራቸው ተስተውሏል።

ከግብፅ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ' ቀጠናዊ ሰላም ለማምጣት ' በሚል የዳቦ ስም በሰጡት መርዛማ ቀጠናውን የማተራመስ ሃሳብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ስጋት የደቀነ ስምምነት አስመራ ላይ ሲፈራረሙ ታይተዋል። ' ነገሩ ሆድ ሲያቅ .. ' መሆኑን ከ30 ዓመቷ ወጣት ሀገር መረዳት ይቻላል።

አንድ አምስተኛውን ህዝባቸውን ስደተኛ ያደረጉ ኢሳያስ በሰው ሀገር ጉዳይ በመፈትፈት የሚስተካከላቸው አይገኝም።

ኢሳያስ አምርረው የሚጠሉት ለኢትዮጵያውያን የሰንደቅ አላማ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድብ ሪቫን ሊቆረጥ መቅረቡ እረፍት ነስቷቸዋል።

ይህንን ዘገባ የተመለከቱ በርካቶች ዘገባው " ወቅታዊውን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን ቁርሾ / ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ያሳያል " የሚል ሃሳባቸውን ሰጥተውበታል።

https://youtu.be/UdzP3vtR4DI?feature=shared

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
"  ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም " - የፌደራል ዋና ኦዲተር

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር የህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ የሥራ ሀላፊዎች፣ ከፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከተሪሸሪው የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማስመልከት በኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምናና  የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ የሚውል በየክልሎች ፣በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ የተሰራጨው 9.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኩፖን ትኬት ጠፍቷል። የሥራ አመራር ቦርዱ አጠቃላይ 17 ሚሊዮን የእዳ ሥረዛ ማድረጉ በኦዲት ሪፖርት ተረጋግጧል።

በህብረተሰቡ ተነሳሽነት የተሰበሰበው ገንዘብ ያለ አግባብ ሲባክንና ለፕሮጀክቱ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል መቅረቱ ተገቢ አይደለም።

ሆስፒታሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ለምስራቅ አፍሪካ ተስፋ ለነበረው ፕሮጀክት የሚሆን በኢምባሲዎች የተበታተነው የሎተሪ ዕጣዎችም የት እንደደረሱ አልታወቀም።

የኦዲት ግኝቱ መነሻ ህዝቡ ያነሳው ቅሬታ ስለሆነ ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል መጠየቅ አለበት።

እስካሁን ባንክ ያልገባው ገንዘብ በማን እጅ እንዳለና ለምንስ ባንክ ገቢ እንዳልተደረገ እንዲሁም የተሸጡ ትኬቶችና ቦንዶች ባንክ ገቢ አልተደረጉም።

የሲቪል ማህበራት እንደገና ሲቋቋም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እንደገና መመዝገብ ቢኖርበትም አልተመዘገበም። ወሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔዎችን መቀበል አለበት።

ቦርዱ ውሳኔ ከወሰነ በኋላ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረገ ነበር። ቦርዱ ስልጣን ሳይኖረው 17 ሚሊዮን ብር የእዳ ስረዛ አድርጓል። የተወሳሰቡ ችግርች ናቸው ያሉት።


የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ምን አሉ ?

🔴 ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም። ቦርዱ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኩፖን ትኬቶችን የጠፉ በሚል ሰርዟል።

🔴 ባንክ ያልገባው ገንዘብ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከሚፈልገው አካል ጋር በመሆን ገንዘቡን ለህዝቡ ይፋ ለማድረግ ወደ ባንክ መግባት አለበት።

🔴 ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፕሮጀክቱ 9.1 ሚሊዮን ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች ተብሎ የወጣ ገንዘብ አለ ይህ መውጣት አልነበረበትም።

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሚናስ ህሩይ ምን አሉ ?

🟠 ለፕሮጀክቱ የታቀደው ገንዘብ 3.5 ቢሊዮን ብር ነበር። የተሰበሰበው ግን 50 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።

🟠 በተለያዩ አካባቢዎች የተበተነው የተንቦላ ሎተሪ ገንዘብ በቸልተኝነት ተረስቷል። ቀጣይ አቅማችን በሚችለው መንገድ ለማስመለስ እንሰራለን።
#HoPR

@tikvahethiopia
#Alert🚨

ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወሰደው ዋና የመኪና መንገድ አጉላዕ በተባለ ቦታ መዘጋቱ ተጓዦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" መንገዱ ከዲሞብላይዜሽን (DDR) ጋር በተያያዘ ጥያቄ ባነሱ የቀድሞ የትግራይ ታዋጊ አባላት ነው የተዘጋው " ብለዋል።

ጥያቄው በዝርዝር ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።

መንገዱ ከዛሬ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከወጣበት ከቀኑ 7:00 ድረስ ተዘግቷል።

መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ከመቐለ የተነሱ መኪኖች 40 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ አጉላዕ ከተማ ደርሰው ወደ ውቕሮ ዓዲግራት እና ሌሎች ቦታዎች ማለፍ አይችሉም።

ከዓዲግራት ፣ ወቕሮ እና ሌሎች ከተሞች የመጡት ደግሞ አጉላዕ ደርሰው ወደ መቐለ ከተማ ማለፍ አይችሉም ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ መንገደኞች።

ተጓዦች መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸው ገልፀው ፤ እስካሁን መንገዱን የዘጉትን የቀድሞ ተዋጊዎች አባላትን ጥያቄ ሰምቶ መልስ የሰጣቸው የለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያለውን መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይጠቁማል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት ይኖረዋል " - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ይስተዋላል።

የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በጥቂት የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ይሆናል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ፣ በደቡም ምዕራብ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ።

@tikvahethiopia