TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ሞያሌ #Moyalle በሞያሌ ከተማ በጠፋው የወገኖቻችን ህይወት ልባዊ ሀዘን እንደተሰማኝ እየገለፅኩ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለዘመድ አዝማዶች፣ ጓደኞች እና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቻናሉ እና በራሴ ስም መፅናናትን እመኛለሁ። የተጎዱት ወገኖቻችንን ፈጣሪ ይማርልን።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
የወገን ሞት ያማል!

በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል። እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ…
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች

በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ  ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ።

ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ ወድቋል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሞያሌ ኢትዮጵያ እና ጋምቦ አካባቢዎች ባደረገው ማጣራት ብርሃናማዉ አካል በተመሳሳይ መልኩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ወደ ሶማሊያና ምስራቃዊ ኬንያ አቅጣጫ ማለፉንና በአከባቢው አለመዉደቁን ለማወቅ ችሏል።

በሞያሌ ጋምቦ የሚገኘው የመረጃ ምንጫችን ስለጉዳዩ በሰጠው ቃል " በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር አከባቢ መደጋገሙን ስንሰማ ስለነበር በዚህም ክስተት ሰዉ ሁሉ ደንግጦ ነበር፤ ነገሩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ሲያልፍ አይቻለሁ " ብሏል።

አክሎ " ሪችት ይመስላል-ሞያሌ ወደቀ የሚል ነገር ሰምቼ እስከ ማርሳቤትና ናይሮቢ ድረስ ደዋዉዬ አጣራሁ ያሉኝ ነገሩ ናይሮቢ አልደረሰም፤ ነገር ግን የማርሳቤት ሰዎች ሰማይ ላይ አይተነዉ ኡጂሩ በተባለች የኬንያ ድንበር አድርጎ ወደ ሶማሊያ መሄዱን ነግረዉኛል " ሲል ገልጿል።

አንዳንድ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስነ ከዋክብትና ስፔስ ሳይንስ አጥኝዎች ይኸው ተቀጣጣይ ነገር " የጠፈር ፍስራሾሽ " ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በኢትዮጵያም ይሁን በኬንያ ተቋማት በኩል ቁርጥ ያለ ነገር ባይነገርም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኩል ጉዳይን በዝርዝር ለማሳወቅና ለማብራራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በኬኒያ ሙኩኩ በተባለ ገጠራማ መንደር 500 ኪ.ግ የሚመዝን ቀለበታማ የጋለ ብረት  መውደቁ የተነገረ  ሲሆን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamily #Moyalle #Gambo

@tikvahethiopia