TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Update የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለከተማ ቀላል ባቡር ባቀረባቸው ጥራት የሌላቸው የኤሌክትሪክ ገመዶች ሳቢያ ባቡር ትራንስፖርት እክል ገጥሞታል፡፡ ኢዜአ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ትራንዚት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር #ሙሉቀን_አሠፋን ጠቅሶ እንደዘገበው በገመዶቹ ሳቢያ የባቡር መቆም እና የሃይል መቆራረጥ ተፈጥሯል፡፡ #ሜቴክ የዘረጋቸው መስመሮች 15 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሲሆን ከሀያት እስከ ለም ሆቴል እና ከቃሊቲ እስከ መሹዋለኪያ ያለውን ርቀት ይሸፍናሉ፡፡ ቀሪዎቹን የዘረጋው የቱርክ ኩባንያ ነው፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia