TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" 7 ሰው ሞቷል ፤ 2 ሰው ተጎድቷል " - በወላይታ ዞን የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን፤ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ 01 ቀበሌ እና ኮይሻ ላሾ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት 7 (ሰባት) ሰው የሞተ ሲሆን በ2 ሰው ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በፊት በዛው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ላይ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ስሰራ ቢቆይም ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ችግሩ እያባባሰው መምጣቱ ተገልጿል።

መረጀው የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሥራ ሂደት ነው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎች እና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መረጃ ከላይ ተያይዟል።

#AddisAbabaTradeBureau

@tikvahethiopia
#ረቂቅአዋጅ

የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቁ ምን ይዟል ?

🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ።

🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ማስተማር ግዴታ ነው። ክልሎች ግን ከዚያ በፊትም የማስተማሪያ ቋንቋ ማድረግ ከፈለጉ ይችላሉ።

🔵 ተማሪዎች ቢያንስ 3 ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይደረጋል። የአፈጻጸም መመሪያ በቀጣይ ይወጣል።

🔵 አንድ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ከፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች መካከል የተማሪን አልያም የወላጅን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ከ3ኛ-10ኛ ክፍል ድረስ እንዲማሩ ይደረጋል።

🔵 በአጠቃላይ አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሎች በሚመርጡት መሰረት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት ይሰጣል። የእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ይሰጣል።

🔵የተማሪዎች ምዘናን በሚመለከት ደግሞ እስከ 1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የሚባለው እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥን ይከለክላል፡፡

🔵 ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወርን በሚመለከት በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የሚቻለው ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት አይነቶች 50 ከመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲያመጡ ብቻ ነው።

🔵 ክልላዊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሁለት ጊዜ በላይ በነጻ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም። ተፈታኞች በግላቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል።

🔵 የመምህራንን ትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮችን በሚመለከት ሴቶች ለመምህርነት ስልጠና በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምልመላ የሚያስፈልጉትን አጥጋቢ መስፈርት አሟልተው በውድድር ወቅት ከወንዶች ጋር እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ወቅት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይደረጋል።

🔵 አንድ መምህር በስራ ላይ እያለ በመንግስት ወጪ ደረጃውን የሚሻሽል ስልጠና ከወሰደ ለእያንዳንዱ የስልጠና ዓመት አንድ ዓመት በሙያው ማገልግል ግዴታ አለበት።

🔵 ወሲባዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች መፈጸሙ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሰው በማንኛውም የትምህርት ተቋም ውስጥ በመምህርነት እንዳይቀጠር ይታገዳል።

🔵 የግል ትምህርት ቤትን ማቋቋም በሚመለከት፥
° በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም እዳ መክፈል ያልቻለ ሰው ፣
° ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ፈቃድ ከሚጠይቀው አመልካች ውስጥ ድርሻ ያለው ሰው
° በወሲባዊ ወንጀል አልያም በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተወሰበት ሰው ፈቃድ ማግኘት አይችልም።

🔵 ሀገር አቀፍ የትምህርት ፈንድ እንዲቋቋም አዋጁ ይፈቅዳል ይላል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአል አይን አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረቂቅአዋጅ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ረቂቁ ምን ይዟል ? 🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ። 🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት…
" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? " - የፓርላማ አባል

አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ በትላንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ቀርቦ በምክር ቤት አባላት አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ለሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትኛ ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

በዋነኛነት በረቂቅ አዋጁ ላይ የምክር ቤት አባላት ምን አነሱ ?

አንዱ የተነሳው ከትምህርት ጥራት እንዲሁም ከመምህራን ጋር የተነሳ ነው።

ከሦስት በላይ የምክር ቤት አባላት የትምህርት ጥራት በቀጥታ ከመምህራን ጥራት ጋር አገናኝተው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በመምህራን የሚቀርቡ ጥያቄዎችንም አዋጁ የሚያስተናግድበት መንገድ እንዲፈጠር ነው የጠየቁት።

የምክር ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? ስለሚበላው ነገር የሚያስብ ፤ የት እንደሚያድር የሚያስብ መምህራንን ይዘን እንዴት ነው የምናሳካው ?

አሁንማ በሚገርም ሁኔታ ወሩን ጠብቆ ደሞዝ ስላልመጣ ሲያምጽ፣ ተቃውሞ ሲያሰማ የሚታሰርባቸው ክልሎች መኖሩን በተለያዩ ሜንስትሪም ሚዲያዎች የምንሰማበት ነውና የመምህራንን የትምህርት ጥራት ሳናሻሽል የትምህርት ጥራትን ማሳካት አንችልም።

ግብዓቶችን በጥቂቱ ሳናሟላ ውጤት መጠበቁ እንደማያዋጣ አያዋጣም።

ለትምህርት ጥራቱ ብዙ ነገሮች መታየት አለባቸው።

የሀገሪቷ የሥራ እድል ሁኔታ ምን ይመስላል ? ተማሪዎች ምንን አይተው ነው ተነቃቅተው የሚማሩት ወንድሞቻቸው እህቶቻቸው የት ደረጃ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩትን አይተው ነው የሚማሩት ?

የሀገሪቷ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ እንደዚህ አይነት በጣም ዘግናኝ የሆኑ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን እያዩስ በምን አይነት ተነሳሽነት አይተው ነው ተማሪዎች የሚማሩት ? እነዚህ ሁሉ ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው "
ብለዋል።

ሌላው በምክር ቤት አባላት የተነሳው ሀሳብ ቋንቋን በተመለከተ ነው።

በዚህ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት የምክር ቤቱ አባል ወ/ሮ አቡኔ ዓለም በተለይ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ጋር በተያያዘ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና ማብቂያውን በክልሎች እንዲወሰን በረቂቅ አዋጁ መቀመጡ የብሔረሰብ አስተዳደሮችን መብት የሚጋፋ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሌላኛዋ የምክር ቤት አባል ወ/ሮ ሲቲ ሬዲዋን ፥ የአፍ መፍቻ ቋንቋ በክልሎች መወሰኑ " የዚያ አከባቢ ሰው ከሌለ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሉ " ሲሉ ለክልሎች ኃላፊነቱ መሰጠቱን ተቃውመዋል።

" የወለኔ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመማር እድል አላገኘም " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ ከአፍ ቋንቋቸው ውጪ " ከፌደራል የሥራ ቋንቋ አንድ መርጠው እንዲሰጡ " የሚለው አገላለጽ ህገመንግስታዊ መሰረት የሌለው ነው ተብሏል።

ይህንን ኃሳብ ያነሱት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ናቸው።

ምን አሉ ?

" ህገመንግስቱ ይሻሻል ችግር የለውም ዜጎች በቋንቋቸው የመማር መብታቸው ይከበር። በጣም የሚበረታታ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ህገ መንግስቱን ሳናሻሽል 5 የሥራ ቋንቋዎች ውስጥ ምረጡ ማለት አስቸጋሪ ነው። " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መገናኛ

" የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ

ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ነው " መገናኛ " አካባቢ።

በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ምን አሉ ?

" መገናኛ በጣም ብዙ ሰዎች ተሽከርካሪዎችም የሚገናኙበት በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ቀድም ብሎ የቀለበት መንገድ የሚባለው ስለነበር መንገዱ ለእግረኞች ማቋረጫ በቂ አልነበረም። በዚህም ህብረተሰቡ በርካታ ችግር እንዲያሳልፍ ሆኗል።

ይሄ ትልቅ ጎዳና እንደመሆኑ የሚሰራው እግረኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይቸገሩ በመሬት ውስጥ መሻገር የሚችሉበት ነው።

የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናልም ይገነባል በማዶ በኩል። በሙልጌታ ህንጻ ስርም ሁለት ወለል ያለው ተርሚናል ይገነባል።

እግረኞች ከአንዱ ተርሚናል ወደሌላኛው ተርሚናል የሚገናኙት በመሬት ውስጥ ይሆናል።

ከላይ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ በማይኖርበት ወይም በኒቀንስበት ሁኔታ ነው እየሰራን ያለነው።

ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።

ትንሽ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ለ45 ቀናት መንገዱን ስንዘጋው የነዋሪዎች እና የመኪና እንቅስቃሴ በተለይ መገናኛ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደመሆኑ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።

ዛሬ የምንወስነው ውሳኔ ምናልባት ለወደፊቱ ለበርከታ ረጅም አመታት ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል።

ለ45 ቀናት በ3 ሺፍት ነው የምንሰራው። ከዛም ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ከሚሰሩት ኮንትራክተሮች ጋር ተግባብተናል " ብለዋል።


የግንባታ ስራውን የሚያማክረው ማነው ? ስራውን የሚያማክረው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ " የመገናኛ እግረኛ መተለለፊያ ስራ በአይነቱ የተለየ እና ዘመናዊ ነው " ብሎታል።

ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የፅዳት ቦታዎችም ይሰራሉ ብሏል።

" ፕሮጀክቱን በተባለው በ45 ቀናት እንደሚያልቅ እርግጠኞች ነን ፤ 24 ሰዓት ነው የሚሰራው  ፣ በቂ ማሽነሪ አለ፣ በተጓዳኝ ብረትና ሌሎች ዥግጅቶች እየተደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤኤምኤን ቲቪ መውሰዱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🙌🏼 ከሳፋሪኮም ወደ ቴሌ መደወል በደንብ ይቻላል ! እነዚህን የድምፅ ጥቅሎች እየተጠቀምን ከ07 ➡️ 09 መስመር እንደዋወል! ከአስተማማኙ ኔትወርክ ጋር አንድ ወደፊት⚡️
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቦታችንን https://yangx.top/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ

ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አሳውቋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ይህንን ያሳወቀው ለከተማው ትምህርት ቢሮ በላከው ደብዳቤ ነው።

" ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ የመጅሊስ መዋቅሮቻችን አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል " ብሏል።

" በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን እድርገው እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ሲል ም/ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች እነማን እንደሆኑ ግን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

በጉዳዩ ላይ ሰሞኑን ከከተማው ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደነበርም ምክር ቤቱ አስታውሷል።

" የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት ተማምነናል " ብሏል።

" ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል " ሲል አክሏል።

" ስለሆነም በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት #እንዲካካስላቸው " ሲል አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል።

ሰሞኑን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ምክንያት ችግሮች መከሰታቸው ፤ በዚህም ተማሪዎቹ ለ3 ሳምንታት ያህል ከትምህርት ገበታቸው እንደተስተጓጎሉ ተገልጿል።

እነዚህን ተማሪዎችን የሚወክሉ ከአዲስ ከተማ ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳተፉበት በዛሬው ውይይት ላይ ፦

🟢 ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

🟢 በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችንና አለባበሳቸውን መነሻ በማድረግ እየተስተዋለ ያለው አግላይነትና ከትምህርት የማራቅ ተግባር ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

🟢 ዛሬ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ነገ ወደ ሌላ የእምነቱ የስርዓተ አምልኮ ላይ ተሸጋግሮ ችግር ይፈጥራል የሚል ስጋት ገብቶናል ያሉ ተማሪዎቹ የተነሳውን ችግር ከወዲሁ እንዲፈታ አሳስበዋል።

የምክር ቤት አመራሮቹ ምን አሉ ?

➡️  ምክር ቤቱ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ሙስሊሙ በሚታወቅበት ሰላም ፈላጊነቱ ምክንያት እስካሁን የነበሩ ጉዳዮችን በሕግ አግባብ ማሳለፍ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ችግር በተለመደው የሕግ አግባብ እልባት ለማስገኘት እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

➡️ ሰሞኑንም ሆነ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ ያገኙ ዘንድ መላው ሙስሊም፣ ተማሪዎችና መሪው ተቋም መጅሊስ የተለመደ ሕጋዊ አካሄዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ከተማሪዎቹ ጋር በነበረው ውይይት የም/ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ፤ የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ዳይሬክተር ኡስታዝ ሀሰን አሕመድ እና የመምሪያው ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ በድር ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “ Best Overall in Africa award ” ሽልማት ማሸነፉን አሳውቋል።

አየር መንገዱ ፦
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “ Airline Passenger Experience Association ” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

በአቪዬሽን ኢንደስትሪውም ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ እንደሆነ አየር መንገዱ ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia