#ረቂቅአዋጅ
የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ለማሻሻል የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል።
የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ? ምን ዋና ዋና ማሻሻያ ተደርጓል ?
🔵 ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የስራ አመራር ቦርድ አሰያየም እና አወቃቀር ጋር በተያያዘ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።
በአዋጁ የተዘረጋው የቦርድ አሰያየምና አወቃቀር የተንዛዛ እና ረጅም ሂደትን የሚከተል መሆኑ ከዘርፉ ተለዋዋጭ ሁኔታ አንጻር አብሮ የማይሄድ መሆኑ፣ ይህም ባለሥልጣኑ መደበኛ ተልእኮዎችንና አስቸኳይ ውሳኔዎችን ከመስጠት አንጻር የመፈጸም አቅሙን የሚያስተጓጉል መሆኑ፣ እንዲሁም በነባሩ አዋጅ የተካተተው የቦርድ አባላት ስብጥር ከባለሥልጣኑ ሬጉላቶሪ ሚና ጋር በተያያዘ የጥቅም ግጭትን የሚፈጥር ሆኖ መገኘቱ እንደክፍተት ተገልጿል።
የተደረጉ ማሻሻያዎች ፦
" አንቀፅ 9/5/ሀ/ የቦርዱ አባላት ለመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ቅርበትና አግባብነት ካላቸው የተለያዩ አካላት እና የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ይሆናሉ " በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ የተደረገበት ሲሆን የቦርድ አወቃቀር ላይ አስቻይ ያልሆኑ ገደቦች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፡
🔵 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የስራ አመራር ቦርድ በወሳኝ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።
በረቂቁ ማብራሪያ ላይ ፥ " በመርህ ደረጃ የባለሥልጣኑ ስራ አመራር ቦርድ ባለሥልጣኑን በፖሊሲ የሚመራ አካል ቢሆንም፣ በአዋጁ አንቀፅ 13(2) መሰረት በዕለት ተዕለት የሚከወኑ የሬጉላቶሪ ሥራዎች በቦርድ እንዲከናወኑ ተደርጓል " ይላል።
" በተጨማሪም የሀገርን ደህንነት ወይም የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርስ ዘገባ በማናቸውም መገናኛ ብዙሃንና በማናቸውም ጊዜ ቢሰራጭ በአንቀፅ 81 መሰረት ፈቃድ የማገድ፣ የመሰረዝና አለማደስን የተመለከተ አስተዳደራዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ለቦርድ ተሰጥቷል " ሲል ያብራራል።
" ስለሆነም አዋጁ ቦርዱ ከሚጠበቅበት የፖሊሲ አቅጣጫ ሰጪነት ሚና ውጭ በዕለት ተዕለት የሬጉላቶሪ ተግባርና ሃላፊነት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህም ባለሥልጣኑ በህግ የተሰጠውን ተልእኮ ለመፈጸም ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ መስጠት እንዳይችል ገድቦታል " ይላል።
" በተመሳሳይ የሚዲያውን አውድ ታሳቢ ያላደረገ የውሳኔዎች መዘግየት በዴሞክራሲ ግንባታም ሆነ በሀገር ደህንነት ላይ አሉታዊ ጎኑ አመዝኖ ይታያል " ሲክ አክሏል።
የተደረጉ ማሻሻያዎች ፡-
➡ " የፈቃድ አለማደስ፣ የፈቃድ ማገድ፣ ወይም የፈቃድ መሠረዝ የሚያስከትሉ ውሳኔዎችን የመወሰን ሥልጣን የባለሥልጣኑ ቦርድ ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ ተሻሽሏል።
➡ የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም አንድ ፕሮግራም ማገድ ወይም መሰረዝ የሚያስከትሉ ውሳኔዎችን የመወሰን ሥልጣን #የባለሥልጣኑ_ይሆናል፡፡
➡ ረቂቁ " ባለሥልጣኑ የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ መሰረዝ፣ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም አንድ ፕሮግራም መሰረዝ የሚያስከትል ቅጣት የሚዳርግ ክስ ሲቀርብለት ባለፈቃዱ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተሰጠው መገናኛ ብዙሃን በጉዳዩ ላይ ያለውን ምላሽ በፅሁፍ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ እንዲያቀርብ እድል ሊሰጠው ይገባል " ይላል።
➡ " በተወሰኑት ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ ባለፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጠው የመገናኛ ብዙሃን ውሳኔው በደረሰው በ14 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለቦርዱ ሊያቀርብ ይችላል፤ ቦርዱ አቤቱታው በደረሰው በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት " በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡
🔵 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አሿሿምን በተመለከተ ማሻሻያ ተደርጓል።
" የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በቦርዱ ተመልምሎ በመንግስት አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰየማል " የሚለው ድንጋጌ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡
የተደረገው ማሻሻያ፡-
☑ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማል፡፡
🔵 ከብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ግዴታዎች ጋር በተያያዘም ማሻሻያ ተደርጓል።
የረቂቁ ማብራሪያ ላይ " በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ከቀጥታ ሥርጭት ውጭ የማናቸውም ፕሮግራም ይዘት በጣቢያው ከመሠራጨቱ በፊት ሕግን የሚያከብር መሆኑን የማረጋገጥ፤ ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
ይህ ድንጋጌ በቀጥታ ስርጭት ወቅት ህገወጥ ይዘቶች ከተሰራጩ የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪዎችን ተጠያቂ የማያደርግ በመሆኑ፣ አስፈላጊውን ኤዲቶሪያል ጥንቃቄ እንዳያደርጉ ያደርጋል፡፡
በመሆኑም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በሚፃረር እና በሀገር ሉአላዊነት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ እንደ ጦርነት ጥሪ እና የጥላቻ ንግግር የመሳሰሉ ይዘቶች እንዲሰራጩ መንገድ ይከፍታል፡፡
በመሆኑም ይህን ለመከላከል የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመውሰድ ማሻሻል አስፈልጓል " ብሏል።
የተደረገው ማሻሻያ፡-
የማናቸውም ፕሮግራም ይዘት በብሮድካስት አገልግሎት ጣቢያው ከመሠራጨቱ በፊት ሕግን የሚያከብር መሆኑን የማረጋገጥ፤ በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሹመት ሰጥተዋል። በቅርቡ ፕሬዜዳንት ሆነው በተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የፍትሕ ሚኒስትሩን ጌዴዮን ጢሞቲዮስን (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። የኢትያጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ሃና አርዓያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል። በተጨማሪም ፥ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ…
#HoPR
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው።
ሹመታቸው የፀደቀው ፦
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣
- የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣
- የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ
- የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ ሹመቱን በአንድ ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቀዋል።

#HoPR የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው። ሹመታቸው የፀደቀው ፦ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣…
#HoP
" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ ? " - ደሰለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ።
የቀድሞው የፍትህ ሚኒስትር አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
" የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆኑ ትራክሪከርዳቸው የውጭ ጉዳይን ለመምራት ብቁ ሊያደርጋቸው አይገባም " ብለዋል።
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ዶ/ር ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ሲመጡ ከፍተኛ ተስፋ አድርገው እንደነበር ጠቁመዋል።
ነገር ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት ሚኒስትሮች ምን የተለየ ነገር አሳኩ ? ሲሉ ጠይቀዋል።
በህግ ከውጭ ዩኒቨርሲቲ ፒኤችዲ ይዘው መምጣታቸውና እዚህም ትልቁ የሀገራችን ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸው ላይ ምን ለውጥ አመጡ የሚለው አልተገመገመም ብለዋል።
በፍትህ ሚኒስትርነት ያላቸው ትራክሪከርድ / የሰሯቸው ስራዎች ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ ያደርጋቸዋል የሚለውም አልተገመገመም ሲሉ ተናግረዋል።
" እኔ በግሌ ቅሬታ አለኝ " ያሉት ደሳለኝ (ዶ/ር) " በፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር አለባቸው ብዬ አይደለም ፤ በተለያዩ መድረኮች አይቻቸዋለሁ ሞያቸውን በጣም ጠንቅቀው ያውቃሉ ፤ ነገር ግን አፈጻጸማቸውን ካየነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን የፍትህ ጥማት ከማስታገስና ያን ከማርካት ይልቅ አሁንም የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን አድርገዋል " የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።
" በሀገራችን በተለይ በኢህአዴግ ዘመን የፍትህ ስርዓቱ ተቃዋሚዎችን ማጥቂያ፣ የፖለቲካ መሳሪያ፣ የገዢው ፓርቲ አንድ አርም ተደርጎ ሲሰራ ነበር አሁንም ያ ተቀይሯል ብዬ አላስብም " ብለዋል።
" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ሌሎች የምክር ቤት አባላት የፌዴሬሽን ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገቢ ፍትህ ሳያገኙ ለአመታት ሲንገላቱ የፍትህ ሚኒስትር ምንም የሰራው ነገር የለም። ከሳሹ እራሱ የፍትህ ሚኒስትር ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) " እንደኔ እንደኔ ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር የለባቸው ግን የፍትህ ሚኒስትር ላይ ያላቸው ትራክሪከርድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገሪቱን ለመምራት የሚያስችላቸው አይደለም። የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆነ ለዛ ቦታ ሊቀርቡ አይገባቸውም " ብለዋል።
#TikvahEthiopia

#HoP " የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ ? " - ደሰለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ። የቀድሞው የፍትህ ሚኒስትር አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…
" ሲሾሙ ' ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ' ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉና እንዳላደረጉ አይነገረንም " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለም ጫኔ (ዶ/ር) ከሚሰጡ ሹመቶች ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄ በምክር ቤት አንስተዋል።
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ " የሚነሱ ሚኒስትሮች ከሾናቸው በኃላ ምን አጉለው እንደተነሱ ፤ ምን ድክመት እንዳሳዩ ፤ ወይ ምን የስነምግባር ጥሰት እንዳሳዩ አይቀርብም ፤ በተጨማሪም እነሱን የሚታኳቸው ሚኒስትሮች ከነሱ በምን እንደሚሻሉ አይነገረም " ብለዋል።
" እርግጥ ሲሾሙ ' ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ' ምናም ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉ በምን ፐርፎርም እንዳላደረጉ አነገረንም። " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርህ አንጻር ጥያቄ እየሚያስነሳ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ሚኒስትሮች ከቦታቸው ሲወርዱ ለምን በምን ምክንያት እንደወረዱ ፤ በምትካቸው የሚመጡትም ከነሱ በምን እንደሚሻሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ ምክር ቤቱም ማወቅ የለበትም ? ሲሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጠይቀዋል።

#ExchangeRate የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ። ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር። ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 116 ብር ከ6699 ሳንቲም የገባ ሲሆን መሸጫው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ገብቷል። በተመሳሳይ…
#ExchangeRate
የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።
ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣው 116 ብር ከ6699 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ነበር።
ዛሬ ይፋ በሆነው ምንዛሬ ዋጋው ጨምሯል።
ባንኩ በመግዣ ዋጋው ላይ ከ2 ብር በላይ ጭማሪ በማድረግ 119 ብር ከ2044 ሳንቲም አስገብቶታል።
መሸጫውም በተመሳሳይ ከ2 ብር በላይ ጨምሮ 121 ብር ከ5885 ሳንቲም ገብቷል።
በግል ባንኮችም ዶላር ከ119 ብር - 120 ብር ባለው እየተገዛ ፤ እስከ 123 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።
(በግል ባንኮች ያለውን የዶላር የምንዛሬ ተመንን እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ገንዘብ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል)

" ሲሾሙ ' ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ' ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉና እንዳላደረጉ አይነገረንም " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለም ጫኔ (ዶ/ር) ከሚሰጡ ሹመቶች ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄ በምክር ቤት አንስተዋል። ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ " የሚነሱ ሚኒስትሮች ከሾናቸው በኃላ ምን…
" እኔ የፓርላማ አባል ሄጀ የተመለስኩ ሌላው ህዝብ እንዴት እየተገለገለ ነው ? " - የፓርላማ አባል
አንዳንድ ሚኒስትሮች ከተሾሙ በኃላ ለሆነ ጉዳይ ወደ ቢሯቸው ሲኬድ ቢሯቸውን እየዘጉ እንደሆነ አንድ የፓርላማ አባል ተናግረዋል።
አንድ ተሿሚ አመራር ከስልጣን ሲወርድ ህዝቡ ጋር እንደሚገባው በሹመቱ ሰዓትም ህዝቡ ጋር መኖር እንዳለበት አንሰተዋል።
ምን ጊዜም ተገልጋዮች ምላሽ እንዲያገኙ ቢሮዎች ክፍት መሆን አለባቸው ፤ በስልክም መገኘት አለባቸው የሚል ሃሳብ ተነስቷል።
የፓርላማ አባል ሄዶ ' ማግኘት አትችሉም ' ተብሎ ከተመለሰ ሌለው ተገልጋይ ህዝብ እንዴት እየሆነ ይሆን ? የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
ወ/ሮ እታፈራሁ ዘገየ (የፓርላማ አባል) ፥
" እኔ አንዳንዴ የሚጨንቀኝ ጉዳይ አለ። ተሿሚዎች የምናውቃቸውና የምናያቸው እዚህ ምክር ቤት ላይ መጥተው ሹመት ስንሰጣቸው ነው እንዴ ?
አንድ ተሿሚ ወይም አመራር ሚኒስተር ሆኖ ሲቀመጥ ሲወርድ ህዝብ ጋር እንደሚገባው ሲኖርም ህዝብ ጋር መኖር አለበት።
እያየን ነው ባለንበት ሂደት ሰው ተቋሙን ካበቃ እንደሚኖር ተቋሙን ካላበቃ ደግሞ ቦታ እንደሚፈለግለት እያየን ነው።
ስልጣን ጊዜያዊ ኮንትራት ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚኒስተር መ/ቤቶች ጋር የሚገጥመን ነገር አለ።
ምን ጊዜም ቢሮዎች ክፍት ነው መሆን ያለባቸው ለተገልጋይ ምላሽ ለማግኘት።
ከፀሀፊ ይጀምራል ' ሚኒስትሩ የሉም ፣ ማግኘት አይቻልም ፣ ቀጠሮ ይዛችሁ ነው ' ይባላል። ይሄ መስተካከልና መሻሻል አለበት።
እኔ አንዳንድ ጊዜ ሚኒስትሮቹን እዛ ስንሾም ብቻ ነው እንዴ መልካቸውን የምናየው ? ለምን ቢሮ ላይ ሄደን አናገኛቸውም ? የምንላቸው ተቋማት አሉ።
እኔ አንድ ሚኒስቴር መ/ቤት ሄጄ ሚኒስትሩን ፈልጌ ነበር አልኩኝ በጣም ተናደደብኝ ጥበቃው ' እንዴት ሚኒስትሩ ትያለሽ ? ' ብሎ አይ እኔ የፓርላማ አባል ነኝ ብዬ በግድ ነው የገባሁት።
ቢሮ ሁሉ ክፍት መሆን አለበት። ፀሀፊዎቹም ኦሬንት መደረግ አለባቸው።
እኔ ሄጄ (የፓርላማ አባል) የተመለሰ ሌላው ህዝብ እንዴት እየተገለገለ ነው ? የሚል ጥያቄና የራሴ ምልከታ አለኝ።
ባለጉዳይ የሚስተናገድበት ጊዜ መወሰን አለበት፤ ሂዶ ማግኘት የሚቻልበት ፤ ስልክ ላይ መገኘት ባለባቸው ሰዓት መገኘት አለባቸው።
ወርዶ ከህዝብ መቀላቀል ስለማይቀር ስንሾምም ደግሞ ነገ ህዝብ ጋር ስንኖር ስንወርድ ያምርብናል። "

#Ethiotelecom
🎉✨ ጥሪ ማሳመሪያ ዳግም በሽልማት ተመልሷል!!
ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎችን እንደገዙ ከ 645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!
📺 ስማርት ቴሌቪዥኖች
💻 ላፕቶፖች
📱 የ5ጂ ስማርት ስልኮችና ሳምሰንግ ታብሌቶች
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ጥቅሎችን በሽልማት ያግኙ!
ለመመዝገብ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም http://www.crbt.et ይጎብኙ!
🗓 እስከ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም ብቻ!
#CRBT #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Photo
#AddisAbaba
የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ፥ " ለ20 ዓመታት ቤት ይደርሰናል ብለን ስንጠብቅ ከሰሞኑን የሰማነው ነገር አሳዝኖናል ፤ ፍትህ ተጓድሎብናል መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ በቤት ኪራይ ተሰቃየን ፤ የቤት ችግር ኑሯችንን ፈተና ላይ ጥሎታል " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል ማብራሪያ ሰጥቷል።
ኮርፖሬሽኑ ምን አለ ?
" ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ብሏል።
" በ1997 ዓ/ም የቤት ባለቤት ለመሆን ተመዝግበው የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች በ2005 ዓ.ም በተካሄደው ዳግም ምዝገባ ወቅት ' ነባር ' የሚል መለያ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን ዳግም ከተመዘገቡና ውላቸውን ካደሱ ጊዜ ጀምሮ ሳያቋርጡ ሲቆጥቡ የነበሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።
" እነዚህ ተመዝጋቢዎች ቀደም ብለው የተመዘገቡ እንደመሆናቸው መጠን በ20/80 የቤት ልማት መርሃ ግብር ተገንብተው ለእጣ ከሚተላለፉት ቤቶች ውስጥ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣው መመርያ ቁጥር 3/2011 መሰረት በነበሩት ዙሮች ቅድሚያ እየተሰጣቸው ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ሲል አሳውቋል።
" በ2005 ዳግም ምዝገባ ያደረጉ ከ140 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎች ሳያቆራርጡ እስከ እጣ ማውጫ ቀን ድረስ እየቆጠቡ ለነበሩት እስከ 13ኛ ዙር በነበረው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ሲሰተናገዱ ቆይተዋል " ብሏል።
" ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለ14ኛ ዙር በተላለፉት የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ላይም የ1997 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነው የተስተናገዱት " ሲል አብራርቷል።
" በ14ኛ ዙር እጣ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ንቁና ብቁ የነበሩ ከ43 ሺህ ያልበለጡ ቆጣቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንዲሰተናገዱ ተደርጓል " ነው ያለው።
" በእጣ ማውጫ ጊዜ በመረጃ ቋት ውስጥ የቀሩት የ1997 ተመዝጋቢዎች በጊዜው ንቁና ብቁ ያልነበሩ ናቸው "ብሏል።
" እነዚህና ሌሎች ቤት ፈላጊዎች በከተማ አስተዳደሩ እየተተገበሩ በሚገኙ የተለያዩ የቤት የልማት አማራጮች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ " ሲልም አመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ፥ " በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተካሄዱ በሚገኙ የልማት ስራዎች ምክንያት ከመኖርያ አካባቢያቸው ለሚነሱ የልማት ተነሽዎች በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የወጣው በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ መመርያ ቁጥር 3/2011 አንቀጽ 23 በተገለጸው መሰረት በከተማ መልሶ ማልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት ለመመደብ በተቀመጠው አሰራር መሰረት እየተስተናገዱ ናቸው " ብሏል።
ኤጀንሲው " በልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት የሚሰጣቸው ከላይ በተጠቀሰው መመርያ ላይ በሰፈረው መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡ የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥ ለልማት ተነሺ በሚል በመጠባበቂያ ከተያዙት ቤቶች እንጂ በመደበኛነት ለተመዝጋቢዎች ከሚተላለፉ ቤቶች አይደለም " ብሏል።
" የልማት ተነሺ ሆነው የጋራ መኖርያ ቤት ምትክ የወሰዱና በ20/80 ወይም በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተመዝጋቢ የሆኑ ነዋሪዎች ከምዝገባ ቋት ውስጥ የሚቀነሱ ይሆናል " ሲልም አመልክቷል።

#MoE የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።…
#MoE #Placement
🔴 " እስካሁን ድረስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፎርም አልሞላንም ፤ ... ውጤት የመጣላቸውን ደግሞ ዝም ብለው መድበዋል " - ተማሪዎች
⚫️ " እውነት ነው ! ጉዳዩን ለክልል ብናሳውቅም መፍትሔ አልተገኘም " - አቶ ዘሪሁን ደርጫቦ
በ2016 ዓ/ም የ 12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ እና በሪሚድያል ፕሮግራም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያመሩ ተማሪዎች በተመደቡ መምህራን ፎርም እንዲሞሉ የት/ት ሚንስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
በዚህም ሀሙስ ቀን ወደ ክፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።
ይሁንና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን አመካ ወረዳ ላይ በዲምቢቾ፣ ጌቻ እና ገነዶ ት/ት ቤቶችን እንዲሁም በጎምቦራ ወረዳ ሀቢቾ እና ቢሻና ትምህርት ቤቶች ፎርም አለመሙላታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ጥቆማ ለማወቅ ተችሏል።
በወረዳው ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እስካሁን ፎርም እንዳልሞሉ እና ከመምህራኖቻቸው ' ሲስተም አስቸግሮናል ' የሚል ምላሽ እንዳገኙ የነገሩን ሲሆን ውጤት የመጣላቸው እንኳን ያልመረጡት እና ፍጹም ካላቸው ውጤት ጋር የማይገናኝ ዩኒቨርሲቲ እንደደረሳቸው ነግረውናል።
በወረዳዎቹ ፎርሙን እንዲሞሉ የተወከሉት መምህራን ፎርሙን ለመሙላት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት እንዳስቸገራቸውና መሙላት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
" እስከ ክልል ደውለን ለማሳወቅ ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም " ሲሉ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዘሪሁን ደርጫቦ ነገሩ እውነት መሆኑን አረጋግጠዋል።
" እኚህ ብቻ ወረዳዎች አይደሉም ዛሬ ብቻ ከሻሸጎ፣ ሾኔ እና ሌሎችም ወረዳዎች እስከ 10 ከሚደርሱ ት/ትቤቶች ተደውሎልኛል" ብለውናል።
ምክንያቱ ምን ይሆን ?
" የተማሪ ዳታ ሲሞላ በአምና user name ላይ ነበር እንዲሞላ የተደረገው የአምና ካልጠፋ / Delete ካልተደረገ በስተቀር አያስገባም እኔ ደግሞ በአምና ስገባ እኔን ያስገባኝ ቤንሻንጉል ላይ ነው የኔ አካውንት ካልጠፋ ሌላኛው ዞኑ ላይ መግባት አልችልም ማለት ነው የኔን አካውንት አጥፍታችሁ ዞኑ ላይ መልሱኝ ብዬ ለክልል ባሳውቅም ሳያደርጉ ቀርተዋል እዚህ ጋር ነው ክፍተቱ የተፈጠረው።
በዚህም ምንም ወረዳዎችን ላግዝ አልቻልኩም።
የትኛው ይሙላ አይሙላ የማውቀው ነገር የለም አድሚን ስትሆን አይደለ ሚያሳይህ እኔጋ የሚመጣው የቤንሻንጉል መረጃ ነው። ይህ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ምናልባት ፌደራል ላይ መረጃ ሲገባ ሊሆን ይችላል ስህተቱ የተፈጠረው።
ምንም መረጃ ልንለዋወጥ አልቻልንም ሪሚድያል ሙሉ በሙሉ አልተሞላም ማለት ይችላል ክልል ላይ በተደጋጋሚ ለማናገር ሞክረን ነበር ነገር ግን አልተሳካም ከወረዳ ሲደወልልኝ ወደ ክልል እየላኳቸው ቆይቻለው " ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት ብዙዎችን ያነጋገር መልእክትና ፎቶ በይፋዊና በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።
ፎቶው ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር አብረው ያሉበት ነው።
አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ትግራዎት ክብር ይስጣችሁ። ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " ብለዋል ከፎቶው ጋር ባያያዙት ፅሁፍ።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ የተነሱትን ፎቶ ብዙዎች በመጋራት አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አብዛኞቹ ምስሉ በአውንታ ተቀብለው ሲያስተጋቡ ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ " ከአንገት በላይ " ያሉትን ፎቶና መልእክት ንቅፈው እየጻፉ ነው።
አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለበርካታ ሳምንታት በሚዲያ እና በፅሁፍ መግለጫ ብዙ ሲባባሉ እንደነበር አይዘነጋም።
ምንም እንኳን ዛሬ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ በዝርዝር ባይታወቅም አቶ ጌታቸው ረዳ ያጋሩት ፎቶ ብዙዎችን እያነጋገረ ሲሆን ለአንዳንዶችም ' መካረሩ ያበቃለት ይሆናል ' የሚል ተስፋ የሰጠ ሆኖ ታይቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Attention🚨
“ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል። የሕሙማን ቁጥር ግን እየጨመረ ነው ” - ሆስፒታሉ
የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መረጃዎች እየጠቆሙ ቢሆንም የሚዲያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ለቫይረሱ ያላቸው ትኩረት እየቀነሰ መሆኑን ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማህጸን ጫፍ፣ የቆዳ ካንሰሮች ኤች አይ ቪ ኤድስ ሲጨመር አብረው የመጨመር እድል ስላላቸው ከዓመታት በፊት እንደነበረው ሁሉ የሚዲያዎችና ሌሎች ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ በአዲስ አበባ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ አሳስበዋል።
ፕሮፌሰሩ በዝርዝር አሉ ?
“ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንደ ህመም አሁንም አለ። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በተወሰኑ የአገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ የህሙማኑ ቁጥሩ እየጨመረ ነው።
እኛ እንደ ተቋም የምንሰጠውን አገልግሎት አላቋረጥንም። እሱን እናካሂዳለን። ግን ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የሌሎች ተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል።
ይሄ ጉዳይ መታሰብና መሻሻል አለበት። ኤች አይ ቪ ኤድስ የተወሰነ ህክምና አለው። ግን አንዳንዴ ህክምና ማለት ራሱ ቀላል ነገር አይደለም። አለመታመምን አይተካምና።
የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በእድሜ ልክ የሚወሰድ ህክምና ነው ያለውና በትኩረተ ሊሰራበት ይገባል የሚል እምነት አለን።
አንዳንዴ ደግሞ መድኃኒቱም ሳይድ ኢፌክት (የጎንዮሽ ጉዳት) አለው። ከመድኃኒቱ በተጨማሪ ከህመሙ ጋር በተያያዣነት ሌሎች ህመሞች ይመጣሉና።
አንዳንዴ ደግም ሰዎች ላያውቁት ይችላሉ፤ ሳያውቁት ሊቆዩ ይችላሉ እስኪመረመሩ ድረስ። ስለዚህ ምርመራውንም በተቻለ መጠን አጠናክሮ መስራት ያስፈልጋል።
ድሮ እናቶች ለእርግዝና ክትትል፣ ሌሎች ሰዎችም ለአንዳንድ ህክምና ሲመጡ ይመረመራሉና ያም ነገር አሁንም በደንብ ተያይዞ መቀጠል አለበት።
አንዳንድ ህመሞች ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር ቁጥራቸውም የመከሰት እድላቸውም ይጨምራል። ለምሳሌ የማኀጸን ጫፍ ካንሰር አንዱ ነው። የአንጀትና የቆዳ ካንሰሮች ሁሉ አሉ።
ሀገርም ደግሞ ምንም ህክምና ቢኖር ካላት ኢኮኖሚ ላይ ሸርፋ ነውና ለዚያ የምታውለውና ከዚህም አንጻር ሲታይ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው።
እኛ እንደተቋም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን ቢያንስ በማከም፣ በማስተማር። ግን አጠቃላይ እንደ አገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚዲያዎችን ጨምሮ አስፈላጊውን ሥራ ሁሉ እንዲሰሩ ይጠበቃል።
ኤች አይ ቪ ኤድስ የጤና ጉዳይ ብቻ አይደለም። የልማት ጉዳይ ነው ተብሎ ለብዙ ጊዜ የተኬደበት ጉዳይ ነውና አሁንም እንደዛው ታስቦ ነው መኬድ ያለበት ” ሲሉ አስገንዝበዋል።