TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.1K photos
1.53K videos
215 files
4.18K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#HappeningNow

በአሁኑ ሰዓት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የአውደ ውጊያ ውሎ የሜዳሊያ ሽልማት እና አዲሱ የመከለከያ ጠቅላይ መምሪያ ህንጻ ምረቃ እየተከናወነ ይገኛል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሰልፍ እና የአየር ትርዒትም ቀርቧል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#Update

ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
2. ጀነራል አበባው ታደሰ
3. ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሌ/ጀ አለምሸት ደግፌ

የአደዋ ድል ጀግና ከፍተኛ ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ጀነራል ጌታቸው ጉዲና
2. ሌ/ጀነራል በላይ ስዩም
3. ሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ
4. ሌ/ጀነራል መሰለ መሠረት
5. ሌ/ጀነራል ሹማ አብደታ
6. ሌ/ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል
7. ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ
8. ሌ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የመዘከሪያና የመከላከያ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት የማስመረቅ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

#PMOEthiopia #FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከግልገል በለስ እስከ አባይ ግድብ የሚደርሠውን መንገድ ስራ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዋና መምሪያው 210 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን ሶስተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ በማሳደግ ነው ስራውን ሰርቶ ያጠናቀቀው።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ሲጓጓዙ በመንገድ ላይ እስከ ሁለት ሳምንት ይቆዩ የነበረ ሲሆን በተከናወነው መንገድ የማሻሻል ጥገና ስራ የግድቡ የግንባታ ግብዓቶች #በአንድ_ቀን ለመድረስ ይችላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #GERD

" አሁን ላይ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የኮንቮይ ጉዞ ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ ችሏል " - ኢ/ር በላቸው ካሳ

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቀጠና በተገኘው ሰላም የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል።

የግድቡ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር በላቸው ካሳ ፤ " በቀጠናው የተገኘው አስተማማኝ ሰላም የግድቡን የግንባታ ሂደት #እያፋጠነው ይገኛል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የፀጥታው ጉዳይ ለግድቡ ግንባታ መሠረታዊ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በጀግንነት በመፈፀም በቀጠናው የከፈለው መስዋዕትነት የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ያኮራ በታሪክ የሚኖር ነው  " ብለዋል።

ኢ/ር በላቸው፤ በቀጠናው በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ወደ ግድቡ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ከሁለትና ከሶስት ቀን በላይ በመቆም መስተጓጎል ይፈጥር እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ የኮንቮይ ጉዞ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ መቻሉን አስረድተዋል።

የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ሌት ተቀን ሃያ አራት ሰዓት ያለ ዕረፍት የሚተጉ የግንባታዉ ሰራተኞች የአካባቢውን የሙቀት ሁኔታ ተቋቁመው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በደማቅ ሞራል እየተወጡ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

በስፍራው ከሚገኙ የሀገር መከላከያ አባላት የቀጠናውን ዘላቂ ሰላም በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ በማረጋገጥ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በሞራል እየተወጣ እነደሆነ ተናግረዋል።

ሰራዊቱ የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ፀረሠላም የሆኑ ኃይሎችን ፍላጎት በማምከን የግድቡን የፍፃሜ ትንሳኤ ለማብሰር ደከመኝ ሳይል ሀገራዊ ተልዕኮዉን እየተወጣ ነው ብለዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ምን አሉ ?

" ለኢትዮጵያ ዕድገት እንቅፋት ለመፍጠር የሚጥሩ በአካባቢያችን ያሉ #ታሪካዊ_ጠላቶቻችን እና #አዳዲስ_ኃይሎች እየተሰባሰቡ እንዳለ እያየን ነው።

እነኝህ ጠላቶች ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ በቅርበት እየተከታተልን እንገኛለን።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንንም ሃገር ብሔራዊ ጥቅም መንካት ተገቢ አለመሆኑን በማመን በዘመኗ የሌላ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ነክታ አታውቅም አሁንም አትነካም ታሪኳም አይደለም።

የሌላን ሀገር ብሔራዊ ጥቅም እንደማንነካው ሁሉ እኛም የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም።

ለሃገራችን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ዘብ እንቆማለን። "

ጄነራሉ ይህን የተናገሩት " አዋሽ አርባ " የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሜካናይዝድ ጦርን እና እየወሰደ ያለውን ስልጠና ከጎበኙ በኃላ ነው።

ሰልጣኞቹ በስነ-ልቦና ዝግጁነት ብቁ በመሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ክብር መረጋገጥ ሲባል የሚወስዱትን ሙያዊ ስልጠና በፍጥነት ማጠናቀቅና ለሚሰጣቸው #ማንኛውም_ግዳጅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው #አፅንኦት ሰጥተዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
" እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድባችን ሁሉ የቀይ ባህር ተልማችንንም ዕውን አድርገን ወሽመጣቸውን ዳግም እንቆርጠዋለን " - ሀገር መከላከያ ሰራዊት

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰራጨው አንድ ፅሁፍ ፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሀገር ስኬት ሁሌም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።

ሰራዊቱ ባወጣው ፅሁፍ ፤ ስማቸውን በግልፅ ያልጠራቸው እና " #እነሱ " ሲል የጠራቸው አካላት " እንደ ጦስ ዶሮ ዙሪያችንን እየዞሩ የብሄራዊ ጥቅማችንን ማረጋገጫ መንገዶች ሁሉ ለመዝጋት ከመፍጨርጨር ቦዝነው ያወቁበት የታሪክ አጋጣሚ የለም " ብሏል።

" አንዳንዴ ከራሳቸው ስኬት በላይ የእኛ በጠና መቸገርና መጎሳቆል በእጅጉ የሚያረካቸው እስኪመስል ድረስ ሀገራዊ የተስፋ ብርሃናችንን ለማጨለም ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም " ሲል ገልጿል።

" አባይን ለሺህዎች ዘመናት ለብቻቸው እንዳሻቸው ሆነውበታል። ለምተው አድገው ሀገራቸውን በጠንካራ መሠረት ላይ አቁመውበታል " ያለው ሰራዊቱ " እኛ ይህ ለምን ሆነ የሚል በከንቱ ምቀኝነት ብቻ ተነሳስተን ያደረግነው አንዳችም ነገር የለም " ሲል አስረድቷል።

" ለኢትዮጵያም ሆነ ለእነሱ ወንዝ ብቻ ያልሆነው አባይ እነሱን ሲያስውብ እኛን ሲያገረጣ ለብዙ ጊዜያት ቆይቷል " ያለው ሰራዊቱ ፤ " እውነት ከእነሱ ቅጥ ያጣ ስጋትና ራስ ወዳድነት በሚመነጭ ሴራ እየተጎነጎነልን በዚህም ዋጋ ከፋዮች ሆነን መቆየታችን ስናስበው የሚተናነቀን መራር እውነት ነው " ብሏል።

ኢትዮጵያ ጥቅሟን በሌሎች መጉዳት ላይ መመስረት እንደማትፈልግም ገልጾ ሁሌም " ማንም ሳይጎዳ እኔም በድርሻዬ ልጠቀም " በሚል መርህ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ይህን ማረጋገጥ መቻሏን አስታውሷል። በዚህም እነዚህ አካላት ወሽመጣቸው መቆረጡን ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ፤ " ከቀጠና እስከ አህጉር፣ ከአህጉር እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት ብዙ ማስነው ሊያስቆሙት ያልቻሉት ታላቁ የህዳሴ ግድብ አሁን ' የተበላ እቁብ ሆኖባቸዋል ' " ብሏል

" እነዚሁ አካላት አሁን ደግሞ የሶማሊያ ' አዛኝ ቅቤ አንጓች ' ሆነው ብቅ ብለዋል " ያለው ሰራዊቱ " የህዳሴ ግድቡስ እሺ ከአባይ ጋር ተያያዘ እንበል። ከወዳጅ ጎረቤታችን ሶማሌላንድ በቀይባህር የባህር በር እና የባህር ሃይል ቤዝ እንዲኖረን በምትኩም ሶማሌላንድን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምንሰጠው ኖሮን ተስማማን። ታዲያ እንዴት ቀይባህር ውስጥም አባይ ሊታያቸው ቻለ ? ... ይህ ታሪካዊ ጠላትነት ካልሆነ ምን ይባላል ? " ሲል ጠይቋል።

መከላከያ ባወጣው ፅሁፍ ፤ " የማይመጡበት የለም " ያላቸው እነዚህ አካላት " ከውስጥ በብሄር፣ በሃይማኖት በሌላም እንድንናቆር፣ ሁሌም በአዙሪት እንድንዳክር.. ይተጋሉ። መቼም አይተኙልንም " ብሏል።

" እኛም እንደ ታላቁ የህዳሴው ግድባችን ሁሉ የቀይ ባህር ተልማችንንም ዕውን አድርገን ወሽመጣቸውን ዳግም እንቆርጠዋለን። እኛ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሀገራችን ስኬት ሁሌም ዝግጁ ነን " ሲል አሳውቋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል።

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር።

ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል። ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር። ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል። #FDREDefenseForce @tikvahethiopia
የመከላከያ_ሠራዊት_ፋውንዴሽን_የቤት_ባለዕድለኞች_ዝርዝር.pdf
11.1 MB
መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላልፏል።

በዕጣ የተላለፉት አጠቃላይ 1,336  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦
- ባለ 4 መኝታ
- ባለ 3 መኝታ
- ባለ 2 መኝታ
- ባለ 1 መኝታ ናቸው።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ለሠራዊት አባላት እና ቋሚ ለሆኑ ስቪል ሰራተኞች ነው የተላለፉት።

(የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ከላይ በPDF ተያይዟል)

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update

የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ?

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ ተሰጥቶ እየሰራ እንዳለ አመልክተዋል።

የፀለምት እና አካባቢው ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ኃላፊነት የተሰጠው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መሆኑን ተናግረው " ስራው እጅግ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው " ብለዋል።

ዛሬን ረቡዕ ጨምሮ ባለፉት ቀናት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ያሉት አስፈላጊና መሟላት አለባቸው የተባሉ ቅድመ ሁኔታዎች ከጎን እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ስራው በፍጥነት እየሄደ ያለው አብዛኛዎቹ አርሶ አደር የክረምቱ ወቅት ሳያልፍ እርሻውን እንዲሰራና ህይወቱን እንዲመራ በማሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በፀለምት ካሉ 25 ቀበሌዎች አብዛኛው ተፈናቃይ ከ22 ቀበሌዎች ነው አሁን ባለው ሁኔታ በአስራዎቹ ቀበሌዎች ተፈናቃይ ተመልሷል ፤ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀሪ 11 ቀበሌዎች  አብዛኛው እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ አሳውቀዋል።

የቀረውም ስራ በቀጣይ ይሄዳል ብለዋል።

ስለ ታጣቂዎች መውጣት ምን አሉ ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የትግራይ ታጣቂዎች በኃይል ገብተዋል " ስለሚባለው ጉዳይ ሌ/ጄነራሉ ፥" ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ በፀለምትም ይሁን በወልቃይት በኃይል የገባባቸው ቦታዎች የሉም " ሲሉ መልሰዋል።

ፀለምት ካሉት ቀበሌዎች 3 ቀበሌዎች ላይ የትግራይ ታጣቂዎች እንዳሉ እነዚህም ጦርነት ሲቆም ባሉበት የቆሙ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ባለው መግባባት ከሁለቱም ክልል ጋር የሁለቱም ክልል ታጣቂ መውጣት ስላለበት ተፈናቃዮችን በመመለስ ታጣቂዎቹን የማስወጣት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ፀለምት ያለው የትግራይ ታጣቂ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ እንዳይመለስ ስለሚሰራ ስራ ምን አሉ ?

በአማራ በኩል " ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ ይገባል " የሚል ስጋት እንዳለ ያልሸሸጉት አዛዡ ፥ በትግራይ በኩልም " ታጣቂዎች (በአማራ በኩል ያሉ) እንደ አዲስ ተደራጅተዋል ስጋት ናቸው " የሚል ነገር እንዳለ ገልጸዋል።

" የሀገር መከላከያው ከሁለቱም በኩል ከተፈናቃዮች እና እዛው ከነበሩት ነዋሪዎች ( ካልተፈናቀሉት ) ሽማግሌዎች እንዲውጣጡ አድርጎ የተፈናቃዮችን ዝርዝር ለመከላከያ ተሰጥቶ ከዛም መከላከያው ከሽማግሌዎቹ ጋር አብሮ ሰዎቹ የዛ ቦታ ነዋሪ መሆናቸውን እየጠየቀና እያረጋገጠ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ " ብለዋል።

' ይሄ ታጣቂ ነው ፣ ይሄ ሚሊሻ ነው ' የሚል ክርክር በሽማግሌ ደረጃ ከተነሳ ወደ ህዝብ ተወስዶ ህዝቡ እራሱ ይፈርዳል ሲሉ ተናግረዋል።

" እንግዳ ሰው ሲገባ ይታወቃል ይህ ጉዳይ አሳሳቢ አይደለም " ያሉት አዛዡ ፥ ገጠር ይሁን ከተማ መሬት ከሌላቸው / ሊገቡበት የሚችሉበት ቤት ከሌላቸው ተለይቶ ይታወቃል ብለዋል።

#Ethiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
" በይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል " - ሀገር መከላከያ ሰራዊት

ሀገር መከላከያ ሠራዊት " 178 የትግራይ ተወላጅ የሠራዊት አባላት ከዛሬ ጳጉሜን 5/2016 ጀምሮ ከእስር በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል " ሲል አሳወቀ።

መከላከያ በአዲስ ዓመት ይቅርታ የተደረገላቸው የህወሓት ታጣቂ ሃይሎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መከፈታቸውን ተከትሎ የተሰጣቸውን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ ወደ ጎን በመተው በሰራዊቱ እና በህዝብ ጥቅሞች ላይ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው ብሏል።

" ጉዳያቸው በወታደራዊ ፍትህ ስርዓቱ አማካኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ምክንያት በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እስከ ሞት ቅጣት ተወስኖባቸው በማረሚያ ቤት ይገኙ ነበር " ሲል አስረድቷል።

ሀገር መከላከያ " እኚሁ የሠራዊት አባላት በፈፀሙት ወንጀል ተፀፅተው የይቅርታ ጥያቄአቸውን ለመንግስት እና ለመከላከያ ሚኒስቴር አሥገብተዋል " ሲልም አክሏል።

በዚህም በአዲሱ ዓመት በይቅርታ 178ቱ የትግራይ ተወላጅ የሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መልሼ አጤነዋለሁ " - ሶማሊያ የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ " መልሶ ለማጤን " ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ " የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል " ሲሉ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ…
#Ethiopia #Somalia

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ።

በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ከኢፌዴሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ  (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንቱ የተላከ መልዕክትን አድርሰዋል።

" በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶማሊያ እና በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል " ያለው ሚኒስቴሩ " ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የAUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል " ሲል ገልጿል።

በቅርቡ የሶማሊያ ከፍተኛ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ ውይይት ለማካሄድ መስማማታቸውም ተመላክቷል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብድርቋድር ኑር ጃማ ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሶማሊያን ሰላም ለማረጋገጥ ለከፈለው መስዋትነት እና ላበረከተው አስተዋጽዖ ያላቸው አክብሮት እና ምስጋና ማቅረባቸው ተነግሯል።

#MinistryofForeignAffairsofEthiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#ADWA129

129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል " በሚል መሪ ኃሳብ እንደሚከበር የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

የመከላከያ ስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን ፥ " በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ከበዓሉ ቀደም ብሎም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች ጭምር እንደሚከበር ጠቁመዋል።

" ዓድዋ የጋራ ድል፣ የአንድነት፣ የአላማ ፅናት እንዲሁም የአሸናፊነት ምሳሌ በመሆኑ የአባቶችን አርበኝነት በመያዝ ዘመኑ የሚጠብቅብንን ኃላፊነት መወጣት አለብን " ብለዋል።

#FDREDefenseForce #FMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቤተክርስቲያን ማሳ እያረሱ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ የአንድ አርሶ አደር ሕይወት ጠፍቷል " - የኮሬ ዞን ጎርካ ነዋሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች ባሳለፍነዉ ቅዳሜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ " ጃሎ " ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በታጠቁ ሃይሎች በተፈፀመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ይታወቃል። ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በወረዳዉ " ዳኖ ቡልቶ " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ…
" ከኬሌ - ዲላ መንገድ ለጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ይደረጋል፤ መንገዱ ክፍት የሚደረገው ግን የፀጥታ መዋቅር በሚያስቀምጠው የሰዓት ገደብ ነው " - አቶ ወገኔ ብዙነህ

በደቡብ ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየውን የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለ የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ የምክክር መድረክ መካሄዱ ተሰምቷል።

በምክክር መድረኩ ህዝብ መካከል ያሉ የተደራጁ ንብረት ዘራፊዎች እና ነፍስ አጥፊዎች ላይ የህግ የበላይነት ማስከበር እንዲሁም ሀገር መከላከያ ሠራዊት ኦፕሬሽን አድርጎ አካባቢውን ለማፅዳት የሚሰራውን ስራ ማገዝ ከዛ ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እዲጠናከርና ሰላም እንዲፀና መስራት ይገባል ተብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እነማን ነበሩ ?

- የሀገር መከላከያ ሰራዊት
- የኮሬ ዞን
- የቡርጂ ዞን
- የምዕራብ ጉጂ ዞን
- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ

ምን ተባለ ?

የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ፤ መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለመጀመር ወሳኝ እና ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

በኮሬ ዞን በኩል እየተሰራ ባለ የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ የፀጥታው ሁኔታ እየተረጋጋ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኣቶ ዳኜ ሂዶ ፤ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ሁሉ። መዋቅሮች ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዱላ ህርባዬ ፤ መድረኩ አላማው የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስተካከል ጥርጣሬ በማስወገድ ግልፀኝነት መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል።

በቀጣይ የቀበሌ እና የወረዳ አመራሮች የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር ቅንጅታዊ ኦፕሬሽን ማድረግ፣ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር ላይ ይሰራል ብለዋል።

ሶስቱም ዞኖች በጋራ ሆነው የቆመው የፍስሃ ገነት - ኬሌ - ነዳሌ የአስፋልት መንገድ እንዲጀመር መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት 37ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ካሳዬ ተገኝ ፤ ቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ ከቀበሌ አንስቶ የህዝብ አመለካከት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ህዝቡ ወንጀለኞችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ ማድረግ ፣ ፀረሰላም ኃይሎች የሚንቀሳሰቁባቸውን ቀበሌያት ወሰን አካባቢ ህዝባዊ ሰራዊት እና ሚሊሻ ማደራጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በሰላም ግንባታ ላይ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን እንዲጫወቱ ጠይቀዋል።

መከላከያ ለሚሰራው ኦፕሬሽን አዋሳኝ ቀበሌያት ያለው ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ፥ " የተጀመረውን የአመራር ለአመራር እርስ በእርስ ግንኙነት ለማደናቀፍ የሚሰራ ፀረ ሰላም አለ " ብለዋል።

በመሆኑን የፀጥታ መዋቅሩ በተጠንቀቅ መቆም አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሁለቱም መዋቅር አመራርና ፀጥታ አካላት እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጋራ ተስማምተው በሚያስቀምጡት የሰዓት ገደብ መሰረት ከኬሌ - ዲላ መንገድ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ገልጸዋል።

" ከዛሬ ጀምሮ በቀጠናው የሰው ነፍስ የሚያጠፉ ንብረት የሚዘርፉ በኮሬ፣ ቡርኪና ጉጂ ስም የሚነግዱ ህገወጦች ወደ ቤት ግቡ " ሲሉ አሳስበዋል።

#KooreZone #BurjiZone #WestGujii #FDREDefenseForce

@tikvahethiopia