TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Ethiopia

ጥሬ ዕቃዎች በዱቤ ወይም በወጪ ንግድ ማበረታቻ ሥርዓት ተጠቅመው ያስገቡ ላኪዎች፣ በአንድ ዓመት ውስጥ አምርተው ወደ ውጭ መላክ ካልቻሉና ለአገር ውስጥ ለመሸጥ #ሳይፈቀድላቸው ለሽያጭ ካቀረቡ 25 በመቶ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተገልጿል።

በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ታትሞ የወጣው የወጪ ንግድ ማበረታቻ ሥርዓት ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1342/2016 በ " ቫውንቸር " ሥርዓት፣ እንዲሁም በ ' ቦንድ ኤክስፖርት ፋብሪካ " ሥርዓት ወደ አገር ውስጥ የገባ የጥሬ ዕቃ ለተጠቃሚ [ለአምራቹ] ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምርቱ ተመርቶ ለውጭ ገበያ መቅረብ እንደሚኖርበት ይደነግጋል።

በተቀመጠ ጊዜ ገደብ ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ካልተቻለ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክንያቱ በቂ መሆኑን ሲያምንበት ብቻ ሊራዘም የሚችል ሲሆን የማራዘሚያ ገደቡ ከመጠናቅቁ በፊት ለኮሚሽኑ መቅረብ እንዳለበት ተገልጿል።

በአገር ውስጥ እንዲሸጥ ያልተፈቀደለት የ " ቫውንቸር " ሥርዓት ተጠቃሚ ጥቅም ላይ ባልዋለው ጥሬ ዕቃ ላይ ሊከፍል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ተጨማሪ 25 በመቶ እንዲከፍል እንደሚደረግ ተደንግጓል።

በቦንድ ግብዓት አቅርቦት መጋዘን ሥርዓት ወደ አገር የገባ ግብዓት ወደ መጋዘን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለአምራቾች ካልተላለፈ መከፈል ካለበት ቀረጥና ታክስ በተጨማሪ የቀረጡንና የታክሱን 10 በመቶ ሊከፍል እንደሚገባ ይህንን ማድረግ ካልተቻለም የጉምሩክ ኮሚሽን ሲያምንበት ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል ተመላክቷል።

አቅራቢዎች በሚሰጡት ዱቤ ወይም በፍራንኮ ቫሉታ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባ አስመጪ ተፈላጊውን ምርት በአገር ውስጥ ከተመረተ በኋላ ፣ የምርቱ ተቀባይነት መኖሩን የሚያረጋግጥ ከገዥው የተላከ ትዕዛዝ ወይም የተደረገ ውል ማቅረብ መቻል እንዳለበት በአዋጁ ተደንግጓል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopia-Reporter-08-26

Credit - Ethiopia Reporter

@tikvahethiopia