TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
2023.pdf
#ETHIOPIA

' አልያንስ 2015 ' የተባለው 8 የአዉሮጳ የልማት ድርጅቶች ያቀፉት ተቋም ሀገራት ያሉበትን የረሃብ አደጋ ደረጃ የሚያመላክተውን የዓለም አቀፍ የረሃብ ኢንዴክስ (Global Hunger Index) ይፋ አድርጓል።

በዚህ የረሃብ መለኪያ ሪፖርት ከ125 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ 101ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የሰቆጣ ቃልኪዳን የፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ሲሳይ ሲናሞ ምን አሉ ?

- ሪፖርቱ ሲዘጋጅ ሀገራት ካሉበት ደረጃ አንጻር የተለያየ ደረጃ ይሰጣቸዋል።
- የረሃብ ደረጃው ባለፉት 20 ዓመታት በተሰሩት ስራዎች ከ53 በመቶ ወደ 26.1 በመቶ ዝቅ ብሏል። በጣም alarming ከነበረበት ወደ serious ደረጃ ነው የወረደው።
- አሁንም ብዙ ስራ ይቀራል።
- በሀገራችን ያለው የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ሁኔታ ብዙ መሰራት አለበት።
- ሪፖርቱ በየዓመት ነው የሚወጣው። በቀጣይ ወጣቶችን ማዕከል ባደረጉ ስራዎች ትኩረት በማድረግ ለመስራት ያለው ሁኔታ ለማሻሻል ይረዳል።
- በአፍሪካ ያለው ከፍተኛ የወጣት ቁጥር በግብርናው ዘርፍ አሰማርቶ መጠቀም አለመቻል አፍሪካ በምግብ ራሷን እንዳትችል አድርጓል።
- ኢትዮጵያ ውስጥ 70 በመቶ የስራ እድል የሚመነጨው ከግብርና ሆኖ እያለ ያላደገው የግብርና ዘርፍ የሚፈለገውን ያህል የስራ እድል እንዳይፈጠር እንቅፋት ሆኗል።

እንደ ዓለም አቀፉ ሪፖርት በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ለታየው በምግብ እራስን ያለመቻል ችግር ፦
የአየር ንብረት ለውጥ
በየቦታው የሚደረጉት #ጦርነቶች
የኢኮኖሚ መላሸቅ
የኮሮና ወረርሽኝ ዋነኞቹ ናቸው።

በከፍተኛ የምግብ እጥረት እና በረሃብ አደጋ ውስጥ ላሉ ሀገራት መፍትሄ ተብሎ የተቀመጠው መንግሥታት ፦

° ትልቅ አቅም ያላቸው ወጣቶችን ወደ ስራ ገብተው ውጤት እንዲያመጡ ቦታ መስጠት፤

° ብድር ማመቻቸት፤

° ለስራ የሚሆኑ የተለያዩ ስልጠናዎች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል  የሚሉት ይገኙበታል።

በግብርናው ዘርፍ ለመዘናት የቆየው በበሬ ማረስ ተግባር ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማዘመን በመጠንም በአይነትም ከፍ ያለ ምርት ማምረት ካልተቻለ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አሳስቢ ደረጃ ወደ መጨረሻው አስከፊ ደረጃ ልትደርስ ትችላለች ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

⚠️ ኢትዮጵያ በ2022 ሪፖርት ላይ 27.6 በመቶ በማስመዝገብ ከ121 ሀገራት 104ኛ ደረጃ ላይ ነበረች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዚህ መረጃ ምንጮች ፦ ሸገር ኤፍ ኤም ፣  የAlliance 2015 እና የGlobal Hunger Index ድረገጽ መሆናቸውን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM