TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ተጨማሪ የሀሰት ፎቶ⬆️

ይህም ባሌ ጎባ ነው በሚል ህዝብን ለማጋጨት እየተሰራጩ ካሉት ፎቶዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል የሚኖር ህብረተሰብ እየተሰራጩ ያሉት ፎቶዎች ህዝብን ለማጋጨት የተዘጋጁ መሆናቸውን አውቆ ጥንቅቄ ሊያደርግ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ⬇️

"ሃይ ፀግሽ ዛሬ ስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ላይ የከተማው ወጣቶች የመልካም አስተዳደርና የታክስ ጥያቄ በአንዳንድ ስሜትን ከእውቀት ባስቀደሙ ወጣቶች አማካኝነት ወደ ሁከትና ብጥብጥ አምሮቶ የግለሰብ እና የመንግስት ንብረት ላይ ጥቂት የማይባል ጉዳት ሲደርስ የወረዳው ፓሊስ መምሪያ ደግሞ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንደማረጋጋት በወገኖቹ ላይ በከፈተው ተኩስ ወደ ስድስት የሚጠጉ ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ አንደኛው ደግሞ ኮማ ውስጥ እንደሆነ ነው የተሰማው። እባክቹ ከስሜታዊነት እና ከጭፍንነት እንፅዳ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ⬆️

"እባክህን ፀጊሽ ይህን ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ይወቅልን በራሳችን ፖሊሶች አማካኝነት በሕፃንትና ወጣቶች ተኩስ ተከፍቶብናል። በአቢይ እንደመር ዘመን ቀንሰውናል። ምክንያቱ አመራሩ reform ያስፈልገዋል ብሎ ህዝቡ በጫዋ መንገድ ሰልፍ ሳይወጣ የዞኑ ሃላፊ የወረዳው አስተዳዳር በተገኘበት በስብሰባ ጥያቄውን አቅርቦ በትንሽ ግዜ ዉስጥ እናስተካክላን ብለውት 3 ሳምንት ያህል በትዕግስት ቢጠብቅም ምንም አይነት ምላሽ ስላላገኘ ቀጣይ ወዴት አቤት ማለት አለብን በሚለው ጉዳይ ወጣቱና ነጋዲው ስብሰባ አድርጎ ወደ ላይ አካል አቤት ለማለት ኮሚቴ መርጦ በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ ወስኖ ከተበተነ በኋላ የተወሰኑ ልጆች ኣስተዳደሩ ጥያቅያቸውን ችላ ማለቱ ንቀት ስለመሰላቸው ስሜታዊ ሆነው አመራሩን ስም አየጠራ ሌባ አያለ መሄድ ሲጀምር የካባቢው ፖሊስ እላያቸው ላይ ተኩስ ሲከፍት እቤቱ የነበረው ሰው በጠቅላላ ግልብጥ ብሎ ወጣ ፖሊሶች ወደላይም አደለም ቀጥታ መተኮስ ጀመሩ ከ6 በላይ ሰው በጥይት ተመቷል። በኋላ ልዪ ሃይል መጥቶ ለምን ተኮሳችሁ ብሏቸው አረጋግቶ ከወጣ በኋላ እየዞሩ ወጣቱን እያሰሩ ነው። ብዙ ሰው ታስሯል እስካሁን አሁንም በየቤቱ እያሰሱ ነው። ነ ከዳሎቻ ወረዳ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይበቃናል

በየዕለቱ አዳዲስ አጀንዳዎችን እየፈጠሩ ወደ ለውጥ እና ልማት የምናደርገውን ጉዞ እያደናቀፉ ያሉ አካላት አሉ። እነዚህን ቀንደኛ የሀገር ጠላቶች እና የጥፋት ሀይሎች አምርረን ልንታገላቸው ይገባናል።

በቃን! በቃን! በቃን! ለብዙ አመታት በጦርነት ተሰቃይተናል፣ ሰዎች ገብረናል፣ ችግር አይተናል፣ ረሀብ ተፈራርቆብናል፣ ድህነት መጠሪያችን ሆኗል፣ ስማችን በዓለም ተዋርዷል፣ የሌላ ሀገር መሬትን ተመኝተን ባህር ገብተን ሞተናል፣ የበረሀ ሲሳይ ሆነናል፣ እርስ በእርሳችን እየተጋጨን የድህነትን ኑሮ ገፍተናል ወገኖቼ አሁን ግን ይበቃናል!!

.ችግሩ ይበቃናል
.ጥላቻው ይበቃናል
.ተንኮሉ ይበቃናል
.ሞቱ ይበቃናል
.ረሀቡ ይበቃናል
.መፈናቀሉ ይበቃናል
.ለቅሶው ይበቃናል
.ለመኖር መስጋቱ ይበቃናል
.ወጥቶ ለመግባት መፍራቱ ይበቃናል

ኑ ያለፈውን ትተን ለመጪው እንስራ። ኑ ታላቅ እንሁን። ለኛ እንኳን ባይሆን ለምንወልዳቸው ልጆች ስንል ጠንካራ ሀገር ገንብተን እንለፍ። ምንም ባናወርስ ፍቅሯ፣ አንድነቷ፣ ሰላሟ የተረጋገጠች ሀገር እናውርስ!

#ይበቃናል

አመሰግናለሁ!
ፀጋአብ ወልዴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤታመጆር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን እንቅጩን መክረዋል⬇️

“በዘር ማሰብ ከጀመርን ህዝባችንን አንጠቅመውም፣ ፕሮፌሽናል አርሚ መገንባትም አንችልም። ስለ ፖለቲካ ፓርቲዎቹም አያገባንም !…”

”ዘር የሚባል ነገር በመከላከያ እንዳታሰሙን ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ዓፋር፣ ሱማሌና ሌሎች ብሔር ብሎ እዚህ መለያየት አይሰራም።

የፓርቲ ሸኩቻ ለኛ አይመለከተንም እኛ የሚመለከተን ህገ መንግሰቱ መጠበቅ ነዉ ።”

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባህር ዳር⬇️

"ሀይ ፀግሽ እረ እባክህ ለሚመለከተው አሳውቅላን በመልካም አስተዳደር እጦት እና በሙስና መስፋፋት ምክንያት ባህርዳር ውስጥ የምንገኝ ዳቦ ቤቶች በጣም ተቸግረናል።

እንደሚታወቀው መንግስት ዱቄት ከነጋዴወች በአነሰ ዋጋ እንደ የመጋገር አቅማችን እንደሚሰጠን ይታወቃል ነገርግን

1⃣ገብያ ላይ ዱቄት ሲወደድ ከጊዜ ወደ ግዜ የሚሰጠን መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ይቀነስብናል:: ዱቄት ሲረክስ ደግሞ በግድ ብዙ መጠን ያለው ዱቄት ውሰዱ እንባላለን። ካልተስማማን ደግሞ ዱቄት እስከመጨረሻው እንከለከላለን።

2⃣ዱቄት ይሰጣችሀል ተብለን ተጨማሪ ማሽኖች በውድ በብድር ገዝተን ዱቄት በኢፍታዊ መንገድ እየተከለከልን ለኪሳራ እየተዳረግን ነው።

3⃣ተጨባጭ ማስረጃ ባልተገኘበት ለተለያዩ ቅጣቶች እንዳረጋለን።

4⃣ጉዳዩ የሚመለከተው የ ባህርዳር ንግድ መምርያ በዘመድ ፣ በትውውቅ እና የሙስና አሰራር ተንሰራፋቷል።

5⃣ቦታው ላይ የተቀመጡት አመራሮች ህዝብን ለማገልገል ሳይሆን ለግል ጥቅም የተቀመጡ ናቸው በአብዛኛው። ተገልጋይ ይሳደባሉ፣ ሞራል ይነካሉ፣ ያስፈራራሉ።

ስሜ ይቆይልኝ ከባህርዳር ነው። We Demand Justice."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢንጅነር ቅጣው እጅጉ ልጅ ጋር የተረገ ቃለ መጠይቅ⬇️

በአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ በኢንጅነርነት ሲያገለግሉ የነበሩት እና ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የአለማችን ታላላቅ ሰዎች መካከል አንዱ የነበሩት ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ

ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ስለ እሳቸው እና ስራዎቻቸው ይህ ነው የተባለ ነገር ሳይሰማ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ ማናቸው ?ስራዎቻቸው እና የግል ህይወታቸው ምን ይመስል ነበር?

ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ያላቸው ስሜት እና ራዕይ ምን ነበር? በሚሉት እና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት

ሸገር ታይምስ በአሜሪካ ከሚኖረው የመጀመሪያ ልጃቸው ቢኒያም ቅጣው እጅጉ ጋር ቆይታን አድርጋለች፡፡

ሸገር ታይምስ ፡-
ስለ ዶክተር ቅጣው እጅጉ ስብእና በመጠየቅ እንጀምር?

ቢኒያም፡ ስለአባቴ እንድናገር እድል ስለተሰጠኝ በቅድሚያ እግዚአብሄር ይስጥልኝ እላለሁ፡፡

አባቴ ፈሪሀ እግዚአብሄር ያደረበት ሰው ነው፡፡ ፈጣሪን ሳያመሰግን ውሎ አድሮ አያውቅም፡፡

አባቴ ከሁሉ ነገር በላይ ሀገሩን የሚወድ ሰው ነበር፡፡

በሚችለው አቅም ሁሉ ሀገሩን ለማበልጸግና ለሀገሩ ትልቅ ነገር ለመስራት ሲመኝ ነው የኖረው፡፡

እርሱን የሚያውቁት ሁሉ ለሀገሩ የነበረውን ጥልቅ ፍቅርና በጎ ምኞት በሚገባ ያውቃሉ፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- የዶ/ር ቅጣው የስኬቶች መነሻን ብትጠቅስልን?

ቢኒያም፡ የአባቴ ስኬቶች የሚመነጩት ከመሰረታዊ እምነቱ ነው፡፡ አባቴ በፈጣሪ የሚያምንና ፈሪሀ እግዚአብሄር ያለው ሰው ነበር፡፡

ልጅ ሆኜ “መጀመሪያ ፈጣሪን አክብር ቀጥሎ ሀገርህን አገልግል” እያለ ይመክረኝ ነበር፡፡

የእርሱ ለትልቅ ስኬት የመብቃት ሚስጥር የሚመነጨው ከዚህ አመለካከቱ ነው፡፡

አባቴ ልክ እንደማንኛውም ሰው ሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለትልቅ ስኬት የበቃበት ሚስጥር ይሄው ነው፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- ይህን ፍልስፍና ለምንድን ነው ይከተሉ የነበረው?

ቢኒያም፡ አባቴ የተወለደው በከፋ ቦንጋ ነው፡፡ አስተዳደጉም ቢሆን ልክ እንደማንኛውም ሰው ነበር፡፡

ቤተሰቡን በእርሻ ስራዎች እያገዘ ነው ያደገው፡፡ በዚህ የተነሳ ቀለል ያለ አኗኗርን የገነባ ሰው ነበር፡፡

አባቴ ላደገበት የከፋ ህዝብ ጥልቅ ፍቅርና አክብሮት ነበረው፡፡

ስለከፋ ህዝብ ሁሌም ፍቅሩን ከመግለጽ ተቆጥቦ አያውቅም፡፡ የአካባቢውን መሬት ልምላሜ ልክ እንደህዝቡ ሁሉ አድንቆ አይጠግብም፡፡


የቤተሰቤ የዘር ግንድ የሚመዘዘው ከጎንደር ነው፡፡

አያቴ አቶ እጅጉ ሀይሌ በኢጣሊያ ወረራ ወቅት ባበረከቱት ጀግንነት በከፋ አውራጃ የጸጥታ ሹም ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው በዛ አካባቢ መኖር ጀመሩ፡፡

የዘር ግንዳቸው ከአንድ የአጼ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ እንደሚመዘዝ የሚናገሩት አያቴ ጠንክሮ ሰርቶና ታግሎ ትልቅ ቤተሰብ የመመስረት ጠንካራ ፍላጎት ነበራቸው፡፡

አባቴን ዶ/ር ቅጣውን በቦንጋ ነው የወለዱት፡፡

አያቴ ከወለዷቸው ልጆች በተጨማሪም ሁለት ልጆችን በጉዲፈቻ ወስደው ያሳደጉ ጠንካራ የቤተሰብ ሰው ነበሩ፡፡

ብዙ የቤተሰባችን አባላት ወደሀይማኖቱ ያዘነበሉ ነበሩ፡፡

በክህነት ያገለገሉ ቤተቦችም አሉን፡፡

ይህ ሁኔታ አባቴ ፈሪሀ እግዚአብሄር ያደረበት ሰው ሆኖ እንዲያድግ እንዳደረገው መገመት ይቻላል፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- ስለአባታችሁ ማንነት በአደባባይ ለመናገርና ለህዝብ ለማሳወቅ ለምን ዘገያችሁ?

ቢኒያም፡ በቅድሚያ የአባቴ መሞት ቤተሰባችንን በሙሉ ያሳዘነና የጎዳን ጉዳይ ነው፡፡

አጋጣሚው ቤተሰባችንን ከባድ ችግር ላይ የጣለ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከግል ነጻነት ጋር በተያያዘ ወደአደባባይ ወጥተን ትኩረት መሳብ ሁላችንም አልፈለግንም፡፡

በሂደት ከሀዘኑ እያገገምን ስንመጣ ስለአባታችን ለህዝብ ለመናገር ደፈርን፡፡

ሆኖም እርሱ ከነበረው ስምና ክብር አንጻር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚጠይቅ በመረዳት ቁጥብነትን መረጥን፡፡

ስለአባታችን ለመናገር መጀመሪያ የእርሱን ፍላጎት ማክበር ነበረብን፡፡

ይሁን እንጂ በየጊዜው ስለአባታችን የሀሰት መረጃዎች እየወጡ ነው የሚገኘው፡፡

የኔ ጥረትም እውነታውን በማጋለጥ እነዚህን የተዛቡ መረጃዎች ማስተካከል ነው፡፡

በተለያዩ መንገዶች ራሳቸውን የአባቴ ቤተሰብ እንደሆኑ የሚያቀርቡ ሰዎች ለገንዘብ ሲሉ የተለያዩ መረጃዎችን ስለቤተሰባችን እየነዙ ይገኛል፡፡

በዚህ መንገድ ሊጠቀሙ ያሰቡ ሁለት ወንጀለኞች ሌላው ቀርቶ የኔን ስም በመጠቀም ጭምር ስለአባቴ የሀሰት ፊልም ሰርተው አሰራጭተዋል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች ወንጌል ሰባኪ የሀይማኖት ሰዎች ነን የሚሉ ጭምር ናቸው፡፡

ስለአባታችን የፈጠራ ፊልም ሰርተው እያስተዋወቁ ገንዘብ ሲሰበስቡ ቆይተዋል፡፡

እነዚህ ሰዎች ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ላለፉት ሁለት አመታት ጥረት አድርገናል፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ጌታቸው መካሻን ጨምሮ፣ የሀይማኖት አባቶችንና

የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ሽማግሌዎችን እነዚህ ሰዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ ቤተሰባችን በሽምግልና ልኳል፡፡

ይሁን እንጂ ግለሰቦቹ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡

አሁን ግን ግለሰቦቹን በህግ ወደመፋረድ ልንገባ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በአባታችን ስም እየነገዱ ነው፡፡ የቤተሰባችንንም ስም እያጎደፉ ነው፡፡

አንዱ እንደውም እዛው አዲስ አበባ ተቀምጦ ነው ይህን ስለአባታችን የተቀነባበረ የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩት፡፡

በዚህ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን ሰዎች እንዲቃወማቸው ነው የምንጠይቀው፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- ዶ/ር ቅጣው እጅጉ ለኢትዮጵያ ይመኙ የነበረው ምን ነበር?

ቢኒያም፡ ይህ ለእኔ ለመመለስ ከባድ የሆነ ጥያቄ ነው፡፡

አባቴም ሆነ ቤተሰባችን በእምነት የታነጸ ነው፡፡

የእርሱ ምኞትና ተስፋ ከዚህ መሰረታዊ አስተሳሰብ የተቀዳ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ከገነቡና መስዋእት ከከፈሉ የቀደሙ ነገስታት ራእይ የሚነሳ ጭምር ነው፡፡

አባታችን ሀገሩ የበለጸገችና ጠንካራ አንድነትን የፈጠረች ሀገር እንድትሆን ነበር የሚመኘው፡፡

“አይምሮአቸው በቅኝ አገዛዝ ስር ከወደቁ ሰዎች ራስህን አርቅ፤ እነርሱ የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላቶች ናቸው” እያለ ይነግረኝ ነበር፡፡

አባቴ ኤርትራና ኢትዮጵያ ታርቀውና ተዋህደው ማየት እንደሚመኝ በአደባባይ ከመግለጽ ተቆጥቦ የማያውቅ ቢሆንም

በግሉ ግን ከዚህም አልፎ ሶማሊያና ጅቡቲ ጭምር ከኢትዮጵያ ጋር እንዲዋሀዱ ይፈልግ ነበር፡፡

ይህ የኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መዋሀድ ደግሞ ከራስዋ አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ጭምር መጠናከርና ሰላም ያመጣል ብሎም ያምን ነበር፡፡

አጼ ሀይለስላሴ ለኢትዮጵያ ወይም የቀድሞው የጋና መሪ ክዋሚ ንክሩማ ለአፍሪካ ይመኙ እንደነበረው ሁሉ አባቴ ዶ/ር ቅጣውም ለሀገሩ ኢትዮጵያ በጎ ነገሮችን ነበር የሚመኘው፡፡

አባቴ በሀገር ቤትም ሆነ በውጪ የሚኖሩ አፍሪካዊያን ነጻነታቸውን እንዲያረጋግጡና የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲገኙ ኢትዮጵያዊያን መታገል ይኖርብናል ይል ነበር፡፡

ሌላው ቀርቶ አፍሪካ (Africa) የሚለውን ስም ሲጠቀም ሆን ብሎ (Afrika) እያለ “C” ፊደልን በ “K” በመተካት ነበር የሚጠቀመው፡፡

ይህን የሚያደርገው ደግሞ ከተስፋና ቃል በዘለለ ለአፍሪካ ተግባር እንደሚያስፈልግ ለማመላከት ነበር፡፡

አባቴ ከጥቁር አሜሪካዊያን ማህበረሰብ ጋር ከመነጋገርና ከመወያት በተጨማሪም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በመዞር ስለአፍሪካዊነትና ስለጥቁሮች አንድነት መጠናከር የተለያዩ ሀሳቦችን አበርክቷል፡፡

በኬንያ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኮንጎ፣ ካሜሩን፣ ሴራሊዮን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያና በብዙ ሀገሮች ዞሯል፡፡

በነዚህ ሀገራ
ት በተገኘባቸው መድረኮችና ምክክሮች ሁሉ የአፍሪካዊነትን መንፈስ ከፍ የሚያደርጉ ሀሳቦችን አበርክቷል፡፡

አፍሪካዊያንና ጥቁሮች በንግድና ኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲያስተሳስሩ፤ በትምህርትና የስራ እድል በመፍጠር እንዲደጋገፉ ግንኙነት ለመፍጠር ጥረት አድርጓል፡፡

አባቴ አፍሪካን አንድ በማድረጉ ረገድ ኢትዮጵያዊያን ግንባር ቀደም ሚና እንዲኖራቸው ይፈልግ ነበር፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- የአባትህን የትምህርት ስኬቶች ብትዘረዝርልን?

ቢኒያም፡ አባቴ ከባህር ዳር ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ነበር የመጀመሪያ ዲግሪውን በግብርና ሜካኒካል ምህድስና ዘርፍ ያገኘው፡፡

በጊዜው በትምህርቱ ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱ ከአጼ ሀይለስላሴ እጅ ሽልማት ለመቀበል የበቃ ሲሆን እርሱ ያመጣው ውጤትም በኮሌጁ ለ 30 አመታት ሪኮርድ ይዞ ነበር፡፡

የመጀመሪያ ፍላጎቱ በትምህርቱ ገፍቶ በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ የተዋጊ ጀት አብራሪ መሆን ነበር፡፡

ይሁን  እንጂ ወደ ጃፓን በማቅናት በሄሮሺማ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ምህንድስና በዲግሪ ከመመረቅ በተጨማሪ በኦሳካ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በቋንቋና ኢኮኖሚክስ ዲፕሎማ ለመቀበል በቅቷል፡፡

በጃፓን ትምህርቱን ሲከታተል በዘጠኝ ወራት ነበር ጃፓንኛን አቀላጥፎ መናገር የለመደው፡፡

በዚሁ ጊዜ በጃፓን ካገኛቸው ጥቁር አሜሪካዊያን ጋር ወዳጅነት በመፍጠሩ ወደአሜሪካ ካሊፎርኒያ እንዲመጣ የመጋበዝ እድልን አገኘ፡፡

አባቴ ከነዚህ ጥቁር አሜሪካዊያን ጋር የበለጠ ያቆራኘው በፓን-አፍሪካዊነት እንቅስቃሴ ላይ የነበራቸው የጋራ አቋም ነበር፡፡

ከጥቁር አሜሪካዊያኑ መካከል “እማማ አለን” የተባሉ የአንዱ እናት አባቴን ለማስተናገድ በመፍቀዳቸው ወደ ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ ለመምጣት አስቻለው፡፡

በአሜሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር ሲያመለክትም ከሎስአንጀለሱ ኖርትሮፕ ዩኒቨርሲቱ ሙሉ የነጻ ትምህርት እድል ስላገኘ በዛ ገብቶ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን እንዲሁም በኤሮናቲክ ምህንድስና የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን ለመከታተል በቃ፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- በስራው መስክ ያገኟቸው ስኬቶችንም ብትዘረዝርልን?

ቢኒያም፡ ከአውሮፓዊያኑ 1977-1981 ድረስ በካሊፎርኒያ ፓሳዴና በሚገኘው የአሜሪካ ጠፈር ምርምር ማእከል ናሳ የጀት በረራ ቤተሙከራ ውስጥ ሲሰራ ነው የቆየው፡፡

በዛ ማእከል አባቴ የጠፈር መብረሪያ አካላትና ስርአት የስራ ክፍል ውስጥ በዋና መሀንዲስነት ሰርቷል፡፡

ይህ የናሳ ማእከል ተቋሙ ወደጠፈር የሚልካቸውን ሮኬቶችና ሳተላይቶች በዋናነት የሚገነባበት ማእከል ነው፡፡

በዚህ ማእከል ውስጥ አባቴ ለጠፈር ተልእኮ የሚውሉ ሁለት የሜካኒካል ስራዎችን ዲዛይን ሰርቷል፡፡

በሌላም በኩል አፖሎ 11 በተባለው የናሳ የጠፈር ተልእኮ ፕሮጀክት ላይም ተሳትፏል፡፡

በናሳ ውስጥ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽዎ ራሳቸው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጂሚ ካርተር ለአባቴ የምስጋና ደብዳቤ ጽፈውለታል፡፡

ከፈረንጆቹ 1982 ጀምሮ ደግሞ ወደግል ስራ በመግባት ኤክሴልቴክ ዳይናሚክስ የተባለ የቴክኖሎጂ ድርጅትን በሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ አቋቋመ፡፡

ይህ ድርጅትም የተለያዩ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ለአሜሪካ መንግስት የሚሸጥ ሲሆን በተለይ በሳንዲያጎ የሚገኘው የአሜሪካ ባህር ሀይል ዋና ደንበኛው ነበር፡፡

ይህ ድርጅት እስከ አውሮፓዊያኑ 1985 ድረስ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ድርጅቱን እኔም በልጅነቴ አውቀው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በ 1986 ላይ አባቴ በሮክዌል ድርጅት ውስጥ መስራት ጀመረ፡፡

ይህን ድርጅትም አውሮፕላን አምራቹ ግዙፉ ቦይንግ ኩባኒያ ሲጠቀልለውም በዛው በመቀጠል እስከ 2005 ድረስ በቦይንግ ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በሮክዌልም ሆነ በቦይንግ ለአሜሪካ መከላከያ የሚውሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመስራት ቆይቷል፡፡

ናሳም የነዚህ ተቋማት ደንበኛ በመሆኑ የተለያዩ የጠፈር ምርምር ቴክኖሎጂዎችን በነዚህ ተቋማት ውስጥ ለመስራት ችሏል፡፡

አሜሪካ ዛሬ ላይ የአለም ወታደራዊ ሀይል ቁንጮ እንድትሆን ካበቋት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውስጥ በስታር ዋርስ ፕሮጀክት በተገነባው የካይኔቲክ ኪል ቴክኖሎጂ ግንባታ ላይ አባቴ ተሳትፎ ማድረጉን በምሳሌነት መጥቀስ እችላለሁ፡፡

ከኢትዮጵያዋ ቦንጋ የወጣው ዶ/ር ቅጣው ከሀገሩ አልፎ ሀያሏን አሜሪካንና አለምን የለወጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በራሱ ድርጅትና በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ለመገንባት የበቃ ተቆጥሮ የማያልቅ ስኬቶችን ያስመዘገበ ነው ብል አባቴን ያጋነንኩት አይመስለኝም፡፡

በሮክዌልና በቦይንግ ቆይታው ከአንጋፋ ጠፈረተኞችና ጠፈር ተመራማሪዎች ጋር ለመስራትና ለመገናኘት በቅቷል፡፡

ቡዝ አልድሪን፣ ኒል 
አርምስትሮንግን ጨምሮ በተለይ በማርስ ምርምር ላይ ከሚሰሩ እውቅ የጠፈር ምሁራን ጋር ሰርቷል፡፡

እኔም ጭምር በልጅነቴ ቡዝ አልድሪንን ለማወቅ እድሉን አግኝቻለሁ፡፡

በተለይ ፕሉቶ የተባለችዋን ፕላኔት በማግኘት ስሙ የሚጠራው ሳይንቲስት ዶ/ር ክላይድ ቶምባግ የአባቴ የቅርብ ወዳጅ ነበር፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ጌታቸው መካሻ ቦይንግን በመቀላቀል ከአባቴ ጋር የስራ ባልደረባ ለመሆን ችለዋል፡፡

አባቴ በተለይ ጂፒኤስ እየተባለ በሚጠራው በግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም የአቅጣጫ መጠቆሚያ ቴክኖሎጂ ግንባታ ላይ ጉልህ ድርሻ ነበረው፡፡

አባቴ ለከወናቸው ለነዚህ ሁሉ ረቂቅ ስራዎችና የስኬቶቹ ምንጭ መንፈሰ ጠንካራ ኢትዮጵያዊነቱና የፈጣሪ እገዛ ነበረበት እላለሁ፡፡

የአባቴ ዋና ምኞት ከሁሉ በላይ ለሀገሩ መስራት ነበር፡፡ ቦኢንግ ሲሰራ ትራንስ ቴክ ኢንተርናሽናል የተባለ የግሉን ፕሮጀክት ጀምሮ ነበር፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ስራም ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ማቅረብ ነበር፡፡

አባቴ እስኪያርፍ ድረስም ይህ ድርጅት ስኬታማ ሆኖ መዝለቅ ችሏል፡፡

የድርጅቱ ድህረ ገጽ እስከዛሬም ያለ ሲሆን ስራዎቹንም ከዚሁ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

ሸገር ታይምስ ፡- አባትህ በህይወታቸው የገጠሟቸው ፈተናዎች ምን ነበሩ?

ቢኒያም፡ አባቴ ብዙ ስኬቶችን በህይወቱ እንዳገኘ ሁሉ ፈተናዎችም አጋጥመውታል፡፡

አሜሪካ ለእርሱ ጣፋጭም መራርም ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ የገጠሙትን መሰናክሎች የሚቀበልበትና ለማለፍ የሚያደርገው ጥረትም በጣም የሚደነቅ ነው፡፡

አሜሪካዊቷ ወላጅ እናቴ ማለትም የአባቴ ባለቤት በብዙ መንገድ አባቴንና እኔን ጎድታናለች፡፡

ከቤተሰቦቿ ጋር ተመሳጥራ ብዙ ግፍ ውላብናለች፡፡

በፈረንጆቹ 1989 በአንድ አጋጣሚ አባቴ ላይ የመግደል ሙከራ ሁሉ ደርሶበታል፡፡

ከ 1980-1990 ባሉት አመታት እናቴ የአሜሪካንን ፍትህ ስርአት ክፍተት ተገን በማድረግና የቆዳ ቀለማችንን በመጠቀም ህይወታችንን ስትበጠብጥና ዘረኝነት ስትፈጽምብን ነው የቆየችው፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ግፊት የተነሳ ነበር አባቴ የከፈተውን ኤክሴል ቴክ ዳይናሚክስ የተባለውን ድርጅቱን ለመዝጋት የተገደደው፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ነበር እኔና አባቴ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድ ላይ ለመሆንና ለመቀራረብ የቻልነው፡፡

እኔም ሆነ አባቴ ባሪያ ተብሎ መሰደብና የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ መሆን እንዴት እንደሚለበልብ በዛ ወቅት አይተናል፡፡

“ልጆቹን አግቶ ወደ እስላም ሀገር ካልወሰድኩ የሚለው አፍሪካዊ መጣ” ብሎ አንድ የፍርድ ቤት ዳኛ ሲናገር ከአባቴ ጎን በችሎት ላይ ቆሜ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡

ያ ዘረኛ ዳኛ ክርስቲያን አፍሪካዊ መሆናችንን እያወቀ ነበር በዘረኛ ምላሱ እንደዛ የተናገረን፡፡

አባቴ ለእንደዚህ አይነቱ ጥቃት እጁን የሚሰጥ ሰው ግን አልነበረም፡፡

የፍርድ ቤት ጭቅጭቁን ለመርታትና ፍትህ ለማግኘት
ሲል በሎስ አንጀለሱ ሎዮላ የህግ ትምህርት ቤት ገብቶ ህግን እስከማጥናት ደርሷል፡፡ ለጥናት ሲሄድ ብዙ ጊዜ አብሬው እሄድ ነበር፡፡

አንዳንዴ ቤተመጽሀፍት ውስጥ በሚያነብበት ወቅት እግሩ ላይ እንቅልፍ ይጥለኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ከዚህ ሁሉ በኋላ እኔን ለማሳደግ ሙሉ መብት በህግ አገኘ፡፡

ከአንድ አመት ተኩል ተጨማሪ ሙግት በኋላ ደግሞ ታናሽ ወንድሜንና እህቴን የማሳደግ መብቱን በችሎት በመርታት አገኘ፡፡

ይህ ሁሉ የችሎት ሙግት 11 አመታትን ያስቆጠረ አስቸጋሪ ሂደት ነበር፡፡

በዚህ ወቅትም ከአባቴ ስለኢትዮጵያ ብዙ ነገሮችን ለመማርና ለማወቅ ችያለሁ፡፡

በዚህ ወቅት አባቴ ከእውቀቱና ከህይወት ልምዱ ብዙ ነገሮችን እንድቀስም አድርጎኛል፡፡

በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ማእከል ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን አባቴ ሲረዳና ሲደግፍ አይቻለሁ፡፡

ማእከሉ በገንዘብ እንዲጠናከር ገቢ በማሰባሰብ ከመደገፍ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን የህግ ድጋፍ እንዲያገኙ ይረዳም ነበር፡፡

ከራሱ ኪስ ገንዘብ እያወጣም ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ይደግፍ ነበር፡፡

የሎስ አንጀለስ ከተማ አስተዳደር ፌርፋክስ በሚባለው ኢትዮጵያዊያን በስፋት በሚገኙበት አካባቢ ትንሽቱ ኢትዮጵያ የምትባል መንደር እንድትመሰረት ፈቃድ እንዲሰጥ አባቴ ያለሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ነበር፡፡

ከሁሉ በላይ ከአባቴ የማይረሳኝ ምሽት ላይ በካሊፎርኒያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት አካባቢ የምናደርገው የእግር ጉዞ ነበር፡፡

በነዚህ አስቸጋሪና ጨለማ አመታት አባቴን ጠልቄ ለማወቅና የበለጠ ለመውደድ እድል አግኝቻለሁ፡፡ የእርሱ ትልቅ ጥንካሬ ለኔም ጥንካሬን ፈጥሮልኛል፡፡

# ሸገር ታይምስ ፡- ዶ/ር ቅጣው እጅጉ በምንድን ነው የበለጠ የሚታወሱት?

◾️ቢኒያም፡ አባቴ ከእኔም ሆነ ከኢትዮጵያዊያን ብዙ ይጠብቅ ነበር፡፡

አንድ ኢትዮጵያዊ መላበስ ይገባዋል የሚለውን ስብእና ሁሌም ይነግረኝ ነበር፡፡

“ኢትዮጵያዊ ፈጣሪን የሚፈራና ሀገሩን የሚወድ ሰው መሆን አለበት፡፡

ኢትዮጵያዊ ቅኔ አዋቂ፣ ጀግናና ጠንካራ ሰው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ለሁሉም ነገር ዝግጁ የሆነ ሰው ነው” በማለት መንፈሰ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ እንድሆን ይመክረኝ ነበር፡፡

አባቴ በኢትዮጵያዊ ስርአት ነው ኮትኩቶ ያሳደገኝ፡፡ ጥብቅ ስርአትን በቤታችን እንድንከተል ያደርግ ነበር፡፡

በሳምንት ሁለቴ ወይም ሶስቴ 
ቤተክርስቲያን እንድንሄድ ያደርግ ነበር፡፡

የተከለከሉ ምግቦችን አሳማ ወይም የባህር አውሬዎችን በፍጹም አንበላም፡፡ ጾም ስንጾም ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡

እኔና አባቴ በኢትዮጵያ የሚወደዱትን አቃጣይ ምግቦችን አፍቃሪ ነበርን፡፡

ቃሪያና በርበሬ ነፍሳችን ነው፡፡ በትንሽነቴ ከበርበሬ እቃ ውስጥ በርበሬ ስቅም የተያዝኩበትን ጊዜ አስታውሳለሁ፡፡

ኢትዮጵያዊያን እንደሚያፈቅሩት ሁሉ እግር ኳስን ከልባችን እንደግፋለን፡፡

በየሄድንበት ሁሉ አባቴ ከሁሉ በፊት የኢትዮጵያ ስም በክብር እንዲነሳ ነበር የሚፈልገው፡፡

ሀገራችንን እንድንወድና እንድናስከብር ነበር የሚፈልገው፡፡ አባቴ መታወስ ያለበት ለፈጣሪና ለሀገሩ ባለው ጥልቅ ፍቅር ለትልቅ ደረጃ የበቃ ሰው ሆኖ ነው፡፡

#ሸገር ታይምስ ፡- በማጠቃለያችን ላይ የምትጨምረው ነገር ካለ እድል እንስጥህ?

▪️ቢኒያም፡ ከናሳ ሰዎችና ከአባቴ የቀድሞ የስራ ባልደረቦች ጋር በቅርብ ጊዜያት ግንኙነት እየፈጠርኩ እገኛለሁ፡፡

በቅርቡም ልገናኛቸው ቀጠሮ ይዣለሁ፡፡

ከዛ ደግሞ ከቦይንግ ጋር በመነጋገር ስለአባቴ ስራዎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እቅድ ይዣለሁ፡፡

የአሜሪካ መንግስት ጥብቅ ሚስጥር አድርጎ የያዛቸው የአባቴ ስራዎች ይኖራሉ፡፡

እነዚህን ስራዎቹን አሁን ላይ ለማግኘት የምችልባቸው እድሎች መኖር አለመኖሩን እያጣራሁ እገኛለሁ፡፡

ከዚህ ቀደም የማናውቃቸው ስራዎቹን እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

በተረፈ ግን ለአሁኑ በዚሁ ማጠቃለል እፈልጋለሁ፡፡

እናም ስለአባቴ ስለ ደ/ር ቅጣው እጅጉ የህይወት ታሪክና ስራ እንድንናገር ሸገር ታይምስ ላመቻቸው እድል በእጅጉ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

በቅርብ ጊዜ ተመልሰን እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ፡፡

*ከሸገር ታይምስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይነበብ⬆️ከኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ልጅ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከራያ ቆቦ⬆️

በራያ ቆቦ ወርዳ 021 ቀበሌ ቡሆሮ ዉሓ ፕሮጀክ  ለቀበሌው ከ 8 ሽ በላይ ቤተሰብ መሪ ያለበትን ለዘመናት በውሓ ችግር የተጎዳ ህዝብ ነው ።ከችግሩ ለማውጣት መንግስት በሰኔ 2007 ዓ/ም 14 ሚሊዮንብር  በጀት በመመደብ ለኮንትራክተር ነብዩ ዳኤል የዉሃ ፕሮጀክት እንዲሰራ ዉል መስጠቱ ይታወቃል።

በ ፕሮጀክቱ የተስሩ የዉሓ ማደያ ብዛት 13 ሲሆኑ ኮንትራክተሩም አቋርጦ ወጥቷል። ለ2ዓመት ንብረት የጠበቁ ስዎችም ያለ ደሞዝ ቀርተዋል። እስከ አሁን ድረስ ውሓው የውሓ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። ነዋሪዎችም ወንዝ ወርደው የወረፋውን ጊዜ ሳይጨመር ከ2ስዓት በላይ ይጓዛሉ ።በ ሸክም የአሕዮች ጀርባ ተልጧል ግመሎች በማይመች መንገድ እየወደቁ ተቸግረዋል። ከብቶችና ሰዎች የተገነባውን ዉሓ አልባ ግንባታ በመመልከት ላም አለኝ በሰማይ ሁኖባቸዋል።

ገራሚው ይህ ብቻ አይደልም እያንዳንዱ ቤ/መሪ 45 ብር እንዲያዋጣ በራያ ቆቦ ወረዳ ውሃ ና መስኖ ጽ/ቤት  ሕዝቡን 81000 ብር ተቋራጩ የበላውን ክፈሉና እንደገና ይሰራላችኋል መባላቸው ነው። ሕዝቡም ከችግሩ የተነሳ እንከፍላለን ግን መጀምሪያ ዉሃው አገልግሎት መስጠቱ ተሞከሮ እንየው ቢሉ መጀምሪያ ካልከፈላችሁ አይሰራም መባሉ ነው።
ለማደያ የተሰሩት ጎርፍ ሲደልልባቸው ሪዘርበሮች ደግሞ የእንስሳት መዋያ ሁነዋል።

ለፕሮጀክቱ የመጣ የብረት ፓይፕ በጎማ ቲዩብ ተቀይሯል። ኩንትራክተሩ ከወረዳ ባለስልጣን ጋ ሽርክ ስለአልው እንጅ ወረዳ ዉሓ ሃብት ምያዝ ይችል ነበር ይላሉ።

ይህ ችግር ይመለከተኛል፤ የህዝብ ጉዳት የኔም ጉዳት ነው የሚል፤ ሁሉ ለሚመለከትው ቢያቀርብልንና ችግራችን ቢፈታ ይላሉ የቀብሌው ነዋሪዎች።

©De
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር እያደረጉ ያሉት ውይይት ቀጥሏል።

ፍቶ ©FANA
@tsegabwolde @tikvahethiopia