TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ⬆️ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ ሴቶች ያልተሸከሙት ጉድ የለም። በሆዳቸው ፅንስ፣ በጀርባቸው ልጅ፣ በትከሻቸው ደግሞ እንደ እኔ ያለ ሰነፍ ባል ተሸክመዋል"

▪️ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ◾️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠንቀቁ⬆️የባሌ ጎባውን ግጭት ተንተርሶ የተለያዩ ሀሰተኛ እና ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩ ፎቶዎች እየወጡ ነው። የምትመለከቱት ፎቶ ባሌ ጎባ አይደለም ፎቶው በአንድ ወቅት ማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ ከነበረ ግጭት የተወሰደ ነው።

*ወጣቶቻችን ለህዝቡ ያለውን ሴራ አሳውቁ ሰዎች በተሳሳተ መልኩ ወደ ግጭት እንዳይገቡ አድርጉ።

*ሀሰተኛ ገፆችን ልቀቁ እንዲሁም ግጭት ለማባብሱ ግለሰቦችን ጓደኛችሁ አታድርጉ።

ሰላማችንን እኛው እንጠብቅ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from BORN TO WIN
#ኦፒያ #የሠርግ #ካርድ
#ባህላዊ እና #ዘመናዊ
ስልክ
0911 19 59 18
0961 33 26 04
አድራሻ 1.መርካቶ ጣና ገበያ 2ኛ ፎቅ ቁ.58
2.መገናኛ ስለሺ ስህን ህ. 1ኛ ፎቅ ቁ.107

ስለምትጎበኙን እናመሰግናለን
ይቀላቀሉን @Opiacard
አፋልጉኝ⬆️

1ኛ. ተፈላጊ ሻለቃ ብስራት ፍልፍሉ የትውልድ ቦታው አምቦ አከባቢ ልዩ ስሙ ቶኬ ኪዳነ ምህረት ይባላል። የታሰረበት ጊዜ በ መጋቢት ወር 1985 ዓ.ም ሲሆን የታሰረበትም ቦታ ማእከላዊ እስር ቤት አዲስ አበባ ነው።

2ኛ. ተፈላጊ ሻለቃ ክፍለ ማርያም በኩረ የትውልድ ቦታ አርሲ ቦቆጂ ሲሆን የታሰረበት ጊዜ በ መጋቢት ወር 1985 የታሰረበት ቦታ ማእከላዊ እስር ቤት አዲስ አበባ። በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ ስለማይታወቅ በዚህ ወቅት ብዙ እስረኞች እየተፈቱ ስለሆነ ስለነሱ ሁኔታ ማለትም ሻለቃ ብስራት ፍልፍሉ እና ሻለቃ ክፍለ ማርያም በኩረ የሚያውቅ ካለ ለፈላጊ ቤተሰቦቹ ለሻምበል ወዳጅ አበበ በ 0910019519 ወይም ደግሞ ለ ይበልጣል ወዳጅ በ 0929274461 በመደወል አይተናቸዋል ወይም የሚያቁትን መረጃ ቢያደርሱን እንማፀናለን ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው!

ተጨማሪ መረጃ :- ቀደም ሲል መስከረም 8 1989 በወጣው ጦማር ጋዜጣ ላይ በ ገፅ 4 " ሁለገብ መድረክ ማስታወቂያ ማስታወቂያ ማስታወቂያ " በሚለው ርዕስ ስር ስም ዝርዝራቸው እና ፎቶዎቻቸው ከተገለፁት እስረኞች መካከል የ ሻለቃ ብስራት ፍልፍሉ ፎቶግራፍ ይገኛል ። ሆኖም በወቅቱ ስለ እስረኞቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በሰጡት መልስ " መንግስት የሚያውቃቸው የታሰሩ ሰዎች አሉ ከተባለ የታሰሩበትን ቦታ ጠቁሙን እና እናስተካክላለን" የሚል መልስ ሰጥተው ነበር ይሁን እንጂ ጉዳዩን በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ስለ እስረኞቹ እስከ አሁን የሚታወቅ ነገር የለም።
እባኮትን ሼር በማድረግ ይተባበሩን!!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👩‍🎓ይድረስ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች👨‍🎓

#ክፍል2

🔍🔍ስራ ስትፈልጉ

📒📒የቃል ፈተና(Interview) ስታደርጉ ማስተዋል ያለባችሁ ቁምነገሮች!

አሁን ባለንበት በዚህ በሰለጠነ ዘመን በ21ኛው ክ/ዘ እኛ ሀገር መረጃ ማግኘት ውቅያኖስ ውስጥ መርፌ እንደመፈለግ ያህል ከባድ ነው።አድካሚ ነው።እናም በዚህ ምክንያት በስራ ፍለጋ ላይ እና Interview ሲደረግ ያስተዋልኳቸው ከራሴም፣ከብዙ ሰዎችም በተደጋጋሚ ያስተዋልኳቸውን መሰረታዊ ስህተቶች እንደተሞክሮ ላካፍላችሁ ወደድኩ።ሁለቱ ጉዳዮች ሁላችንም ት/ት አጠናቀን ከተመረቅን በኋላ የምንጋፈጣቸው አይቀሬ ፈተናዎች ናቸው።እኔም እስኪበቃኝ ታሽቼባቸዋለሁ።ከተራ መኪና ማጠቢያ ድርጅት እስከ ትላልቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች Interview ተደርጌአለሁ።
አንዳንዴ ተስፋ ሰጪ ይሆናል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚፈትን ይሆናል።ያም ሆነ ይህ መገንዘብ ያለብን ነገር "There is no such a thing as a free lunch" እንደሚሉት ነጮቹ ወይም የእኛ አባቶች "እንበለ ሕማም ወጻም ኢይትረከብ ጸጋ" እንደሚሉት ሳይደከም እና ሳይፈተን የሚወጣልን እንጀራ የለም።ትንሽ መታሸትን (ups and downs) ይጠይቃል።(ይህ ግን የተደላደለ እና ባለሀብት የሚባል ቤተሰብ ያላቸውን ምሩቃን አይወክልም።) የህዝብ ብዛት በፍጥነት እየጨመረ ሰለሆነ የስራ እና ስራ ፈላጊው (supply and demand) አልተመጣጠነም።ይህም የሰው ኃይል ገበያው ላይ ብዙ ፉክክር እንዲኖር እያደረገ ነው።
ባጭሩ ካስተዋልኳቸው በጣም common እና ብዙዎቻችን የምንሸወዳቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።

🔍🔍ስራ ስትፈልጉ
CV is mandatory!! ፦መጀመሪያ መደረግ ያለበት ነገር cv ማዘጋጀት ነው።CV( curriculum vitae) ማለት ራሳችሁን እና የትምህርት ደረጃችሁን የምተገልጹበት ከ2 ገጽ ያለበለጠ info ነው።ለዚህ google ላይ ከsample ጋር ማግኘት ትችላላችሁ።የሚቀጥራችሁ ድርጅት መጀመሪያ የሚያየው cv ስለሆነ ያልተጋነነ፣ያልበዛ፣ትክክለኛ info የያዘ መሆን አለበት።

አካላዊም ስነ ልቦናዊም ቅድመ ዝግጅት፦ስራ መፈለግ ራሱ ስራ እየሆነ ሰለሆነ ለነገሮች መዘጀት ይገባል።በነገሮች ማዘንና ተስፋ መቁረጥ ወይም ብዙ expect ማድረግ አግባብ አደለም።ሁሉንም እንደአመጣጡ ማስተናገድ ይገባል።ወጣም ወረደ የፈለገ ቢያታግላችሁ ዘግይቶም ቢሆን የምትፈልጉት ነገር እጃችሁ መግባቱ አይቀርም። It's a matter of #Effort & #Time.

የህትመት ውጤቶችን፦
ጋዜጣ፣መጽሔት፣ብሮሸር
+የሀገር ውስጥ ድረገጾች
+የሀገር ውስጥ ስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች
+የድርጅቶች የግል ድረገጾች
+የራድዮ ፕሮግራሞች
+የሰሌዳ ማስታወቂያዎች....እነዚህ በብዛት ስራ የምታገኙባቸው አድራሻዎች ናቸው።በጣም በንቃት እነዚህን መከታተል ይጠቅማል።ጊዜአችሁን የምታሳልፉበትን ቦታ ና ጉዳይ በማስተዋል ለዩ።በረሃብ ሰአት በግ ስጋ ቤት በር ላይ፣ ውሻስ ግጦሽ ምስክ ላይ ምን ይሰራሉ🤔???ለማለት የፈለኩት አሁን ኃላፊነት የምትሸከሙበት ጊዜ ነው፤እናም ብዙ ጊዜአችሁን ስራ ጋር ከተያያዙ ነገሮች ጋር ማዋል ይግባል።ፓርቲ፣ክለብ፣መዝናናት፣ከሰፈር ልጆች ጋር ቁጭ ብሎ ሙድ መያዝ...ሁሉም ይደረስበታል።

የስራ ማስታወቂያአንዳንድ ድርጅት cv አትስጡ። ብዙ ሰዎች 100 ኮፒ cv አድርገው የከተማዋን ድርጅት ሁሉ ያድሉታል። It won't work that way!!! Dust bin ውስጥ ነው የሚጨመረው።የስራ ማስታወቂያ ላወጣ ድርጅት ብቻ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቀን submit ማድረግ።

ያገኛችሁት ስራ የሰለጠናችሁበት እንኳን ባይሆን ሞክሩት።አንዳንድ ድርጅቶች ማንኛውንም አይነት ወይም ተዛማች ምሩቃንን ይቀበላሉ።ከዚህ በፊት እንዳልኩት ያገኛችሁትን ስራ አትግፉ።አንዳንዴም ባንዴ ብዙ ቦታዎች ተቀባይነት ታገኙ ይሆናል።በዚህ ጊዜ ወደተሻለው መሄድ ነው።መረጃ ለሌሎች ማካፈልም መልካም ነው።እናንተ ካልተሳካላችሁ ለሌላው አሳውቁ፤ይሞክሩት።


📒📒፦Interviw (የቃል ፈተና)
Interview ያላችሁ ቀን(ብዙ ጊዜ ጠዋት ነው) በቀዝቃዛ ውሃ ሻወር መውሰድ፤ምግብ በደንብ መመገብ(ተፈጥሯዊ የሆነ መደናገጥ ስለሚኖር ሰውነታችሁ ዝለት እንዳይሰማው ምግብ ወሳኝ ነው)፤ ንጹህ ልብስ መልበስ።ምንም አይነት መደናገጥ እና ስጋት አያስፈልግም።

Protocol/አለባበስ ይታያል።ሊቀጥራችሁ ቃለመጠይቅ የሚያደርጋችሁ አካል ብዙ ሀብቱን ፈሰስ ያደረገበትን፣የደከመበትን ድርጅት እንድትሰሩበት፣ትርፋማ እንድታደርጉት ስለሆነ የሚፈልጋችሁ ለዛ ኃላፊነት ከወዲሁ ነው የሚገመግማችሁ።"አንድ በአለባበስ፣ በንጽህና ራሱን ያልጠበቀ ሰው እንዴት ድርጅቴን በአግባቡ ይመራልኛል?!" የሚል ትርጉም ይሰጠዋል።አስታውሳለሁ...ለinterview ተጠርቼ ጫማዬን በቫዝሊን ጠርጌ የሄድኩበትን😊።በጣምም ደሞ ለፋሽን ሾው የምትሄዱ እስክትመስሉ መጋነን የለበትም። Just be gentle።ማካፕም በልኩ፤ሽቶም በልኩ።እነዚህ ሲበዙ የምትጠየቁበትን ክፍል ይንጠውና እናንተን ለመገላገል ጠያቂ ቶሎ ያሰናብታችኋል።

በራስ መተማመን ያለው አነጋገር(confidence)። Interview ስትደረጉ እናንተ ስራውን እንደምትፈልጉት ሳይሆን ስራው እናንተን በጽኑ እንደሚፈልጋችሁ አስቡት። Interview ላይ ከሚታዩት ዋና ነገሮች አንዱ ይሄ ነው። ጥያቄ ስትጠየቁ ሳትርበተበቱ በነጻነት የመሰላችሁን መልስ መስጠት ነው።ከናንተ የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። confidence ሲበዛ ደሞ ትእቢትም ስለሚመስል ሁሉንም በልኩ ማድረግ።

የምትመልሰውን መልስ አስተውል!!! የቃል ፈተና ላይ ብዙ ሰው የሚሳሳተው ነገር ለተጠየቀው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ትክክለኛ የራሱን ማንነት የሚገልጽ ሳይሆን "ጠያቂው ይወደዋል? Impress ያደርገዋል? ብሎ ያሰበውን ነው።በዚህ ዙርያ " #ጠብታ_ማር "የምትል መጽሐፍ ላይ አንድ ከ20 አመት በላይ በHR (ሰው ኃይል አስተዳደር) የሰራ ሰው ልምዱን ሲያካፍል ይሄንኑ ጉዳይ እንደተቸገረበት ይገልጻል።እኔም በቅርቡ የታዘብኩት "" ልጁ ስለ marine engineering ሰው ሲያወራ ይሰማል።አዲስ ምሩቅ ነው።እናም ስራ በጣም ስለፈለገ ብቻ አመልክቶ ለቃልሀገሪቱ ይጠሩታል።ስለስራው ምንም ስለማያውቅና ስላልተዘጋጀ አብዛኛውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸገረ። በመጨረሻ ጠያቂው "እሺ ለምን ይህን ስራ ፈለክ?ለምን ከእኛ ድርጅት ጋር ለመስራት ፈለክ?" ሲለው ልጁም " because it's my dream job from childhood" አለው። marine engineering ኢትዮጵያ ውስጥ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን ከትንሽ አመታት ወዲህ ነው የተጀመረው።ሀገሪቱ ውስጥ ብዙም አልታወቀም።እንዴት የልጅነት ህልም ሊሆን ይችላል? በልጅነት ዶክተር ኢንጅነር ነበር የምንለው።በዚህ ምክንያት reject ተደረገ።
እናም ለምትጠየቋቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ እና ጤነኛ መልስ መስጠት ዋጋችሁን ከፍ ያደርገዋል።

ጸሎት፦እንደዚህ አይነት ለህይወታችሁ በጣም አስፈላጊ ሁነቶች ላይ እና በጽኑ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሲኖሩ በየእምነታችሁ መጸለይ ያግዛችኋል።ያ የምትፈልጉት ነገር ወደ እናንተ ቢመጣ አመስግናችሁ በአግባቡ ልትይዙት፣ እንደፈለጋችሁት ሳይሆን ቢቀርም ወይም ባይመጣም ወትሮም የማይጠቅማችሁ መሆኑን መለያ ነው።እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን ለኛ
የሚያስፈልገንን እንዲሰጠን በትሁት ልቦና ፈጣሪን መጠየቅ ጥሩ ነው።ምክንያቱም የእኛ ፍላጎት በስሜት የተነዳ እና አመክንዮአዊ ያልሆነ ነው።ፈጣሪ ግን መቼ ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል።ስለዚህ በየእምነታችን እንደየአቅማችን መጸለይ ይመከራል። so attach to him and let him do what's best for you:)

ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው።ከዚህ ውጭ የተለያዩ ጽሑፎችን (web publication, how to articles..) ድረ ገጾች ላይ በማንበብ ፣ ሰዎች ጋር መረጃ በመለዋወጥ...ራሳችሁን ለመረጃ ቅርብ አድርጉት። አደራ ታዲያ ስራውን ካገኛችሁ በኋላ የመጀመሪያው ደሞዝ ላይ እንዳትረሱን😊😉

የባለፈውን ጽሑፍ ተከትሎ በጣም ብዙ ምስጋናዎች እና ጥያቄዎች እየመጡ ነበር።ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። በዚች ምድር ላይ ያለን ሰዎች ሁሉ ስለምንዘነጋው ነው እንጂ በ Eco system እርስ በእርሳችን የተደጋገፍን ነን።የአንዳችን መጠቀም ሌላችንን በተዘዋዋሪ ይጠቅማል።የሀገርንም ኢኮኖሚና ገጽታ ያሳድጋል።የአንዳችን ጉዳትም እንዲሁ ጉዳቱ ለሁላችንም ነው።እናም ያለንን፣የምናውቀውን እናካፍል፤ በስራ ፍለጋውም በቃለ መጠይቁም መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ።

እነዚህ መጽሐፍት ይረዷችኋል።

How to win friends and influence people (Dale Carnegie)
በራስ መተማመን በሚል ተተርጉሟል።

Pursuit of happyness (Chris Gardner)
በፊልም ተሰርቷል።

@Fafi_G21


@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባሌ ጎባ⬇️

"ፀጋ ዛሬ ከትናንቱ ይቀንሳል ብሎም መውጣት ብዙም አልቻልንም ቅድም 8 ሰዓት አካባቢ ተኩስ ነበር አሁን ግን ዝም ብሏል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐረሪ ክልል⬇️

የሐረሪ ክልል ርዕሰ-መሥተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ከሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ሊቀ-መንበርነታቸው ተነስተው በአቶ ኦርዲን በድሪ ቢተኩም"ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ተፈፃሚ እስኪሆን ድረስ" በሥልጣን ይቆያሉ ተብሏል።

©እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት⬇️

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አበባ 234 ሽጉጥና 17 ሺሕ የሽጉጥ ጥይት፤ ጋምቤላ 32 ክላሽንኮቭና 2 መትረየስ፣ ምዕራብ አርማጭሆ 298 ሽጉጥ፣ ሸኖ 53 ሽጉጥ፣ ደብረ ፅጌ 20 ሽጉጥና 1 መትረየስ ተይዟል ብሏል።

©እሸት በቀለ(ጀርመን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠላት መቼ ስራ ፈቶ ያውቃል⬆️

አሁንም ተጨማሪ የሀሰት ፎቶዎች እና መረጃዎች መውጣታቸውን ቀጥለዋል። ባሌ ጎባ ከፍትኛ የሀይማኖት ግጭት ተነስቷል እያሉ የሌላ ሀገር ፎቶዎችን እዚህ እንደሆነ የሚያቀርቡ በዝተዋል።

*ጠላቶቻችን 24 ሰዓት እኛን ለመበተን እየሰሩ ነው ተጠንቀቁ!

@tsegabwolde
6 ሰው ህይወቱ አልፏል⬇️

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ለዋልታ እደገለፁት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተከሰተ ግጭት እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን አረጋግጠናል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvhethiopia
ከባሌ ጎባ⬇️

"....በርግጥ ሰው እየሞተ ቢሆንም ከሁሉም በላይ ግን ከዚህ ሳይብስ ነገሩ ቢቆም ብለን እየፀለይን እንገኛለን ማምሻውን ብዙ መከላከያ ሰራዊት ገብቷል እርግጠኛ ባልሆንም የክልሉ ፖሊሳች ስራ እንዲያቆሙ ተነግሯል ምሽቱም በጣም ፀጥ ያለ ነው እስካሁን። ፀልዩልን ሰላሙን እንዲሰጠን ብሮ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia