#ወንጂ🕯
ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ።
እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።
" አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል።
ከተገደሉት መካከል 3ቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዛሬ ተፈፅሟል።
ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ቀብሩ ዛሬ የተፈፀመ ሲሆን ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።
4ቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም ተገልጿል።
ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።
አንደ ኃላፊው ገለጻ ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን " ዶዶታ " ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።
ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር ? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።
ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም ነገር እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።
ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።
ስለ ግድያው እንዴት ? እና ስንት ሰዓት ? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።
በፋብሪካው እንዲህ እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም አስረድተዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ወንጂ🕯 ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ። እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል። " አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል። ከተገደሉት…
#ወንጂ🕯
ለስራ በወጡበት #በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ ተገድለው ከተገኙት ዜጎች መካከል አንዱ አቶ ግርማ በላቸው እንደሚባሉና የኢትዮ ስኳር ፋብሪካ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አ/ማ የስራ ባልደረባ እንደነበሩ ተነግሯል።
ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በታጣቂዎች ታግተው ፤ በግፍ ተገድለው የተገኙት ለወንጂ ስኳር ፋብሪካ ድጋፍ ለመስጠት በወጡበት ነው።
በኦሮሚያ ክልል ፤ በቅርቡ የጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 አባቶች ታግተው በግፍ መገደላቸው የሚዘነጋ አይደለም።

Photo
#ወንጂ
" ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻልም " - የሟች ቤተሰብ
ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ስለተገኙት 5ቱ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ቤተሰቦቻቸው ምን አሉ ?
ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜ አጠቀስ ያሉ የሟች ቤተሰብ አባል ፦
" 6 ሰዎች ነበሩ ፤ ለስራ በሄዱበት ነው የታገቱ። ምንድነው ሲባል ገንዘብ ነው የሚፈልጉት ፤ መጀመሪያ በሰው 600 ሺህ ብር አሉ ከዛ ደግሞ 300 ሺህ ብር አሉ።
የተጠየቀውን ገንዘብ መ/ቤቱ እንደ ህግ አይፈቅድም ብሎ ህዝብ፣ ሠራተኛው በሙሉ ማሰባሰብ መሯራጥ ጀመረ፤ እነሱን ለማትረፍ።
በዛ መሃል ከቤተሰብም ከምንም ገንዘቡ ተሰባስቦ ከእነሱ ጋር ግንኙነት አድርገን ገንዘብ ሰጥተን ለማስለቀቅ ሲባል ይሄ ወንጀል ነው ተብሎ የቤተሰብ አካል ሁሉ እንዲያዝ ተደርጎ ግንኙነቶቹም እንዲቆሙ ተደረገ።
ከዛ ፌዴራል እነሱን እናስለቅቃለን በሚል ገብቶ ግጥሚያ ገጥሞ ወንድሞቻችን በዚያ ምክንያት ህይወታችን አለፈ።
ምንም ማድረግ አይቻልም ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር። ስድስት ነበሩ አምስቱን ገደሏቸው። አንዱ አምልጧል ተብሏል አንዴ ሞቷል ይባለል ጭራሽ ሌላ ሰቀቀን ነው ለቤተሰብ ያ ሰውየ በህይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም። "
ሌላ አንድ የቤተሰብ አባል ፦
" እስከ ማክሰኞ ዕለት የሚፈልጉትን ብሩን ሰብስበን ፤ በአንድ ሰው 300 ሺህ ብር ነው የተስማማነው ፤ ለእሮብ ጥዋት ብሩን እንድንሰጥና ቤተሰቦቻችንን እንድንወስድ ተነጋገርን።
ከዛ ብሩ ተሰብሰቦ ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን በካሽ እየቆጠርን እያለ መጡ ፖሊስ አባላት ከነብራችን ያዙን ከዛ " ብር መያዝ ብር መሰብሰብ እንደ ወንጀል እንደሚቆጠር አታውቁም ወይ ? " ብለው ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አሰሩን። የተገረፈም አለ፣ ከየቤቱ አንድም ሁለትም ሰው ታሰረ ብቻ በጅምላ ነገሮችን እንደዛ አደረጉ፤ ወንጀለኛን በመርዳት በመደገፍ በሚል።
አጋቾች ሀሙስ ይሄ ነገር እንደ ሰሙ ብሩም እንደተያዘና ከዚህ መረጃ ተነግሯቸዋል (ብሩ ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ነው ቀጥታ ተይዞ የገባው ከቤተሰቦቻችን ጋር) ፤ አጋቾቹ ያገቷቸውን ቤተሰቦቻችንን ከተነጋገርንበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ህይወት እንዳጠፉ ተነገረን።
5ቱ ሰዎች ናቸው የተገደሉት። እጅግ በጣም አዘንን በቀል የእግዚአብሔር ነው ብለን ሁሉንም ነገር ትተናል።
6 እና 7 ቀን ከ60 ኪ/ሜ በላይ በእግር አስጉዘዋቸዋል። በየጫካው አሳድረዋቸዋል። ይህን በየአካባቢ ያሉ ሰዎች ነግረውናል። በጣም አዝነናል፤ ሞት አንድ ነው ግን እንዴት እንደዚህ አንድ ሞትን ለምኖ እስኪሞት ድረስ የተለመኑትን ሞት እንኳን ሳይሰጧቸው ተሰቃይተው ነው ቤተሰቦቻችን የሞቱት፤ ባሉበት በስብሰው።
መሳሪያ ብቻ አይደለም ያገኛቸው #በስለትም እንደተቆረጡ ሆስፒታል ሄደን አይተናል። በጣም አዝነናል። "
➡ 6ቱ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የካቲት 29 ነበር በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ለስራ ወደ ፋብሪካው የሸንኮራ ማሳ በማቅናት ላይ እያሉ የታገቱ። ከፍተኛ ገቢ አላቸው ተብለው የተገመቱት ሲታገቱ ሌሎች ተለቀዋል። ከ6ቱ አምስቱ ተገድለዋል።
➡ 4ቱ ፋብሪካውን ለረጅም አመታት ያገለገሉ አንጋፋ ሰራተኞች ናቸው አንዱ ገና ወጣት ነው። ሁሉም ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሟች ቤተሰቦችን ቃል ያዳመጠው ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ / ጋዜጠኛ ኬኔዲ አባተ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።