TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት። 70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ…
#Update

" ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ብሎ ተሸንፏል " የተባለው ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበል ለ70 የጤና ባለሙያዎች በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል #ተገዶ ከፈለ።

በገባው ቃል መሠረት የኮቪድ ወቅት ልዩ አበል ባለመክፈሉ ከ60 በላይ በሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክስ ተመስርቶበት፣ " ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ቢልም ተሸንፏል " ፣ " የፍርድ ቤት ውሳኔንም በተደጋጋሚ ሲጥስ ነበር " የተባለው ጤና ሚኒስቴር በመጨረሻ ገንዘቡን ለከሳሾቹ በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል ተገዶ መከፈሉን የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎቹን ወክለው ጉዳዩን በጥልቀት ሲከታተሉት የነበሩ ተወካይ የፍርድ ቤት ሂደቱና ጤና ሚኒስቴር ስንት ጊዜ ይግባኝ እንደጠየቀ ሲያስረዱ፣ " ከዋናው መዝገብ እስከ አፈፃፀሙ ከ6 ጊዜ በላይ ይግባኝ ብለው አሸንፈናል። ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው አስገድዶ የተቆረጠበት " ብለዋል።

ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበል ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል በመቁረጥ እንዲፍላቸው ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የጤና ባለሙያዎችን ብዛትና የልዩ አበሉን መጠን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪም፣ " 70 ናቸው። አጠቃላይ የገንዘብ መጠን በግልፅ አልተቀመጠም ነበር። በግምት ግን ከነታክሱ ከ33 ሚሊዮን በላይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤት ልዩ አበሉን እንዲከፍል ለመስሪያ ቤቱ ውሳኔ ቢያሳልፍም በተደጋጋሚ ፈቃደኛ ሳይሆን የክሱ ሂደት ብዙ ጊዜ በመውሰዱ የኮቪድ ልዩ አበሉ መጠን አልጨመረም ወይ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ፣ " ወለድና ሌላ ነገር ሳይሆን  የዋናው መዝገብ ክርክር የክስ ሂደቱ ጊዜ ስለረዘመ ጨምሯል " ነው ያሉት።

ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ልዩ አበሉን በመጨረሻ በንግድ ባንክ በኩል እንዲከፍል ተገዶ ከሳሿቹ ፍትህ ያገኙት ከሁለት ዓመታት ተኩል በላይ እንደሆነ የገለጹት ታማኝ ምንጭ፣ " ገንዘባችን እንዲከፈል ከማድረጉ ባሻገር ምንም አይነት ካሳም ወይም ቅጣት አልከፈለም " ብለዋል።

ሌላኛው ሁነቱን ሲከታተሉ የነበሩ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው፣ የፍትህ ስርዓቱ ተጽዕኖ ቢበዛበትም የጤና ባለሙያዎቹ ታግሰውና እውነትን ብቻ ይዘው ችሎቱን ተደጋጋሚ እንዳሸነፉ፣ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው ተቋም (ጤና ሚኒስቴር) የፍርድ ውሳኔውን ለመፈጸም ፌቃደኛ ባለመሆን ተደጋጋሚ ይግባይኝ እንደጠየቀ ገልጸው፣ " የመጨረሻ የፍርድ ቤት ውሳኔዉ ተፈጻሚ ሆኗል " ብለዋል።

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ ፦
- የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን 1,050 ብር፣ 
- ለየመጀመሪያ ድግሪ ባለሙያዎች 900 ብር የኮቪድ ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ቢወሰንም፣  ተቋሙ የሰሩበትን የተወሰኑ ወራት አበል ከፍሎ ሙሉውን ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ክስ እንደመሰረቱ፣ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት ልዩ አበሉን እንዲከፍል ቢወስንም ጤና ሚኒስቴር ውሳኔውን እየጣሰ መቆየቱን መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መዘገቡ የሚታወስ ነው።

መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia