TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Grade12NationalExam

ከዚህ ቀደም በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ሲሰጡ ከነበሩ የትምህርት አይነቶች መካከል ሥነ ምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርት (Civics and Ethical Education) በዘንድሮው ዓመት 2016 ዓ/ም #አይሰጥም

የሥነምግባር እና ሥነ ዜጋ ትምህርት (Civics and Ethical Education) ፈተና ያልተካተተው በሁለቱም የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ነው።

ይህ ፈተና ለምን በብሄራዊ ፈተናው ላይ እንዳልተካከተተ / እንዳይካተት ውሳኔ እንደተለለፈ ትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት ዓመታት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሳይሰጥ የቆየው #የኢኮኖሚክስ ትምህርት በዚህ ዓመት 2016 ፈተና ላይ ተካቷል።

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እኩል ስድስት ትምህርቶችን ይወስዳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ፤ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ ፣ ፊዚክስ ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ሶኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ፈተና ሲወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ ፣ ጂኦግራፊ ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

በዚሁ ዝርዝር መሰረት ከሁለቱም ዘርፎች የሥነ ዜጋና ሥነምግባር (Civics and Ethical Education) ትምህርት የወጣ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ላይ ባለፉት ዓመታት ሳይሰጥ የቀረው ኢኮኖሚክስ ተካቷል።

ፈተናው የሚሰጥበት ትክክለኛውና ቁርጥ ያለው ቀን ባይታወቅም እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ዓመታት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (#ዩኒቨርሲቲዎች) በማስገባት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#DStv

📣 ሰምተዋል?

በማንኪያ ሲሉ በጭልፋ ፤ በጭልፋ ሲሉ በአካፋ!

👉 ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ድረስ ከሚጠቀሙት ፓኬጅ ከፍ ካሉ በእኛ ወጪ ወደ ቀጣዩ ትልቅ ፓኬጅ ለአንድ ወር ከፍ ይላሉ!

ይህ አገልግሎት ክፍያ ከፈፀሙ ከ48 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።

*ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን 

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!

👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #StepUp
#CBE

CashGo (ካሽ ጎ)

ከውጭ ሀገራት ገንዘብ መላኪያ የሞባይል መተግበሪያ
===========================
በሞባይል ስልክዎ አማካኝነት ቪዛና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም

• ከውጭ ሀገር በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ መላክ ይችላሉ፣ አሊያም
• ተቀባዩ ከ1900 በላይ በሚሆኑት የባንካችን ቅርንጫፎች መቀበል ይችላሉ!
**
የCashGo ሞባይል መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306
TIKVAH-ETHIOPIA
" በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ሲሄድ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር   የአምቡላንስ ሼፌሩ በተተኮሰበት ጥይት #ተገደለ። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይዎት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ሰዓት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት…
#UPDATE 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያወጣውን የሃዘን መገለጫ ዋቢ በማድረግ ጥር 3 /2016 በትግራይ ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይወት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉ መዘገባችን ይታወሳል።

የቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌሩ እንዴት ለህልፈት እንደበቃ የሚያትት ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ እንዳባፃሕማ ወረዳ፤ ዕዳጋ ዓርቢ ከተማ ፓሊስ የደረሰን የምርምራ ወጤት እንደሚከተለው አቅርበናል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በእምባስነይቲ እንዴት ተመታች ? ሹፌሩስ እንዴት ለህልፈት ተዳረገ ? 

ፖሊስ ፤ አከባቢው ህጋዊ ያልሆነ ትጥቅ በተምቤን ትግራይ ክልል አድርጎ ወደ ሰቆጣ አማራ ክልል የሚተላለፍበት እንደሆነ በጥናትና ክትትል ቀደም ብሎ እንደደረሰበት ይገልጻል።

ስለሆነም ጥር 2/2016 ቀን ላይ በአምባስነይቲ ነበለት በተምቤን ወደ ሰቆጣ 80 መሳሪያ ከነተተኳሹ በሌሊት እንዲተላለፍ እየተደሎተ መሆኑ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል።

ገዢና ሻጮች ወደ እምባስነይቲ ዕዳጋ ዓርቢ ነበለትና አከባቢው መግባታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ፓሊስ በአከባቢው ከሚገኙ ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች በመቀናጀት መሳሪያው ከገዢና ሻጭ እንዲሁም አሻሻጭ ደላሎች እጅ በፈንጅ ለመያዝ በተጠንቀቅ ቆመ። 

ፓሊስ ቀን ላይ ገዢና ሻጭ እንዲሁም አሻሻጭ ደላሎች ያረፉበት ሆቴል የሚዘዋወሩባቸው ቤቶችና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲከታተለ ውሎ አመሸ። 

ፓሊስ ከአከባቢው ተገዝቶ የሚጓጓዘው መሳሪያ ከነተተኳሹ በመኪና እንደሚጓጓዝ መረጃው ቢደርሰውም፤ መኪናዋን የሚያሽከረክራት ሹፌርና የመኪናዋ ዓይነት አልለየም ነበር።

ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  አምቡላንስ በወሊድ ምጥ የተያዘች እናትን ከአከባቢው የተሻለ ህክምና ወዳለበት ከተማ ለመውሰድ በእምባስነይቲ ነበለት ዓዲ ፌላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ተገኘች። 

ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ፓሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ህጋዊ ያልሆነ ትጥቅ ከትግራይ ወደ አማራ ክልል ለማሸጋገር የምትበረው መኪና ከነግብረአበሮችዋ ለመያዝ በተጠንቀቅ እያሉ አምቡላንስዋ ተከሰተች።

አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት አምቡላንስ የወላጅ እናት ህይወት ለመታደግ በጉዞ ሳለች በድቅድቅ ጨለማ በአሳቻ ቦታ " ቁም ! " የሚል የፀጥታ አካላት ትእዛዝ እንደተሰጣት ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ፤ ሟች " ቁም " የሚለውን ወታደራዊ ትእዛዝ ሳይቀበል በመቅረት አምቡላንስዋን መንዳቱን ቀጠለ ይላል።

" ቁም !ቁም !ቁም " የሚለው ድምፁ እንጂ መልኩ የማይታየው ከድብቅ ቦታ የሚሰማው ማስጠንቀቅያ ትእዛዝ ቀጠለ። ሟች አምቡላንስዋ አላቆማትም ። አንደኛ ኬላ አልፎ ሁለተኛ ኬላ ደርሶ ለማለፍ ሲሞክር አምቡላንስዋ ተተኮሰባት ሟችም ተተኮሰበት። መኪናዋ ቆመች ፤ የወልዱ ህይወትም በዚህ መንገድ ተቀጠፈ።

ይህ አደጋ ካጋጠመ በኃላ ቀን ሙሉ በድብቅ የፓሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ክትትል የዋለችው ህጋዊ ያልሆነ መሳሪያ የጫነችው መኪና ተከትላ እንደመጣች ፖሊስ ገልጿል።

መኪናዋ ከተወሰኑት ግብረ አበሮች ከጫነችው ህጋዊ ያልሆነ መሳሪያና ተተኳሽ ጭምር በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ዋለች። 

በአምቡላንስዋ የነበሩና ከአደጋው የተረፉ ሃኪሞች ሟች ቁም ሲባል ለምን እንዳልቆም አስመልክቶ ከፓሊስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ቃል፤ እንዲቆም የተጠየቀበት ቦታ ከከተማ ውጪ እንዲሁም ጨለማ ስለነበር #ዘራፊዎች መስለውት ለማምለጥ እሰቦ ነው ብለዋል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት ነበር።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ

@tikvahethiopia
#ቤኒሻንጉልጉሙዝ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ አጎራባች አካባቢዎች የሚወስደው መንገድ በፀጥታ ምክንያት ዝግ በመሆኑ፣ ለከፍተኛ ሕክምና ሪፈር የሚጻፍላቸው ሕሙማን ሕክምና ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

ከአሶሳ ከተማ ተነስቶ ወደ መተከልና ኦሮሚያ ክልል የሚወስደው መንገድ በፀጥታ ችግር ምክንያት በመዘጋቱ ሕሙማን የከፋ ችግር ውስጥ ወድቀዋል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶፊያ አወት ምን አሉ ?

- ከአጎራባች ሱዳን ፈልሰው የመጡ ስደተኞችና ምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ የሠፈሩ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙት አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በመሆኑ፣ ሆስፒታሉ አገልግሎት ለመስጠት ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል።

- ሆስፒታሉ ከፍተኛ የሆነ የሕክምና ግብዓት እጥረት አለበት።

- ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ሕክምና እንዲያገኙ ሪፈር የሚጽፍላቸው ሕሙማን አቅም ያላቸው ብቻ የአየር ትራንስፖርት ተጠቅመው የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ነው።

- በክልሉ አብዛኛውን ነዋሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማም ሆነ ወደ ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች በአየር ትራንስፖርት ሄደው ለመታከም የገንዘብ ችግር ስለሚገጥማቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቁጥር አንድ ከሚባሉት ሆስፒታሎች ውስጥ አንዱ ነው። በአሁኑ ወቅት በቀን ከ150 በላይ ለሆኑ ሕሙማን አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

- ለሆስፒታሉ የሚቀርበው መድኃኒትና ሆስፒታሉ የሚሰጠው አገልግሎት ጭራሽ የማይመጣጠን ነው።

- በፀጥታ ችግር ምክንያት መድኃኒት እየቀረበ ያለው በአየር ትራንስፖርት ነው።

- በአየር ትራንስፖርት መድኃኒት ቢመጣም ቶሎ ቶሎ የሚያልቅ በመሆኑ መድኃኒት ለመግዛትም ሆነ ለመድኃኒት ማጓጓዣ ሆስፒታሉ ከፍተኛ ወጪ እያወጣ ይገኛል።

- ሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና፣ የማዋለድ፣ የዓይን ሕክምናና ሌሎች አገልግሎቶችን ይሰጣል።

- ከዚህ በፊትም የፀጥታ ችግር ባልነበረበት ወቅት ሕሙማንን በፍጥነት በአምቡላንስ በማመላለስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር፤ ይሁን እንጂ የፀጥታ ችግር በክልሉ በመባባሱ አምቡላንሶች እንደ ልብ ተንቀሳቅሰው አገልግሎት እንደማይሰጡ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አንድ አምቡላንስ በታጣቂ ኃይሎች መቃጠሉንና ውስጥ የነበሩ ሕሙማንና ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለም ደበሎ ምን አሉ ?

* በክልሉ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ስድስት ሆፒታሎች አሉ፡፡ ሆስፒታሎቹ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የግብዓት ችግር ገጥሟቸዋል።

* በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረዋል።

* የመድኃኒትም ሆነ ሌሎች የሕክምና ግብዓቶችን በተመለከተ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በአየር ትራንስፖርት እያስገባን ቢሆን ችግሩ ግን ከፍተኛ ነው።

* በክልሉ የሕክምና አገልግሎቶች የሚሰጡ ሆስፒታሎች ለሕሙማን ሪፈር ሲጽፉ አብዛኞቹ ሕሙማን በአየር ትራንስፖርት ሄደው ለመታከም ይቸገራሉ፤ በዚህ ምክንያት እዚያው ሕክምናቸውን ለመከታተል ተገደዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ታልፍ ይሆን ?

የኢትዮጵያ #ከ20_ዓመት_በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከሞሮኮ አቻው ጋር በአዲስ አበባ ፤ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እያደረገ ይገኛል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሳምንት በፊት ከሜዳው ውጪ ያደረገውን የማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ በሞሮኮ የ2ለ0 ተሸንፏል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን በድምር ውጤት የሚያሸንፍ ከሆነ በቀጥታ ኮሎምቢያ ለምታዘጋጀው የ2024 ዓለም ዋንጫ ውድድር ያልፋል።

በ " አበበ ቢቂላ ስታዲየም " እየተካሄደ ያለውን ጨዋታ በቲክቫህ ስፖርት መከታተል ይችላሉ ፦ https://yangx.top/+VvwzStMNcNHmhK0x

በተጨማሪ በቀጥታ ለመመልከት ፦ https://www.youtube.com/live/fGyiYbhaj-k?si=_DGAQyXg1Oo7q5u_

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ እና የሞሮኮ እግር ኳስ ቡድን አባላት (Tikvah Ethiopia Sport Image)

@tikvahethiopia @tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TeamEthiopia 🇪🇹

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን የሞሮኮ አቻውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ወደ ኮሎምቢያ ዓለም ዋንጫ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

የ2024 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ውድድር በኮሎምቢያ አዘጋጅነት የሚካሄድ ይሆናል።

More 👉 @tikvahethsport    
Tecno | AFCON

የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ይፋዊ ስፖንሰር የሆነው ቴክኖ ሞባይል፣ በአዲሱ (spark 20pro+) እየተዝናኑ ጨዋታውን እንዲመለከቱ ይጋብዞታል!

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia
#ደበሶ

ዛሬ 8 ሰዓት ላይ በደበሶ ደብረ ልዕልና ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መነሻውን ከድሬደዋ ያደረገና ወደ ጭሮ ጭነት ይዞ ሲጓዝ የነበረ ከባድ የጭነት መኪና የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩና ታቦት ከባሕረ ጥምቀት ወደ መንበረ ክብሩ በዝማሬ ፣ በሆታና በዕልልታ እያጀቡ ባሉ ምዕመናን ላይ በፍጥነት በመውጣት ባደረሰው ገዳት  7 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ ከ7 በላይ ሰዎች ከባድ ጉዳት ፣ ወደ 10 የሚደርሱ ከቀላል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንና አሁን ላይ በጭሮ ሆስፒታል በድንገተኛ ጽኑ ሕሙማን ክፍል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሟቾች መካከል ህፃናት እና የፀጥታ አካላት ይገኙበታልም ብሏል።

ጉዳቱን ያደረሰው መኪና መንሥኤው ምን እንደሆነ በባለሙያዎች ይጣራል ሲልም አሳውቋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን በበኩሉ በጦሎ ወረዳ ደበሶ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ 5 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲል ለኤፍቢሲ ተናግሯል።

5 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

" አደጋው የተከሰተው ከድሬዳዋ ወደ ጭሮ ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ #ፍሬን አስቸግሮት ፍጥነቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ በመንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን በመግጨቱ ነው " ሲል ዞኑ ስለ አደጋው መንስኤ አብራርቷል።

በተያያዘ መረጃ ትላንት በጥምቀተ ባህሩ ስፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።

@tikvahethiopia