TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ዜና_ዕረፍት:የቀድሞው የዓረና ፓርቲ ሊቀመንበር እና ያሁኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃኑ በርኸ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Via አብርሃ ደስታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዜና_ዕረፍት

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ጋዜጠኛው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሀገር ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተነግሯል።

ጋዜጠኛው ቀድሞ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ህይወቱ እስካለፈበት ሰዓት ድረስ ደግሞ የEBS ቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ በመሆን ሰርቷል።

በተለይ በEBS ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው " ኑሮ በአሜሪካ " ፕሮግራም እና " እሁድን በEBS " ፕሮግራም በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሎ ነበር።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሸ ባደረበት ህመም ምክንያት ህክምና ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።

ለወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!

Via @TikvahethMagazine