TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም። የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም። " - ኢትዮጵያ

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" ... ይህ ሰነድ ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝ እና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታገኝበትን ዕድል የሚያስገኝ ነው።

መንግሥት አስቀድሞ ይፋ ባደረገው አቋሙ መሠረት ሶማሌ ላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል።

ከዚህ ባሻገር በሂደት ሶማሌ ላንድ #ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት በጥልቀት አጢኖ #አቋም የሚወስድበትን አግባብ ያካትታል።

... ስምምነቱ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ጭንቀትና ቁዘማ ለማከም የሚያስችል አጋጣሚን የፈጠረ ነው።

በመሆኑም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስደስት ታሪካዊ ክስተት ነው።

ሁሉም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም የቀጣናው ሰላም የሚገዳቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ሁሉ ሊደሰቱ ይገባል።

በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም።  የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም።

እውነታው ይኸው ቢሆንም ማንም እንደሚገምተው በዚህ አወንታዊ ድምዳሜ #የሚከፋ#የሚደነግጥና #ሁኔታውን_ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ አካል አይኖርም አይባልም።

በመሆኑም በተለይ ኢትዮጵያውያን በርግጥም ሀገራችን በመልኳና በቁመናዋ ልክ በቀጣናው፣ በአህጉራችንና በዓለም አደባባይ ተገቢ ሥፍራዋን ስታገኝ፣ ገንቢ ሚናዋን ስትወጣ፣ ጥቅሞቿንም ስታስከበር ብቻ በጋራ እንደምንከበር ማመንና ለዚህም ልዩነቶቻችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማቻቻል ተያይዘን ከፍ እንል ዘንድ ይህን አጋጣሚ እንደንጠቀምበት የኢፌድሪ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

ይህ በዘመናት አንዴ የሚከሠት የታሪክ እጥፋት በመሆኑ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሀገራችንን በጋራ እንታደግ።

ከዘመናት በኋላ በታሪክ የማንወቀስ እንድንሆን ያለንበትን ምእራፍ ከመወራረፍና ከመጠላለፍ ተላቀን የኢትዮጵያችን ከፍታ ማብሠሪያ ለማድረግ በአንድነት አብረን እንትጋ። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia