#ጅግጅጋ
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር #የፀጥታ እና #ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤስአርቲቪ ሶማሊኛ ክፍል ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia

በM-PESA እንክፈል በተመረጡ ስልኮች ላይ እስከ 10% ቅናሽ እናግኝ። በወሎ ሰፈር ፣ ቦሌ ፣ ጀሞ እና መስቀል ፍላወር ወደሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች ጎራ በማለት አዲስ ስልካችንን እንግዛ።
#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

ሚና ፈርኒቸር .. ከዘመኑ ጋር 🤌
ከታህሳስ 20- ታህሳስ 28 የሚቆይ ልዩ ቅናሽ
አዘጋጅተናል::
👉KSA4O:-ይህን code ይዞ ለመጣ ደንበኛ ልዩ ቅናሽ!!ከነጻ ትራንስፖርት 🚚እና 4 አመት ዋስትና ጋር አዘጋጅተናል🎄
☎️0932325151
Join Our telegram channel 👇
CLICK HERE ‼️https://yangx.top/minafurniture

TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#ኢትዮጵያ🇪🇹
" በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም። የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም። " - ኢትዮጵያ
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
" ... ይህ ሰነድ ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝ እና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታገኝበትን ዕድል የሚያስገኝ ነው።
መንግሥት አስቀድሞ ይፋ ባደረገው አቋሙ መሠረት ሶማሌ ላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል።
ከዚህ ባሻገር በሂደት ሶማሌ ላንድ #ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት በጥልቀት አጢኖ #አቋም የሚወስድበትን አግባብ ያካትታል።
... ስምምነቱ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ጭንቀትና ቁዘማ ለማከም የሚያስችል አጋጣሚን የፈጠረ ነው።
በመሆኑም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስደስት ታሪካዊ ክስተት ነው።
ሁሉም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም የቀጣናው ሰላም የሚገዳቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ሁሉ ሊደሰቱ ይገባል።
በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም። የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም።
እውነታው ይኸው ቢሆንም ማንም እንደሚገምተው በዚህ አወንታዊ ድምዳሜ #የሚከፋ፣ #የሚደነግጥና #ሁኔታውን_ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ አካል አይኖርም አይባልም።
በመሆኑም በተለይ ኢትዮጵያውያን በርግጥም ሀገራችን በመልኳና በቁመናዋ ልክ በቀጣናው፣ በአህጉራችንና በዓለም አደባባይ ተገቢ ሥፍራዋን ስታገኝ፣ ገንቢ ሚናዋን ስትወጣ፣ ጥቅሞቿንም ስታስከበር ብቻ በጋራ እንደምንከበር ማመንና ለዚህም ልዩነቶቻችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማቻቻል ተያይዘን ከፍ እንል ዘንድ ይህን አጋጣሚ እንደንጠቀምበት የኢፌድሪ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።
ይህ በዘመናት አንዴ የሚከሠት የታሪክ እጥፋት በመሆኑ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሀገራችንን በጋራ እንታደግ።
ከዘመናት በኋላ በታሪክ የማንወቀስ እንድንሆን ያለንበትን ምእራፍ ከመወራረፍና ከመጠላለፍ ተላቀን የኢትዮጵያችን ከፍታ ማብሠሪያ ለማድረግ በአንድነት አብረን እንትጋ። "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

አውሮፓ ህብረት ምን አለ ? የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር። በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል…
#ኢጋድ #ሶማሊያ
ዛሬ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።
የሶማሊያ መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።
የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።
ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።
(የሁለቱም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

Photo
#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያ ምን አለች ?
" ... ምንም እንኳን ሶማሊላንድ እስካሁን የተሟላ ዕውቅና ባታገኝም የወደብ አገልግሎትና ልማትን ጨምሮ ከአንዳንድ ሀገራት ጋር ስምምነት ፈርማለች።
ከዚህ ቀደም በርበራ ላይ ለኢትዮጵያ የ19 በመቶ ድርሻ እንዲኖራት ይፈቀድ የነበረ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ እንደነበርም ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት ሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ሂደት እየተከተሉ መሆኑም ይታወቃል። ይሄ ሲሆን የተሰማ ኮሽታም ሆነ ቅሬታ አልነበረም።
ኢትዮጵያ የወታደራዊ ቤዝና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሰጥቶ መቀበልና በኪራይ ለማግኘት የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድና ሂደትም በመሠረቱ አንድና ያው ነው። "
(ሙሉ መግለጫ ፦ https://yangx.top/tikvahethiopia/83987)

#Update የሶማሊላንድ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ። የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዜዳንት አብዲራህማን ሳይሊች የሶማሊላንድን ካቢኔ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ይኸው የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ በሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ እና የፌዴራል ምክር ቤቶች ለተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ #ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር አብዲረሺድ ኢብራሂም ያገኘው…
#Update
ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች።
ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች።
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር።
ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦
- ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024 በአዲስ አበባ የተፈርመውን የመግባቢያ ስምምነት በሙሉ ድጋፍ አፅድቆ እንደተቀበለውና እንደሚያደንቅ ገልጿል።
- ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሉዓላዊነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያ ሀገር በመሆኗ ምስጋናውን አቅርቧል።
NB. (የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ ስምምነቱ በሂደት ሶማሌላንድ ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት በጥልቀት አጢኖ አቋም እንደሚወስድበት መግለፁ ይታወቃል)
- ምክር ቤቱ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሶማሌላንድ ምድሯን፣ አየሯን እና ባህሯን ሙሉ በሙሉ የምትቆጣጠር ነፃ ሀገር ናት ብሏል። በተጨማሪም " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሕገ መንግሥት መሠረት " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ከማንኛውም ብሔራዊ ጥቅሟን ከሚያስጠብቅና ከሚጣጣም አካል ጋር ስምምነት የማድረግ ሥልጣን አላት ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ የሶማሊያ መንግስት የሰጠውን መግለጫ እና ድርጊት በጽኑ አውግዟል። የሶማሊያ መንግስት በመሰል ጉዳዮች ከመሳተፍ እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል።
- ምክር ቤቱ ከሶማሊያ የወጡት መግለጫዎች " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በሶማሊያ መንግስት መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶችን የሚጻረር መሆኑን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይወቅልኝ ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍ ወይም ለመቃወም ለሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
- ምክር ቤቱ የሶማሌላንድ ህዝብ ለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላደረገው ደማቅ አቀባበል እና ድጋፍ ያለውን አድናቆት ገልጿል።
- ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክን አርአያነት በመከተል በዓለም ዙሪያ ያሉ መንግስታት " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እውቅና ለመስጠት ድፍረት እና ጥበብ እንዲያሳዩ አሳስቧል። ይህን መሰሉ ዕውቅና ለአህጉራዊ መረጋጋት፣ ለደህንነት እና ለአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ መርሆች መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥቷል።
ℹ ሶማሊላንድ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እራሷን እንደ አንድ ነፃ ሀገር የምትቆጥር ሲሆን የራሷ ህገመንግስት፣ የመገበያያ ገንዘብ፣ የፀጥታ ኃይል፣ ፓስፖርት፣ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ስርዓት አላት። እስከዛሬ ግን ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት አልቻለም። ሶማሊያ እንደ አንድ የራሷ ግዛት ነው የምታያት።
#ቲክቫህኢትዮጵያ

#DStvEthiopia
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የገና በዓልን ከወዳጅ ዘመድ ጋር ሰብሰብ ብለን ‘እያየሁ ነው … አትቀይሩት’ የሚያስብል
የመዝናኛ አማራጭ ያጣጥሙ!
መልካም በዓል!
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው

" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ
ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦
* ኤልጎ
* ወዘቃ
* ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ ጊዜ ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተው ነበር።
በተለይ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ውዝግቡ እየተባባሰ እንደመጣ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች ምን አሉ ?
በተለያዩ መድረኮችና ወቅቶች በሚያነሱት በዚህ የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ ምክንያት እና በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ፣ ለሁለቱም ም/ቤቶች የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጣቸው ምክንያት የጋሞ ዞን አስተዳደር በተለያየ መንገድ ስልታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸመብን ነው ብለዋል።
ኢሰመኮ ስለጉዳዩ የዞኑን አስተዳደር መጠየቁን ገልጾ አስተዳደሩ ፤ የመዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች የአካባቢ ምርጫ ተካሂዶ አካባቢውን ለማስተዳደር ሕግን በተከተለ መንገድ ምርጫውን በማሸነፍ ሥልጣን ሳይረከቡ መንግሥት ቀበሌዎቹን ማስተዳደር የለበትም በሚል ምክንያት በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር እንዲፈርስና አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረጉ ነው ብሏል።
ከጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአስተዳደር መዋቅር ጥያቄ አቅራቢዎች እና በጋሞ ዞን አስተዳደር መካከል ያለው አለመግባባት ውጥረት እየጨመረ ቆይቶ፣ ጥቅምት 11/2016 ዓ/ም አንድ በወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በኤልጎ ቀበሌ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በዋለበት ሂደት እና በቁጥጥር ሥር በነበረበት ወቅት በተፈጸመበት ድብደባ #መሞቱን ተከትሎ ሁኔታው እጅግ ተባብሶ ወደ ግጭት አምርቷል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አስተዳደር ከግለሰቡ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለኢሰመኮ አስረድቷል፡፡
ሆኖም ከጥቅምት 11/2016 ክስተት ጀምሮ በተለያዩ ሰዎችና ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች የነዋሪዎች የሙዝ እርሻዎች እና በመንግሥት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ንብረት ማውደም ጉዳት ደርሷል።
ከኅዳር 16/2016 ጀምሮ በተለያዩ ጊዜዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት በግለሰቦች እና በጸጥታ አካላት በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አባላት ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በርካታ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁንም የቀጠለው ውጥረት፣ ግጭትና እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች በነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትል ኮሚሽኑ ያለውን ሥጋት ገልጾ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።