TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ADWA129

129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል " በሚል መሪ ኃሳብ እንደሚከበር የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

የመከላከያ ስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን ፥ " በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

ከበዓሉ ቀደም ብሎም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች ጭምር እንደሚከበር ጠቁመዋል።

" ዓድዋ የጋራ ድል፣ የአንድነት፣ የአላማ ፅናት እንዲሁም የአሸናፊነት ምሳሌ በመሆኑ የአባቶችን አርበኝነት በመያዝ ዘመኑ የሚጠብቅብንን ኃላፊነት መወጣት አለብን " ብለዋል።

#FDREDefenseForce #FMC

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያስፈፅሙ አሳሰበ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ * የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ መዘንጋት የለባቸውም " ሲሉ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰኒያ የሰጡት ዛሬ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

" ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል " ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፥ ተቋማቱ በአካባቢ ሳይታጠሩ ለተመሠረቱበት ዓላማ መኖር አለባቸውም ብለዋል፡፡

- የሙስና መንሰራፋት፣
- ግብረ-ገብነት ማጣት
- ዕውቀት የመቀያየር ባሕል በምሁራን ዘንድ መቀዛቀዙን አንስተዋል

እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የዕውቀት ማዕከል እንዳይሆኑ አድርገዋል ብለዋል።

" ሀገራችን በዘርፈ-ብዙ ችግሮች ውስጥ በመሆኗ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት እና የእውነት ማዕከል እንዲሆኑየሪፎርም ሥራ እየተከናወነ ነው " ሲሉም አመልክተዋል።

ተቋማቱ፤ ጥራት ባለው ትምሕርት ትውልድን መቅረጽ እና የማሕበረሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም በአጽንኦት አሳስበዋል።

Credit -
#FMC

@tikvahethiopia