TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ኤዶ

በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ  በምትገኘው በሲዳማ ክልል፣ ወንዶ ገነት ወረዳ የኤዶ ቀበሌ በትላንትናው ዕለት አለመረጋጋት መፈጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፀጥታ አከላት እንዲሁም ከነዋሪዎች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

" ኤዶ " በኦሮሚያ እና ሲዳማ አዋሳኝ የምትገኝ ቀበሌ ስትሆን ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ መሰል አለመረጋጋት ፣ መንገድ የመዝጋት፣ ንግድ እና ትራንስፖርት የማስተጓጎል ችግሮች ሲከሰቱ ነበር።

በተለይ አካባቢው ላይ ከዓመታት በፊት ህዝበ ውሳኔ ከተደረገ በኃላ ውጤቱን ተከትሎ አስተዳደራዊ መዋቅር ከተዘረጋ ወዲህ በተለያዩ ጊዜ መንገድ መዝጋቶችና አንዳንድ የብጥብጥ ሙከራዎች ሲደረጉ ይስተዋላል ብለዋል ነዋሪዎች።

በትናንትናው እለትም እንዲህ ያለዉ ሙከራ መሞከሩን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡና የቀበሌዋ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል።

ወቅት እየጠበቀ በሚፈጠረው መሰል ችግር ሰዎች ስራ ወጥተው መግባት፣ መንገድ ሄደው መመለስ እንደሚቸገሩና የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ እንደሚያስተጓጎል ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ የወንዶ ገነት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፤  " በሲዳማ ክልል በውንዶ ገነት ወረዳ በኤዶ ቀበሌ ታሕሳሰ 19 ከቀኑ 4 ሰአት ጀምሮ መንገድ ዝግ ሆኖ ዛሬም ተዘግቶ ወሏል " ብለዋል።

" ኤዶ " ላይ ችግር መኖሩን ተከትሎ ነዋሪዎች በሻሸመኔ አድረገው ወደ ወንዶ ገነት ለመጓዝ መገደዳቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የወረዳዉ የጸጥታ ጉዳይ ተጠሪ አቶ ሀማሮ ሀይሶ እንደሚገልጹት ፤ በአንድ ትምህርት ቤት ዉስጥ የተጀመረ ረብሻ በመስፋቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመቋረጡ በላይ አንድ ሞተረኛ #ተጎድቶ ሆስፒታል መግባቱን የገለጹ ሲሆን ምሽቱን የሲዳማ ክልል የጸጥታ ኃይል ቀበሌዋን መቆጣጠሩንና የትራንስፖርት ችግሩ መፈታቱን ገልጸውልናል።

በትምህርት ቤት የተጀመረዉ ረብሻ ወደት/ቤቱ የሄዱ እንግዶች ላይ ተቃዉሞ መሰማቱን ተከትሎ የተጀመረ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሀማሮ ይህን ችግር የሚያስጀምሩና የሚመሩ ጸረሰላም ወንጀለኞች እንደሚታወቁና በዚህና በሌሎች ወንጀሎች እንደሚፈለጉ ገልጸዋል።

ከዚህዉ ጋር በተያያዘ አስተያዬታቸዉን የሰጡን የአካባቢዉ ነዋሪና የጸጥታ አካል ደግሞ እንዲህ ያለዉ ሙከራ በተደጋጋሚ እየተሞከረ መሆኑን በማንሳት ችግሩን ከስሩ ለመፍታት በዛኛዉ በኩል  አጎራባች የሆኑ የኦሮሚያና በዚህኛዉም በኩል ያሉ የሲዳማ ቀበሌ ነዋሪዎች ዉይይት ያስፈልጋቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia