TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ባለቤቴ ፓርቲው በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም " - ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ

የብልጽግና ፓርቲ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ዳንዳአ መታሰራቸው " በምንም መለኪያ ትክክል አይደለም " ሲሉ ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አላማየሁ ተናገሩ።

የአቶ ታዬ ባለቤት ፤ አቶ ታዬ ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት ይሄን ስርዓት መሰረት ለማስያዝ ሲሉ ከብዙ ሰዎች እና ቤተሰቦች ጋር እየተጋጩ  እራሳቸውን ሰጥተው እየሰሩ ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን እሳቸው ፓርቲው በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው ፤ እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ወይዘሮ ስንታየሁ አላማየሁ ከትላንት በስቲያ ፌደራል ፖሊስ ከምሽቱ 5 ሰአት ላይ ወደ ቤታቸው መጥቶ ፍተሻ እንደጀመረና ፍተሻው እስከ ምሽቱ 10 ሰአት ድረስ እንደቀጠለ ገልጸዋል።

" ፍተሻው እንደተጠናወቀ ተቀያሪ ልብስ ጠየቁኝና ባለቤቴን ከተኛበት ይዘውት ሄዱ " ሲሉ ተናግረዋል።

" በማለዳው በሜክሲኮ አከባቢ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እንደታሰረ ነግረውን ፣ እዛ ሄደን ስንጠይቅ ምረመራ ላይ ነው ጠብቁ ተባልን። ከጊዜ ቆይታ በኃላ አዚህ የለም በአራዳ የሚገኘው 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሂዱ ተባልን" ሲሉ ገልጸዋል።

እዚያ እንደደረሱ ግን " በአካልም ሆነ በስልክ ልታገኙት አትችሉም፣ ምግቡን ቀምሳችሁ ለፓሊስ ሰጥታችሁ ሂዱ ተባልን " ሲሉ ባለቤታቸው ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ደንደአ ፤ ሰኞ ምሽት በፌደራል ፖሊስ አባል ከተወሰዱ በኋላ የት እንዳሉ እና ምን ላይ እንደሆኑ ለማወቅ እንዳልቻሉም ባለቤታቸው ገልጸዋል።

ትናንት ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ ደግሞ ስልክ ተደውሎ የመንግስትን ቤት በሶስት ቀን ውስጥ ለቃችሁ እንድትወጡ የሚል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ተናግረዋል።

አሁን እየኖሩበት ያሉትን ቤት ከዚህ በፊት በደብዳቤ የተሰጣቸው መሆኑን በመናገር  " አሁንም ውጡ ካሉን እንወጣለን፤ እኛ ቅንጦት አንፈልግም፤ በሰላም ወጥተን መግባት እንፈልጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የጸጥታ ሃይሎች በአቶ ታዬ ዳንዳአ ቤት ነው ያገኙት ተብሎ በሚዲያ የተለቀቁትን እቃዎችን ባለቤታቸው #ያወገዙ ሲሆን ስለ ዝርዘር ሁኔታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አቶ ታዬ በመንግስት ላይ ከሰነዘሩት ትችቶች የላቀ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደነበሩ ወይዘሮ ስንታያሁ ተናግረዋል።

" አቶ ታዬ ደንደአ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ሆኖ ሳለ መብቱን በማጣት መታሰራቸው ትክክል አይመስለኝም " ሲሉም ከኦኤምኤን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ  ተናግረዋል።

@tikvahethiopia