TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም አይታሰብም አሉ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ - የትግራይ ግዛቶችን በወረራ የያዙ ኃይሎች ሳይወጡ፤ - ተፈናቃዮች ወደ ቀደመው ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም የሚባል ነገር #አይታሰብም ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚስተር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ የፈፀመው ወንጀል በሽግግር ፍትህ የሚዳኝ አይደለም " አሉ።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የፓለቲካና ኢኮኖሚ አማካሪ ጆን ሮቢንሰን ትላንት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና የፓለቲካና ኢኮኖሚ አማካሪ ጆን ሮቢንሰን በዋነኝነት በሽግግር ፍትህ ጉዳይ ፣ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በክልሉ የሚገኙ ኃይሎች ስለመውጣት መሰረት በማድረግ መወያየታቸው ተሰምቷል።

አቶ ጌታቸው ፤ " በተለይ ወራሪው የኤርትራ መንግስት በትግራይ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው " ያሉ ሲሆን ይህ ወንጀል በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ፍትህ መዳኘት አለበት ብለዋል።

በኢትዮጵያ እንዲተገበር የሚጠበቀው የሽግግር ፍትህ ትግራይን የዘነጋ እንዳይሆንም ያሳሰቡት አቶ ጌታቸው ፤ " ትግራይ በአሁኑ ሰአት በፌደራል መንግስት ተወካይ የሌላት ፣ የትግራይ ህዝብ ድምፅ የሚሆን አካል በሌለበት የተመሰረተው የሽግግር ፍትህ ክልሉ ያገለለ እንዳይሆን ሊሰራበት ይገባል " ብለዋል።

ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ስለመመለስና የትግራይ ክልልን ግዛታዊ አንድነት ስለ ማስጠበቅ አስመልክተው ማብራርያ የሰጡት ፕረዚደንቱ ፤ " ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ባልተመለሱበት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የፌደራል መንግስት የገለፀው የሪፈረንደም ጉዳይ በፍፁም አይሆንም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በክልሉ ምዕራባዊ ዞን ሙሉ በሙሉ  ፣ እንዲሁም በተወሰኑ የምስራቅ ፣የሰሜናዊ ምዕራብና ደቡባዊ ዞን አከባቢዎች የሚገኙ ወራሪ ሃይሎች በማእከላይ መንግስቱ ትእዛዝ እንዲወጡ ፤ በአከባቢዎቹ ያለው አስተዳደር ፈርሶ በጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር መተካት አለበት " ብለዋል አቶ ጌታቸው ረዳ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ከአሜሪካው ዲፕሎማት ጆን ሮቢንሰን በነበራቸው ቆይታ አገራዊ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በማንሳት የተወያዩ ሲሆን አሜሪካ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ አወንታዊ አስተወፅኦ እንደሚኖራት ዲፕሎማቱ መግለፃቸውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ፅህፈት ጠቅሶ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ዘግቧል።
                    
@tikvahethiopia            
ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎቹ በመኪና አደጋ ተነጠቀ።

ትናንት በቀብሪደሀር ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ፋርዶሳ መሀመድ እና ቢሻሮ አህመድ የሶሲዮሎጂ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንደነበሩ ተገልጿል።

የተማሪዎቹ ህልፈት የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ልብ የሰበረና አስደንጋጭ ክስተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተቋሙ ለሟች ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቻቸው እና ለአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via @tikvahuniversity
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ በክልሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ #መጋለጡን አሳወቀ።

እስከ አሁን 25 ህፃናት የሚገኙባቸው 400 ሰዎች በራብ ምክንያት ሞተዋልም ብሏል። 

በክልሉ ያጋጠመው የድርቅ አደጋ ለመከላከል ያለመ 22 አባላት ያሉት ከተለያዩ የህብረተሰብ ልፍሎች የተውጣጣ " አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ " የተሰኘ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተሰምቷል።

የ " አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ " ግብረ ሃይል ሰብሳቢ የሆኑት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ  ዛሬ ለጋዜጠኞች መገለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ በአሁኑ ሰአት ለረሃብ አደጋ የተጋለጠው ከ2 ሚሊዮን ትግራዋይ ህይወት ለመታደግ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ የክልሉ ተወላጅና ወዳጅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የ " አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ " ግብረ ሃይል ድጋፍ የሚያግዙ ግለሰቦችና ደርጅቶች የሚገለገሉባቸው ሶስት የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች የከፈተ ሲሆን ቁጥሮቹ ፦

* አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 👉00112180095-49

* ወጋገን ባንክ 👉 1001077411101

* የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ 👉 1000592420809 መሆናቸውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                    
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace #GoE #OLA

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA መካከል ከዚህ ቀደም ታንዛኒያ ላይ ሁለት ጊዜ የሰላም ድርድር ተደርጎ ያለ ስምምነት / ወጤት መበተኑ ይታወሳል።

አሁንም ሌላ #ሶስተኛ_ዙር የሰላም ውይይት/ድርድር ሊኖር የሚችልበት ዕድል መኖሩን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

- የመጀመሪያው ንግግር በጣም ጥሩ ርቀት ሄዶ ነበር ፤ በዚህም ብዙ መካሰስ ቀርቶ ለሚቀጥለው ዙር ለመነጋገር እናመቻች በሚል ነው የተጠናቀቀው።

- ሁለተኛው የሰላም ድርድር መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገን አግባቢዎች ሄደው ከሳምንት በላይ ፈጅተዋል። አዝማሚያው ጥሩ ነበር።  መጨረሻ የማያግባቡ ነጥቦች መጡ። በዚህም ትንሽ የተሻለ ኃይል ያለው ሰው ይምጣ ተብሎ ከመንግሥትም ከነሱም ሄዷል። በዚህም ጊዜ ጥሩ ሂደት ነበር።

- በህገ-መንግስት ጥላ ስር "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት መቀበል ላይ ፤ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት በምርጫ የመጣ Legitimacy ያለው መሆኑ ላይ መግባባት ተደርሶ ነበር። ወደ ዝርዝር ሲመጣ ግን እነዚህን መግባባቶች የሚሸረሽር ነገር ነው የመጣው።

- ስምምነቱ በመጨረሻ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ደረጃ / ወደ ሰነድ ደረጃ ሲደርስ ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ተነስትዋል።

ምንድናቸው ?

* አንደኛው --- ' #ስልጣን_አካፍሉኝ ' ነው እያንዳንዱን ጠብመንጃ የያዘ፣ ጫካ የገባ ሁሉ ስልጣን ለማግኘት ከሆነ የሚደራደረው ይሄ ለሀገር ሰላም አይሰጥም።

ጫካ እየገቡ ፣ ግጭት የፈጠሩ ፣ ህዝቡን እያበሳሰቡ ከዛ እንነጋገር እያሉ " እሺ " ሲባል ስልጣን አካፍሉኝ የሚባል ነገር ካለ መቼም ስርዓት አይመጣም። ሀገር ሰላም አይሆንም።

ምሳሌ ብንወድስ ፦ ከአማራ፣  ከቤንሻንጉል ጉምዝም ከሌላውም የታጣቁ ኃይሎች ስልጣን አካፍሉኝ ካሉ ስንት የታጠቀ ኃይል ስልጣን ሲካፈል ይኖራል ? ይሄ ኢትዮጵያን ይጎዳል።

እንዲህ አይነት ጥያቄ ነው ይዘው የቀረቡት (OLAን ማለታቸው ነው)።

መንግሥት ስልጣን ላካልፍ ቢልም ፍፁም አይችልም ፤ መብትም የለውም። #ማሳተፍ ግን ይችላል። ሸኔን ጭምር ማሳተፍ ይችላል።

ዋናው መሰረታዊ ልዩነት ይሄ ነው። ስልጣን አካፍሉኝ ስሉም እራሳቸው ፕሮፖዛል አስቀምጠው ፤ እዚህ ላይ ስልጣን ስጡኝ የሚል ነበር።

* ሁለተኛው --- ወደ ' DDR ' አልገባም ነው።

በሰላም ለመታገል ፣ ፓርቲ አቋቁሞ ለመታገል ፣ ወደ ህዝብ ምርጫ ለመቅረብ የገጠር ትጥቅ ትግል ትቶ በሰላም ወደ ህዝብ መመለስ ነው። ለዚህ ደግሞ ትጥቅ መፍታት አለባቸው።

DDR / Disarm, Demobilized , Reintegrate መሆን አለባቸው። ይሄ ዓለም የሚሰራበት ነው። ማንኛውም ግጭት የተፈታውም በዚህ ነው። ይሄን ለመቀበል የመቸገር ነገር ተከስቷል።

ትጥቅ ሳይፈታ ፦
° እንዴት እንደራደራለን?
° እንዴት Demobilize ይሆናሉ?
° እንዴት ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ?

መንግስት በግልፅ DDR ፕሮግራም ውስጥ መግባት አለብን ብሏል። በአንድ ሀገር በፍፁም ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም። ትጥቅ የመያዝ መብት ያለው መንግስት ብቻ ነው።

ይሄንን #መቀበል_ነበረባቸው። በዓለም ላይ ይሄን ሳይቀበሉ ስምምነት የለም። ድርድር ብሎ ነገር የለም።

ንግግሩ ጥሩ ሄዱ ከላይ ባሉት ሁለት ምክንያት ነው መጨረሻ ላይ የቆመው።

- ሶስተኛ ዕድል ይኖራል ? እኔ የሚኖር ይመስለኛል።

- ሁለቱን #ያልተስማማንባቸው_ነጥቦችን በተሳሳተ መንገድ እንዲወስዱ በማድረግ ሌሎች ኃይሎች እጅ አላቸው። OLA ላይ ታዝሎ የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። ከሀገር ውስጥም ከሀገ ውጭም አሉ። ባዕዳንም ዜጎችም እነዚህ ኃይሎች OLA በሰከነ መንገድ አይቶ ስምምነቱን እንዳይቀበል አድርገውታል። OLA ሌላ መስማት አልነበረባቸውም፤ ችግር ውስጥ ያሉት እራሳቸው ስለሆኑ እራሳቸው መወሰን ነበረባቸው።

(ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እነዚ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተናገሩም)

- ሌላው ኃይል ጣልቃ ስለገባ በዓለም experience ታይቶ የማይታወቅ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ መንግሥትን አስቸግረዋል (OLA ማለታቸው ነው)።

- ሶስተኛ ዕድል ሊኖር ይችላል። ሰከን ብለው አስበው አደራዳሪዎች ጭምር የሚያምኑበት የመጨረሻው ወረቀት / ዶክመንት / የቀበል ደረጃ ከደረሱ ሶስተኛ ውይይት ሊኖር ይችላል።

- ምናልባት ሶስተኛ ውይይት እንደሁለተኛው ውይይት ሰፊ ላይሆን ይችላል እስካሁን የተደከመበት ሰነድን መቀበል ላይ ከተደረሰ ሶስተኛው ውይይት ሊኖር ይችላል፤ ሶስተኛው ውይይት የመጨረሻም ይሆናልም ብዬ ገምታለሁ ወደሰላም ለመምጣት ወይም እስከመጨረሻው ሁለተኛ ላለመነጋገር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል።

🕊 የኢጋድ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሳምንታት በፊት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ሰጥተው በነበረው መግለጫ ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀመራል ብለው #ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን አዲሱን Kimem Itel Pro እናስተዋዉቅዎ! በአቅራቢያችን ወደ የሚገኝ የሳፋሪኮም ሱቅ ጎራ ብለን የግላችን እናድርገዉ።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
ዓመታትን የፈጀው መንገድ . . .

" የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

ግንባታው ከተጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ወደ መጠናቀቁ መድረሱ ተነግሯል።

ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደቡብ የአዲስ አበባ ክፍል እየገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው መንገድ ፤ ከደቡብና ከምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለመግባትና ለመውጣት፣ ለረጅም ዓመታት ብቸኛው የወጪና ገቢ መተላለፊያ መስመር ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

መንገዱን ያለውን የትራፊክ  እንቅስቃሴ በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችል በሚል ግንባታ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እንደሚለው ፤ ከመንገድ ፕሮጄክቱ አጠቃላይ ግንባታ ሂደት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተፈፅሞ በከፊል አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ነገር ግን፦
- #ከፋይናንስ
- #ከወሰን_ማስከበር ጋር በተያያዘ በገጠሙ ችግሮች ምክንያት ቀሪው የግንባታ ሥራ በተፈለገው ልክ ሳይፈፀም መቆየቱን አመልክቷል።

ለችግሮቹ በተሰጠ መፍትሄ የፕሮጀክቱ ግንባታ ቀጥሎ አሁን ላይ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩን አሳውቋል።

መ/ቤቱ በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ክረምት በጭቃ፣ በጋውን በአቧራ ሲፈተን እንደነበር ገልጿል።

በዚህ መንገድ ምክንያት የትራፊክ እንቅስቃሴው እንደ ኤሊ ጉዞ እያዘገመ ይጓዝ እንደነበረም ገልጾ አሁን ግን ወደመጠናቀቁ መድረሱን አሳውቋል።

አሁን ላይ ቀደም ሲል ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ በቆየው የመንገዱ የቀኝ ክፍል ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የእግረኛ እና የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መስመርና ቀሪ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።

ቃሊቲ ማሰልጠኛ የቀለበት መንገድ መሸጋገሪያ ላይ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ ማገጣጠሚያ ግንባታ ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃሉ ብሏል።

አሸከርካሪዎች በግንባታው ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ችግሮች እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ድርቁ ከ1977ቱም የከፋ ነው " - የትግራይ ክልል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) በትግራይ ስላለው የድርቅ ሁኔታ ምን አሉ ?

- ድርቁ በ5 የትግራይ ክልል ዞኖች ተከስቷል።

- በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 ነበር። አሁን ያጋጠመን ከዚህም በላይ ነው።

- በዚህ ድርቅ ምክንያት 2 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ተጋልጧል።

- ከ400 በላይ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። 25ቱ ሕጻናት ናቸው።

የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ያቋቋመው "  አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ " የተሰኘው ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ሰብዓዊነት የሚሰማው ሁሉ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ። እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦ - ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ - ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ…
#ሙስና #ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ኃላፊ የነበሩት ታምሩ ግንበቶን ጨምሮ 60 የተቋሙ ባልደረቦች 15 የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው።

የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር ከነበሩት ታምሩ ግንበቶ በተጨማሪ የውጭ ዜጎች ቁጥጥር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ የኬላዎች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ቦጋለም ይገኙበታል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በክሱ የእያንዳንዱ ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን ዘርዝሯል።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ፦

* ፎርቲን አቬጋ በተባለ ድርጅት የሚሠሩ 12 ግብፃዊያን ለቪዛ ቅጣት ይከፍሉ የነበረውን 24 ሺህ ዶላር በራሳቸው ትዕዛዝ 14 ሺህ ዶላሩን በመቀነስ በመመሪያው መሠረት ባልተገባ መንገድ የተቀነሰውን በዶላር መክፈል ሲገባቸው በኢትዮጵያ ብር እንዲከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል።

* ሀይንፊን፣ ሀድዙ የተሰኙ የቻይና ኩባንያ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ብሎም ሻሎም አስመላሽ ኪዳኔ እና ነጃት ዓሊ መሐመድ ለቪዛ ቅጣት በዶላር መክፈል ከነበረባቸው 4 ሺህ ዶላር ያህል መመሪያ በመጣስ እንዳይከፍሉ በማድረግ መንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

* የማይገባ ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ ተገቢ ማጣራት ሳይከናወን ነዋሪነታቸው በሶማሊ ላንድ ሐርጌሳ ለሆኑ 68 ግለሰብ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጥ በማድረግ የሀገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት የፈፀሙ በመሆኑ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከስሰዋል።

1ኛው ተከሳሽ ታምሩ ግንበቶ እና 2ኛ ተካሽ ጅላሉ በድሩ በወንጀል ከሀገር እንዳይወጡ ትዕዛዝ ለተላለፈባቸው 6 ቻይናውያን መካከል ዙ ጂያን እና ዛንግፒንግል የተሰኙ ሁለቱ የተጣለባቸው እግድ ተነሥቶ የመውጫ ቪዛ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው በማድረጋቸው ዐቃቤ ሕግ ሁለቱንም ግለሰቦች በፈፀሙት ሥልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል ከሷቸዋል።

ዐቃቤ ሕግ የእያንዳንዱን ተከሳሽ የወንጀል ተሳትፎን በመጥቀስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የሙስና ወንጀል ጉዳይ ችሎት አቅርቧል።

በተከሳሾች ስም ፦

- 14,523,647.36 ብር (14 ሚሊዮን 523 ሺህ 647 ከ36 ሣንቲም)
- አክሲዮን 383,000.00 ብር (383 ሺህ)
- 8 ቤቶች ያሉ ሲሆን በፍትሕ ሚኒስቴር በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በኩል ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት እንዲሁም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅርብ ወንጀል ምርመራ እየተጣራ እና ምርመራ እየቀጠለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ክሱን በንባብ ለማሰማት ፍርድ ቤቱ ለሰኞ ታኅሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለመካሄድ 3 ቀን ቀረው፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

#Global_Bank_Ethiopia #Our_Shared_Success #Bank_In_Ethiopia #Shareholders_Meeting
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ባለቤቴ ፓርቲው በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም " - ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ

የብልጽግና ፓርቲ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ዳንዳአ መታሰራቸው " በምንም መለኪያ ትክክል አይደለም " ሲሉ ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አላማየሁ ተናገሩ።

የአቶ ታዬ ባለቤት ፤ አቶ ታዬ ሙሉ ጊዜያቸውን በመስጠት ይሄን ስርዓት መሰረት ለማስያዝ ሲሉ ከብዙ ሰዎች እና ቤተሰቦች ጋር እየተጋጩ  እራሳቸውን ሰጥተው እየሰሩ ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን እሳቸው ፓርቲው በእግሩ እንዲቆም መስዋእትነት ከፍለው ፤ እንደዛ ሰርተው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ወይዘሮ ስንታየሁ አላማየሁ ከትላንት በስቲያ ፌደራል ፖሊስ ከምሽቱ 5 ሰአት ላይ ወደ ቤታቸው መጥቶ ፍተሻ እንደጀመረና ፍተሻው እስከ ምሽቱ 10 ሰአት ድረስ እንደቀጠለ ገልጸዋል።

" ፍተሻው እንደተጠናወቀ ተቀያሪ ልብስ ጠየቁኝና ባለቤቴን ከተኛበት ይዘውት ሄዱ " ሲሉ ተናግረዋል።

" በማለዳው በሜክሲኮ አከባቢ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እንደታሰረ ነግረውን ፣ እዛ ሄደን ስንጠይቅ ምረመራ ላይ ነው ጠብቁ ተባልን። ከጊዜ ቆይታ በኃላ አዚህ የለም በአራዳ የሚገኘው 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሂዱ ተባልን" ሲሉ ገልጸዋል።

እዚያ እንደደረሱ ግን " በአካልም ሆነ በስልክ ልታገኙት አትችሉም፣ ምግቡን ቀምሳችሁ ለፓሊስ ሰጥታችሁ ሂዱ ተባልን " ሲሉ ባለቤታቸው ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ደንደአ ፤ ሰኞ ምሽት በፌደራል ፖሊስ አባል ከተወሰዱ በኋላ የት እንዳሉ እና ምን ላይ እንደሆኑ ለማወቅ እንዳልቻሉም ባለቤታቸው ገልጸዋል።

ትናንት ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ ደግሞ ስልክ ተደውሎ የመንግስትን ቤት በሶስት ቀን ውስጥ ለቃችሁ እንድትወጡ የሚል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ተናግረዋል።

አሁን እየኖሩበት ያሉትን ቤት ከዚህ በፊት በደብዳቤ የተሰጣቸው መሆኑን በመናገር  " አሁንም ውጡ ካሉን እንወጣለን፤ እኛ ቅንጦት አንፈልግም፤ በሰላም ወጥተን መግባት እንፈልጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የጸጥታ ሃይሎች በአቶ ታዬ ዳንዳአ ቤት ነው ያገኙት ተብሎ በሚዲያ የተለቀቁትን እቃዎችን ባለቤታቸው #ያወገዙ ሲሆን ስለ ዝርዘር ሁኔታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አቶ ታዬ በመንግስት ላይ ከሰነዘሩት ትችቶች የላቀ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደነበሩ ወይዘሮ ስንታያሁ ተናግረዋል።

" አቶ ታዬ ደንደአ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ሆኖ ሳለ መብቱን በማጣት መታሰራቸው ትክክል አይመስለኝም " ሲሉም ከኦኤምኤን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ  ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለማባረር ዘግይተዋል " - ጠበቃና የህግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ ከቀናት በፊት አዳማ በነበረ መድረክ " ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር እራሱ #ሰላም_ነው_ወይ ? ሰላም ሚኒስቴር ሰላም መስበክ ሲገባው በመ/ቤቱ ሆነው በስውር አማፂያንን የሚደግፉ ሰዎች አያለሁ " ሲሉ በወቅቱ የሚኒስትር ዴኤታ ለነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ጥያቄ ያቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ኢብሳ የአቶ…
#ከትላንት_የቀጠለ

" ታዬዎች እና የታዬ ቢጤዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደሉም፣ ብልፅግና ውስጥ አሉ። ብልፅግና ብልግና የበዛበት ነው " - አቶ ወንድሙ ኢብሳ

የአቶ ታዬ ደንደዓ ሰሞነኛ ጉዳይ እውነትም በሕግ ሊያስጠይቃቸው ይችላል ? 

ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ኢብሳ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የተናገሩት ፦

* በሕግ አግባብ እኔ ከአመት በፊት ነው የጮኹት በተጨባጭ ታዬ የአገሪቱን ሕገ መንግሥት እየጣሱ ነው ብዬ፤ ለጠ/ ሚኒስትሩ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ስወተውት ነበር። 

* በሕግ ተጠያቂነት አለባቸው። አንደኛ የሕዝብ ተመራጭ ናቸው። የብልፅግና ፖርቲ አባል ነኝ ብለው በ2013 ዓ.ም ተወዳድረዋል። አሸንፈዋል። ሥልጣን ላይ ተቀምጠዋል። 

* ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ናት። ከባድ ማኖ ነው የነኩት። ይሄ 'መንግሥት ሰላም አይፈልግም፣ ፀረ ሰላም ነው፣ እርቁን አክሽፏል ብለው ሲናገሩ '፣ ሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግርም እንደሚያስጠይቅ ይታወቃል።

* የጨፌ ኦሮሚያ ራሱ ኢሚዩኒቲውን አውርዶ በሕግ መጠየቅ ይችላል።

* ምንም ሳያስፈልግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊጠየቁ ይችላሉ። 101 አንቀፆች አይሰሩም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜ። 5 አንቀፆች ናቸው የሚሰሩት። 

* ይሄ ኢሚዩኒቲ አለው፣ ያለመከሰስ መብት አለው የሚሉት የሕገ መንግሥቱ አንቀፆች በሙሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት አይሰሩም። በዚህም ሊጠየቁ ይችላሉ።

* የጥላቻ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ በፅሑፍ በማቅረባቸውም ሊጠየቁ ይችላሉ።

* ወይ ለይቶላቸው እንደነ ክቡር ለማና ገዱ ተቃውሞ በሰለጠነ ቋንቋ ገልፀው አርፈው አልተቀመጡ፤ ሥልጣን አልፈልግም ብለው እኮ ከመከላከያ ሚኒስቴር አለቀቁም ፤ ለማ መገርሳ እኮ የመከላከያ ሚኒስቴርን ነው የለቀቁት።

* ታዬ በሕግም በምክንያትም ሊጠየቁ ይችላሉ። እንዳውም ግብረ ኃይል ቤቱን ፈትሾ ያገኘው መሳሪያ እውነት እንደሚባለው ከሆነ።

* ታዬን መሳይ ብልፅግናዎችም ተደብቀው አሉ። በየመ/ቤቱ መፈተሽ አለበት።

አቶ ወንድሙ ከሳምንት በፊት በሰጡት ገለጻ፣ "ለምሳሌ የሁለተኛው የ " ሸኔ " እና የመንግሥት ድርድር ሲደረግ ከሰላም ሚኒስቴር ውስጥ የሆኑ ሰዎች (ስማቸው ከተፃፈ አላውቅም) ከሕውሓት ጋር የተደራደርክ፣ ሰላም የፈጠርክ " ሸኔ " ኦሮሞዎችን ለምንድን ነው እነርሱ የጠየቁትን ጥያቄ በሙሉ መልስ እሺ ያላልከው ? ያሉ አሉ" የሚሉ ሰዎች ከሰላም ሚኒስቴር ውስጥ እንዳሉ አስረድተው ነበር።

ከላይ የጠቀሱትን ንግግር አቶ ታዬ ደንደአ ናቸው የተናገሩት ? የሚያውቁት ነገር አለ ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸው አቶ ወንድሙ ተከታዩን መልሰዋል፦

- በሚገባ እንጅ። እኔ እኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ላይ ለማባረር ዘገይተዋል የምለው ለዚህ ነው። የዛሬ ዓመት ሰላም ሚኒስቴር በታዬ ደንደአ ምክንያት ሰላምን አጥቷል፣ ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ናችሁ ወይ ? ብዬ ጠይቄ ነበር።

- ታዬ፣ ለማ መገርሳ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ከሚቃወመው አክራሪ ፅንፈኞች ጋር በመከለከያ ሚኒስቴር ውስጥ ሌሊት ሌሊት ስብሰባ ሲያደርጉ እንደነበር መረጃ ስላለኝም ጭምር ነው።

- የኦሮሚያ ክልል ሕጋዊ መንግሥት ይነሳና የአማፂው ኃላፊ ይቀመጥ፣ ይሄ አሁን ያለው የኦሮሚያ ክልልም ሆነ ፌደራል ይፍረስና አማፂዎች መንግስት ያቋቁሙ የሚል ነው አቋማቸው።

- ታዬዎችና የታዬ ቢጤዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደሉም፣ ብልፅግና ውስጥም አሉ። ብልፅግና ብልግና የበዛበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያደረጉት ትዕግስት እና ደግነት ይበቃቸዋል።

https://telegra.ph/TE-12-13-2

@tikvahethiopia