TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ #ባሌ

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባባሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና እና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተካሄደው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል።

የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተመዘገበው በኢትዮጰያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ ሲሆን በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን ነው።

በትላንትናው ዕለት የጌድኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር #በዓለም_ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።

#የቱሪዝም_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia