TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.6K photos
1.54K videos
215 files
4.22K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት በተመደቡ የመቐለ ከተማ አመራሮች አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። አመራሮቹ በሰራዊት ታጅበው ሬድዮ ጣቢያውን እንደተቆጣጠሩት ተነግሯል። ምናልባትም በቀጣይ ደግሞ የድምፂ ወያነ እና ትግራይ ቴሌቪዥን ሚድያዎችን ሊያዙ እንደሚችሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ለመስማት ችሏል።…
#NewsAlert

የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የኒውዚላንድ፣ የጃፓን፣ የኖርዌይ፣ የቤልጂየም፣ የቡልጋሪያ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የዴንማርክ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቬንያ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ህብረት ልኡክ በኢትዮጵያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም መግለጫቸው ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ለውጦችን / ሁኔታዎችን እና እየተባባሰ ያለውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

" እ.ኤ.አ. ህዳር 2022 ለተፈጸመው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ ደግመን አጽንኦት እንሰጣለን " ብለዋል።

ይህ ስምምነት የመሳሪያ ድምጽ ጸጥ እንዳደረገም አመልክተዋል።

በፍጹም ወደ ሁከት ፣ ግጭት ፣ ጦርነት መመለስ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።

ሁሉም ወገኖች ተባብሰው አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ውጥረቱን በማርገብ ስምምነቱን እንዲጠብቁ አጥብቀው አሳስበዋል።

ማንኛውም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ ከአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም በአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች ጋር በትግራይ ስላለው ሁኔታ እና አስተዳደራቸው እየገጠመው ስላለው ፈተና ሰፋ ያለ ውይይት አድርገው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሻዕቢያ ? ➡️ " በፕሪቶሪያ ስምምነት አኩርፎ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተጣላ ኃይል ጋር ተሰልፈህ የኢትዮጵያን መንግሥት ማስወገድ የሚቻልበት እድል ካለ ብለህ መንቀዥቀዥ በጣም አደገኛ ነው !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ " ትግራይ ውስጥ በሚፈጠር ትርምስ እናተርፋለን የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ። የኤርትራ መንግሥት አንዱ እንደሆነ አውቃለሁ። …
#Tigray

🔴 " ከኤርትራ መንግስት ግንኙት አላችሁ የሚል ወሬ በሬ ወለደ ውሸት ነው " - ጉባኤ ያካሄደው ህወሓት 

" የኤርትራ መንግስት የያዘው ትግራይ መሬት የለም " - የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን 


ጉባኤ ያካሄደ ህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ኣማኒኤል ኣሰፋ " ' በትግራይ መፈንቅለ መንግስት ተካሂደዋል ' የሚባለው ፍፁም ውሸት ነው ፤ ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለውን የስልጣን ድርሻ ከማስተካከል የዘለለ አንዳች የወሰደው እርምጃ የለም " አሉ።

" ህዝቡን በተዘባ ወሬ ወደ አላስፈላጊ ውዥንብር በማስገባት መሬት ላይ በሌለ ግጭት ውጥረት ውስጥ ማስገባት ሃላፊነት ከሚሰማው ፓለቲከኛ የሚጠበቅ አይደለም " ሲሉም ተናግረዋል።

" ህዝቡ የሚያሰጋ ነገር በሌለበት ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ ለማወጣትና አስቤዛ ለመገዛት መሯሯጥ አይገባውም " ሲሉ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል በስፋት ከባንክ ገንዘብ እያወጡ አስቤዛም በስፋት እየገዙ ይገኛሉ።

አቶ አማኒኤል ፤ " ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ለፌደራሉ መንግስት የሰጠው እውቅናን በማጠናከር በመመካከር መስራቱን ይቀጥላል " ያሉ ሲሆን " ፓርቲው ባነሳቸው የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ምትክ ከፌደራል መንግስት በመተማመን አዲስ ፕሬዜዳንት ይመርጣል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ህወሓት የትግራይ ሰራዊት በማያሳምን መንገድ ለመበታተን የሚደረግ ሴራ እንጂ DDR መተገበርን አይቃወምም " ያሉት ምክትል ሊቀ-መንበሩ ፤ " ፕሬዜዳንት ነበር " ሲሉ የጠሩዋቸው አቶ ጌታቸው ረዳ በከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የወሰዱት እርምጃ " በሌለ ስልጣን የተደረገና ተቀባይነት  የሌለው " ሲሉ አጣጥለውታል።

አቶ አማኒኤል የተወሰኑ የህወሓት አንጃዎች ከሻዕቢያ ጋር  ግንኙነት አላቸው በሚባለው ጉዳይ " ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙት አላችሁ የሚል ወሬ በሬ ወለደ ውሸት ነው " ሲሉ መልሰዋል።

" ከኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ውጪ የሚካሄድ ግንኙነት የለም "  ሲሉም አክለዋል።

በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ስለሚገኙ የኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ቦታዎች ምንም ያሉት ነገር የለም።

በተያያዘ " የኤርትራ መንግስት የያዘው የትግራይ መሬት የለም " ሲሉ አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን ፅፈዋል። 

ባለስልጠኑ የማነ ገ/መስቀል  " ይድረስ ለግጭት ጠማቂዎች " በሚል በX ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መተግበርና አለመተግበር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እንጂ ኤርትራ አይመለከትም " ብለዋል።  

" የህወሓት መከፋፈል ኤርትራን አይመለከትም " ያሉት ባለስልጣኑ " የትግራይ ህዝብ የውስጥ ሰላም እንዲበጠበጥ ኤርትራ ምንም ዓይነት ፍላጎት የላትም " ብለዋል።

" የተለያየ የፓለቲካ እሳቤ ያላቸው የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች የቀይ ባሀርን አጀንዳ እንደ አዲስ በማቀጣጠል የአፍሪካ ቀንድን ለሌላ ተጨማሪ ውጥረት ከማስገባት እንዲቆጠቡ " በማለትም ባለስልጣኑ በX ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አሳስበዋል።

ባለስልጣኑ ይህን ይበሉ እንጂ  የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ የትግራይ የደንበር አከባቢ በርካታ ቦታዎች ይዞ ይገኛል።

በርካታ በትግራይ ምስራቃዊ ፣ ማእከላዊ ሰሜን ምዕራብ ዞን የሚገኙ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ደጋግሞ የዘገበው ቲክቫህ  ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አሁንም በመሬት ላይ የተለወጠ አዲስ ነገር እንደሌለ የአከባቢው ነዋሪዎች በመጠየቅ አረጋግጧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንዲሁም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ነበር። ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያን መስጠታቸው ታውቋል። ምን ተባለ? …
" በውጭም ሆነ በውስጥ ግፊት የሚካሄድ ጦርነት የለም " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ የትግራይ የፓለቲካ ችግሮች ለመፍታት በውስጥም በውጭም ለመፍታት ሲደረግ የቆየው ጥረት አልተሳካም ፤ ቢሆንም ይቀጥላል ብለዋል።

የተካሄደው ጥረት ሊመክን የቻለው በአደራዳሪዎች የተነሳሽነት ማነስ ሳይሆን  በተደራዳሪዎች ድክመት ምክንያት ነው ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ ፤ ቢሆንም ችግሩ ተባብሶ በውስጥም ይሁን በውጭ ጫና  የሚካሄድ ጦርነት እንዳይፈጠር እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ያለው የፓለቲካ ችግር ከክልሉ አቅም በላይ ስላይደለ የፌደራል መንግስት ችግሩ ለመፍታት ጣልቃ አይገባም ያሉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ ችግሩ ፓለቲካዊ መፍትሄ ያገኛል ሲሉ አመላክተዋል።

" ወቅታዊ ችግሩ አንዱን በመሾምና ሌላውን በመሻር አይፈታም ፤ ችግሩ ፓለቲካዊ ነው መፍትሄውም እንዲሁ ፓለቲካዊ ነው " ሲሉ አክለዋል

በወጣቱ የለውጥና የተጠቃሚነት ፍላጎት አለ ፤ ቢሆንም የለውጥ እና የተጠቃሚነት ፍላጎቱ በስርዓት እንጂ በዘፈቀደ መሆን የለበትም ስለሆነም ወጣቱ የፀጥታና የሰላም ባለቤት መሆን አለበት ብለዋል።

በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት አሳዳጅ እና ተሳደጅ የሚል ትርክት እንዳይፈጠር ስጋት አለ ያሉት ጀነራሉ ፤ ይህንን የተሳሳተ አስተሳሰብ ከወዲሁ ለማረም በጊዚያዊ አስተዳደር የስልጣን እርከን የሚገኙ  አመራሮች ተረጋግተው ስራቸው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
" በውጭም ሆነ በውስጥ ግፊት የሚካሄድ ጦርነት የለም " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ የትግራይ የፓለቲካ ችግሮች ለመፍታት በውስጥም በውጭም ለመፍታት ሲደረግ የቆየው ጥረት አልተሳካም ፤ ቢሆንም ይቀጥላል ብለዋል። የተካሄደው ጥረት ሊመክን የቻለው በአደራዳሪዎች የተነሳሽነት…
በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ?

(ከቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል)

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና በክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ላይ ያሳለፉትን ጊዚያዊና ዘላቂ እግድ ተከትሎ በትግራይ ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች በመታየት ላይ ይገኛሉ።

የቲክቫህ አባል ከመጋቢት 1/2017 ዓ/ም በኃላ በትግራይ ያለውን ፓለቲካዊ ትኩሳትና አጠቃላይ ሁኔታ ሲከታተል ቆይቷል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከበፊት ባልተለመደ ሁኔታ የግል ሚድያ ጋዜጠኞች በማሳተፍ ሰኞ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ተከትሎ ከምሸቱ 4:00 ሰዓት 3 ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች በጊዚያዊነት ማገዳቸው በደብዳቤ አስታወቁ።

በነጋታው መጋቢት 2/2017 ዓ.ም የክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ የሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች እግድ " ተቀባይነት የሌለውና የማይተገበር " ሲል የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት የሚፃረር መግለጫ ሰጠ።

የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫ ፈጣን ማሰተባበያ መግለጫ በመስጠት ያጣጣለው የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት አስከትሎ የቢሮው ሃላፊ ከማንኛውም የመንግስት ስራ በዘላቂነት ማገዱን አስታወቀ።

በዛው ቀን መጋቢት 2/2017 ዓ.ም አመሻሽ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ አዲስ አበባ ተጓዙ።

መጋቢት 3፣ 4፣ 5
/2017 ዓ/ም ለአገር ውስጥና የውጭ ሚድያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ከአዲስ አበባ ሰጡ።

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ተቀማጭ ለሆኑ ዲፕሎማቶሽ የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን አብራርተዋል ።

ፕሬዚዳንት
አቶ ጌታቸው ረዳ ከጻፏቸው የእግድ ደብዳቤዎችና መግለጫዎችና ውይይቶች በኋላ ያሉ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ ?

ከመጋቢት 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ የተፈጠረው ፓለቲካዊ ቀውስ ተከትሎ ባንኮች (በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) በሮች በረጃጅም ሰልፎች ተሞልተው ፤ የተለያዩ ባንኮች የATM ማሽኖችም ገንዘባቸው ተሟጦ ታይቷል።

መቐለ ጨምሮ በሌሎች ከተሞች እህል ጨምሮ በበርካታ መሰረታዊ ሸቀጦች ከፍተኛ የሚባል የዋጋ ጭማሪ አለ ፤ በጤፍ ብቻ በኩንታል አስከ 2 ሺህ ብር ጭማሪ ተደርጓል።

በአውቶቡስ እና በአውሮፕላን ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ የሚጓዝ ህዝብ ቁጥር ብዛት አለው።

እስከ ቀጣዩ ሀሙስ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም ድረስ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ የአየር ጉዞ ትኬት ተቆርጦ አልቋል።

ሰላም ባስ በመሰሉ ትልልቅ የአገር አቋራጭ የአውቶቡስ አገልግሎት የሚሰጡ የትራንስፓርት ድርጅቶችም እስከ ማክሰኞ መጋቢት 9
/2017 ትኬታቸው ሸጠው ጨርሰዋል።

የተፈጠረው ውጥረት በሆቴል ቱሪዝም ኢንዳስትሪው ላይ አሉታዊ ጫናው ማሳደር መጀመሩ የሆቴል ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች ተናግረዋል።

ውጥረቱን ተከትሎ በተፈጠረ የነዳጅ  ዋጋ መወደድ  ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረገው ክፍያ በእጥፍ ጨምሯል።

በነዳጅ እጥረት  ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች ይታያሉ።

አስርና ማንገላታት
?

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም አመሻሽ ለሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ   " በትግራይ ያለው የፓለቲካ ቀውስ ከክልሉ አቅም በላይ ስላይደለ የፌደራል መንግስት ችግሩ ለመፍታት ጣልቃ አይገባም ፤ በተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት ምክንያት አሳዳጅ እና ተሳደጅ እንዳይኖር እየተሰራ ነው ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ  የስራ ኋላፊዎች ተረጋግተው ስራቸው ይስሩ " በማለት ቢያሳስቡም መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ግን እሳቸው ያሉትን አያሳይም።

አሁን በተጨባጭ በጊዚያዊ አስተዳደሩ በተሾሙ አመራሮች በመመራት ላይ የሚገኘው ደቡባዊ ዞን ብቻ ነው። ከዛ በመለስ ባሉት ዞንና ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ሹመኞች የሉም።

ባለፉት ቀናት በተፈጠረው ፓለቲካዊ ቀውስ ምክንያት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጨምሮ ሌሎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ሹመኞች ከተሞች ላይ አይታዩም። ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙም በርካታ ናቸው።

ባለፈው ሰኞ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ለአጭር ጊዜ ተይዘው የተለቀቁት የምስራቃዊ ዞን የፀጥታና ሰላም ሃላፊ ኪዱ ገ/ፃድቃን ዳግመኛ ከተያዙ ቀናት ተቆጥረዋል ፤ የዓዲጉዲም ከተማ ከንቲባና ጥቂት የካቢኔ አባላት ታስረው መለቀቃቸው ፣ በሳምረ ከተማ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ አንድ አባል መታሰራቸው ተረጋግጧል።

አቅጣጫውን ባልለየው ውጥረት ምክንያት የትግራይ ነዋሪዎች ግራ ተጋብተዋል።

በአጠቃላይ በክልሉ ሁኔታዎች ልክ አይደሉም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘገባና ትዝብቱ እየተከታተለ ያቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" ከቀበሌ የነዋሪ መታወቂያ ውጪ ሌላ  መታወቅያ ይዞ መንቀሳቀስ ይከለከላል "- የትግራይ ክልል ሰላምና የፀጥታ ቢሮ 

➡️ " መታወቂያው በሁሉም አከባቢዎች ተማልቶ ባልተዳረሰበት ሁኔታ ይህንን መሰል አስገዳጅ መግለጫ ማውጣት ተገቢ አይደለም " - የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች  

የትግራይ ክልል የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ከቀበሌ ነዋሪ ማረጋገጫ መታወቂያ ውጪ በሌላ መንቀሰሳቀስ ይከለከላል ሲል ያወጣው  መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል።

መግለጫውን በማስመልከት " ፋይዳ ፣ ፓስፓርት ፣ የባንክ ደብተርና የተለያዩ የመንግስትና የግል መስራቤቶች መታወቅያዎች ዋጋ  የሚያሳጣ ልክ ያልሆነ መግለጫ ነው " በማለት አስተያየት የሰጡ አሉ።

" ከነዋሪዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ ከማለም ውጪ የሚተገበር መግለጫ አይደለም " ያሉም አልጠፉም።

" በክልሉ ወጣት ያለውንና የሚታየውን ሰፊ የለውጥ ተነሳሽነትና ፍላጎት ለማዳካም እና ለማፈን ያለመ ነው " የሚል ጠንካራ  አስተያየት ያንሸራሸሩ ወጣቶችም  አሉ። 

የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያወጣው መግለጫ የቀበሌ ነዋሪ ማረጋገጫ መታወቅያ ተዘጋጅቶ ለእደላ ዝግጁ መሆኑን እና ነዋሪው እየወሰደ እንደሆነ ያመላክታል። 

" ከቅርብ ጊዜ በኋላም ያለ የቀበሌ የነዋሪ ማረጋገጫ መታወቅያ ሌላ መታወቅያ ይዞ  መንቀሳቀስ ስለሚቆም ሁሉም ነዋሪ ተገቢውን ነገር አማልቶ ወደ ሚኖርበት የቀበሌ አስተዳደር በመሄድ መታወቅያ መያዝ ይኖርበታል " ይላል መግለጫው።  

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫን ለማረጋገጥ ወደ ተወሰኑት የመቐለ የቀበሌ መስተዳደሮች ተዘዋውሮ እንደተመለከተው የተባለውን የነዋሪ መታወቂያ ተሟልቶ አልቀረበም።

የመቐለ ከተማ የአንድ ቀበሌ አስተዳደር ለቲክቫህ በሰጡት አስተያየት " ቢሮው የሚለው እና መሬት ላይ ያለውን አይገናኝም፤ ለምሳሌ የእኛ ቀበሌ ነዋሪዎች መታወቂያው እንዲዘጋጅ የሚጠየቀው ገንዘብ አሟልተው ባለመክፈላቸው ምክንያት የደረሰን የህትመት ውጤት ስለሌለ እደላ አልጀመርንም " ብለዋል።

ከጦርነቱ በፊት ለነዋሪዎች ሲሰጥ የነበረው የወረቀት የነዋሪ መታወቂያ ካርድ ወደ ዲጂታል ለማሳደግ ሲደረግ የነበረው እንቅስቃሴ በመቋረጡ ምክንያት ነዋሪዎች ከጦርነቱ በኋላ ለተለያዩ ስራዎቻቸው ማሳለጫ መታወቂያ አጥተው ሲጉላሉ ማየት የተለመደ ነው።

ከቀርብ ጊዜ በኋላ በክልሉ አገልግሎት መስጠት የጀመረው አገራዊው የፋይዳ ዲጂታል መታወቅያ እንዲሁም የአዲስ ፓስፓርት እደላና እድሳት ችግሮቻቸው በመጠኑ ሊያቃልላቸው ችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Sudan : መጋቢት 10/2017 ዓ/ም የትግራይ ተፈናቃዮች በሚገኙበት የሱዳን አምራኩባ የመጠለያ ጣብያ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ቃጠሎ አደጋ የ6 ዓመት ህፃን ህይወት ወዲያው ተቀጥፏል።

ሌላ የሁለት ዓመት ህፃን በደረሰበት ጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ተልኳል።

የእሳት ቃጠሎው ላለፉት ሦስት ዓመታት መደጋገሙ አደጋውን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል ተብሏል።
#TMH

መጠለያው በሚገኝበት አከባቢ በቂ የህክምና እና የመድሃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት አደጋውን የመከላከል ስራ አዳጋች አንደሆነ ተፈናቃዮችን ዋቢ በማድረግ ቲኤምኤች እና ድምጺ ወያነ ዘግበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነት ምን አሉ ? " ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦ " የፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል ፤ ያም ሆኖ አሁንም በበቂ ሁኔታ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች አሉ። ከዚህም አንደኛው የታጣቂዎች ተሃድሶ (ዲዲአር) ስራ ነው። ይህ…
" እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

በአሁኑ ባለው የትግራይ ቀውስ " አሸናፊም ሆኖ ተሸናፊ የለም " አሉ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ።

እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያሉ ሲሆን " የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " ብለዋል።

" ሆኖም ያሉንን ችግሮች በአንድነት መንፈስ ለመፍታት የሚያስችል እድል ከተፈጠረ ሃላፊነቱ ያለመቀበል ፍላጎት የለኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ከመቐለ ወጥተዋል፤ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ወጥቶ የሚቀርባት ትግራይ መኖር የለባትም ፤ ትናንት እንደዛ ከነበረ ዛሬና ነገ መኖር መደረግ የለበትም " ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ' በራኸ ሾው ' ለተባለ የዩቱብ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ምን አሉ ?

➡️ ለውጥ መቀበል የግድ ነው ተወደደም ተጠላም በቆየው የፓለቲካ አካሄድ መሄድ አይቻልም።

➡️ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ስለሆነም በትናንት አንኑር ወደ ነገ እንመልከት እናተኩር ፤ ትግራይ ሳትድን የሚድን አከባቢ የለም። 

➡️ በወጣቱ ያልተመራ ትግል እውነተኛ ለውጥ ነው ማለት አይቻልም ስለሆነም  ከአፍ በዘለለ ወጣቱ የመሪነት ሚናው እንዲረከብ ከልብ መሰራት አለበት። 

➡️ የትግራይ ችግር የተከማቸ ነው፤ ከህወሓት መከፋፈል በፊትም የነበረ ነው፤ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ላለመስማማት የተስማሙ መሆናቸው አሁን ያለውን የትግራይ ፓለቲካ እጅግ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል።

➡️ የሁለቱ ቡድኖች የከረረ መከፋፈል ወደ ለየለት አደጋ እንዳያድግ የሰራዊቱ አመራር ሚናውን ለመወጣት ሞክሯል ይህ ሆኖም ሁለቱ ቡድኖች ፊት ለፊት ተቀምጠው እንዲወያዩ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

➡️ የእኛ ጥረት ብቻ አይደለም ያልተሳካው  የትግራይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ሙሁራንና ሌሎች አካላት ሁለቱ ቡድኖች ለማቀራረብ ያደረጉት ጥረት ውጤት አላማጣም።

➡️ በመጨረሻ የሰራዊቱ አመራር ለሁለት በመከፈል አንዱ ክፍል ጉባኤ ያካሄደውን የህወሓት ቡድን ሲደግፍ የተቀረው ደግሞ የህዝብና የአገር ተልእኮ ከማስከበረ በዘለለ የቡድኖች የፓለቲካ አቋም አልደግፍም ያለ አለ።

➡️ ቡድኖቹ በየአከባቢው ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ዞን የየራሳቸው አስተዳዳሪ መሾም ሲጀምሩም የሰራዊት አመራሮች ድርጊቱ ልክ እንዳልሆነ ለማሳመን ሞክረዋል ሆኖም አድማጭ አልተገኘም። በፊት በትግራይ የተለመደ የሹመት ስነ-ስርዓት አለ። ፓርቲ ነው ከቀበሌ እስከ ዞን አስተዳዳሪ የሞሾመው። አሁን ግን ፓርቲው ይመድባል ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ድግሞ ይሾማል። ይህ አካሄድ የመንግስት የስራ ሃላፊነት ከአንድ ማእከል የሚቀዳበት አሰራር እያጠፋው ሄደ። ስለሆነም ከአሁን በፊት ያልተለመደ ምደባው ህዝቡ መንግስታዊ አገልግሎት ከማሳጣት በዘለለ የፀጥታ ችግር እስከ መሆን ደርሷል።

➡️ የፀጥታ ሃይሉ በዚህ መሃል በሁለት ገመድ እየተጎተተ ስራውን ለመሰራት ተቸግሯል።

➡️ የአሁኑ መከፋፈል ከ93 ዓ.ም መከፋፈል የከፋ ነው። 93 ዓ.ም ያጋጠመው መከፋፈል የመንግስት ስልጣን የተቆጣጠረው ቡድን  ነው ያሸነፈው ከመንግስት መዋቅር ውጪ ያለውም ደግሞ ተሸናፊ ሆነ። የአሁኑ ግን እንደዛ አይደለም ምክንያቱም ሁለቱ ልዩነት የፈጠሩ ቡድኖች በመንግስት የሰራ ሃላፊነቱ የነበሩ ስለሆኑ።
  
➡️ ችግሩ ሲጀመር የፀጥታው አካል የሁለቱ ቡድኖች የመከፋፈል አካል አልነበረም። ፓርቲው እንጂ የፀጥታ አካሉ በሚያስከፋ መልኩ ሳይከፋፈል ለረጅም ጊዚያት ተጉዘዋል። ኋላ ላይ ግን የፓርቲው መከፋፈል ምሁሩን ፣ ፓሊሱን ፣ የፓለቲካ ኤሊቱን ሌላውን እንደተከፋፈለ ሁሉ የፀጥታ ሃይሉም እንዲከፋፈል ሰለባ አድርጓል።  ይህ ሆኖ ቀውሱ ከአቅም በላይ ሆኖ ትርምስ እንዳይፈጠር የፀጥታ ሃይሉ ከባድ የሆነ ስራ ሰርቷል።

➡️ ሰራዊቱ የፓለቲካ ብልሽቱ ተጠቂ (Victim ) እንጂ ግጭትና ቀውስ ጠማቂ አይደለም።

➡️ በአሁኑ ወቅት አሸናፊ የሚባል የፓለቲካ ሃይልም ይሁን ቡድን የለም ፤ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የወጣቱ ስሜት ከማጋጋል ባለፈ ያመጡት ለውጥ የለም ስለሆነም ነው አሸናፊና ተሸናፊ የለም የሚባለው።

➡️ አሁን በትግራይ ያለውን የከፋ ሁኔታ በጠበንጃ እፍታለሁ ብሎ መንቀሳቀስ  ውጤቱ የባሰ እንጂ የተሻለ ተብሎ የሚወሰድ አይደለም። እርስ በራሳችን ለመዋጋት ከሆነ የሚፈለገው ? በዚህ አካሄድ የሚገኝ አወንታዊ ውጤት የለም። ስለሆነም በእርጋታ ማሰብ ያለብን ጊዜ ቢኖር አሁን ነው።

➡️ ዳግም ጦርነት ይፈጠራል ወይ ? የውስጣችን ችግር በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በመነሳት በውስጣችን የእርስ በርስ ጦርነት ይካሄዳል የሚል አልቀበልም አይኖርምም።

➡️ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚታየውን መሳሳብ ወደ ጦርነት እንዳያመራ እንደ ትግራይ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የውስጣችን ችግር ከፈታን ደግሞ ከውጭ የሚመጣ ጦር ይኖራል ብዬ አልገምትም አላምንም።

➡️ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር በተዋዋዮች መካከል ቅንነት እና ትብብር መኖር አለበት።

➡️ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ናቸው ፤ የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔ እካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም። ሆኖም ያሉንን ችግሮች በአንድነት መንፈስ ለመፍታት የሚያስችል እድል ከተፈጠረ ሃላፊነቱ ያለመቀበል ፍላጎት የለኝም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" በአደጋው የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድማል " - ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ

ዛሬ ሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት በትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው ከተማ በሚገኘው ችፑድ ፋብሪካ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

የፋብሪካው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ በሰጠው ቃል
የእሳት ቃጠሎ አደጋው የተነሳው በፋብሪካው የምርት ክፍል መሆኑን ጠቁሟል።

" የአደጋው መነሻ ምክንያት ገና አልታወቀም " ሲልም ገልጿል።

ይህን መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አንድ ሰው ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ሌሎች አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውም ወደ ጤና ማእከላት ተወስደዋል።  

የተነሳው ቃጠሎ በፋብሪካው ማሽነሪዎችና ህንፃ ላይ በሚሊዮን ብሮች የሚገመት ወድመት መድረሱ ነው የተገለፀው።

ዛሬ ረፋድ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎው በሰው ሃይልና በማሽነሪ ተደግፎ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ ከትእምት (#ኢፈርት) ካምፓኒዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን ልኳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo : Social Media

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ፕሬዜደንት አድርጎ የሾመኝ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በአሁኑ ባለው የትግራይ ቀውስ " አሸናፊም ሆኖ ተሸናፊ የለም " አሉ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ። እስካሁኗ ሰዓት ድረስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው ያሉ ሲሆን " የሚጠበቅ ማስተካከያ ቢኖርም እኔን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ…
#Tigray

የትግራይ ህዝብ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም ጥሪ ቀረበ።

ጥሪውን ያቀረቡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው።

ጥቆማ የሚቀርብበት አድራሻ በኢሜል
[email protected] መሆኑ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቆማው መቼ ተጀምሮ እንደሚያልቅ እንዲሁም በህዝብ ጥቆማ የተመረጠው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት እንዴትና መቼ ይፋ እንደሚሆን አስመልክተው በዝርዝር ያሉት የለም።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አሕመድ  (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ምንድነው ያሉት ?

" ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጥቆማ አስመልክቶ ለመላው የትግራይ ህዝብ የቀረበ  ጥሪ !

በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 62(9)፣ እንዲሁም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ ለመግባት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር  359/1995 መሰረት እንዲሁም በትግራይ አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር በሚመለከት የተደነገገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 533/2015 መሰረት የቆመው ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመታት መቆየቱ ይታወቃል።

በአዋጅ 359/1995 አንቀፅ 15(3)  መሰረት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለሁለት ዓመት ብቻ እንደሚቆይ ይደነግጋል። ይሁን እንጂ በተጨባጭ ምክንያቶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ማራዘም ይቻላል። ከላይ በተጠቀሱት ህጎችና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር የተቀመጡለት ተልእኮዎች አጠናቅቆ በህዝብ ለተመረጠ መንግስት ሃላፊነቱ ማስረከብ ይገባ ነበር።

ይሁን እንጂ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሰጡት ዋና ተልእኮዎች በተወሰነለት ጊዜ ማጠናቀቅ አልቻለም።

ከተሰጡት ዋና ተልእኮዎች አንዱ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር ነው። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ቁልፍ ተልእኮ ባለማሳካቱ ምክንያት ዕድሜውን ለአንድ ዓመት ለማራዘም አስገድዷል።

የፌደራል መንግስት መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዕድሜ ለማራዘም ፣ ፓለቲካዊ ፣ አስተዳደራዊና የህግ ስራዎች በማከናወን ላይ የሚገኝ ሆኖ ከዚሁ ጎን ለጎን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል።

በደንብ ቁጥር 533/2015 አንቀጽ 3(2) መሰረት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት የመሾም ሃላፊነት የጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ቢሆንም ህዝብ በምርጫ መሪዎቹ እስኪመርጥ ድረስ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመምረጥ በኩል ተሳትፎ እንዲኖረው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎች በብቃት መፈፀም ይችላሉ ሰላምና ደህንነት ያረጋግጣሉ የምትሉዋቸው እጩዎች በ
[email protected] የኢሜል አድራሻ ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ከዛሬ ጀምራችሁ ጥቆማችሁን መላክ እንደምትችሉ እናሳውቃለን። "

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቋወመ።

ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር  ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ  ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት " የተናጠል ውሳኔና ተግባር " ሲል ተቃውሟል።    

" የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ተኩል ሆኖታል " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " ስምምነቱ በሙሉነት ተተግብሮ ትግራይ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሊኖራት ይገባ ነበር "  ብሏል። 

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት ያልተተገበረው የፌደራል መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀምና አተገባበር በተከተለው የተሳሳተ አካሄድና ፓለቲካዊ ቀውስ እንዲፈጠር በመስራቱ ነው "  ሲልም ክስ አሰምቷል።

" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 3 መሰረት ተዋዋይ ወገን ሌላውን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ በፕሮፓጋንዳ ማጥቃት ይከለክላል  ይሁን እንጂ ይህንኑ የስምምነቱ አካል በፌደራል መንግስት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው " ብሏል።

" የፌደራል መንግስት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መንፈስና ይዘት በወጣ አካሄድ አግባብነት በሌላቸው 359/1995፤ ደንብ 533/2015 ህግና አዋጆች እንዳሻው እየወሰነ ይገኛል " የሚል ወቀሳም አቅርቧል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 10 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግስት መግባባት እንዲቋቋም ያዛል " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ውሳኔ መወሰን አይችልም " ብሏል።    

" ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ማስነሳቱ ተከትሎ ፤ ጀነራል ታደሰ ወረደ ፕረዚደንት እንዲሆኑ ማእከላይ ኮሚቴ ወስኖ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀብሎታል " ያለም ሲሆን " ይህንን ወደ ጎን በመተው በጠቅላይ ሚንስትሩ የተናጠል ውሳኔ በሚያስመስል  መልኩ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጥስ አካሄድ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።

" የፌደራል መንግስት ህዝብን ከሚጎዱ ግልፅ ተግባራት በመቆጠብ ዘላቂ ጥቅምና የጋራ ሰላም በሚያረጋግጡ ተግባራት እንዲያተኩር ጥሪ እናቀርባለን " ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " የተናጠል ውሳኔዎች እንዲቆሙ " ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia