TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በነዳጅ ማደያዎች ለዲጂታል ነዳጅ ግብይት ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሙያዎች እንዲነሱ ውሳኔ ተላልፏል።

በነዳጅ ማደያዎች ለዲጂታል ነዳጅ ግብይት ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሙያዎች እንዲነሱ ውሳኔ መተላለፉን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

ዲጂታል ነዳጅ ግብይት ውሳኔ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ባለሙያዎችና ወኪሎች በነዳጅ ማደያዎች ግብይቱን ለማፋጠን ሲሰጥ የነበረ ድጋፍ ከዛሬ ሰኔ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ #እንደሚያቆሙ ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል፡፡

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ብቻ ከመፈፀሙ ጋር ተያይዞ አሰራሩን ለማለማመድ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ የአሰራር ለውጥ መደረግን ተከትሎ የሚከሰቱ ችግሮችን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋእፆ እንደነበረው ተገልጿል።

በቀጣይ ተጠቃሚው መተግበሪያዎችን መጠቀም መለማመድና ክፍያውን በራሱ መፈጸም ለማስቻል ሲባል ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ አካላት እንዲነሱ የሚል ውሳኔ ተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን

@tikvahethiopia