#Kabba
ካባን ይቀላቀሉ እና ስኬትን በጠዋት ይድረሱበት !
ለስኬት ከሚሮጥ ጠንካራ ሰራተኛ ጀርባ ያለው ካባ ጠዋት እና ማታ ከቦሌ እና አካባቢ ለሚሰሩ ሰራተኞች ወደ ተመረጡ የጉዞ መስመሮች የሰራተኞች ሰርቪስ አዘጋጅቷል።
ከዚህ በኃላ ሰርቪስ ለመጠቀም መኪና መከራየት ቀረ፤ ሰራተኞች በራሳቸው ወይም በድርጅቶቻቸው በመመዝገብ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። ለድርጅቶች እና በጋራ ለሚመጡ ሰራተኞች ልዩ ቅናሽ አለን፡፡
ስኬትን በጠዋት ይድረሱበት፡፡
በ 0960009900 ይደውሉልን
ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ እና ማህበረሰባችንን ይቀላቀሉ : http://bitly.ws/FkNL

በነዳጅ ማደያዎች ለዲጂታል ነዳጅ ግብይት ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሙያዎች እንዲነሱ ውሳኔ ተላልፏል።
በነዳጅ ማደያዎች ለዲጂታል ነዳጅ ግብይት ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ባለሙያዎች እንዲነሱ ውሳኔ መተላለፉን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
ዲጂታል ነዳጅ ግብይት ውሳኔ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ባለሙያዎችና ወኪሎች በነዳጅ ማደያዎች ግብይቱን ለማፋጠን ሲሰጥ የነበረ ድጋፍ ከዛሬ ሰኔ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ #እንደሚያቆሙ ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል፡፡
የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ብቻ ከመፈፀሙ ጋር ተያይዞ አሰራሩን ለማለማመድ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ የአሰራር ለውጥ መደረግን ተከትሎ የሚከሰቱ ችግሮችን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋእፆ እንደነበረው ተገልጿል።
በቀጣይ ተጠቃሚው መተግበሪያዎችን መጠቀም መለማመድና ክፍያውን በራሱ መፈጸም ለማስቻል ሲባል ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ አካላት እንዲነሱ የሚል ውሳኔ ተላልፏል፡፡
ምንጭ፦ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን
@tikvahethiopia

አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው የምግብ እርዳታ እንዲቋረጥ ወሰነች።
የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ " ለተረጂዎች ሳይደረስ ሌላ ጥቅም ውሏል " በሚል እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል።
USAID እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " ለኢትዮጵያ ሕዝብ መቅረብ የነበረበት የምግብ እርዳታ በከፍተኛ መጠን እና በተቀናጀ ሁኔታ ከታቀደለት አላማ ውጪ ጥቅም ላይ በመዋሉ " መሆኑን ገልጿል።
ውሳኔው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመቀናጀት የተወሰደ መሆኑን የገለጸው የተራድኦ ድርጅቱ፣ ይህንን የምግብ እርዳታ አቅርቦትን ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር ተሳታፊ የሆኑ ወገኖችን እንዳልጠቀሰ ሮይተርስ ዘግቧል።
ድርጅቱ " የተደረገውን አገር አቀፍ ቅኝት ተከትሎ USAID በእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ለውጥ እስኪደረግ ድረስ በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለማይቻል፣ አስቸጋሪ ነገር ግን አስፈላጊ ውሳኔ አሳልፈናል " ብሏል።
ባለፉት ሁለት ወራት የተካሄደ ምርመራ በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ከታለመለት አላማ ውጪ መዋሉን እና ለገበያ መቅረቡን እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎችም #ወደ_ውጪ_አገራት መላኩን ደግሞ ብሉምበርግ ተመለከትኩት ያለው ሰነድ አሳይቷል።
ከጥቂት ወራት በፊት ዩኤስኤአይዲ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በተመሳሳይ ሁኔታ ትግራይ ውስጥ ስርቆት ተከስቷል በሚል በክልሉ ያቀርቡ የነበረውን የምግብ እርዳታ ማቋረጣቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል ፥ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እየተካሄደ በሚገኝ ስብሰባ ላይ በተጓዳኝ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንተኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ መነጋጋራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከል የእርዳታ ምግብ ከታለመለት አላማ ውጪ መዋሉ አንዱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ቁርጠኛ በመሆኑ ብሊንከን አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት ቃል አቀባይ የእርዳታ አቅርቦቱ ሥርዓት አስተማማኝ መሆኑ ከተረጋገጠ እርዳታውን መልሶ እንደሚጀመር መግለጻቸውን በመግለጫው ላይ ተካቷል።
መረጃው የቢቢሲ/ሮይተርስ/ብሉንበርግ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በእስር ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች በሙሉ ከእስር በሚፈቱበት አግባብ ላይ ስምምነት ተደርሷል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
ዛሬ ከፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽነሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራሮች ሼይኽ ሁሴን ጨምሮ የፕሬዝዳንቱ አማካሪዎች ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እንዲሁም ከኦሮሚያ መጅሊስ ሼይኽ ሚስባን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና ከፍተኛ የፀጥታ ሐይሉ አመራሮች ተካፍለዋል።
በውይይቱ ላይ በሸገር ከተማ የፈረሱ መስጂዶችን ተከትሎ በሁለት ጁምዓዎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተወሰዱት ኢ ሰብዓዊ እና ከልክ ያለፉ የኃይል እርምጃዎች ተቀባይነት የሌላቸው እና ህዝበ ሙስሊሙን እጅግ ያሳዘነ መሆኑ ተገልፆል።
ሀገር ወዳድ እና ሰላማዊ ለሆነው ህዝበ ሙስሊም ህጋዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በማቅረቡ በምላሹ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደው የኃይል እርምጃ በምንም መመዘኛ የሚገባው እንዳልነበር እና ጥፋት እንደሆነ ለፀጥታ አመራሮቹ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
በፀጥታ ኃይሉ በኩልም የሙስሊሙን ህጋዊ ጥያቄ ሽፋን በማድረግ የራሳቸው አጀንዳ ለማራመድ የሞከሩ ኃይሎች መኖራቸውን መረጃ እንዳላቸው በማንሳት የነበራቸውን ስጋት ገልፀዋል።
በውይይቱ መቋጫ ላይ በሁለቱ ጁምዓዎች በተወሰደው የኃይል እርምጃ በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች በሙሉ ከእስር በሚፈቱበት አግባብ ላይ ከስምምነት ላይ መድረስ መቻሉ ተገልጿል።
ከህግ አግባብ ውጪ የኃይል እርምጃ የወሰዱ የፀጥታ ሀይሉ አባላትም በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ኮሚቴ ተዋቅሮ የማጣራቱ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ህዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸው ህጋዊ ጥያቄዎቹ በኦሮሚያ ክልል መንግስት በኩል መፍትሄ ለመስጠት ቃል በመገባቱ እና ይህም መፍትሄ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ህዝበ ሙስሊሙ በተለመደው ጨዋነቱ በትዕግስት በመጠበቅ ከመሪ ድርጅቱ መጅሊሱ ጎን በመቆም በተቋሙ የተሰጡትን መመሪያ እና የመፍትሄ አቅጣጫ በመተግበር እና በዱዓ በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
ከፀጥታ አመራሩ ጋር የተደረገው ፍሬያማ ውይይት በመግባባት የተቋጨ ሲሆን በቀጣይ ባሉ ጁምዓዎች ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከር እና በዱዓ በመበርታት መደበኛ የጁምዓ ሰላቱን ብቻ እንዲያከናውን ጥሪ ቀርቧል።
በሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ አቅጣጫ የተቀመጠለት በመሆኑ በሁሉም መሳጂዶች ከቁኑት ዱዓ ውጪ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ባለመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደ ታዣዥነቱን በማሳየት የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ ብቻ መመለስ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።
Via ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

#አቢሲንያ_ባንክ
ወደ ቅርንጫፎች መሄድ ሳያስፈልግ ባሉበት ሆነው የአቢሲንያ ባንክ አካውንት መክፈት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
አፖሎ መተግበሪያን በማውረድ ካሉበት ሆነው አካውንት በቀላሉ ይክፈቱ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
ስለ አፖሎ የዲጅታል ባንክ መተግበሪያ አጠቃቀም እና የተለያዩ መረጃዎች ለማግኘት የአፖሎ የቴሌግራም ቻነልን ይቀላቀሉ። https://yangx.top/apollodigitalproduct
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#AddisAbaba
የዛሬው የጁምዓ ሶላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተሰግዶ ህዝበ ሙስሊሙም ወደየቤቱ መግባቱ ተገልጿል።
ባለፉት ሁለት የጁምዓ ሶላት ወቅቶች ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ከተፈፀመው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዝ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ማለፉና ጉዳት መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም።
ይህንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንዲሁም ከፌዴራል ፖሊስና አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር ተከታታይ ውይይቶች ማድረጉና መግባባት ላይ መደረሱ የሚታወቅ ነው።
በሸገር ከተማ ከመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያቀረበው ጥያቄ የመፍትሄ አቅጣጫ የተቀመጠለት በመሆኑም በሁሉም መስጂዶች ከቁኑት ዱዓ ውጪ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ ባለመሆናቸው ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደ ታዣዥነቱን በማሳየት የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ ብቻ መመለስ እንዳለበት ትላንት ማሳሰቢያ መተላለፉት ይታወቃል።
በዚህም ዛሬ የነበረው የጁምዓ ሶላት በሰላም ተከናውኖ ህዝበ ሙስሊሙ ወደቤቱ ገብቷል።

#AddisAbaba የዛሬው የጁምዓ ሶላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተሰግዶ ህዝበ ሙስሊሙም ወደየቤቱ መግባቱ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት የጁምዓ ሶላት ወቅቶች ላይ በሸገር ከተማ ውስጥ ከተፈፀመው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዝ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ማለፉና ጉዳት መድረሱ የሚዘነጋ አይደለም። ይህንም ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት…
" ህዝበ ሙስሊሙ ሁልጊዜም ሰላም ፈላጊ እና የሰላም ዘብ መሆኑን እንደወትሮ ሁሉ ዛሬም አስመስክሯል " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
በታላቁ አንዋር መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙ እንደወትሮ ሁሉ የጁምዓ ሰላቱን ሰግዶ በሰላም ወደ መጣበት መመለሱን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ገልጸዋል።
" ባለፉት ሁለት ጁምዓዎች በተፈጠሩ ችግሮች በርካታ ሙስሊሞች ከህይወት መስዋትነት አንስቶ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል " ያሉት ኡስታዝ አቡበከር " የነሱ መስዋትነት ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ሲታወስ የሚኖር ነው " ብለዋል።
" ህዝበ ሙስሊሙ ሁልጊዜም ሰላም ፈላጊ እና የሰላም ዘብ መሆኑን እንደወትሮ ሁሉ ዛሬም አስመስክሯል " ያሉት ኡስታዝ አቡበከር " ለህዝበ ሙስሊሙ ሰላም የእምነቱ መርህ እና መመሪያው በመሆኑ ሰላሙን ለመጠበቅ ሁሌም ዝግጁ እና ንቁ ነው " ሲሉ ገልጸዋል
በዛሬው ጁምዓ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የመንግስት የፀጥታ ኃይል በመስጂዱ ዙሪያ ለጥበቃ በመሰማራቱ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ስጋት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ከሚመለከተው የፀጥታ አመራሮች ጋር በመነጋገር ዙሪያውን ከቦ የነበረው የፀጥታ ኃይል ወደኃላ እንዲመለስ በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ ፀጥታውን በራሱ በምእመናን እና በአስተባባሪዎቹ እንደወትሮ በማስጠበቅ የጁምዓ ሰላቱ በሰላም ተሰግዶ ማጠናቀቅ መቻሉ ተገልጿል።
ኡስታዝ አቡበከር ፤ የዛሬው ጁምዓ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረበተው ህዝበ ሙስሊም እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩ በድርሻው ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ሰላሙን ማስጠበቅ እንደሚችል እምነት በማሳደር የበኩላቸውን በመወጣታቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የፀጥታ ኃይሉ በትብብር እና በመናበብ ከህዝበ ሙስሊሙ እና ከአመራሩ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የጋራ ሰላማችንን ማስጠበቅ እንደሚቻል ከዛሬው ጁምዓ ትምህርት መውሰድ ይቻላል ብለዋል።

ያልተገደቡ የድምጽ ጥቅሎች እስከ 30% ቅናሽ ተደርጎባቸው ቀረቡ!
ያልተገደቡ የሞባይል የድምጽ ጥቅሎችን አቅምን ባገናዘበ ዋጋ እስከ 30% ቅናሽ አድርገን ስናቀርብ በልዩ ደስታ ነው !!
ዕለታዊ ድምፅ 35 ብር የነበረው 25 ብር
ወርሃዊ ድምፅ 999 ብር የነበረው 699 ብር
ወርሃዊ ድምፅ እና ዳታ 1700 ብር የነበረው 1399 ብር
እንደፍላጎትዎ በዕለታዊ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ አማራጮች የቀረቡትን ያልተገደቡ ጥቅሎች በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ማይ ኢትዮቴል ወይም *999# የራስዎ ያድርጉ።
(ኢትዮ ቴሌኮም)

አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው የምግብ እርዳታ እንዲቋረጥ ወሰነች። የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ " ለተረጂዎች ሳይደረስ ሌላ ጥቅም ውሏል " በሚል እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል። USAID እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " ለኢትዮጵያ ሕዝብ መቅረብ የነበረበት የምግብ እርዳታ በከፍተኛ መጠን እና በተቀናጀ ሁኔታ ከታቀደለት አላማ…
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ርዳታ ስርጭት አቆመ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የኢትዮጵያ የርዳታ ምግብ ሥርጭቱን ማቆሙን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ለኢትዮጵያ ተጎጂዎች ሲያሠራጭ የቆየውን የምግብ ርዳታ፣ " #ስርቆት_በመንሰራፋቱ " ምክንያት ለጊዜው ማቆሙን ዛሬ ገልጿል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የርዳታ ምግብ የማቆም ውሳኔውን ይፋ ያደረገው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ተመሳሳይ ርምጃ መውሰዷን፣ በዩኤስኤአይዲ በኩል ካሳወቀች ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑን ቪኦኤ ዘግቧል።