አርቲስት ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የክላርኔት ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የአርቲስቱን ህልፈት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ጣቢያ ከቅርብ ወዳጆቹ ማረጋገጡን አሳውቋል።
አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ ጣሊያን ሀገር ተጉዞ እንደነበር የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያለመለክታል።
ክላርኔት ተጫዋቹ እና ሙዚቀኛው ዳዊት ህይወቱ አልፎ የተገኘው #በተኛበት_ክፍል መሆኑና የጣሊያን ፖሊስ የአሟሟቱን ሁኔታ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጣሊያን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የሞያ አጋሮቹ ከሀገሪቱ ፖሊስ ጋር ተነጋግረው የአርቲስቱን አስክሬን በሀገሩ #ኢትዮጵያ ለማሳረፍ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 አሳውቋል።
ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሰራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅ ነው።
ከአርቲስት ዳዊት ፍሬው ስራዎች መካከል አንዱ " ጥላ ከለላዬ " የተሰኘው በመሳሪያ የተቀነባበረ መዚቃ ሲሆን በዚሁ ስራ ይህ ስንኝ ይገኝበታል።
" ጥላ ከለላዬ ፤ #ኢትዮጵያ ❤ሀገሬ
#ኩራት ይሰማኛል ፤ ካንቺ መፈጠሬ።
@tikvahethiopia