#Ethiopia🇪🇹
ዛሬ 82ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል።
የአርበኞች የድል በዓል ለምን ይከበራል ?
ጣሊያን የዓድዋን ድል ለመበቀል በሚል በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አማካኝነት፥ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ወራ ነበር።
በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያውያንም ወራሪውን ሀይል ለአምስት ዓመታት በጽናት ታግለው 1933 ዓ.ም ድል ነስተውታል።
የወቅቱ አርበኞቻችን ለሀገራቸው ነጻነት የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ያስገኙትን ድል ለማሰብም ነው በየአመቱ ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል የሚከበረው።
እንኳን አደረሳችሁ !
@tikvahethiopia

አርቲስት ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የክላርኔት ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የአርቲስቱን ህልፈት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ጣቢያ ከቅርብ ወዳጆቹ ማረጋገጡን አሳውቋል።
አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ ጣሊያን ሀገር ተጉዞ እንደነበር የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያለመለክታል።
ክላርኔት ተጫዋቹ እና ሙዚቀኛው ዳዊት ህይወቱ አልፎ የተገኘው #በተኛበት_ክፍል መሆኑና የጣሊያን ፖሊስ የአሟሟቱን ሁኔታ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጣሊያን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የሞያ አጋሮቹ ከሀገሪቱ ፖሊስ ጋር ተነጋግረው የአርቲስቱን አስክሬን በሀገሩ #ኢትዮጵያ ለማሳረፍ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 አሳውቋል።
ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሰራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅ ነው።
ከአርቲስት ዳዊት ፍሬው ስራዎች መካከል አንዱ " ጥላ ከለላዬ " የተሰኘው በመሳሪያ የተቀነባበረ መዚቃ ሲሆን በዚሁ ስራ ይህ ስንኝ ይገኝበታል።
" ጥላ ከለላዬ ፤ #ኢትዮጵያ ❤ሀገሬ
#ኩራት ይሰማኛል ፤ ካንቺ መፈጠሬ።

#ኢትዮ_ቴሌኮም
ውድ ደንበኞቻችን ፦
በቅርቡ ወደናንተ ያደረስናትንና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን በተመለከተ ለጥያቄያችሁ ፈጣን ምላሽ የምትሰጠውን አርዲ ቻትቦት በማስመሰል እንዲሁም በኢትዮ ቴሌኮም እና ቴሌብር ስም በተከፈቱ የቻትቦት ገጾች እንዳይታለሉ፤ ትክክለኛዎቹ የአርዲ ቻትቦት መገኛዎች ይጠቀሙ:
በድረገፅ - ethiotelecom.et/
በፌስቡክ - facebook.com/ethiotelecom እና በትዊተር - twitter.com/ethiotelecom በመልዕክት መላኪያ ላይ
በዋትስአፕ - wa.me/251994000000?text
በቴሌግራም - t.me/EthiotelecomChatBot
ማስታወሻ፡ የቴሌብር የሚስጥር ቁጥርዎን ወይም ሌሎች ግላዊ መረጃዎችዎን በፍፁም አያጋሩ!!

#አቢሲንያ_ባንክ
አፖሎን ተጠቅመው ቪዛ ካርድ ሲያዙ በ72 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተመችዎት ቦታ ካርድዎን እናደርስሎታለን
መተግበሪያውን ኣውርደው ካርድዎን ይዘዙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#Thebig5Constract
ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሞያዎች የቀረበ ድንቅ አውደ ርዕይ!
ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ስመጥር የግንባታ ዘርፍ ተዋንያን እንዲሁም የዘርፍፉ ግብዓት አቅራቢዎች የሚገኙበት ይህን ታላቅ አውደ ርዕይ ለመጎብኘት ዝግጁ ኖት? በዚህ ድንቅ መድረክ ተሳታፊ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ለመመልከት ድረ ገጻችንን ይጎብኙ፣ ለጉብኝቶ ቀድመው ያቅዱ!
በዘርፉ ያልዎትን ዕውቀት ለማስፋት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ግንኙነቶን ለማጠናከር ይህ ወርቃማ ዕድል አያምልጥዎ! https://bit.ly/3LpCdHH

#ባህርዳር
የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ በጀግኖች አርበኞች ስም መንገድ ሰየመች።
82ኛው የጀግኖች አርበኞች ቀን በባሕር ዳር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ዛሬ ተከብሯል።
በዚህም በባሕር ዳር ከተማ " ከገጠር መንገድ እሰከ ኤርፖርት " ያለው መንገድ በጀግኖች አርበኞች ስም መሰየሙን በአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር አሳውቋል።
ዛሬ በነበረው ዝግጅት የአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዜዳንት ዳኝነት አያሌው ተከታዩን መልዕክት አስተላልዋል ፦
" ለሀገር በመስዋዕትነት ከፍለው ሀገር ያጸኑ ጀግኖችን መዘከር ይገባል።
' ጀግናን መፍጠር ጀግናን ከማክበር ይጀምራል' የሀገርን ነጻነት፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ያጸኑ ጀግኖቻችን እንኮራባቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን።
የዚህ ዘመን ትውልዶች ከድል ታሪኩ በመማር በመከባበር፣ በመደጋገፍ ፣በአንድነት ሀገርን ማጽናት ይገባናል።
በአንድ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመተባበር ሀገርን ማሻገር ይገባል። ' ሀገሩን የማያውቅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ የማያውቅ ሕጻን እንደማለት ነው ' እና ሀገራችን በምንና እንዴት እንደቆመች መረዳት ይገባናል።
በሚጠበቅብን ዘርፍ ሁሉ የአርበኝነት ሚናችን መወጣት ይገባል። "
#AMC

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo ፦ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል። @tikvahethiopia
የጀርመኑ መራሄ መንግስት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከነማን ጋር ተገናኙ ?
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ በኢትዮጵያ የስራ ገኝታቸው ከኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ሹልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ስለመገናኘታቸው ተሰምቷል።
ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር አ/አ ውስጥ በተገናኙበት በወቅት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙሪያ በቀሪ ተግባራት ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደነበሩበት መመለስ ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት፣ በትግራይ መልሶ ግንባታ ጉዳይ መምከራቸውን ተዘግቧል።

#Sudan
የጎረቤት ሱዳን ዜጎች በሰላም እጦት ሳቢያ የገዛ ሀገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።
ሱዳን አሁንም በጦርነት እየታመሰች ሲሆን ተዋጊዎቹ ኃይሎች ውጊያ የማቆም ፍላጎት እያሳዩ አይደለም።
በተደጋጋሚ በተለያዩ ሀገራት ጥረት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲሁም ዳጋሎ እና አል ቡርሃን ችግሩን እንዲፈቱ ጥረት ቢደረግም ውጤት አላስገኘም።
ዛሬም በርካቶች የሱዳን ዜጎች ሀገራቸውን ጥለው እየሸሹ ናቸው። የውጭ ሀገር ዜጎችም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሱዳንን ምድር እየለቀቁ ይገኛሉ።
በሱዳን ጦርነት ምክንያት እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ በመተማ በኩል ፤ የ61 ሀገራት ዜጎች የሆኑ 7726 ሰዎች ገብተዋል።

#AmharaRegion በአማራ ክልል በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰ መሆኑን እንዲሁም ከደሴ - አ/አ መንገድ በተለያየ ጊዜ መዘጋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ” በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ…
#AmharaRegion
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ፤ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በአማራ ክልል ላሉ ውጥረቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ።
ይህ ጥሪ ያቀረበው ዛሬ አርብ ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ፤ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በአማራ ክልል ላሉ ውጥረቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ።
ይህ ጥሪ ያቀረበው ዛሬ አርብ ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ። ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ጤና ስጋትነት የታወጀበት ዋነኛው ምክንያት በቻይና እየሆነ ባለው ሳይሆን…
#NewsAlert
የዓለም ጤና ድርጅት ከ3 ዓመት በኃላ ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋት መሆን #ማብቃቱን ይፋ አደረገ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከዚህ ቀደም አውጀውት የነበረው የኮቪድ-19 የምድራችን አጣዳፊ የጤና ስጋት አሁን ላይ ማብቃቱን አሳውቀዋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው ኮሚቴ ለ15ኛ ጊዜ በመገናኘት ባደረገው ስብሰባ ወቅት ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸው በዚህም መሰረት የኮሚቴውን ምክረ ሃሳብ በመቀበል የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋትነት ማብቃቱን አውጀዋል።
ይህ ማለት ግን ኮቪድ አብቅቷል ማለት እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ ጥር 20/2020 ላይ ነበር ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ብሎ ያወጀው።
ይኸው ወረርሽኝ በትንሹ 20 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል (እንደ WHO መረጃ) ፣ በርካቶችን ቤተሰብ አሳጥቷል ፤ የዓለምን ኢኮኖሚ እንዳልነበር አድርጓል።

የብር የምንዛሬ ለውጥ ሊደረግ ነው ?
" የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ሀሰት ነው " - አቶ ማሞ ምህረቱ
በኢትዮጵያ " የገንዘብ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ ሊደረግ ነው " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።
የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ፥ " እስከዛሬ ድረስ / እስካሁን ድረስ በአንድ ጊዜ የሚደረግ የብር የምንዛሬ ተመን ለውጥ / one time devaluation / ለማድረግ የተደረገ ውይይትም፣ የተወሰነ ውሳኔ ፈፅሞ የለም " ብለዋል።
የብር የምንዛሬ ለውጥን / devaluation በተመለከተ የተደረገ ውይይት ወይም የተወሰነ ውሳኔ የለም ያሉት አቶ ማሞ ዜጎች በተረጋጋ ሁኔታ በገበያ ስርዓቱ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
አቶ ማሞ ምህረቱ ፥ " በማህበረሰቡ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው የሚል ብዙ ወሬ አለ ፤ ይሄን ተከትሎ ገበያ ውስጥ ስካር በሚባል ሁኔታ ሰዎች አንዳንዴ እቃ ይይዛሉ፤ አንደንዴ ደግሞ መሰረታዊ በሚባሉት እቃዎች ላይ አላስፈላጊ የሆነ ዋጋ ይጨምራሉ ከዛም አልፎ የኢኮኖሚ ጥቅም በሌለው ጉዳይ ላይ ያላቸውን ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ ይሄ ፈፅሞ ትክልል ያልሆነና ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰሞኑን በተለይ በመዲናዋ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው በዚህም መሰረታዊ እና ሌሎች ቁሶች ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ወሬ በስፋት እየተሰራጨ ነው።