TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
መቀለ ሊገባ የነበረ ዘይት ተያዘ‼️

የጉምርክ አሰራርን #ሳያሟላ ወደ መቀለ ሊገባ የነበረ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የመቀሌ ቅርንጫፍ የኢንተሊጀንሲና ኮንትሮባንድ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ገብረእግዚአብሄር ገብረህይወት ለኢዜአ እንዳስረዱት ዘይቱ በአራት ተሽከርካሪዎች ከነ ተሳቢያቸው ተጭኖ ከጅቡቲ ወደ መቀለ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ሥር ውሏል። የምግብ ዘይቱ በቅጥጥር ስር የዋለው በህብረተሰቡ ጥቆማ #አሸጎዳ በተባለው አካባቢ ነው፡፡

በተለያየ መጠን የታሸገው ዘይት 159 ሺህ 360 ሊትር እንደሆነ ተናግረዋል። ዘይቱን ይዘው የመጡ ተሽከርካሪዎች የንብረቱን ዝርዝር መረጃ፣የንብረቱ ባለቤትና የጉምሩክ ይለፍ ሰነዶችን ያለመያዛቸውን አመልክተዋል።

አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ማጣራት ከተደረገ በኋላ በጉምሩክ መመሪያ መሰረት መለቀቃቸውን የተናገሩት አስተባባሪው፣ የንብረቶቹ ባለቤቶች ግን አልቀረቡም ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia